ከገዥው ወገን የምንለይበት፤ አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘገጅ

June 24, 2015

ማክሰኞ፤ ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፯ ዓመተ ምህረት

እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለትግሬዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦሮሞዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአማራዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሶማሌዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአፋሮች ጥብቅና እቆማለሁ፣  እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦጋዴኖች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአኙዋኮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሲዳማዎች ጥብቅና እቆማለሁ፤ የሚል ግለሰብም ሆነ ድርጅት፤ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይልቅ ከአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የበለጠ የጋራ የሆኑ መቀራረቢያ ጉዳዮች ስላሉት፤ ሰፈሩን ወደዚያ ቢያቀና ይቀለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ጋር መሠረታዊ ልዩነቱ፤ እያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን፤ “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ። በሀገሬ በኢትዮጵያ የማደርገው ማንኛውም የፖለቲካ ተሳትፎ፤ በኢትዮጵያዊነቴ ብቻ ነው። በኢትዮጵያዊነቴ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ባልተለዬ ሁኔታ፤ እኩል በፖለቲካ ምኅዳሩ፤ የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብቴ ተከብሮልኝ፤ በማንኛውም የሀገሬ ክልል፤ የመኖር፣ ሀብት የማፍራት፣ በአካባቢውና በሀገር አቀፍ የፖለቲካ ሂደት ተሳትፎ የማድረግ ሙሉ መብት አለኝ።” ስንል፤ አምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ደግሞ፤ “የለም ኢትዮጵያ የትግሬዎች፣ የአማራዎች፣ የኦሮሞዎች፣ የደቡቦች፣ የሶማሌዎች፣ የአፋሮች፣ የአኝዋኮች ነች። ግለሰብ ኢትዮጵያዊ የሚባል የለም። እናም የፖለቲካ ተሳትፎ የሚደረገው በነዚህ ክልሎች ዙሪያ እንጂ፤ በኢትዮጵያዊነት አይደለም።” የሚለው ነው።

ከዚህ በመነሳት፤ አምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ አስተዳደሩን በዚህ ላይ ተከለ። በሂደቱም የተለያዩ ለየብቻቸው የተካተቱ ክልሎችን መሠረተ። አያንዳንዱ የዚህ ገዢ ቡድን ተቀጥላ ጥገኛ የክልል የፖለቲካ ድርጅት፤ የራሱን የክልሉ ተወላጆች ብቻ በክልሉ ለመክተትና ለማስተዳደር ሙሉ መብት አገኘ። እናም በገዥው ቡድን ፈቃድና ፍላጎት፤ ሌሎችን ከክልሉ ማባረር፣ ሀብታቸውን መዝረፍ፣ መግደል፣ አይቀሬ ሆነ። በተግባርም ተፈጸመ። ሀገራችንን ፍጹም ወደማትመለስበት አዘቅት ለመክተት፤ ይኼው ገዥ ቡድን ተሯሯጠ። ተከትለው የሚሄዱት የሕዝቡን ድምጽ ማፈን፣ ሀገሪቱን እስር ቤት ማድረግ፣ አንገቱን ሰብሮ የማይገዛውን ማሰር፣ ማባረርና መግደል፤ ተዥጎደጎዱ። ለዚህ ተቃውሞ፤ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ ድርጅቶችን መሥርተው በመታገል ላይ ናቸው። እንግዲህ በዚህ ትግል፤ ሁለት ሰፈሮች ብቻ በገሃድ አሉ። አንደኛው የሕዝቡ ሰፈር ነው። ሌላው የአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሰፈር ነው። የግለሰብ ሆነ የድርጅት ጉዳይ እዚህ ቦታ የለውም። የግለሰብ እምነት ወይንም የድርጅት መርኀ-ግብር፤ ከሁለቱ መርጠን ባንዱ ሰፈር እንድንሰለፍ ያደርገናል። የሰልፉ መለያ ደግሞ፤ የፖለቲካ ፍልሰፍናችን እና ከዚህ የሚመነጨውና በተግባር ለማዋል የምንፈልገው የአስተዳደር መመሪያ ነው።

ይህ ነው የአሁኑ የሀገራችን የኢትዮጵያ የፖለቲካ እውነታ። ይሄን በጁ ያልጨበጠ ማንኛውም ሂደት፤ መዳረሻው ተመልሶ ያው ነው። የድርጅት መሪዎችም ሆኑ ታጋይ ግለሰብ ኢትዮጵያዊያን፤ መሠረታዊ የሆነውን የልዩነት ነጥብ በማንገት፤ ትግሉን መልክ ሠጥተን መሄድ አለብን። አማራ ነኝና ከሌሎች የበለጠ ለአማራዎች እኔ ነኝ ተቆርቋሪ፣ ለኦሮሞዎችም፣ ለትግሬዎችም፣ ለሶማሌዎችም፣ ለአፋሮችም፣ ለአኙዎኮችም፣ ለሲዳማዎችም እኔ ነኝ ተቆርቋሪ የሚለው አባባል፤ የኢትዮጵያዊነት ጠላት ነው። እንደ ኢትዮጵያዊ ካላሰብን፤ ኢትዮጵያዊነት በውስጣችን የለም። እንደ ኢትዮጵያዊ ካልታገልን፤ ኢትዮጵያ የለችም። በሀገራችን፤ ለኢትዮጵያዊያን ሉዓላዊነት፣ ለሀገራችን ዳር ደንበር መከበር፣ ለያንዳንዳችን ዴሞክራሲያዊ መብት የምንታገለው በኢትዮጵያዊነታችን ነው። አንዳችን ከሌላችን ጎን የምንሰለፈው፣ የያንዳንዳችን ጉዳይ የሌላችን በመሆኑ ነው። አለዚያ፣ አንተም ለራስህ እኔም ለራሴ ከሆነ፤ ትግሉ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ሳይሆን፤ በየኪሳችን ለያዝነው ዘውድ ነው። መነሻችን ይሄ ከሆነ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ ናት።

ይሄን እንድጽፍ ያስገደደኝ፤ ስለሰላማዊ ትግል የመጀመሪያውን ክፍል ባቀረብኩበት ወቅት፤ ከሌሎች የተላኩልኝ አፀፋዎች ነው። የገዥውን ስም ለምን “ትግሬዎች” ትላለህ የሚለው በተደጋጋሚ የቀረበልኝ ቢሆንም፤ ባሁኑ ሰዓት ቁንጮው ላይ ደረሰ።

እናም ይሄን ጻፍኩ። እኔ ራሳቸውን እንዲጠሩበት በመረጡት ስም ነው የጠራኋቸው። ለኔ ካላይ እንደገለጽኩት የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ነው። ኢትዮጵያ አንድ ናት። ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊያን ናት። በትግራይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን፤ ትግሬዎች ይባላሉ። በአፋር ያሉት ኢትዮጵያዊያን አፋሮች ይባላሉ። ታዲያ ትግሬዎችን ነፃ አወጣለሁ ብሎ የተነሳ ግንባር፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነኝ ሲል፤ ሌላ ምን ብዬ ልጠራው ነው። የትግራይ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ካልኩማ፤ ሰፈሬ ከገዥው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አይሆንም ወይ? ለኔ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የትግራይ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ፣ የሶማሌ ሕዝብ፣ የሲዳማ ሕዝብ፣ የአኝዋክ ሕዝብ፣ የቤንሻንጉል ሕዝብ፣ የወላይታ ሕዝብ የለም። እናም፤ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ብዬ አልጽፍም። ለምን ይሄን ጽፍክ የሚለኝ ካለ፤ ሄዶ ስም ያወጣውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ይጠይቅ።

በሀገራችን ያለው ትግል፤ ሀገርን ከአምባገነን ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ ጠላታችን አንጻር፤ ልዩነታችን በግልጽ ወጥቶ፣ ተሰላፊዎች ባደባባይ ታውቀን የቆምንለት እንጂ፤ አንዳችን ሌላችንን የምንለማመጥበት ጉዳይ አይደለም። ትግሉ የመላ ሕዝቡ እንጂ፤ የዚህ ወይንም የዚያ ወገን የግል ጉዳይ አይደለም። ታጋዩን የሕዝብ ወገን ወደ አንድ ማሰባሰቡ የትግሉ የመጀመሪያ ግዴታ ነው። በርግጥ መተባበር የዲፕሎማቲክ ሥራ እንጂ፤ አንተም ባፈተተህ የሚባልበት ሂደት አይደለም። በቅርቡ የተለያዩ ታጋይ ድርጅቶች ቢያንስ ተገናኝተው ለመነጋገር ይችሉ እደሆነ በማሰብ፤ ጥረት አድርጌ ነበር። ይሰበሰቡና መፍትሔ ያቀርቡልናል የሚል ብዥታ አልነበረኝም። ነገር ግን፤ በሂደቱ ሁላችን ሀገራችን ያለችበትን አደጋ በመመልከትና ቅድሚያ ለሀገር ብለን፤ በድርጅት ያሉትም ሆነ ግለሰብ ታጋዮች፤ የመሰባሰቡን ሂደት ያቀላጥፉታል ብዬ ነበር። አልተሳካም። ትግሉ ከገዥው አምባገነን ጋር የምንፋለምበትን ጉዳይ በቅርብ በልብ አንግተን፤ የጠራና ፀሐይ የሞቀውን ልዩነታችንን ባደባባይ አንግተን የተነሳንበት ግብግብ ነው። ይሄን ላስደስት፤ ያንን ላቆላምጥ የሚባልበት አይደለም። በተለይ በሥልጣን ላይ ያለን መንግሥት ለመለወጥ የሚደረግ ትግል፤ የጠራ አመለካከት ከሌለው፤ ትግሉ ውጤታማ አይሆንም። ጠላት ማነው፣ የምንታገለው ለምንድን ነው? ግባችን ምንድን ነው? መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎች ናቸው። በዚህ ትግል፤ ጠርተው የሚወጡ ጽንሰ-ሃሳቦች አሉ። እኒህ የትግሉን ሂደት ይተረጉሙታል። ግንዛቤን ያዳብራሉ። በሥልጣን ላይ ያለውን ገዢ ቡድን ማንነቱን ለመግለጽ የምንጠቀምበት ስም፤ ራሱን ግልጽ አድርጎ የሚጠራበትና የሚጠራበት መሆኑ፤ በትግሉ ላይ ትልቅ አስተዋፅዖ አለው። የምናየው የትግል አሰላለፍ ትርጉሙ የሚመነጨው፤ ከግንዛቤያችን ላይ በመቆም ነው።

በአንድ በኩል ጠላታችን የሚታወቀው ራሱ ነኝ ብሎ ባወጣው ስም እንጂ፤ እኛ በምናወጣለት ስም አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ በመካከላችን እብሪተኛን እብሪተኛ ማለት ካልቻልን፤ ታጋዮች ሳንሆን ወሬኞች ነን። ከሁሉም በላይ የሀገሬ ጉዳይ ብሎ ያልተነሳ ታጋይ፤ የሕዝቡ ወገን ሊሆንም ሆነ ታግሎ የሕዝቡን ድል ሊያስገኝ አይችልም። ቢሳካለት ገዥውን መተካት ነው ሩጫው።

 

3 Comments

 1. We have heard this type of preaxh ing for the last several years from the wishers of the old system. I wish the writer, as a journalist, lives what he writes in this article. Including the writer, all new generation old system dreaming journalists are doing symmetrically opposite in their reporting and actions. The central piece of their report focuses on injustice happening inAmhaean region and on the lost power of Amhara Orthodox elites in Ethiopian political fabrics.
  For this writer and many of his “professional” friends the center of their professional service is addressing only the Amhara and Orthodox chrsitan problems as if their issues are extraordinarily different from the cases of the other nation and nstionalities in the country. But they try to preach differently in some of their articles. They tell us that their belief is about each individual right in the country. But they don’t work to address injustice happening to individuals in different regions while they try to make a big story out of happening in a remote village of Amhara region, especially in Gojam and Gonder as many of them are from.these to arras.

  Please note that people if different nations in Ethiopia are aware of all your efforts. No one can be fooled. You may find some who still try to portray themselves as Amhara telling us “my grandfather was Oromo, Gurage, Sidama, Aga’uu (Agaw) etc., but call themselves Amhara or Ethiopian denying their that they have nothing yo do with grandfather identity. But their peers from Amhara grandfathers are proud of their heritage and language.

  In short, please don’t try to foolish the others, the people you try to preach has already aware of the passage from where you are preaching from. Many people like you have tried to preach them the passage and sang the same song to them for the last 40 years.

  Adios,
  Hunde

 2. አንዱአለም:-ጽሑፍህን ተመልክቸዋአለሁ ቢቻል መልካም ነበር መጀመርያው ላይ ያስቀመጥከው አልቻል ብሎ እንጅ እንዲቻል የሚታገለውን ስንመለከት ደግሞ አንተ እንዳልከው ዘውዱን በኪሱ አድርጎ ቀን እየገዛና ያለ ትግልና መስእዋትነት በአቋራጭ ሥልጣን ላይ ፊጥ ለማለት ነው::ይህን በእንግሊዝኛ የጻፈ ተመልከተው ብዙ ጊዜ ሰለጠን የሚሉ ኦሮሞች አንዲትም ትሁን በአማርኛ አይጽፉም;በዚህ ጹሑፍ ታርጌት አድርገው የምናገኘውም አማራውንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ነው:: ነገሩ የሚሉሽን ብትሰሚ ገበያ ባልወጣሽ ነውና የኦሮሞ ወረራ በኢትዮጵያ ሲካሄድ ምን እንዳደረሰ ባለፉት ገዥዎችና በኢትዮጵያ ትልቁን የመንግስት ሥልጣን ማን ይዞት እንደነበረ ልንነግራቸው ይገባል::ስንት ጊዜ ከህወሃት ጉያ ተሸጉጠው እንደሚኖሩም ወደፊት የምናየው ጉዳይ ነው::

Comments are closed.

jacki gossee1
Previous Story

ጎሳዬ ቀለሙን ምን ነካው ?

Next Story

In Dexter’s laboratory lives the smartest boy you’ve ever seen

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop