June 30, 2014
3 mins read

ድምጻዊ ተመስገን ገ/እግዚአብሔር (ተሙ) አድናቂ መስላ ያልሆነ ፎቶ ስለለጠፈችበት ወጣት ተናገረ

“ትግስት የፈተናዎች ሁሉ ማለፍያ ድልድይ ናት”

(ዘ-ሐበሻ) ከሰሞኑ በማህበራዊ ድረገጾች ላይ መነጋገሪያ የሆነው ድምጻዊ ተመስገን ገብረ እግዚአብሔር ነው። አንዲት በስዊዘርላንድ የምትኖር ወጣት የመልበሻ ክፍሉ ድረስ አድናቂ መስላ በመግባት አስገድዳ እንደመሳም አድርጋ የተነሳችውን ፎቶ በመልቀቅ የድምጻዊውን መልካም ገጽታ ለማጥፋት መሞከሯ መነጋገሪያ ሆኗል። እነዚህ ፎቶዎች መለቀቃቸውን ተከትሎ በአውሮፓ እየተዘዋወረ ሥራዎቹን በማቅረብ ላይ የሚገኘው ድምጻዊው በፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት እንዲህ ብሏል:-

የተከበራቹ አድናቂዎቼ በሙሉ

ከታች የምትመለከቱት ፎቶ በ June 27,2014 በ ዙሪክ(Zurich, Swiss) በነበረኝ ኮንሰርት ላይ የመድረክ ስራዬን ጨርሼ ባክ ስቴጅ ከመግባቴ ገና ከላዬ ላይ ያለው ላብ ሳይደርቅ አድናቂዎቼ ከኔ ጋር ፎቶ ለመነሳት ከገቡት ውስጥ ይቺ ፎቶ ላይ የምትመለከቷት ወጣት ከኔ ጋር ፎቶ እንድትነሳ በጠየቀችኝ መሰረት አብረን ፎቶ ለመነሳት ባረገችው ከልክ ያለፈ አድናቆቷን ባከብርላትም ፣ ነገር ግን ከልክ ያለፈ የፎቶ አነሳሷን አልተቀበልኩትም ነበር።

በነበረው ግርግር እንዲህ ማድረግ እንደሌለባት እየነግርኳት ባለው ሰዓት ውስጥ ፎቶው ተነስቶ ነበር።

እኔ አድናቂዎቼን የማከብር ከመሆኑም ባሻገር አግባብ ባለው ሁኔታ ከአድናቂዎቼ ጋር ፎቶ መነሳትን አከብረዋለው። ሆኖም ግን በተገቢውና ባግባቡ ሲሆን ብቻ ነው። ስለዚህ ይህ ፎቶ ከኔ ፍላጎት ውጪ የተደረገ በመሆኑ አልተቀበልኩትም ፣ አድናቂዎቼም በእኔ ላይ መጥፎ አመለካከት እንዲኖራቸውም አልሻም።
ተመስገን ገ/እግዚአብሔር (ተሙ)
“ትግስት የፈተናዎች ሁሉ ማለፍያ ድልድይ ናት”

በበለጠም በሸገር ኤፍ ኤም የሬድዮ ጣብያ በአሁኑ ቅዳሜ ምሽት በኢትዮጲያ አቆጣጠር ከ 3 ሰዓት በኋላ መግለጫ እሰጣለው

ውድ አንባቢያን በዚህ ጉዳይ ምን ትላላችሁ? *

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop