የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ፣ ግንቦት7 እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን ስምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል። ሶስቱ ድርጅቶች በላኩት ጋዜጣዊ መግለጫ ከዚህ በኋላ የህወሃት ወያኔን እድሜ የማሳጠሩ እና ሀገራችን ነጻ የማውጣት ሂደቱ በተናጥል የሚደረግ አለመሆኑን አመላክተዋል።
ሶስቱ ድርጅቶች የወያኔን መንግስት በሃይል ለመጣል ከሚንቀሳቀሱት ንቅናቄዎች ዋናዎቹ ሲሆኑ፤ በአሁኑ ሰአት ሌሎች ተመሳሳይ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል። በተለይም የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ በወያኔ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ የትግል አቅጣጫው የተቀየረ እና የኢትዮጵያ ህዝብና ለነጻነት እንታገላለን የሚሉ ድርጅቶች ወደ አንድ ጎዳና እየመጡ መሆናቸው በርካታዎችን ያስደሰተ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰአት ማህበረሰቡ ተንካራ የሆነ እንቅስቃሳሴ ማየት እንደሚሻ በተደጋጋሚ እየጠየቀ ሲሆን፤ አሁን የጀመረው የስምምነት መስመር ምናልባትም የነጻነት ሃይሎች በከፍተኛ ደረጃ ትግሉን ግብ ለማድረስ የተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያሳይ ምልክት ነው ሲሉ አንዳንድ ከዜናው በሆላ ያነጋገርናቸው ሰዎች ይገልጻሉ።
ግንቦት 7 በተዳጋጋሚ ጠንካራ የሆነ በወያኔ ላይ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል።
እንደሚታወቀው የአርበኞች ግንባር ንቅናቄ በወያኔ ወታደሮች ላይ የተለያዩ ጥቃቶችን እየፈጸመ ይገኛል። ይህ የውህደት መስመር ስምምነትም ይህን የተጀመረውን መራራ ትግል ወደ አንድ በማምጣት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ስራ ለመስራት እንደሚያስችል ይታመናል።