ፕሮፍ. መስፍን ወልደማርያም፡- አማራ የሌለው የት ሄዶ ነው?

ከመለክ ሐራ

እኔ ልናገረዎ የማይገባ ብላቴና ነኝ፡፡ በብዙ ነገር አድናቂዎ እና ብዙዎችን ጽሁፎችዎን ያነበብኩ ነኝ፡፡ አሁን ለያዝኩት ማንነትም የእርስዎ አስተዋጽኦ አለበት፡፡ ይሁንና በአማራ ጉዳይ ላይ ባለዎት አቋም ላይ ከረር ያለ ልዩነት አለኝ፡፡ ሰው መሆን አቅቶኝ እና የጎሰኝነት ስሜት አጥቅቶኝ ሳይሆን ይህ የለም እየተባለ መከራ የሚወርድበት ህዝብ ረፍት ስላጣና ዜግነቱን ስለተነጠቀ እንዲሁም አለሁልህ የሚለው ስላጣ አቅሜ በፈቀደው ሁሉ ልሟገትለት ራሴን ስላዘጋጀሁ እርስዎንም አሻቅቤ ለመናገር ተገድጃለሁ፡፡ ስለራሴ ስል የእርስዎ እምነትና ፍልስፍና ነው ያለኝ፡፡ ስለህዝቤ ስል ግን ከዚህ ሸሽቻለሁ፡፡ እንዳይቀየሙኝ፡፡

የክህደት ቁልቁልት በተባለው መጽሀፍዎ ምእራፍ 11 ላይ ያተቱት የአማራ አለመኖር

አማራ ማለት ሀይማኖት ነው ስላሉ በአለም ላይ ያሉ ትናንሽና ትላልቅ እምነቶች ውስጥ ዝርዝሩን ለማግኘት ብዙ ደክሜ ሳላገኘው ቀረሁ፡፡ አማራ ማለት ክርስቲያን ከሆነ አገው ለምን አማራ እንዳልተባለ እንዲያብራሩልኝ እጠይቃለሁ፡፡ ሁለቱም ቅዱስ ላሊበላ የምትሄዱ አልጋ ባልጋ ነው መንገዱ እያሉ ለዘመናት በአንድ የክርስትና ማእድ ሲሳተፉ ኖረዋል፡፡ አንዱ አገው አንዱ አማራ ሆነው፡፡ አማራው ታዲያ ለምን ሁለት የክርስትና ስም አስፈለገው–አማራ እና ክርስቲያን የሚል? ከተለያዩ ጸሀፍት እንደጠቃቀሱትም አማራ ማለት ነጻ የወጣ ህዝብ (ከአረማዊነት የተመለሰ) ማለት ነው፡፡ ታዲያ አገው ነጻ አልወጣም ማለት ነው? ትግሬ ነጻ አልወጣም ማለት ነው? ወይስ የተለያየ አይነት ክርስትና ነው ያለው–አንዱን ነጻ የሚያወጣ ሌውን ነጻ የማያወጣ? እንደገና በአማራ መሀል የሚኖሩት አርጎባዎች እስላም ናቸው፡፡ ከሌላው እስላም ተለይተው ለምንድን አርጎባ የሚል ስም የያዙት? እነሱ የአርጎባ ጎሳ እስላሞች ሲሆኑ ከአርጎባ ውጭ ያለው ምን ሊሆን ነው?

የጠቀሷቸው ጸሀፍት ወደሀይማኖታቸው የሚያደሉ እንጅ ቁሳዊ ምሁራን እንዳልሆኑ እርስዎ ያውቃሉ፡፡ ከዛም የተነሳ ለእምነታቸው ያደላሉ፡፡ አማራ የሚለውንም የእምነታቸው ዘብ አደረጉት፡፡ ይሁንና አማራ ነጻ ህዝብ የሚለው ራሱ ከጠቀሷቸው ጽሁፎች መረዳት እንደሚቻለው ሀይማኖታዊ ይዘት ብቻ አይደለም ያለው፡፡ ሁለት አንድምታ ነው ያለው፡፡ ወደክርስትና የገባ እና ጦረኛ ሆኖ በነጻነት የሚኖር የሚል፡፡ እርስዎ ግን ጦረኛነቱን ሊያተኩሩበት አልፈለጉም፡፡ ለምን ቢባል ጦረኛነት ክርስትና ከሚለው ትርክትዎ ሊየስወጣዎ ስለሚችል፡፡ እንደሚታወቀው ሰው ወደክርስትና ሲገባ የጎሳ ጦረኝነቱ ይቀንሳል፡፡ እርስዎ የጠቀሷቸው ምንጮች የሚሉት ግን ጦረኛ የሆነና ራሱን ከሌላ ጎሳ ይሁን ከምንም ነገር አስከብሮ የሚኖር ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ጥያቄው ታዲያ ይህ ህዝብ እርስዎ እንደጠቀሱት ከየነገዱ ጦረኛው ተሰብስቦ አማራ ተባለ ወይስ መጀመሪያውንም አማራ የተባለ ጦረኛ ነገድ ነበር የሚለው ነው፡፡ የእርስዎን ትርክት ብንቀበል እንኳ ቤተ አምሐራ የሚለው ነገር ያፈርሰዋል፡፡ ለምን ላስቴዎች ናቸው ይህን የተሰባሰበ ህዝብ አምሐራ ያሉት፡፡ እናም ይህንን አምሐራ ላስታ በቤተምንግስታቸው ዙሪያ አሰፈሩት ወይስ ራቅ አድርገው ቤተ አምሐራ የተባለ ቦታ ውስጥ ወስደው አሰፈሩት የሚለውን ጥያቄ በግድ መመለስ አለብዎት፡፡ ለምን ቢሉ ሁለቱ የሰማይና የምድር ያህል የሚራራቁ ተቃራኒ አስተሳሰቦች ስለሆኑ፡፡

ከአለቃ አስሜ የጠቀሱት “ያልተማረ ጨካኝ ጭፍራ” የሚለው አረፍተ ነገር መላ አማራን ክርስቲያን የማድረግ ክርክርዎን አፈር የሚያበላ ነው፡፡ ለምን ቢሉ ክርስቲያን ሆነ ማለት ጭካኔው አበቃ ማለት ነው፡፡ ክርስቲያን ሆነ ማለት ተማረ ማለት ነው፡፡ የዛ ጊዜ ትምህርት ሀይማኖትን ከማወቅ የዘለለ ሚና ስለሌለው በተለምዶ ክርስትያን ሆነ ማለት የተማረ ማለት ነው፡፡ የሚማረውም የክርስትና ስነምግባርን ነው፡፡ እርሱም ዋናው ትምህርት የአረማዊ ጸባይ የሆነውን ጭካኔን ማስወገድ ነው፡፡ እና እዚህ ላይ ራስዎን ተዋግተው ወድቀዋል፡፡

አንድ የትግርኛ መዝገበ ቃላት አምሐራ የሚለውን የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎ ቅልብጭ አድርጎ አስቀመጠው ብለዋል፡፡ ይህ ደራሲ ከራሱ ያመነጨውን ሀሳብ ነው የጻፈው ወይስ ከሌላ ምንጭ ያገኘውን ነው ብለው መጠየቅ ነበረብዎት፡፡ ጸሀፊው እንዳለው አማራ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት ከሆነ ለምን የትግራይ ሰዎች አማራ አልተባሉም? ወይስ የትግራይ ሰዎች ኢትዮጵያዊ አይደሉም ማለቱ ነው? ቀጥለውም የንቡረ እድን አምሐራ ማለት ከየነገዱ ተሰበስቦ ክርስቲያን የሆነው የእግዚአብሔር ህዝብ እና ፍጹም ሙሉ አንድ አይነት ለሆነው ለኢትዮጵያ ዘር የተሰጠ የሚል የባህታዊ ሀተታ ተቀብለዋል፡፡ እንግዲህ አማራ ማለት የኢትዮጵያ ከእግዜር በጥምቀት የተሰጠ መለኮታዊ ዘር ሀነ ማለት ከባድ ነገር ነው፡፡ አንድ እርስዎ መኖሩን የሚያምኑትን ኦሮሞና ሌላውን ከጨዋታ ውጭ የሚደርግ ነው፡፡ ሲቀጥል ኢትዮጵያዊ ማለት ክርስቲያን ማለት ስለሆነ እስላሞች ኢትዮጵያዊ አይደሉም ማለት ሊሆን ነው፡፡ በዚህም ኢትዮጵያዊ ፍጹም አንድ ዘር የሚለው ሙግት ኢትዮጵያዊነት የማይመለከታቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ስለፈጠረ እዛው ላይ አፈር በላ ማት ነው፡፡ የሆነ ሆኖ አምሐራ ማለት ፍጹም ኢትዮጵያዊ ዘር የሚለው ራሱ ስለዘርና ጎሳ ያለዎትን አረዳድ ፈተና ላይ የሚጥል ነው፡፡ በዘርማ ከሄዱ ብዙ ጣጣ ሊመጣ ነው፡፡ የሰው ዘር ሁሉ አንድ ስለሆነ፡፡ ኢትዮጵያዊ ዘር የሚባል ራሱ የለም በዚህ መንገድማ፡፡ የአማራን አለማዊ ህልውና ለመጻፍ ተነስተው ስለሰማያዊ ህልውናው የሚያትቱ ጽሁፎችን ዋቢ ማድረግ በራሱ መልካም አይመስልም፡፡

ማተብ የሚል ሌላ ሃሳብም ተውሰዋል፡፡ ማተብ ማሰር ክርስትና ነው ከተባለ ማተብ ማሰር የተለየ ክስተትን ተከትሎ እንደመጣ መጠርጠር ያሻል፡፡ ከመጀመሪያው የክርስትና ደንብ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ክርስትናና አማራ ከማተብ ጋር ተያይዘው መገለጽ የጀመሩት ከማተቡ ክስተት በፊት ነው ወይስ በኋላ የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ይህ ጥያቄ ደግሞ ከማተብ በፊት ይህ ህዝብ ማን ይባል ነበር የሚል ሌላ ተቀጣይ ጥያቄ ይወልዳል፡፡ አማራ የለም ብሎ ለመደምደም ይህንን ሁሉ መመለስ ያስፈልጋል፡፡

ሌላው ትልቁ ስህተት አማራ ማለት ሰፊ ነው፤ ማጥበብ አያስፈልግም፤ ጎሳዎች ዝግ ናቸው፤ ማንም ሰው ወደነሱ ገብቶ የነሱን ማንነት ሊያገኝ አይችልም ያሉት ነው፡፡ ይህም ማለት አማራ ጎሳ ስላልሆነ ማንም ቋንቋውን የቻለና ባህሉን የተቀበለ አማራ መሆን ይችላል፡፡ በተጻራሪው ግን ጎሳዎች ዝግ ናቸው ብለዋል፡፡ ይተው እንጅ ፕሮፌሰር፡፡ መቸም ከአይሁድ በላይ ዝግ ነገድ ወይም ጎሳ እንደሌለ ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን መጽሀፍ ቅዱስ ወደይሁዲነት የገባ እያለ የሚጠቅሳቸው አይሁዳዊያን ያልሆኑ ህዝቦች የትየለሌ ናቸው፡፡ በዚህ ብቻ ሳይሆን አማራ በደረሰበት የማህበረሰብ የእድገት ደረጃ ያሉ ነገዶች ወይም ጎሳዎች የእነሱን ባህል ለተቀበለ ሁሉ በራቸው ክፍት መሆኑ ያለና የነበረ ነው፡፡ እዚህ ላይ የአማራ ብቻ ተለይቶ እንደ ተአምር የሚቆጠርበት ምክንያት አይታየኝም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአማራ ባንዳ ሆይ ይብቃህ! ይብቃህ!

በምእራፍዎ መጨረሻ ላይ የአማራ ወደጎሳዊ ማንነት መለወጥ የወያኔ ሴራ እንደሆነ፤ አንዳንድ አማሮች እንዳስተጋቡት እና ኢትዮጵያዊነትን አደጋ ላይ የሚጥል ብለው ስጋትዎን አስቀምጠዋል፡፡ ጥሩ፡፡ ጎሰኛነት የአገር አንድነትን ይጎዳል፡፡ ከሰውነት ደረጃ መውረድ እንደሆነም አምናለሁ-አውቃለሁ፤ እቀበላሁ፡፡ ከዚህ ፍልስፍናዎ ጋር አንዳች ልዩነት አይኖረኝም፡፡ ይሁንና ሁሉም ወደየጎሳው ከረጢት ሲከት እያዩት፤ ሁሉም የራሱን የጎሳ ማንነት የሚቀርጸው አማራን ከመጥላት እንደሆነ እያወቁ፤ ኢትዮጵያዊነት በጎሳ ተመንዝሮ የሁሉም ጠላት በተባለ ነገር ግን እርስዎ የለም በሚሉት ጎሳ ላይ ቢላ እየሳለ፤ እያረደም እያዩ፤ ሽንጥዎን ገትረው አማራ የለም ማለትዎ ለማን አተርፍ ብለው ነው? እውን ይህ ህዝብ አውላላ ሜዳ ላይ የማንም ጥቃት ሰለባ መሆኑ እንዴት ሳይታይዎ ቀረ? አማራ ለኢትዮጵያዊነት ሲባል አፈር ደቸ ይብላ የሚል ፍልስፍና የሚያራምዱ ነው የሚመስሉት፡፡ ይህ ማለት ደግሞ አማራ የሚጠፋባት ኢትዮጵያ ለሌሎች ጎሳዎች አገር እንድትሆን አንጅ ለአማራ እንዳትበጀው ያውቃሉ፡፡ እና ጠፍቶ በጥፋቱ ላይ አገር የሚገነባበት እንዴት ያለ ህዝብ ነው? እና በጠቅላላው በዚህ ጽሁፍዎ አማራን አንዴ ከሀይማኖት፤ ሌላ ጊዜ ከዜግነት፤ አለፍ ሲልም ከጦረኝነት ሲቀጥልም ከኢትዮጵያዊነት ጋር እያምታቱ ጻፉ፡፡

የጠቀሷቸው ጽሁፎች ሁሉ ሀይማኖታዊ ይዘት ያላቸውና በይሆናል የተባሉ፤ ሀቅነት የጎደለቻው የግልሰብ አስተያዮቶች ናቸው፡፡ የእምነት ሰዎችን መጥቀስ ተገቢ ቢሆን እንኳ እርስዎ ከጠቀሷቸው በእጅጉ የሚልቀውን የነገረ ሀይማኖት አዋቂ ፈላስፋ ዘርአ ያዕቆብን ይጠቅሱ ነበር፡፡ ከአራት መቶ አመታት በፊት ጀምሮ የኖረው ይህ ሰው ከአክሱም ወጥቶ ተከዜን ተሻሯል፡፡ ከተከዜ ተሻግሮም የኖረባቸውን ሰዎች “የአማራ ሰዎች” እያለ ነበር የጠቀሳቸው፡፡ ከዚህ ሰው የሀይማኖት እውቀት አንጻር እና ከጊዜውም ርቀት ዋጋ የተነሳ የእርሱን ዘገባ መቀበል የግድ ነው፡፡

በጣም የሚገርመው ነገር እዚሁ ጽሁፍ ላይ አንድ የጎጃም ሰው እንዲህ አለኝ ብለው የዛን ሰው ቃል እንደመደምደሚያ ተጠቀሙበት፡፡ ከዛም የወሎ ሰፋሪዎች ብለው አከሉበት፡፡ በእውነቱ ይህ ትልቅ ጉድለት ነው፡፡ አንድ ሳይንሳዊ ጥናት ቢያንስ መረጃው ሞልቶ ድግግሞሽ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ድረስ አዋቂ ሰዎችን እየፈለገ ማናገር እንዳለበት ያሰምርበታል፡፡ መጀሪያ ብዙ አዋቂ ሰዎችን አፈላልጎ ማግኘት፤ እነሱን በተለያየ አንግል እያመሳከሩ መጠየቅ፤ የታሪክ ድርሳናትን ማገላበጥ፤ እና ያንን የተገኘውን መረጃ በጥንቃቄ አመሳክሮ መተርጎም፤ መተንተንና ድመዳሜ ላይ የሚደርስ ነገር ከሆነ መደምደም ካልሆነ ግን ጥያቀውን ለሌላ ሰው ክፍት አድርጎ መተው የሚሉት ናቸው ዋነኛ ሳይንሳዊ የጥናት ሂደቶች፡፡ እርስዎ ግን ከቃለ ምልልሱም ሆነ ከጽሁፍዎ እንደተረዳሁት ወደጥናት የገቡት መጀመሪያ ደምድመው ነው የሚመስለው፡፡ የለም ብሎ ድምዳሜ ለመድረስ ብዙ ድካም የሚጠይቅ ነው፡፡ የለም የሚል ውጤት ላይ ቢደርሱ እንኳ ከእርስዎ የተለዩ በርካታ አጥኝዎች እስኪያረጋግጡት እና ተመሳሳይ ግኝት ላይ እስኪደርሱ ከመናገር መቆጠብ ተገቢ ነበር፡፡ ምናልባት እንደደንቡ ይመስለኛል ቢሉ ትንሽ የሚመስል ነገር ይሆን ነበር፡፡ ግን ከስሁት ዘዴ ተነስተው የደረሱበት ስሁት ድምዳሜ ነው፡፡

እርስዎ መቸም የአማራ ጉዳየይ ምሁር አይደሉም፡፡ ብዙ ጽሁፎችዎን እንዳነበብኩት ፖለቲከኛ ነዎት፡፡ የፖለቲካ ፍልስፍናወ ደግሞ ሁለንተናዊ ሰውነት ዝቅ ሲልም አንድ ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ ይህ በራሱ ክፋት የለውም፡፡ ችግሩ በዚህ ሚዛን እየለኩ አማራን አለና የለም ማለትዎ ነው፡፡ እንደኔ እይታ የእርስዎ አማራ የለም ድምዳሜ ተቀባይነት ያገኘው በአማራ ላይ ባደረጉት ልዩና ረጅም ጊዜ የወሰደ ምርምር ሳይሆን በሌላው ዘርፍ ባለዎት እውቅናና ተሰሚነት ተጠቅመው ነው፡፡ በእርስዎ የስም ክብደት ነው አማራ የለም የሚለውን አስተሳሰብ ማስረጽ የቻሉት፡፡ ዋናው ቁም ነገር የእርስዎ አለና የለም የሚል ድምዳሜ አልነበረም፡፡ ግን እርስዎ ትልቅ ስም ስላሎዎት አማራን ለመካድና ለመጉዳት ለሚደረገው ርብርቦሸ የእርስዎ ቃል በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቀሰ ጥቅም ላይ መዋሉ ነው፡፡ ይህም አማራ የለም የሚለው ትርክትዎ በአንድ ወገን አማራው በአማራ ዙሪያ መሰባሰብን እንደነውር እንዲቆጥር አደረገ፡፡ በሌላ ወገን አማራ አለ በማለት ጉዳት የሚያደርሱብት ቡድኖችና ድርጂቶች የእርስዎን ቃል እንደ ይለፍ ይጠቀሙበታል፡፡ አማርኛ ተናጋሪ በሚል ድንግርግርም የሚናገርለትና ብሶቱን የሚረዳለት አጣ፡፡ የእርስዎ ሀሳብ ተከታይ የሆኑትም ለአማራ መመቻ እንጅ መመከቻ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ወያኔ በእነርሱ ንዴት አማራን ይመታል፡፡ እነሱ ግን አማራ የለም የሚሉ ናቸውና ይህ አማራ ላይ የሚያርፍ ዱላ የማይሰማቸው ሆነ፡፡

ከመአዛ ብሩ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ

እንደተለመደው ሁሉ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ አማራ የለም አሉ፡፡ ደመደሙ፡፡ በጣም የሚገርመው ጥናት አጥንተው ነው የደመደሙት–እንደተናገሩት፡፡ ግን የጥናትዎ ውጤት ስለ አማራ ህልውና ሳይሆን ስለኢትዮጵያ ህልውና መሰለኝ፡፡ እንዳሉት ያገኙት ገኝት ሶስት ሀይሎች አሉ፡-እነርሱም አካባቢ፡ ሀይማኖት እና ቋንቋ ናቸው፡፡ አንዱ ሲላላ እንዱ እየወጠረ ኢትዮጵያን ጠብቆ ኖረ ነው፡፡ እግዜር ይይልዎትና ይሄ ከአማራ መኖርና አለመኖር ጋር እንዴት እንደሚገናኝ አላውቅልወትም፡፡ አማራ የሚባል ነገር የለም አሉ፡፡ ከማስረጃዎችዎ አንዱ ወሎና ጎንደር፡ ወሎና ጎጃም ምን ያገናኛቸዋል ነው፡፡ ሁለተኛው ሀረር ውስጥ አማራ የሚባሉት ክርስቲያኖች ናቸው ነው፡፡ ሶስተኛው ጎንደር ውስጥ የእስላም መንደር ምናምን የሚባል አይቻለሁ ነው፡፡ አንድ በአንድ እንያቸው፡፡

ወሎና ጎንደር እንዲሁም ወሎና ጎጃም ምን ዝምድና አላቸው ሲሉ የምርዎትን ነው? አንድ ኢትዮጵያ አንድ ነው ብለዋል እዛው ቃለ መጠይቅ ላይ፡፡ ሰው አሁንም እየተጋባ እየተዋለደ ነውና አንድ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ አንድ ሆና ሳለ እንዴት ጎጃምና ወሎ፡ ወሎና ጎንደር ዝምድና ሳይኖራቸው ቀረ? በጣም ያስተዛዝባል፡፡ እዚህ ላይ ከቃልዎ ባሻገር የንግግርዎ ድምጸት ራሱ የሚናገረው አሉታዊ ነገር አለ፡፡ በሞቴ ዝምድና ስንት አይነት ነው በመጀመሪያ? በየትኛውስ የዝምድና መስፈርት እነዚህ ህዝቦች ሳይዛመዱ ቀሩ? ሀቁ ይህ አይደለም፡፡ ምናልባት ወሎ ውስጥ የአገውና የኦሮሞ መኖር ይሆን አማራ የለም ያስባለዎት? እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሁለት አካባቢዎች ብቻ ናቸው ድብልቅ ማንነት ያላቸው፡፡

ንግግርዎ የሳይንስ ጉዳይ ቢሆን ኖሮ እውነታው እንዲህ ነበር መቀመጥ የነበረበት፡-“ወሎ ውስጥ ውስን አካባቢዎች ድብልቅ ቋንቋና የዘር ሀረግ ያላቸው አካባቢዎች አሉ፤ የተቀረው ግን አማራ ነው፡፡” እውን እርስዎ እንደሚሉት የሁለቱ አካባቢዎች ህዝብ ቁጥር ከአማራው በልጦ አማራ የለም የሚያሰኝ አልነበረም፡፡ የዘነጉት ነገር ወሎም ሆነ ጎንደር ወይም ሸዋ ወይም ጎጃም ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ብሄረሰቦች በጣም አንድ አይነቱ ነው፡፡ ምናልባት አካባቢያዊ ዘይቤዎችና ልማዶች ከመኖራቸው በቀር በዋና ዋና መስፈርቶች አማራ ከጫፍ እስከጫፍ አንድ ነው፡፡ በቋንቋ፡ በሙዚቃ፡ በስነቃልና በስነኪን፡ በመልክ፡ በባህርይ፡ በልማድ፡ በታሪክ፡ በመሬትና የአየር ንብረት ጸባይ፡ በምርትና አመራረት፡ በስነልቡና፡ በጠቅላላ እይታ-አለም (worldview): ለረጅም ዘመናት እንደአንድ የፖለቲካና ሚሊታሪ ማህበረሰብ መኖሩና በመሳሰሉት ዋና ዋና አሃዶች ልዩነት የለውም፡፡ እርስዎ ምኑን እንደሆነ አይዛመድም ያሉት ለሰሚው ግራ ነው፡፡ እስኪ በምን በምን አሃዶች የማይዛመድ ሆኖ እንዳገኙት ያስቡና ያብራሩ፡፡ ይሄ የለም ያሉት ዝምድናስ አብሮ መኖርን ሲከለክል፤ ጋብቻን ሲከለክል አዩት? በሀሳብ ተለያይተው ቁርቁስ ውስጥ ሲገቡ አዩ? በቋንቋ ሲለያዩና ሳይግባቡ ሲቀሩ አዩ? በባህርይና በተክለቁመና ሳይመሳሰሉ ሲቀሩ አዩ? እንዴው ምን ልዩነት አዩ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ማይን ካምፕፍ (Mein Kampf) የሂትለር የጥላቻ ማኒፌስቶና ያስከተለው የዘር ፍጅት - ገለታው ዘለቀ

እዚህ ላይ የእምነት ጉዳይ ጠቅሰዋል፡፡ የአንጾኪያ ሰዎች አማሮች አይባሉም፤ እስላሞች ናቸው የሚባሉት ብለዋል፡፡ እንዴ ፐሮፍ.? አንድ ህዝብ ሲጠራ እኮ ከአንጻራዊ ስፍራ ነው፡፡ ማለትም ለምሳሌ እርስዎ የአዲስ አበባ ሰው ነዎት፡፡ ከኢትዮጵያ አንጻር የጉምዝ ወይም የጋምቤላ ኢትዮጵያዊያንን አይመስሉም፡፡ መልክዎ ከወደ ሰሜን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ እርስዎን የሰሜን ሰው ነው የሚልዎት፡፡ ከቆሙበት ቦታ አንጻር ፈካ ያለ ገጽታ ያለው የሰሜን ሰው ነዎት፡፡ ወደ ዩጋንዳ ቢሄዱ አንድ ዩጋንዳዊ ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው የሚልዎት፡፡ እርስዎ፡ ዶር. ነጋሶ ጊዳዳ እና ሽፈራው ሽጉጤ ጉምዝ ውስጥ ብትሄዱ ሶስታችሁም አማራ ናችሁ፡፡ ደቡብ ኦሞ ውስጥ ብተሄዱ ሁላችሁም አማራ ናችሁ፡፡ ሱማሌ ብትሄዱ ሁላችሁም አማራ ናችሁ፡፡ አፋርም ብትሄዱም እንደዛው ነው፡፡ እና የአንጾኪያ ሰዎች እስላም ናቸው መባሉ ምንድን ነው ግርታው? ሁሉም አማሮች ስለሆኑ እስላም አማራና ክርስቲያን አማራ ናቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ አይጠራሩበትም፡፡ ምክንያቱም አማራ ዋናው ማንነት ስለሆነ በዛ መጠራራት አይቻልም፡፡ ክርስቲያኖቹ በተለምዶ አማራ ነን ይላሉ፡፡ ያ ማለት ግን እስላሞቹ አማራ አይደሉም ማለት አይደለም፡፡ ምናልባት ከግራኝ ጦርነት ጋር ተያይዞ የሰለሙትን አማሮች ከአማራነት ወጡ የማለት አዝማሚያ የያዘ አጠራር ሊሆን ይችላል፡፡ ታዲያ አማራ ማለት ክርስቲያን ማለት ከሆነ እስላም ማለት ምን ሊሆን ነው? ነው ወይስ ክርስቲያን እና እስላም የሚባሉ ብሄረሰቦች ናቸው ሊሉ ፈልገው ነው? አማራ አማርኛ ቋንቋ የሚናገር ህዝብ ነው ብለው ስለሚምኑ እንደዛ ካሰቡ እንኳ እነዚህ የገጠር መንደሮች ዋና ከተማ ሆነው አያውቁምና እንዴት ሆነው ከማን ር ተቀላለቀሉ? እንደሚታወቀው የአንጾኪያና አካባቢው ህዝብ ለዘመናት ራሱን ከአጎራባች ብሄረሰቦች ወረራ ሲከላከል የኖረ ነው፡፡ ይህም ድብልቅነቱን እና የቋንቋ ብቻ ማንነቱን የሚያመለከት ሳይሆን ወጥነቱን ነው የሚያመለክተው፡፡

እሽ የሸዋን አማራ አለመሆን ለማረጋገጥ የአንጾኪያ ቀበሌ እስላም መባል በቂ ሆነልዎት፡፡ ምናለበት መላውን ሸዋ ወስደው አንጾኪያን ቢለኳት፡፡ ቢባል ቢባል እንኳ የአንዲት ቀበሌ ህልውና ነው የአብዛኛውን አንድ ክፍለ ሀገር ህዝብ አለመኖር ለማረጋገጥ መዋል ያለበት ወይስ ናሙና መወሰድ የነበረበት ከትልቁ ነው፡፡ የሳይንሱ የአጠናን ዘዴ ግን ከአብዛኛውም ከአነስተኛውም ወካየይ ናሙና መውሰድ እንደሚገባ ነው፡፡ ከመቶው የመላው ሸዋ አስር ድምጽ ቢወስዱ፡ ከአስሩ አንጾኪያ አንድ ይወስዳሉ ማለት ነው፡፡ ይህ የሳይንሱ ህግ ነው፡፡ በሁለተኛ ይሄም አላስኬድ ሲልዎት ወደሀረር ሄዱ፡፡ የወሎና ጎንደርን፡ የወሎና ጎጃምን አለመዛመድ ለማስረዳት ሀረር ሄዱ፡፡ ይሄን ጎንደር ሊሄዱ ጠዳ ተሸኙ እንለዋለን፡፡ ሀረር ውስጥ ያሉት ድብልቆች ናቸው፡፡ ስለዚህ ሁሉንም አማራ ከማለት ምናልባት ክርስቲያኖች ብሎ መጥራት ተገቢ ሆኖ ይሆናል፡፡ አማራው በታሪክ አጋጣሚ ባህሉ የሁሉም ስለሆነ የአማራውን ዋነኛ መገለጫ ክርስትና ቢሰጡአቸው ምኑ ያስገርማል? ደግሞስ የዚህ አካባቢ ልዩ ተጨባጭ ሁኔታ እንጅ የወሎ፡ ጎንደርና ጎጃምን አማራ አለመሆን እንዴት ብሎ ለማረጋገጫ ይቀርባል? ሌላው ክፍተት ደግሞ ከአንድ ወገን ብቻ የሚሰበሰብ መረጃ ተአማኒ አይደለም፡፡ ክርስቲያኖቹ እነዛ እስላሞች ናቸው አሉ ብለዋል፡፡ በጀ፡፡ እስላሞቹስ ራሳቸውን ምን ብለው እንደሚረዱና ምን ብለው እንደሚጠሩ ጠይቀዋል? ክርስቲያኖች አማሮችን ምን ብለው እንደሚጠሯቸውስ መጠየቅ አልነበረብዎትም? በእርግጥ ከሁለቱም ወገን መረጃ መሰብሰብ ነበረብዎት፡፡ የሁለቱንም ወገን እርስዎ እንደሶስተኛ ወገን ሆነው ተርጉመውና አጣጥመው መደምደም ነበረብዎት፡፡ ግን መረጃዎ ሚዛናዊ ስላልሆነ ድምዳሜዎም ሚዛናዊ አይደለም፡፡ ስለዚህ የተናገሩት ነገር አይረባም፡፡ ለምን ቢሉ የጥናቱ ዘዴ ካልረባ መደምደሚያውም አይረባም፡፡

ሶስተኛው ደግሞ የአማራ አለመኖርን ያረጋገጡበት መንገድ በጣም የሚገርም ነው፡፡ ጎንደር ውስጥ የእስላም መንደር ምናን የሚባል አይቻለሁ አሉ፡፡ ምነው ፕሮፍ. ምናምን አይቸ ተብሎ የህዝብን ህልውና የሚመለከት ከባድ ነገር ድምዳሜ ላይ ይደረሳል እንዴ? የጤና አልመሰለኝም፡፡ የእስላም መንደር ምናምን የሚባል አይቸ አማራ አለመኖሩን አረጋገጥኩ ብለው መናገርዎ በእውነቱ ለትልቅነትዎ የሚመጥን አይደለም፡፡ እውነቱ ጎንደር ዋና ከተማ በነበረች ጊዜ አከፋፈልዋ እንዲህ ነበር፡- ሸዋ ሜዳ–የሸዋ ሰዎች የሚያርፉበት፤ ትግሬ መጮሂያ–የትግሬ ሰዎች የሚያርፉበት፤ እስላምጌ–እስላሞች የሚኖሩበት፤ አዲስጌ–ፈላሾች የሚኖሩበት፤ ወለቃ–ፈላሾች የሚኖሩበት፤ አቡን ቤት–የካህናት አካባቢ፤ መሀል ላይ የነገስታቱ መቀመጫ ወዘተርፈ ተብላ የተከፋፈለች ነበረች፡፡ ከዚህ ሁሉ የአሰፋፈር ስምሪት የእስላም መንደር መኖሩ ብቻውን የአማራን አለመኖር ማረጋገጫ ሆነልዎት፡፡ ይህ በእውነቱ ያሳዝናል፡፡ ሀይማኖት ራሱ የነገድ ወይም ጎሳ መለኪያ ሆኖ አያውቅም–በጭራሽ፡፡ በእርስዎ አረዳድ እስላም ስላልሆኑ ብቻ የአሌክሳንድሪያ ግብጾች ግብጻዊያን አይደሉም ማለት ነው፡፡ ካቶሊክ ኖርዲኮች ፕሮቴስታትንት ስላልሆኑ ኖርዲክ አይደሉም ማለት ነው፡፡ ብዙም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ግን ነገር ያረዝማል፡፡

በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ ሁለት ጊዜ ስሜት የሚለውን ቃል አነሱ፡፡ አንዱ አማራ የሚባል አንድ አይነት ስሜት ያለው ህዝብ የለም ብሏል ብለው የዶናልድ ሌቪኒን ድምዳሜ ያለምንም ማንገራገር አምነው የተቀበሉበት ነው፡፡ ስሜት ብቻ ነው እንዴ የአንድ ህዝብ አንድነት መለኪያው? አንድ አይነት ስሜት የለውም ለማለት ስንት አይነት መለኪያዎች ተወስደው ነው እዚህ ድምዳሜ ላይ የተደረሰው? አንድ አይነት ስሜት ማለት ምን ማለት ነው? እንዴያው በሞቴ የአንድ እናትና አባት ልጆች እንኳ በስሜት ደረጃ አንድ አይነት ናቸው? በእርግጥ እርስዎ አማራ ላይ የፈለጉት የስሜትም ይሁን የምንም ነገር አንድነት በአንድ ሰው ብቻ የሚገኝ እንጅ በ35 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ የሚገኝ አይደለም፡፡ እርስዎ የፈለጉትን አይነት ስሜት ማግኘት የሚቻለው አንድ ሰው ላይ ብቻ ነው፡፡ ለዛውም የአንድ ሰው ስሜት ራሱ በየጊዜው ተለዋዋጭ ስለሆነ ረዘም ላለ ጊዜ ከተከታተሉት አንድ አይነት ስሜትና ባህርይ አይደለም ያለው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዲስ ዓመት - በነተበ ሥርዓት

ሌላው ስሜት የሚለውን ቃል የተጠቀሙት አማራ አለመኖሩን ያረጋገጡት በስሜት አለመሆኑ ለማጤን ነው፡፡ እዚህ ላይ መክሽፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ በሚባለው መጽሀፍዎ የስሜትን ጠቀሜታ አትተዋል፡፡ ራስዎ እንደጻፉት ስቬን ሮቢንሰን የተባለው የኢትዮጵያ ታሪክ አዋቂ ነኝ የሚል ብለው የወረፉት የባህር ማዶ ዜጋ አለ፡፡ እርሱም አንድ ቀን ታሪክ ስትጽፍ ስሜትህ ይንጸባረቅበታል አይነት ነገር ተናገረዎ፡፡ እርስዎም እርሱ ስለኢትዮጵያ ሲጽፍ ስሜት የሌለው ኢትዮጵያዊ ስላልሆ፤ እርስዎ ግን የራስወን አገር ሲጽፉ ስሜት እንደሚኖርና ተገቢ እንደሆነ ጠቅሰው “ልኩን” ነገሩት፡፡ እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ችግሩ፡፡ ለኢትዮጵያ ሲሆን ስሜት አለዎት፡፡ ለአማራ ሲሆን ደግሞ ምንም ስሜት የለዎትም፡፡ ለኢትዮጵያ ስሜት ስላለዎ በስሜትም በእውቀትም ተከራከሩላት፡፡ ለአማራ ደግሞ ስሜት ስለሌለዎ “ከስሜት በጸዳ” ምክንያታዊነት ካዱት፡፡ አንዱን ፈረንጅ አማራ አንድ አይነት ስሜት የለም ሲል ለምን እና እንዴት ሳይሉ ተቀበሉ፡፡ ስለኢትዮጵያ ሲጽፍ አላግባብ ተይቧል ያሉትን ፈረንጅ ግን ቁም ስቅሉን አሳዩት፡፡ ከዚህ ተነስቸ እንዲህ እደመድማለሁ፡፡ አማራን ሲክዱት የኖሩት ለአማራ ስሜት ስለሌለዎ ነው፡፡ ለአማራ ስሜት እንዳይኖረዎ ያደረገ ደግሞ አንዳች ነገር አለ፡፡ በስሜት ስለማይጋሩት ህዝብ መጻፍዎ ታዲያ የማይመለከተዎትን ነገር ልወክል ማለት አስመሰለብዎ፡፡ ሲጀመር ይህን አታጥና ይሄን አጥና ተብሎ ሰው ገደብ አይጣልበትም፡፡ አማራን ማጥናት መብትዎ ነበር፡፡ ግን በወጉ አላጠኑትም፡፡ ቢያጠኑ እንኳ ለህዝቡ ያለዎ የስሜት ቀረቤታ የጥናትዎ ውጤት ላይ ያጠላበታል፡፡ እዚህ ላይ የእርስዎ ቦታ በ19ኛው መቶ ክፍለዘመን ለቅኝ ገዥዎች የማህበረሰቡን ባህልና ስነልቡና እያጠኑ የሚሰጡ ጸሀፍትን ይመስላል፡፡

እዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ በኦሮሞ ዘር ቋንቋ ነው፤ በወለጋ ዘር ቋንቋ አይደለም አሉ፡፡ ይህ ማለት ኦሮሞ ማለት ኦሮምኛ የሚናገር፤ ቋንቋውን እንደዘር ማንነት መገለጫ የሚጠቀም ማለት ነው የሚል ይዘት ያለው ነው–እንደተረዳሁት፡፡ በዚህ አረዳድ በእርግጥ ለአማራ ቋንቋ ማለት አማርኛ ማለት አይደለም፡፡ ለአማራ አማራ ማለት አማራ ብቻ ነው፡፡ ለምን ቢባል አማርኛን አማራ ያልሆኑ ሌሎችም ስለሚገሩት ቋንቋው የአማራነቱ መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ ምናልባት አማራነቱ የሚታወቀው በቋንቋው ቢሆን እንኳ አማራ ብቻ የሚናገራቸው አካባቢያዊ የአማርኛ ዘይቤዎች ነው የሚሆነው፡፡ እዚህ ላይ ነው እግዲህ የእርስዎ “አማርኛ ተናጋሪ” እና የእኛ አማራነት ልዩነቱ፡፡ አማራ ያልሆኑ አማርኛ ተናጋሪዎችም ስላሉ አማራው ራሱን በቋንቋው ተመስርቶ ትርጉም ሊሰጥ አይችልም፡፡ ልክ አሜሪካዊያን እንግሊዝኛ በመናገራቸው ብቻ የኢንግላንድ ተወላጆች ሊሆኑ እንደማይችሉት ሁሉ፡፡

እና ቃለ ምልልሱ ላይ እንደተረዳሁት ሀረር የተገደሉት አማሮች ሳይሆኑ የሰላሌ ኦሮሞዎች ናቸው አሉ፡፡ አማራ አለመሆናቸውን እንዴት አወቁ ታዲያ? አማራ ከሌለ ሀረር የተገደሉት እንዴት ሆነው ነው አማራ ያልሆኑት? ምናልባት ኦነግ እነዛን ሰዎች ሲገድል የሸዋ ኦሮሞ ኦሮሞ አይደለም ብሎ ነው የገደላቸው ወይስ አማራና ኦሮሞ መለየት አቅቶት ነው? እዚሁም ላይ የሰላሌን ሰው ኦሮሞነት ሳያቅማሙ ተቀብለው ሲያበቁ አማራን ግን አማራ ለማለት ተናነቀዎት፡፡ እዚህ ላይ የኢሰመጉ መሪ ስለነበሩ አማራ አይደሉም የተገደሉት አልኩ አይነት ነገር ብለዋል፡፡ ምናልባት እዚህ ላይ ሀጢአት ሰርተዋል ብየ አስባለሁ፡፡ በወቅቱ አማራ እየተገደለ ነው ብለው ተናግረው ቢሆን ኖሮ ከዛ ወዲህ እስካሁን የሚገደሉት አማሮች ቁጥር ይቀንስ ነበር ብሎ ማሰብ ይቻላል፡፡ በቀጥታ አማራ ተገደለ ብለው ቢሆን ኖሮ አገዛዙም ከዛ ወዲህ የሌላውን አማራ ተቃውሞ በመገንዘብ ጠበቃ ሊያደርግ ይችል ነበር ብየ አስባለሁ፡፡ ግን የኢሰመጉ ሀላፊ ሆነው የተገደለው አማራ አይደለም ማለትዎ መቸም አሉታዊ ተጽእኖ አልፈጠረም ብሎ ማሰብ አይቻልም፡፡ ኦሮሞ የሆነው ኦነግ አማራ ብሎ ገደላቸው፡፡ እርስዎ ደግሞ አማራ አይደሉም አሉ፡፡ በግርግሩ ምናልባት ከለላ ሊሆናቸው የነበረ አካል ከነበር እጅና እግሩን አሰሩት ብየ እገምታለሁ፡፡ ለኦሮሞ የሚታገል ኦነግ አማራና ኦሮሞ መለየት አቅቶት ኦሮሞ ገደለ ማለትዎ መቸም ማንን እደሚያሳምን አላውቅም፡፡ ኢሳት ላይ የቀረበ የአንድ ከዛ ፍጅት የተረፈ መነኩሴ ቃለመጠይቅ አለልዎት እና ይዩት፡፡ ያ መነኩሴ ስለማን እንደሚያወራ እና እርሱም ማን እንደሆነ እርስዎ በደምሳሳው ከሚክዱት የበለጠ ተአማኒነት አለው፡፡ ከእርስዎ ይልቅ ትክክለኛውን የታሪክ ተሳታፊ ለማመን እገደዳለሁ፡፡

እንደ መደምደሚያ

አንድ ህዝብ ጎሳ የሚሆነው በውስጣዊ እምነቱና ስሜቱ ብቻ አይደለም፡፡ የውጫዊ ግፊቶችም አንድን ህዝብ ቅርጽ የመስጠት አቅም አላቸው፡፡ በዚህ አንግል ካዩት አማራ ከኦሮሞ መስፈፋፋት ጋር ሲፋሎም የኖረ ነው፡፡ ይህም ውጫዊ ግፊት የውስጥ አንድነት እንዲፈጥር አስገድዶታል ማለት፡፡ ይህንን ውጫዊ ገግፊት የተከሰተበትን ጊዜ ብንወስድ እንኳ አራት መቶ አመት ይሆነዋል፡፡ አንድን ጎሳ ለመፍጠር ደግሞ ይህ ክስተት ብቻውን ከበቂ በላይ ነው፡፡ ችግሩ ብዙዎች ስለአማራ ሲናገሩ ከአለም ህዝብ በተለየ ሁኔታ አማራ እስከ አዳምና ሄዋን የደም ሀረግ እንዲመዝ መፈለጋቸው ነው፡፡ ይህ ግን አንድን ጎሳ ሊፈጥሩ የሚችሉት ሁለት አመክንዮዎችን የጣሰ ነው፡፡ አንዱ እኔ በደሜ አማራ ነኝ ብሎ ማመን ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የጠቀስኩት ውጫዊ ግፊትና ይህንን ግፊት ተከትሎ የሚመጣው ፖለቲካዊ ቅርጽ ነው፡፡ አማራ በትውልድም አማራነቱን ያምናል፡፡ እርስዎ አዲስ አበባ በመወለድና ማደግዎ ብዙ የማያውቁት ነገር እንዳለ እገነዘባለሁ፡፡ እኔ ደግሞ ከመሀሉ ስለተወለድኩ አውቀዋለሁ፡፡ አማራ ሲጋባ እስከሰባት ቤት ይቆጥራል–ወደኋላ፡፡ ወደጎን ደግሞ “አጥንተ ሰባራ” እና “ጨዋ” የሚሉትን የማንነት መገለጫዎች ያጣራል፡፡ የዚህ እሳቤ ጥንካሬው እርስዎ ከሚገምቱት በላይ ነው፡፡ ዝርዝሩን አልናገረውም፡፡ ካወቁት ያውቁታል፤ ካላወቁትም ሩቅ ነዎት ማለት ነው፡፡ ወሎ፤ ጎጃም፤ሸዋ፤ ጎንደር ዝምድና የላቸውም ያሉት ትርክት በጣም የማይረባ ነው፡፡ ለዘመናት ሲደጋገሙ የኖሩ የወታደራዊ፤ የንግስና ሽኩቻና መሳፍንታዊ ዝውውሮች ግምት ውስጥ ያላስገባ ነው፡፡ ሁሉም የአማራ ክፍለ ሀገሮች ተራ በተራ አንዱ አንዱን ሲወረው፤ አንዱ አመጸኛ ሰራዊቱን ይዞ ወደሌላው ሲሸሽ፤ እና የመሳፍንቱም ጦር በየጊዜው ኡደታዊ ሰፈራ ሲያደርግ ነው የኖረው፡፡ ይህ ሁሉ ተደማምሮ አማራ ሊገለጽ የማይችል የእምነት፤ የባህርይ፤ የታሪካዊ ውርስ፤ የስነልቡና፤ የአኗኗር ዘዴ፤ የልማድ፤ የስነጥበብና ቋንቋ ወዘተርፈ አንድነት እንዲኖረው አስቻለ፡፡

በመጨረሻም አማራ የለም ባሉበት አንደበትና ብእርስ ምነው ትግሬ ወይም ኦሮሞ አለመኖሩን ሳይጽፉ ቀሩ? ምናልባት የአማራን አለመኖር ለማነጻጸር አጎራባች ጎሳዎችን መዳሰስ አልነበረብዎትም? በእርግጥ አማራ የለም የሚለው ትርክት ምን ጥቅም ያመጣል ብለው አስበው ነው? አሁንስ የጥናትዎን ዘዴ ደካማነት ለመፈተሸና ድምዳሜዎን እንደገና ለማየት ወኔው አለዎት ወይ?

22 Comments

  1. It is interesting article. But the issue is badly framed-Is there Amhara or no? Factually there are the people assuming themselves as Amhara. what is the base for this group to be considered as Amhara-religion, race or geography is controversial. But this controversial base for the identity of the group cannot negate the historical and the present fact. I want to give an example. take the region wollo called before as beteamhara. Whatever you call it as oromo migration or oromo movement except Saint, delanta, last and wag, most of the area was occupied by the oromos claiming then as orormos. but presently most of this region peoples call themseves as Amhara and their language is Amharic except bati and kemise. This is more strengthened after TPLF controls the political power. While TPLF forced the PEOPLES CLAIMING THEMSELES AS AMHARA FROM THE OTHER PARTS OF THE COUNTRY on the contrary it strengthened the Amhara identity in the region called Amhara whatever it is bad or good for the future of Ethiopia.

    The aspect of religion as a base for Amhara identity, take the same area that is wollo. Let me give an example. There is a Shah in Wollo calling him as Borena that is a group of oromo people. And before when a muslim change his religion to Christianty it is called as he become Amhara. And this Shah before according to the standard of being Amhara in the area he was no more amhara but muslim and oromo. after TPLF took power from the derge, this Sheh to make haji in Meca his identity must be established by Ethiopian govt either he is oromo, amhara, etc. And since this sheh speaks Amharic not oromifa he is given an identity of Amhara and he himself presently calls himself as Amhara. Then in this region arguement is made between the son and mother. The son calls himself as Amhara while the mother calls herself as muslim. And the son told her you are amhara and she replied no I am not amhara because I muslim. The son then told her oh mother Sheh …. is amhara and do you know about Islam more than the Sheh?
    Now all muslims in the region particularily the young generation call themselves as Amhara and Amhara as a religion ceased to exist and goes beyond that as an identity. Hence after TPLF rule the concept of Amhara transcends as a transnationality identity but less than Ethiopian identity and transreligion identity incorporating those christians and muslims including those who make tribute to atete(qalu) wuqabi.

    hence please look not only the past history but also what history we are making now for the future generation what Amhara is and what Amhara will mean. Any ways when TPLF is trying to destroy Amhara the concept of amhara embraces muslims, oromos and beyond that those chased immigrants and refugees export amhara to middle east, and to the west together with injera and wot.

    • አንተ አለባቸው እምትባል እውር
      የ ጣፍከው ዝባዝንኬ ከየት ያመጣህው አተላ ነው ባክ? ስማ እኔ የ ወሎ ዋስል ሰው ነኝ አንተ የምትለው ዝባዝንኬ ግን ከየት እንደመጣ አይገባኝም! ምነው የሆነ አይምሮህን የሚበክል መዳኒት ወስደህ ነው እንዴ አንተ እና መሰሎችህ እምትዘባርቀው? የጠቀስከው ምሳሌ እውነት በ እውኑ የሆነ ነው ወይስ በቅዥት? ለነገሩ አይፈረድብህም ምክንያቱም ጵሮፌሰር ተብየው ሼባው መስፍን(የማንነት ቀውስ ዘልቆ የገባው ) ሲዘባርቅ ይደመጣል እና አንተ ተራው የ እሱ ተማሪ ባትዘላብድ ነው የሚደንቀው!
      ስማ ቁዋንቅዋችንን ብታቅ አትዘባርቅም ነበር! እስቲ ይሚከተልወን ስንኝ ተመልከት እና ተረዳ!
      ላሜ ቦራ ስንለ
      በሬው ቦረና እንላለን!
      ቦረና የ ገበሬ አገር ነው ማለቴ የ ስራ የ አራሽ አገር! ግብርናን ያስተማረ ሃገር ነው! አንተ ግን ገና ለገና ቦርና (በ ነገራችን ላይ የ ኦሮሞው ጎሳ ቦረና ተብሎ ሳይሆን ቦረን ተብሎ ነው የሚጠራው)የሚባል የ ኦሮሞ ጎሳ አለና ወሎ ውስጥ ያለውም የ ኦሮሞ ጎሳ አርገከው አረፍክ! የሆንክ ሸለፈታም ነህ! በተረፈ እንደናንተ ግራ የገባቹ እና ግራ አጋቢዎችን ነው የ ቦረና ሳይንት ጀግናው ዋለልኝ አሸቀንጥሮ ከ ፖለቲካው ጨዋታ ውጭ ያረጋቹ! ዳግማዊ ዋለልኞች ደሞ እንቀብራችዋለን! ያነበብከው ጥሁፍም ያመላክትሃል መነሳታችንን!
      ቆሻሻዎች!

      • You gay don’t expose yourself as idiot and crooked. Before you try to argue think to be gentle, honest and truthful. the problem on you is not willing to understand but intentional stupidity which is deviated from the normal course of rationality because of spoiled mind. Be relax, learn more to be polite not as idiot cadre.

      • This comment concerns this “Zehabesha” media owner. If you get the comment I made above is contrary to your media policy, it is up to you to remove it from your page. It didn’t insult any one or defame, simply making a short explanation as to the concept of Amhara with respect to the present context. It is argument on the idea without doing any prejudice on others interest. But for I did this comment someone in the name of “Sayint did a reply to the extent of saying “ewur”(blind). And I respond to him how idiot and stupid he is. Because there is no more enemy for Ethiopia like him from whatever group he is. It is just to let him he must know himself by asking himself who he is. I didn’t ask this media to remove his comment, but why you remove that I responded to him? What is the standard for allowing someone give comment on this page?

  2. Excellent piece! ፕሮፌሰር መስፍን አማራ የለም ማለታቸው በተዘዋዋሪ አማራውን ይጠቅማል ብለው አስበው ካልሆነ የምራቸውን “አማራ የለም” ማለታቸው በየትኛውም መስፈርት ፍጹም ትክክል አይደለም። እውነት ነው የአማራውም ሆነ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ትልቁ ዓላማ በጎሳ ላይ የተመሠረተውን ፓለቲካና አስተዳደር ከአገራችን ማስወገድ ነው። አማራው ለዚህ ትልቅ ዓላማ መሥራቱ መቀጠል አለበት። አሁን ግን የራሱ ሕልውና አደጋ ላይ ወድቋል። ወደፊት ደግሞ ከዚህም የከፋ ነገር ይጠብቀዋል። ይህ እየታወቀ ባለፉት 24 ዓመታትና አሁንም በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፓለቲካ በስፋት እየተከናወነና አማራው በጠላትነት በ”ማኒፌስቶ” ተጽፎ፣ በተግባርም ተዘምቶበት እያለ እርሱን ብቻ ነጥሎ የለም ማለት ፕሮፌሰር መስፍና ባይሆኑ ኖሮ በሌላ የሚያስጠረጥር ነው። የጎሳ ታሪካዊ አፈጣጠር/አመጣጥ ምንም ይሁን ምንም አማራ ነኝ የሚል በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ እያለ እርሱን አማራ አይደለህም ማለት ምን ማለት ነው? ይህን ማለትስ 24 ዓመት ተግባራዊ የሆነውን የጎሳ/የክልል አስተዳደርና የአማራውን መነጠል ማስቀረት ችሏል ወይ? በዚህ ጊዜ እንኳን አማራ ነኝ ብሎ የሚያምነው ሰው ይቅርና በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት (በሚናገረው ቋንቋ፣ በባሕሉና በእድገቱ) ምክንያት እርሱ ሌላ ነኝ/ ድብልቅ ነኝ የሚል ቢሆን እንኳን በሌሎች ዘንድ ግን በአማራነቱ የተፈረጀ ከሆነ ያ ሰው ወደደም ጠላም አማራ ነው። በደም ቢሆንማ ኖሮ አይሁድም አይሁድ አይሆኑ ነበር። ጥቃት ነው ከየዓለሙ ተሰባስበው አንድ እንዲሆኑ ያደረጋቸው። ራሳቸውንም ማዳን የቻሉት “አይሁድ አይደለንም” ባሉበት ጊዜ ሳይሆን “አይሁድ ነን” ባሉበት ጊዜ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል። ጸሐፊውም እንዳለው አማራ የሚባል ጎሳ ከሌለ ፕሮፌሰር የሌሎቹስ ያኢትዮጵያ ጎሳዎች መኖር እንዴት ነው የሚያረጋግጡልን? ዋናው ነገር አማራው አማራ ነኝ ሲል ሌሎች እንዳደረጉት ለመጥበብና ለዘረኝነት ሳይሆን በአስገዳጅ ሁኔታዎች ራሱን ከጥፋት ለመከላከል መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። ይህን እየተጠነቀቀና ከሌሎቹ ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹና እህቶቹና ነፃነት ወዳድ ዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ ጋራ እየተደጋገፈና እየተረዳዳ ከመሰባሰብና ከመደራጀት በስተቀር ሌላ ምርጫ የለውም።

  3. Oops,moment,ahun man yimut,enante sewoch abdachual,weyis tilefadedalavhihu,he is a professor,how anout you?procursor right?we all know when some one write somthing,the first question is,to know who is the writer,if he is tplf agent(telalaki with fake identity) we know the purpose of the writer,since habesha.com is not paid by tplf,it is goi.g ro to be likable.since tplf have alot of fan by mouth,not by heart things alwyas goes wrong behind the door.so the exista.ce of amhara bla bla…we ethiopia donot care about the so called cadre’s propoganda.what we care is to pee on tplf gravwyard inorder to do that we ha e a plan,a plan of peeing on melese zenawi grave yard.

  4. esachew sele Gojjme Amaranetachew kidew

    letawem Amaranetun indekid yefelgalu

    menalba mestachewen ena lijachewen lemasdeset yehon ? huletu ke Tigray selehonu !

  5. ፕኦፍ መስፊን ሰለ አማራ ማነነት በፈት
    እስተ ሰለራሰዎ ማነነት የንገሩን !!!
    የሚናውቅወ ሰለቀድሞ ባለበትዎ ቲግራዋይነት ነው
    የርሶው ዘር ማነው? ጎጃምነበትዎን ኢንደካዱ,, አማራነታችንን ኢንደንኪድ የፈልጋሉ ?
    ያወም ባለቀ ሰአት ክክክክ የሀ ነው የዘመናችን አረጋወ አባት !!! ክክክክክክ

  6. I think we ethiopians play hard with ethnics. People should intitle to call themselves whatever they choose to call themselves. The thing I hated the most is categories ethnics in one religion. After all one should remember that we are a disedent of Adam and eve. Ethiopian will stay long after we gone. It’s better we pass on love for future generations.

  7. Professor is quite right and being referred as Amhara is imposed by the tribal regime for the purpose of eroding national sentiment from the people and mainly to squeeze the territory of Gondar,Gojjam and Wollo and there by to legitimize parts of Wollo and Gondar illegally annexed to Tigray. I am Wolleye not Amhara, as professor already had said it all,Amhara is the people who can speak Amharic and at the same time in some parts of Wollo those who follows Christianity are also referred as Amhara. So professor is quite eight. Social study is not atomic science that should be investigated under laboratory. This government would like to try every thing on our country as they have implemented Federalism on Ethiopia. I donot want to be named Amhara am Wolleye like wise people from Gonder is Gondere and from Gojjam is Gojjame apart from that what we share in common is Ethiopian-ism. So Professor is absolutely right. TPLF always targeted to ridicule our scholars but you always fail to succeed. Who gave you the mandate to call me Amhara while am Wolleye. Human Right emanates from individual right so respect my will. Stop talking your fabricated story and respect my identity. People killed in Harar couldnot be refered as Amhara they are labled as Amhara by the regime that commits that hoorible attrocity for their political agenda to create animosity among Wollloye+Gondere+Gojjame and Oromos.

    • አንተ ከብት! በ ስመ ወሎ ዋስል ትነግዳለ አይደል! የሆንክ ከብት! ሲጀመር የ ወሎ ሰው አይድለህም! ቀጥሎ እኔ አማራ ነኝ ለዛውም ከምንጩ ከ ወሎ! አማራነቴን አስበልጨ ከ ወሎየነት እመርጠዋለው! ግቢቶ? አብየ ይመር መርገም ይድረስብህና አንተ በፍጡም ከወሎ አይድለህም! እኛ ወሎ ስንል አማራ እንዳልን ነው እምንቆጥረው! ወሎ, ጎጃም, ጎንደር, ሸዋ የ ስፍራ ወይም አካባቢ ስሞች እንጂ የ ህብረተሰቡን ማንነት አይገጥም! ስለዚህም ሁለተኛው መለያች ነው! ወሎ ዋስልም የ ጥንት ስሙዋ ቤተ ኣማራ ነው! ስለዚህም እርምህን አውጣ! እንዲ እያላችሁ አማራው ስለራሱ እንዳያስብ, እንዳይደራጅ, ስለራሱ ቀየ እና ማንነት እንዳይቆረቆር, ድምጥ እንዳይኖረው ለመዋጥ እምታደርጉት ስራ አብቅቱዋል! እርሳው! የ ሸባው ፕሮፌሰር አባባል እና አስተያየት ልክ እንደ እድሚያቸው ወደ መቃብር በግብያው ጫፍ ላይ ነው! ስለዚህም ቻው ቻው እንላለን!
      ዘላለማዊ ክብር ለ ቤተ አማራው አንበሳ ወሎየው ዋለልኝ መኮንን! ዋለልኝ መኮንን ለ ጭቁን ብሄረሰቦች ታግሎ አልፉዋል ታያ ለራሱስ ወገን ያንሳል? እንዴት ተብሎ! ዳግማዊዎች ዋለልኞች አፍርቶ አልፍዋል! አዳሜ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እምትይ በ አማራ ስም እምትነግጅ ዘረቢስ መድረሻችውን ፈልጉ!
      የ አብየ ይመር ልጅ
      ከ አደይ እና አማራ ቀበሌ-ደሴ ዙርያ!

  8. One of the best article I have read in recent time!
    The writer proved the confused Professor wrong beyond doubt. People should examine the Professor’s political activism which in most part is destructive. His involvement in Dergu’s infamous “Atari Committee”, Kinijit, and Andenet has been nothing but disgraceful.

  9. መልክ ሃራ:
    የፕሮፌሰሩን ሃሳብ ለመረዳት ስለተቸገርህ(መረዳት ስላልፈለግህ) ይህን መጣጥፍ ለማቅረብ ይህን ሁሉ ጊዜ ባታባክን ጥሩ ነበር ; ከጻፍህ ላቅይቀር ግን እይታየን ልስጥህ::

    በመጀመሪያ ደረጃ ማወቅ የሚገባህ ነገር , ፕ/ር መስፍን የማራውን ስነልቦና አስመልክቶ በፍልስፍና የተመራ አንዲት የራሳቸውን ሃሳብ አንጸባርቀው አያውቁም:: በርግጥ ይህ አባባል ላይገባህ ይችላል:: ምክንያቱም ; በጠቅስኸው መጽሃፋቸው ውስጥ ስለአማራ የተናገሩትን እንኳ ስታጣምመው , “አማራ ማለት ክርስቲያን ነው” አሉ በማለት ነው:: ትክክለኝውን ለማወቅ ከፈለግህ ግን እኔ ተወልጀ ወዳደግሁበት የጎጃሙ ክፍል ብትሄድ ; ህዝቡ በተለምዶ እንኳን ልዩነቱን በተረት ሲገልጽ “እኔና እሱ እስላምና አማራ ነን” በማለት ነው::

    ሌላው ያንተ አይነት ሊገባቸው ያልቻሉና ያልፈልጉ ሰዎች ደጋግመው የሚያንጸባርቁት ፕር መስፍን “አማራ የሚባል ስነልቦናዊ የብሄር ትሥስር አለ” ካላሉ በቀር ; አማራ መሆን የምይችሉ ይመስል ; እራሳቸው ውስጥ የሚንጸባረቅውን የማንነት ቀውስ ; ፕ/ሩ እንዲያክሟቸው መዳከራቸው ነው:: እሽ “አማራ ነን የምትሉ , ለምን አማራ ነው የምትሉትን በአማራነቱ አሰባስባችሁ አታደራጁትም?” ህዝብኮ በውስጥ የተሳለ የአማራ ማንነት ካለ እንደናንተ ያለ መሪ ብቻኮ ነው የሚፈልገው::

    እንዴው ልበለው ብየ እንጅ ; መዓህድ ወደ መኢአድ የተለወጠበት ምክንያት በፕ/ር መስፍን ቅስቀሳ እንዳልሆነ አትስትቱትም:: ኢትዮጵያ ውስጥ የብሄርተኝነት ስሜት ያለው ትግራይ ብቻ ነው:: ከትግራይ ውጭ ያለው ሁሉ ; እንዲሁ ለስሜቱ እና ለብሽሽቅ ድንፋታው “ብሄሩን” ይጠራል እንጅ ; አማርኛ ተናጋሪው በለው ኦሮሞው ; አፋሩ በለው ጉራጌ… ሁሉም ውስጣዊ እኔነቱ ኢትዮጵያዊነት ነው:: ለብዙ የኢትይጵያዊነት እሴቶች መፍለቂያ የሆነው ትግሬው ግን ; “በኢትዮጵያዊነት ውስጥ” እራሱን አስገብቶ ሲመለከተው ; ታሪኩ ፍጹም የበታችነት ; የባንዳነት ; የችጋር እና … ስለሆነ ; ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ትግሬነቱ ብቻ ይሰማዋል:: ለዚህም ትልቁ ማሰጃ ; የወያኔዎች ትሥስርና የትግሬው አብሮነት ነው:: ይሄ ትግራይ እንደሌው ህዝብ ተብድሏል … የሚሉቱ ጋለሞታ ፖለቲከኞች ናቸው እንጅ ሃቁ አንድና አንድ ነው::

    እንዴውም የወያኔዎችን እድሜ ያራዘመው በህዝቡ ስነልቦና እውቀት ላይ ያልተመስረተ የፖርቲ ብዛት በተቃዋሚው ጎራ መስፋቱ እንጅ ; እያንዳንዱን የዘር ፖለቲከኛ መሪ ቀረብ ብለህ ከስሜት በወጣ መልኩ ስታናግረው በኢትዪጵያዊ አብሮነት ውስጥ ቅንጣት ታህል ቅሬታ የለውም:: ከትግሬው በቀር!!!

    ስለዚህ ፕር/ር ለቀቅ አድርግ…

    • ክፍሌ ጎጃሜው ልበልህ? እንደ ሕጣን ስትፈነድቅ ታየኝ! ሰውየ አማራ አይደሉም አራት ነጥብ! ስለዚ ስለማያቁት ወገን ደርሶ መልፍለፋቸው ለምንድን ነው? ወይስ ሽኮኮ አርገን እሳቸውን እና የ እሳቸውን አምሳያ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት እንድናገባ ፈልገው ነው? እኛ ሸኮኮ ማድረጉ ና ጫንቃችን ላይ ይህቺ ኢትዮጵያ እምትሉዋት ጉም ለመጨበጥ የማንንም አጋሰስ መሸከም አቁመናል! ዋለልኝ መኮንን ብዙ ተምረናል! እና እርማችሁን አውጡ! ይህቺ ጉም የሆነች ኢትዮጵያን ለመጨበጥ እናንተ አማራውን ማጥፋት አለባቹ? እስቲ ኦሮሞው , ትግሬው, ወላይታው, ሶማሌው እንዲሸከማት አትለምኑም?
      ሌላው! መዓህድ የፈረሰው ለምንድን ነው? እሱን እማ ሸዋየዎችን ጠይቅ! ይህን ስለ ለ አማራው ለቀሩት ሸዋየዎችን ሳይሆን ከዛ ውጭ ያሉትን! ለምሳሌ እንደ ሃይሉ ሻውል, ጵሮፈ መስፍንን የመሳሰሉትን የ ሸገር ዲቆችን! የውስጥ የ ፖለቲካ ስልጣናቸው! ሲጀመር እነሱ አማራ አይደሉም! ቅልቅሎች ናቸው(ዲቃላዎች) እና አማራ ስትላቸው ይጎረብጣቸዋል! ስለዚህም ሊሆንላቸው አልቻለም! ስማ እኔ እንዳንተ አማረኛ ተናጋሪ ሳልሆን አማራ ነኝ! አማረኛ ተናጋሪ እማ መለስም እኮ ነው! ምነው ጃል! በተረፈ ሁለቱን ለይ! አማረኛ ተናጋሪ እና አማራ! ሁለቱ የ ሰማይ እና የምድር ልዩነት አላቸው! ጵሮፈ አማራውን እስቲ እንየው ማለታቸ ግን አስቂኝ ነው! ምክንያቱም እንደ ሃዲስ ኪዳን ተከታይ ደቀ መዝሙሮች ጌታን በ ሰይፍ መሲ እንዲሆን ሲጠብቁ እሱ ግን በሞቱ ድል ነሳ! እኛም እንደዛው ነን! እና ጵሮ ተሸውደዋል!

  10. የወቅቱ አንገብጋቢ ችግር የማንነት ችግር አይደለም መጀመሪያ የሀገር ህልውና ጉዳይ ቅድሚያ ይሰጠው ወያኔ እድሜውን ለማራዘም በተበተበው ሴራ እራሳችንን አናሳምም ወያኔ ሲወድቅ ሁሉም ነገር ይፈታል ስንነጋገር እና ስንወያይ እንደማመጣለን ስለ እያንዳንዱ ብሄረሰብ ምንነትና ማንነት መልስ የሚሰጠው ታሪክና ወቅት ስለሆነ ጊዜውን ይጠብቅ የወቅቱ ችግር አማራ ማነው ኦሮሞ ማነው ትግሬ ወላይታ….
    ጉራጌ…..አይደለም ይህ ችግር የሆነባቸው ህውሀቶች ብቻ ናቸው ዝም ብለን ወደ ዋናው ትግል እናተኩር ።

  11. Professor Mesfin is not your Enemy!!
    =====================================
    He hasn’t done anything malevolent to the Amhara people! After making a kind of survey he succinctly forwarded his genuine opinions. In fact, he has given the credit how Amhara is a transformed society. He praised Amharas as true Ethiopians rather than ethnocentric. His unanticipated but timely argument was irrefutable by TPLF and most importantly, it was likely to ruin their clandestine project. As Woyane feared and Mesfin stated correctly, the Amhara people failed to accept “Beaden” as their representative. Woyane decided to attack Mesfin and other Ethiopianists relentlessly with all the resource at their disposal (Anybody interested can confirm this by reviewing governmental press releases since then). I hope we all remember the so called “Tigray people and bar of soaps from the same factory saga” during 1997 E.C election. But still Woyane is unable to stop Mesfin! In the contrary, Mesfin’s Ethiopianism slogan is spreading more and resonating loudly here and there. To make it even worse, influential separatist political parties such as OLF and ONLF relinquished their secessionist ideology. After a desperate 20+ year Woyane (Beaden) seem to leave with nothing. Like a mad dog, it started to bite anybody nearby and even chases its own shadow frantically.
    Meanwhile, Mesfin’s comments on Amhara (most of them are edited) are becoming very popular among some Facebook users. Some emotional individuals, even say “Mesfin is Amharas enemy” without knowing why he say so and what his intentions was. They repeatedly say how he dare to say “there is no Amhara”? So, my message for those of you who viewed Mesfin as an enemy of Amhara people you better to consider your decision before you spoil the others mind and post spiteful comments on social media. Because, the one who will benefit most from it is not the Amhara people. But for Woyane (beaden) it is a billion dollar lottery! It may not be true, but it is good to suspect and scrutinize if Woyane is trying to twist Mesfin’s rewarding comments to suit its own purposes. If you are opting to be an Amhara to that of an Ethiopian, it is your choice. You do not need a certificate from our beloved hero!

  12. To the Admin: Why do you not post my comment if you are really neutral and impartial politically. Every time you are dumping my critics. Because they are very critical to the Government for that reason I have decided not to waste my time on your blog but in this particular case I couldn’t find this article somewhere where I could afford to enjoy and exercises genuine freedom of writing without any bias like yours.

    Coming to the point I would like to suggest here it is as follows.

    My honourable Professor Mesfin Woldemariam is right in what he has said regarding to the real existence of a tribe called Amhara. There is no a tribe called Amhara in Ethiopia it is a general reference to the people who can speak Amharic irrespective of the area where they are residing. For that reason there is no a tribe called Amhara whatsoever. The TPLF government would like to impose this name on us against our will because to legitimise the districts (fertile areas) annexed to Tigray through time. From Wollo RAYA KOBO,KOREM,ALEMATA and others from Gondar places like WOLKAYET TSEGEDAY, METEMA,HUMERA and others.

    I am Wolleye not Amhara as a tribe but so long as I can speak Amharic I donot have any objection to be generalized as Amhara based on my efficiency in speaking the language but I am and will remain to be named Wolleye as a tribe if need be not Amhara.

    The TPLF regime has stuck this name to the people of three distinct areas Wollo,Gondar and Gojjam to put them in one bag made by TPLF. With the intension to rob there fertile areas and demolition their real being like Wolleye,Gondere and Gojjame.

    I am proud of being Wolleye then Ethiopian apart from that I do not want to be referred as Amhara rather its a universal reference for any one from Ethiopia capable of speaking Amharic regardless of their ethnic background.

    At the same time as Professor has said it all, it is also used to describe any person following Christianity. So please do not try to ridicule our beloved scholar professor Mesfin Woldemarina.

    The main objective of TPLF is to disgrace a nation and a country and then ridicule scholars and old people.

    So I am Wolleye not Amhara.

    • ከብቱ! ምን እንደምትል ተርድተክዋል? ስማ ዋለልኝ መኮንን ለ ጭቁን ብሄር ብቻ የታገለ ምስሎሃል? ወሎየው ዋለልኝ የ አማራው አንበሳ ለ አማራ ነው የታገለው! ግራው ከ ቀኙ መንጠቁ እንዲህ ነው ጃል! አንተ ግን የ ወሎ ሰው አይደለህም? ዲቆ ነህ! አማራ ማለት ክርስትና ነው ያለህ ደንቆሮ ጵሮፈ ተሸክመ ዙር! ኢትዮጵያ ላትመለስ ተለውጣለች! አማራውም ላይመለስ ባማራነቱ ይገሰግሳል! ኢትዮጵያን የሚሸከም ሌላ ፈልጉ!
      የ ሼህ ወለላ ይመር ልጅ!

  13. ግሩምና ሊነበብ የሚገባው አጭርና ግልጽ ታሪካዊ ድርሳን:: እናት በድባብ ትሂድ ይሉዋል እንዲህ ነው::አዋቂ የሚመስል ነገር ግን ውስጡ ባዶ የሆነ ሰው ከወያኔ ብሶ ወያኔን ደግፎ ሲሞግተን ውስጤ እያረረ ብዙ ጽሑፎችን አዘጋጅቸ ይህን ግትር ሃሳብ ለመምታት አይመጥንም እያልኩ ሳነሳ ስጥል እንዲህ አድርጎ መጥኖ ማስረዳት መቻል መታደል ነው::እንደ ሰማሁት ከሆነ ፕሮፌሰሩ የአማራ ደም አላቸው ይባላል;ምሁር የሚል ስምም ተሰጥቷቸዋል እግዚአብሄር ከክፉ አድነን ምሁር እንዲህ ከሆነ የለንም ማለት ይቻላል:;ለዚያውም ነው እንዲህ ያለው ደረጃ ላይ የደረስነው::የአማራው ጠላትስ አማራ መሆኑን መች አጣነው::ላለፈ ክረምት ቤት አይሰሩም እንዲሉ እኛ አማራዎች ወደፊት የሚበጀን እንዳንደራጅ አስሮ የያዘንን ገመድ በጥሰን ራሳችን መከላከልና መመከት ስንችል አማራነታችንን እንዲያውቁት ይሆናል::
    መለስ አማራ አለ ፕ/መስፍን አማራ የለም የሚለውን እሰጥ አገባ ቭዲዮ ፈልጋችሁ ተመልከቱት በተለይ የዚህ ሰው አድናቂዎች::

    • ነገዱ
      የ አማራ ጠላት አማራ አይደለም! ምናልባት አማረኛ ስም የ ያዘና አማረኛ የሚናገርን አማራ ብሎ መውሰዱ ላይ ነው ጠላታችንን መለየት የሚከብደን! የ እሳቸውን ትውልድ ሃረግ ብታጥና ጉድ ትላለ! ምናልባት ትግሬ ሚስት ስላለቻቸው እሱዋን እና ዘመዶችዋን ለማስደሰት ፈልገው ይሁን ወይም እሳቸውን እና መሰሎቻቸውን የ ፖለቲካ ፍልስፍና ተከታዮችን የ መንግስት ስልጣን ለማስያዝ ሸኮኮ እንድናደርግ መጋበዝ ፈልገው ይሁን አልያም በስተርጅና የሚመጣ ዳሜንሽያ በሽታ ልክፍት እንዲ ባማራ ላይ አፋቸውን መክፈት መርጠዋል! ግና በ ሞት አፋፍ ላይ ስለሆኑ አፍ እየመጠጥን እንሸኛችዋለን! ለምሳሌ አሁን ኦሮሞው አንዳርጋቸው ጽጌ አብዛኛው ሰው አማራ ይመስለዋል. ግን አይደለም! የሚያስቀው ደሞ እሱም ስለ አማራ ጥፉዋል! የሚደንቅ ነው!

  14. For the record, I have no idea as to how such trash talk will be published as a comment by “Alebachew”. Zehabesha must and should filter worthless TPLF cadre comments for the sake of civility. Furthermore, the persecution, killing of Amharas by the TPLF was true while they were in the bushes and it is no different now. They have killed, imprisoned, millions of them. The goal is to eliminate and subdue the rest under the TPLF rule. What Prof. Mesfin wrote is the truth for those who dare to double check facts instead of TPLF’s rubbish propaganda. Wake up and try to think your country in terms of one entity, instead of ethnic lines.

Comments are closed.

Share