በላተኛው አባ-መላ ከያሬድ አይቼህ

ከያሬድ አይቼህ ፤ ሜይ 20፥2013

Ato Birhanu Damte (Aba mela)

የፓልቷኩ አባ-መላ ሰሞኑን ገኗል። መግነኑ አልከፋኝም … ይግነን … ለሁሉም ጊዜ አለውና። ግን አባ-መላን ብዙ ጊዜ አዳምጨዋለሁና የአባ-መላን ነገር መዳሰስ ፈለኩ። ሰሞኑን አባ-መላ ገዢውን ፓርቲ መተቸት ጀምሯል። ይህንን የሰሙ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በጣም ፈንጥዘዋል ፡ እኔ አልፈነጠዝኩም። ለምን?

አባ-መላ የሚናገረውን ነገር በየሳምንቱ ፡ አንዳንዴ አልፎ አልፎም ቢሆን ፡ አዳምጨዋለሁ። አባ-መላ የሚያረገውን የሚያረግው ለአንድ አበይት ምክንያት ብቻ ነው፦ የግል ጥቅም። አባ-መላ ሌላ ንዑስ ምክንያት የለውም። የሚያደርገው ፡ የሚናገረው ፡ የሚተነፍሰው ፡ የሚስቀው ፡ የሚያለቅሰው … ወዘተ … ለግል ጥቅሙ ነው (ለግል ጥቅሙ መቆሙ መጥፎ ነው ማለቴ አይደለም ፡ ያ ምርጫው ነው)።

በ2008 እ.አ.አ. አባ-መላ ክፍል ውስጥ አስተዳዳሪ የነበረ ሰው (“addis_ababa_1”? በሚል መጠሪያ ስም ሚሳተፍ) ክፍሉ ውስጥ በተነሳ ቅራኔ ምክንያት የክፍሉን ሚስጥር በተቃዋሚ ክፍሎች ውስጥ ገብቶ ሲናገር ሰምቻለው። ከተናገረው ሚስጥር አንዱ ፡ ቃል በቃል ባላስታውስም ፡ አባ-መላ ከሚድሯክ ወይም ከሼህ መሃመድ አልሙዲ በአመት $50,000 ዶላር እንደሚከፈለው ነው። ይሄ ነገር የአባ-መላን ባህሪ እና የፓለቲካ ፕሮፓጋንዳ ትኩሳት ለመረዳት ወሳኝ መረጃ ሆኖ አገኝቼዋለሁ።

አባ-መላ የሚያደርገው ነገር ሁሉ ከሚድሯክ ጥቅም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነው ብዬ አምናለሁ። የሚድሯክ ጥቅም ሲከበር ፡ አባ-መላ ለኢህአዴግ እስክስታ ይወርዳል። የድርጅቱ ጥቅም ስጋት ላይ የወደቀ ሲመስል ፡ አባ-መላ ደረቱን ይመታል።

አባ-መላ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆኖ አያቅም። አባ-መላ የሚድሯክን ገጽታ የሚያሽሞነሙን ፡ የደርግ ስርዓት ያፈራው ፡ አንደበተ ምላጭ ፡ የሚያደርገውን የሚያቅ ፡ ፕሮፓጋንዲስት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሎሬት ህመሙ ቢያመኝ!

ታዲያ ምነው ሰሞኑን የፓልቷክ ተቃዋሚ ክፍሎች ባዶ ሆነው የሲቪሊቲ ክፍል ሞልቶ የፈሰሰው? ተቃዋሚ ባካችሁን በአባ-መላ አትበሉ። አባ-መላ ሚያደረገው ሁሉ ለአገራዊ ጥቅም ብሎ ሳይሆን ለግል ጥቅሙና ለሚያገለግለው ድርጅት ጥቅም ብቻ ብሎ መሆኑን እንገንዘብ።

ሚድሯክ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የስራ እድል የከፈተና ፡ አያሌ ካፒታል ያፈሰሰ ድርጅት በመሆኑ ድርጅታዊ ገጽታውንና ጥቅሙን መንከባከቡ ተገቢና የሚጠበቅ ነው። ሆኖም ግን የገዢው ፓርቲ ተቃዋሚዎች በሚድሯክ እና በኢህአዴግ መካከል ሆነን ልንፈጭ ነውና ፡ በአባ-መላ የፓለቲካ ስልት እንዳንበላ ጠንቀቅ እንበል።

አባ-መላንም ሆነ ሌሎች ገዢው ፓርቲን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚደግፉ ሰዎችን ተስገብግበን ወደ ተቃዋሚው ጎራ መጨመር የለብንም። በጊዜ ውስጥ ሊፈተኑ ፡ አመኔታችንን ቀስበቀስ ሊያገኙ ይገባል እንጂ ተንሰፍስፈን መርዝ ይሁን መድሃኒት እንደያዙ ሳናቅ አንቀበላቸው።

ወቅቱ የህወሃት/ኢህአዴግ መጨረሻ ወቅት ነውና የሚደናበሩትን የገዢውን ፓርቲ በላተኞች ለጥቅማችን እንጠቀምባቸው እንጂ እነሱ አይጠቀሙበን።

_ _ _ _ _ _

ጸሃፊውን ለማበረታታት ፡ ለመውቀስና ለማስፈራራት በዚህ ይጻፉ፦ yared_to_the_point@yahoo.com

 

8 Comments

  1. Tiru bileha ato Yared. ke and amet akababi befit semechew nebber yihen afe-choma. chilite yale lesemiw yemizegenin yewoyane degafi nebere. Ena ahun min tegegne? Yihe yefitefaw sew kale, esu bequmu yemote bicha new!

  2. The long walks of Aba Mela. He begun his journey by joining the Eprp, then Anja, then a Derg Cadre, then a Woyane Cadre, and today an icon of Qale room and tomorrow???? Where will his destination lead him before he finally turns to dust and his waggling tongue get rest..?

  3. ato yared what are you talking ? i know aba mela almost five years but i do not know you , how can i believe you ? please do not judge some one with out evidence,,,,,teregaga bro ,,tplf must go down by any means,,so do not be,,,,

  4. leba belew esun blo degmo “aba mela” hodam woyane new esu degmo oromo negn sil ayafrm… ye oromia ljoch be dur be gedelu sigedelu sitaseru sigerefu woyanen neber midegfew esu aba mela meta kere legna mnem lewt yelewn jib woyane new esu

  5. We are tired of people judging people rather than ideas. I thought you ae going to argue his stand. But you take a typical weyane cadre position, character asassination. WHat he is saying is the misdoings of weyane gone beyond defendable. he is saying ‘though I’m enjoying the ‘shake alamudi bonus’, i don’t have any more consious to defend the undefandable’. The irony is you r still enjoing the ‘bonus’ and denfending the undefendable. Moron

  6. aba mela lemin genene? its simple because he gave interview for ESAT so if weyan want to addresse diaspora they have to use Esat ………..

  7. እባካችው እየተስተዋለ እስቲ ምን ኣዲስ ነገር ኣይቶ ነው ኣሁን ግልብጥ ያለው? እውነት የሚናገረው ኣሳስቦት ነው ብላችው ታስባላችው? እኔ የሚመስለኝም በትክክል የማምንበትም ይህ ሰው ዛሬ ይሄን ለማለት ያነሳሳው ልናገር።

    ታስታውሱ አንደሆነ ኢትዮጵያ ከ ኤርትራ ጋር በነበረባት ጦርነት ከባድሜ መለስ ወደ መለስ ተብሎ እንደነበር ታስታውሳላችው፤ ታዲያ የመለስና የበረከት ግሩፖች ከተቀረው ኢትዮጵያዊ ጋር ጥሩ ቅርርብ የታህትን ግሩፕ እያጥላሉ “እኛ የታገልነው ለሚትዮጵያ እንጂ ለትግራይ ብቻ ኣይደለም አንዳንድ አክራሪዎች እና ጎጠኞች ሙሰኞችም” አያለ በእንደ አባ መላ መሰሎችን ነበረ የተጠቀመው እና አሁንም እነበረከትን ለመጥቀም በእነሱ የታዘዘውን ስራ እየሰራ ነው። ግዜ ይስጠን እናየዋለን

Comments are closed.

Share