March 18, 2015
9 mins read

ድርጅት በሕዝብ ካልተደገፈ የመርካቶ ሱቅ ነው – አማኑኤል ዘሰላም

በአቶ ትግስቱ አወሉ የሚመራው የሕወሃት ተለጣፊው ቡድን መጋቢት 5 ቀን የጻፈውን አንድ መግለጫ አነበብኩ። በአንድነት እና በምርጫ ቦርድ መካከል ስለነበረው ሁኔታ፣ በቂ ሰነዶች ለህዝብ ይፋ ስለሆኑ እዚያ ላይ ማተኮር አልፈልግም። አቶ በላይ ከአንዴም ሶስት ጊዜ በአባላት የተመረጠ ወጣት አመራር ነው።

የአንድነት ፓርቲ በበላይ አመራር በአጭር ጊዜ ዉስጥ ጠንካራ ሆኖ ወጣ። «ምርጫዉን ያለ ቅድመ ሁኔታ እንሳተፋለን» የሚል በወቅቱ ተወዳጅ ያልነበረ አቋም አንድነት ያዘ። እነ በላይ አቋማቸዉን በማስረዳት ብዙዎችን ወደ ጎናቸው አሰለፉ። የፖለቲካ መሪ በሕዝብ ስሜት የሚነዳ ብቻ ሳይሆን ህዝብን አሳምኖና አስከትሎ መሄድ የሚችል መሆን አለበት። ብርሃንና ሰላም ሕገ ወጥ በሆነ መልኩ አላትምም ሲል፣ በርሱ ሲዘጋ፣ የማተሚያ ማሽን እና ጀኔሬተር በመግዛት፣ ሁለት ሳምንታዊ ጋዜጣዎችን ማተም ተጀመረ። ከሰላሳ አራት በላይ ጽ/ቤቶች በየዞኑ ተከፈቱ። ከ480 በላይ የፓርላማ ከ1200 በላይ የክልል እጩዎችን ተዘጋጁ። የምርጫ ማኒፈስቶ በማዘጋጀት ደንዲ በምትባል የንድፈ ሐሳብ ማጋዚን በማተም ለሕዝቡ ለማስተዋወቅ ዝግጅቱ ተጠናቀቀ።

ትግስቱ አወሉ በራሱ፣ ከሕወሃት የተላኩለትን ካድሬዎች አሰባስቦ፣ በነጻ በተዘጋጀለት ትልቅ የሆቴል ቤት አዳራሽ ጠቅላላ ጉባኤ አደረኩ ብሎ አወጀ። ሕወሃቶች ትግስቱን የተለጣፊው ቡድን መሪ አድርገው ሾሙት። «አንድነትን ለመጥቀም ነው። የአንድነት ደጋፊዎች ከትግስቱ ቡድን ጋር ናቸው። የትግስቱ ቡድን ሕግን ያከበራል ፣ ለኛም ይታዘዛል …» በሚል ምክንያት ነበር ምርጫ ቦርድ የአንድነት እውቅና ለትግስቱ ቡድን የሰጠው። በነጋታው እንደ ወንበዴ፣ ይወሃት ታጣቂዎች ምንም፣ አይነት የሕግ መረካከብ ሳይኖር ፣ የአንድነት ጽ/ቤትን ወረሩ። ትግስቱ አወሉ፣ ያ ትልቅ ንቅናቄ ሲደረግበት የነበረዉን ጽ/ቤት ለብቻው ተቆጣጠረ።

በጽ/ቤቱ የሕትመት ማሽኖች አሉ። ግን እየዛጉ ነው። ምንም አይነት የሕትመት ሥራ አይታይባቸውም። ጋዜጣ ብሎ ነገር የለም። በጽ/ቤቱ ኮምፒተሮች አሉ። ምንም አይነት የድህር ገጽም ሆነ የሶሻል ሜዲያ እንቅስቃሴዎች የሉም።

አብዛኛው የአንድነት አባል የሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቅሏል። የትግስቱ ቡድን የሚደገፍ ሊገኝ አልተቻለም። ትግስቱ ብቻዉን ቀረ። በየክፍለ ሃገራቱ ሲደዉል እየሰደቡ ዘጉበት። በነበላይ አመራር ከ1700 በላይ ተወዳዳሪዎች ሊያሰልፍ የነበረው አንድነት አሁን 200 ብቻ ነው እንደሚያሰለፍ የገለጸው፡( ወደ 80 ብቻ ለፓርላማ) ። «የአንድነት አመራር በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለየ በኃላ በተሰጠው የሰባት ቀን እጩ የማስመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ለተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤቶች በ80 ምርጫ ክልሎች ተደራሽ በማድረግ 230 እጩዎችን ለማስመዝገብ ችለናል» ሲል ነው ትግስቱ በመግለጫ ውየገለጸው።

«የአንድነት አመራር በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለዬ በኃላ በተሰጠው የሰባት ቀን እጩ የማስመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ ለተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤቶች በ80 ምርጫ ክልሎች ተደራሽ በማድረግ 230 እጩዎችን ለማስመዝገብ ችለናል፡፡ በዚህ ውስን ቀናት ውስጥ ይህን ያህል እጩ ማስመዝገብ ከአንድነት ቁመና ህዝብ ይጠብቀው ከነበረው ተስፋ አንፃር በእጅጉ ያነሰ ነው፡፡» ሲልም ትግስቱ ራሱ፣ አንድነት ድንክ እንደሆነ አምኗል። ይሄም ታቅዶበት በሕወሃት የተደረገ መሆኑም ግልጽ ማረጋገጫ ነው። የተፈለገው አንድነት በምንም መስፈርት እንዳይወዳደር ነበር። ያስቡት ተሳካላቸው።

ሐፍረትና ይሉኝታ የማያሰማው፣ ሕሊና ቢስና ደካም ሰው በመሆኑ፣ ትግስቱ አወሉ በአንድነት ዉስጥ ለተፈጠረው ሁኔታ የነበላይን አመራር ለመክሰስ ይሞክራል። «ይህንን ሁኔታ ተክትሎ የእነ በላይ ቡድን ከምርጫ ቦርድ ውሳኔ በኃላ በወሰዱት ስሜታዊና ግብታዊ አቌም በታላቅ መስዋአትነት በተመሰረተው ፓርቲ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ አሳድሩዋል፡፡ ለዚህም ነው ፓርቲያችን በአሁኑ ሰአት ተስፋ የተጣለበትን ያህል ሆኖ ያልተገኘው» ሲል በአንድነት ዉስጥ ለተፈጠረው ችግር ጣቱን እነበላይ ላይ ይቀስራል።

በላይ ፍቃዱ አንድነትን የመራው ለሶስት ወራት ብቻ ነው። በሶስት ወራት ዉስጥ ምን እንደተደረገ ለማየት ብዙም ገፍቶ መሄድ አያስፈልግም። ሕወሃት ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ድርጅቱን ሲመራ ምን አላደረገም። ሕወሃት አሁን የወሰነዉን ዉሳኔ የወሰነው፣ በአንድነት ዉስጥ ያለው የለዉጥ ኃይል የሆነው የነበላይ አመራር ከዚህ በፊት ያልተሰራ ሥራ ስለሰሩ ነው። አንድነትን ጠንካራ ተፎካካሪ ማድረግ ስለቻሉ ነው። አራት ነጥብ። ይሄንንም የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ ያዉቀዋል።

አንድን የፖለቲካ ድርጅት ጠንካራ የሚያደርገው የድርጅቱ ስም አይደለም። የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች እንጂ። ከዚህ በፊት ቅንጅትን ቅንጅት፣ አንድነትን ደግሞ አንድነት ያደረገው፣ አሁን ደግሞ ሰማያዊን ሰማያዊ እያደረገ ያለው ህዝብ ነው። ህዝብ ከሌላ አንድ የፖለቲክ ድርጅት እና አንድ መርካቶ ያለ ሱቅ አንድ ናቸው።

እስቲ በዚህ በምርጫ ወቅት የአየለ ጫሚሶ ቅንጅትን ጽ/ቤት ይመልከቱ። እንደዉም የመርካቶ ሱቅ ከዚህ የተሻለ ነው። አንድ ጦማሪ እንደጻፈው ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ጠባቂ ነው ። በምርጫ ቅስቀሳ ድካም የተነሳ በጠራራ ፀሀይ ጋደም በሎ ነው።

እንደነዚህ አይነት አሽኮሎሌና ትርኪምርኪ ድርጅቶች እያሰባሰበ ነው ሕወሃት መድበለ ፓርቲ አለ ለማስባል የሚሞክረው። ጥሩነቱ ግን ይች የሕወሃት ጨዋታ ድሮ የነበረችና የተበላባት ናት። ህዝቡ ያወቃል። ለዚህም ነው እነ ትግስቱና አየለ ጫሚሶ ተደብቀው የሚኖሩት።\

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop