ሰኔ 1 (June 8)፡ የሰቀቀን ሰዓት የማይረሳ ትዝታ

June 8, 2013


(ከያሬድ ኤልያስ)
አስታውሳለው ልክ የዛሬ 8 አመት ሰኔ 1 1997 ልክ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ነበር ከረንቡላ ከምንጫወትበት የመዝናኛ ክበብ ባስቸኳይ እንድትወጡ የሚል ትዕዛዝ እዛው በዕለቱ ይሰሩ የነበሩ ሰዎች ይደርሰንና እንወጣለን የተክለዓይማኖት አካባቢ እንደወትሮ ሰው የሚበዛበት ብቻ አልነበረም ይልቁንም ከእድገት በስራ እና ከአለምማያ ትምህርት ቤት ልጆቻቸውን ለማምጣት የሚሮጡት እናት አላስችል ብሏት ከ3 ሰዓት በፊት በሰላም ትምህርት ተምረክ ናሃ ብላ የላከችውን ልጇን በ እነዛ ሰው በላ አጋዚ እንዳትነጠቅ ላይዋ እላይ እንኳን ምንም ነገር ሳታደርግ እንጀራ ከምትጋግርበት ማዕድ ቤት ወጥታ ሩጫዋን ወደ ተክለዓይማኖት ቤተክሪስቲያን ሽቅብ ትወጣለች ሌላዋ እናት ደግሞ ጉሊቷን መተዳደሪያዋን ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ህይወቷን እንደተወች ሌላው ደግሞ መርካቶ በንግድ ስራ ላይ የሚተዳደረው ሱቁን ዘግቶ ወደመኖሪያው እግሬ አውጪኝ ይላል ብቻ የነበረው ሁኔታ ዘግናኝ ነበር
እኔን ጨምሮ 5 ጓደኞቼ የዛሬን አያድርገውና በወቅቱ የምርጫ 97 በጣም ታዋቂ የቅንጅት ቀስቃሽ በአሁን ሰዓት የወያኔ የወጣቶች ዋና ሊቀመንበር ከሆነው ሰው ጋር አብረን ነበርን በዕድሜም በለጥ ስለሚለን ያለንን እሺ ነበር የምንለው ታዲያም ግርግሩ ወደ ተቀሰቀሰበት አካባቢ ለምን አንሄድም ከዚሁ ካልኳችሁ ሰው የመጣ አሳብ ነበር በወቅቱ እድሜ ለቅንጅት መሪዎች ብለን ሰለወያኔ ምንነት ማንነት የዛሬን አያደርገውና ኢቲቪ ላይ በጣም ብዙ ነገር አሳውቀውን ነበር ሰለዚህም ግጭቱ ተቀሰቀስ ወደተባለበት ቦታ አመራን ያው ግን የደረሰነው በርበሬ ተራ ነበር ከዛ ወደላይ ማለፍ ግን አይቻልም ነበር ሆኖም ግን ፌደራል ፖሊስ የነበሩት በአብዛኞቹ ዱላና ዱላ ስለያዙ ብዙም አልፈራንም ነበር ያው አጠገባቸው ጋር ባንደርስም መጮዋችንን ግን አላቆምንም ነበር ግን ብዙም ስላልቻልን እያፈገፈግን ጉዞአችንን ወደመጣንበት ወደሰፈራችን ገባን የወረዳ 3 አካባቢ ከወትሮ ለየት ባለ መልኩ ሰዉ ሁሉ ከቤቱ በራፍ ላይ ሆኖ ከመርካቶ በመመለስ ላይ የነበረውን ወጣት ይመለከትና ይደግፍ ነበር በወቅቱም ፡
አትነሳም ወይ
አትነሳም ወይ
ይሄ ባንዲራ ያንተ አይደለም ወይ የሚለውንና ሌላም እየተዘመረ፦ ከዚህ ሁሉ በኋላ ነበር በግምት ከቀኑ 9፡ 30 አካባቢ ላይ አጋዓዚ የተባለው ወታደር ቀይ ኮፍያቸውንና ስናይፐር መሳሪያቸውን በ1 ፒካፕ 7 ሆነው የመጡትና ይቅርታ ሊያስጠይቅ የማይችልና ታሪክን ለዘላለም ያጠፉበትን ነብስ ማጥፋት የጀመሩት ከዚያማ መሮጥ የቻልነውና ሮጥን ሰው ቤት መደበቅ የቻልነውም እንደዛው ሆነና ያው ዛሬ ላይ ቁጭ ብለን የዛን ግዜ የነበረውን እንደታሪክ እያነሳን እናወራለን ሌላውማ እንደ አድራ አይነቱ የዛሬን ቀን ማየት ተስኖት ሜዳ ላይ ቀርቷል። ከዚያማ ምኑ ቅጡ ወያኔ የፈጸመውን የህዝብ ድምጽ ማጭበርበርን በመቃወም የህዝብ ድምጽ እንዲከበር በአደባባይ በሰላማዊ መንገድ መጠየቃቸን ወንጀል ተደርጎብን በጥይት ተደበደብን፣ ታሰርን እናት ሆይ ደግሞ ልጆቼን በሌሊት መጥተው ወሰዷቸው” ብላ አለቀሰች፣ እናቶችልጆቻቸውን ወደ ሆዳቸው መዋጥ ቢችሉ ኖሮ ያን ግዜ ጥሩ ነበር ። ልጆቻቸውን መልሰው አይውጧቸው ነገር ሆነባቸው እናቶች፣ ሆስፒታሎች በእናቶች ለቅሶዎች፣በቁስለኞች እና በእሬሳ ተሞሉ፣ የገዢው ቡድን ደጋፊ ያልሆነ ወጣት ታሰረ፣ ተጋዘ፣ ተደበደበ፣ ተገደለ እንደደርግ ዘመን፣ ካለ ምንም ክስ እና የፍርድ ቤት ማዘዣ ወታደሮች በየግቢው እየገቡ ወጣቶችን እየለቀሙ ወደማይታወቁ ቦታዎች ወሰዱ፣ እስረኞች ከአካባቢዎች በወታደር የጭነት መኪናዎች እየተጠቀጠቁ ማንም ወደማይደርስበት አካባቢ ተጓዙ፣

በወቅቱ አጠገባችን ጋር በአጋዓዚ ጭንቅላቱን ተመትቶ የሞተው ጓደኛችን እድሜ እዛው ሰፈር ላለ አንድ ሰው በወቅቱ እሱ እና የሰኔ 1 ዝናብ ባይኖር ኖር የጓደኛችን እሬሳም ወደ ሆስፒታል ይሄድና የፈረደባት እናት የደረሰባት ችግር አልበቃ ብሏት እንደገና የልጇን እሬሳ ለመወሰድ ብር ትጠየቅ ነበር ደግነቱ ዝናቡ ፌደራሎቹን ጋብ አድርጓቸው ስለነበር የአድራን ሬሳ ተሸክመን እናቱ ቤት አስገባነው ከዛ በዑላ እዛ አካባቢ ድርሽ እንድንል እንኳን አልተፈቀደልንም አብረን አፈር ፈጭተን ያደግነውን ጓደኛችንን እንኳን ለመቀበር አልታደልንም መጨረሻው ግን የሚያሳዝነው በወቅቱ እኛን ሲቀሰቅሰን የነበረው እና ይሄን ሟች ልጅ ከቤቱ ጠርቶ ወደዛ እንዴሄድ ያደረገው ልጅ በአሁን ሰዓት የወያኔ የወጣቶች ሊቀመንበር እንደሆነ ስሰማ በጣም ገርሞኛል ነገር ግን ይህ ልጅ ከ 19 97 በፊት በጣም ብዙ ክስ ያለበትና በፖሊስ የሚፈለግ ነበር ያው ግን ወያኔ እንደዚህ አይነቱን መጠቀሚያ ሲያደርገው ማየት ደግሞ ያማል ለነገሩ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ያንን በሙሉ ወጣት ሲያስጨርስ እንደዚሁ ክስ የነበረበትን ማለትም በሌብነት በሌላም ነገር ተጠርጥረው በፖሊስ የሚፈለጉ ሰዎችን ክሱ ከትግል መልስ ይሰረዛል እየተባሉ ሄደው ነው ምንም በማያወቁት እንደ እሳት ማገዶ የሆኑት በመጨረሻም ከ8 ዓመት በፊት ሜዳ ላይ በእርኩስ ኢትዮጵያዊ ባልሆኑ አጋሃዚ ተብዬዎች ህይወታቸውን ላጡ ወንድሞቼ ያለኝን ክብር ልገልጽ እወዳለው ለቤተሰቦቻቸውም ሁልግዜም መጽናናትን እመኛለሁ::

afewerek 1
Previous Story

የሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ንብረት እያወዛገበ ነው

BELES inlet
Next Story

ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው? “በሩ ይከፈት፣ በአባይ ጉዳይ አገራዊ አቋም እንያዝ”

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop