June 21, 2014
14 mins read

Health: የባህል መድሃኒት (ዶ/ር ቁምላቸው አባተ)

ዶ/ር ቁምላቸው አባተ (ሜዲካል ዶክተር)

ባህላዊ ህክምና በነባር (ኢንዲጂኒየስ) ኀልዮቶች፣ እምነትና ልምዶች ላይ የተመሰረተ የእውቀት፣ ክህሎትና ድርጊት ድምር ውጤት ነው፡፡ ጤናን ለመጠበቅ እንዲሁም በሽታን ለማወቅ፣ ለመከላከል ብሎም አካላዊና ስነ አእምሯዊ ህመሞችን ለመሻር ወይ ለማከም አይነተኛ ጥቅም ያበረክታል፡፡

ባህላዊ ህክምናዎች ከቀዳሚ ባለቤቶች ውጪ ሲጠቀሙት አማራጭ ወይም አጋዥ ህክምና በሚል ስያሜ ይጠራሉ፡፡

ዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት በአንዳንድ እንደ እስያ እና አፍሪካ ሃገራት ለመጀመርያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ባህላዊ ህክምናን እስከ 80 በመቶ ያህሉ ኗሪ እንደሚጠቀመው ያትታል፡፡ በኢኮኖሚ በበለፀጉ ሃገራትም ከ70 እስከ 80 በመቶ ያህሉ ኗሪ የሆነ አይነት አጋዥ ወይም አማራጭ ህክምና ተጠቅመው ያውቃሉ፡፡

ባህላዊ መድሃኒቶች በአንዳንድ ማህበረሰቦች ለዘመናት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ እየዋሉም ይገኛሉ፡፡ የአዳዲስ ማህበረሰቦች ተጠቃሚነት እየጨመረ በሄደ ቁጥር እክሎችም ይታያሉ፡፡ በተለያዩ ዓለማት እየጨመረ የመጣው የባህል መድሃኒት ዓለም አቀፍ ደረጃውን(ጥራቱን) የጠበቀ መድሃኒት ስለመውሰድ በቂ(ተመጣጣኝ) መገምገሚያ መንገድ አልተዘጋጀለትም፡፡ ብዙ ሃገራት የባህል መድሃኒትን ያማከለ ፖሊሲ የላቸውም፡፡ በተለያዩ ሃገራት የባህል መድሃኒቶች፣ አጠቃቀምና የባህል መድሃኒት አዋቂዎችን እንዲሁም የባህላዊ ህክምናዎች አተረጓጎምና አከፋፈል ልዩነቶች የተነሳ ለቁጥጥር አመቺ አይደለም፡፡

አንድ የተፈጥሮ ተክል ውጤት ምግብ፣ ተጨማሪ ምግብ ወይም የባህል መድሃኒት ሊሆን ይችላል፡፡ (ይሄ እንግዲህ እንደየሃገሩ ሊለያይ ይችላል) በየሃገራቱ ያለው የመድሃኒቶች ቁጥጥር (ፖሊሲ) ልዩነት በሌሎች ሃገራት ሊከተል የሚችለውን የባህል መድሃኒት አቅርቦትና ስርጭት ሊያከብደው ይችላል፡፡ የባህል መድሃኒቶችን ጥቅም (ጤናማነት) እና ውጤታማነት አስመልክቶ በቂ ሳይንሳዊ መረጃ አለ ለማለት ያዳግታል፡፡ ምንም እንኳ በዓለም ሁሉ በሰፊው ጥቅም ላይ የዋሉና ውጤታማ የሆኑ ባህላዊ መድሃኒቶችም ይሁኑ ህክምናዎች ቢኖሩም ስለውጤታማነታቸው ተጨማሪ(ተከታታይ) ጥናቶች ማካሄዱ መልካም ነው፡፡ ከጤናማነትና ውጤታማነታቸው ባሻገር ጥራታቸው ምን ያህል እንደሆነ ማወቅ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ትልቅ ፋይዳ ያበረክታል፡፡

የባህላዊ ህክምናን ጥቅም ለማስቀጠል በቂ እውቀት ያስፈልጋል፡፡ ለምን እንጠቀመዋለን? መጠኑ ምን ያህል መሆን ይገባዋል?. . . ወዘተ የሚለው በመረጃ ተመዝግቦ ተጨማሪ ጥናት ተደርጎበት ለትውልድ ማስተላለፉ መልካም ነው፡፡

የህሙማን(የባህል መድሃኒት ተጠቃሚን) ጤና አጠባበቅና ጥቅም በተመለከተ አዘውትሮ የሚዘነጋው ነገር የባህል መድሃኒቶች ጉዳት የማስከተል እጣ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ‹‹ትክክለኛ›› የባህል መድሃኒቶች የእፅዋት ውጤቶች (የተፈጥሮ)ስለሆኑ ጤናማ ናቸው ወይም ጉዳት አያስከትሉም ብለው ያምናሉ፡፡ ነገርግን የባህል መድሃኒቶችም ይሁኑ የባህል ህክምና ጥራት ከሌለው፣ በወጉ ጥቅም ላይ ካልዋለ ወይም ደግሞ ከሌሎች ያልተገቡ መድሃኒቶች ጋር ከተወሰደ ያልተገባ ብሎም ለጤና ቀውስ የሆኑ እክሎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም የህሙማንን ግንዛቤ ለመጨመር ያስችል ዘንድ ውጤታማ መንገዶችን ለማሳየት የሙያተኞች ምክክር መሰረታዊ ሚና ይጫወታል፡፡

(በእርግጥ የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት የባህል ህክምናን እንደ አንደኛ የመጀመርያ ደረጃ ህክምና ይቆጥረዋል፤ ይሄም እንክብካቤን ለማዳረስ እንዲሁም እውቀትንና ሃብትን ለማቆየት ይጠቅማል፡፡ ከዚህም ባሻገር የህሙማን ጤናም እንዲጠበቅ የባህል ህክምና የሙያተኞችን እውቀትና ክህሎትን ለማጎልበት ያግዛል)

የባህል ህክምና እንደሚታወቀው በሃገራችን ኢትዮጵያ ረዥም ታሪክ አለው፡፡ ወደ 90 በመቶ የሚሆነውም ህዝብ ተጠቃሚ እንደሆነ ይገመታል፡፡ አጠቃቀሙ በራስ አቅም፣ በወዳጅ ዘመድ ወይም በባህል ሃኪም ትእዛዝ ሊሆን ይችላል፡፡ በአዋጅ ለመጀመርያ ጊዜ እውቅናን ካገኘም ወደ 70 ዓመት አካባቢ ይሆነዋል፡፡ የጤና አቅርቦቱንም ለማስፋት እንዲሁም ውጤታማ ለማድረግ ከዘመናዊ ህክምናው ጋር ማስተግበር መልካም ነው፡፡

የተፈጥሮም ይሁን ዘመናዊ መድሃኒቶች አሰራራቸው ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፡፡

የሚከተሉት ከብዙ በጥቂቱ ያመሳስሏቸዋል፡፡

  1. ቁጥጥር እና ክትትል የሚደረግባቸው፡- በትእዛዝም ይሁን ያለ ትእዛዝ የሚወሰዱ መድሃኒቶች ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት ጤናማ መሆናቸው፣ ዓላማ ያደረጉትን ህመም የሚያሽሉ፣ የሚያድኑ ወዘተ መሆኑ ይረጋገጣል፡፡ የባህል መድሃኒቶች ግን በተጠቃሚው ላይ ጉዳት የማስከተል አለማስከተል ጥናት እንዲያደርጉ አይገደዱም፡፡ ከዚህም ባሻገር መድሃኒቶች ሊያስከትሉ የሚችሉትን ተያያዥ ጉዳት (መጥፎ ችግር) እንዲመዘግቡና ሪፖርት እንዲያደርጉ ግዴታ አይጣልባቸውም፡፡
  2. ቁጥጥር የሚደረግባቸው መድሃኒቶች በአጠቃላይ የተጣሩ ውህዶች ናቸው፡፡ ከተደረገባቸው መሰረታዊ ምርመራ መካከል መድሃኒቱ ጤናማ መጠን ምን ያህል ነው? አንዱ ከሌላኛው እኩል መጠን አለው ወይ? የመሳሰሉትን ማረጋገጥ ይጠቀሳል፡፡ ለምሳሌ ፓራሲታሞልን በወሰዱ ቁጥር አንድ አይነት መጠን ለው መድሃኒት እንደወሰዱ ይሰማዎታል፡፡ ከዚህ አንፃር በአንድ ብልቃጥ ወይም በሌላ መለኪያ የተሰፈረ የባህል መድሃኒት ከሌላው በመጠንም በይዘትም ላይመሳሰል ይችላል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ጤናን ሊያውኩ የሚችሉ ንጥረ ነገሮችንም ሊይዙ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ጥሩ ያልሆነ ጉዳይ በባህል መድሃኒት (ከተፈጥሮ በመነጨ ህክምና) ስም በማዘዣና ያለማዘዣ የሚወሰዱ ዘመናዊ መድሃኒቶችን እየቀመሙ መስጠት ነው፡፡ በውጪ ሃገር የተሰሩ ጥናቶችም ይሄንኑ አረጋግጠዋል፡፡ (ለምሳሌ ያህል አስፕሪን፣ቪያግራ እንደ ኮርቲሰን አይነት ሆርሞኖችን የያዙ የባህል መድሃኒቶች እንዳሉ ተረጋግጧል፡፡)

ለብዙ ሰዎች መድሃኒት መውሰድ የእለት ተእለት ልምዳቸው ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህ መድሃኒቶች ህመሞችን ለማከምና ጤናን ለማሻሻል የሚሰጡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳ የጥቅማቸው ነገር ባይዘነጋም የባህል መድሃኒቶችም እንደ ዘመናዊ መድሃኒቶች(ምናልባትም ከላይ በጠቀስናቸው ምክንያቶች የተነሳ በባሰ ሁኔታ) ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ጉዳታቸው ከቀላል እስከ ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ መድሃኒቶችን በምንጠቀምበት ጊዜ ጥቅምና ጉዳታቸውን ማመዛዘን መልካም ነው፡፡ ጥቅሙ ከጉዳቱ በልጧል ማለት መድሃኒቱን ቀጥታ መጠቀም እንችላለን ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ ይሄ የሆነበት ምክንያት መድሃኒት ስንጠቀም የተለያዩ ጉዳቶች የማድረስ እድል ስላላቸው ነው፡፡

  • የባህል መድሃኒቱ ከሌሎች መድሃኒቶች፣ ከምግብ ከመጠጥ . . . ወዘተ ጋር ሊፈጥር የሚችለው መጥፎ ግጭት፡፡ ውሑዱ (መደባለቁ) ሊፈጥር የሚችለው ግጭት መጥፎ የመሆን እድሉን ይጨምረዋል፡፡
  • መድሃኒቱ ይሰራል ተብሎ የተውን ያህል ላይሰራ ይችላል፡፡
  • መድሃኒቱ ይባሱኑ ተጨማሪ ጉዳት የማስከተል እድልም ይኖረዋል፡፡ ማንኛውንም መድሃኒት በሚወስዱበት ጊዜ ሊያገኙት ስለሚችሉት ጥቅም ብቻ ሳይሆን ሊከተሉ የሚችሉ ጉዳቶችንም ማሰብ መልካም ነው፡፡

ጉዳታቸውን ቀንሶ ጥቅማቸውን ለመጨመር የሚያስችሉ መንገዶችን በጥቂቱ ለመዘርዘር ያህል፡-

  • አልፎ አልፎ ቢሆን እንኳ የሚወስዷቸውን መድሃኒቶች በዝርዝር ይያዙ
  • ዝርዝሩን ጤናዎን ለሚከታተለው ባለሙያ ይስጡ
  • አለርጂ ካለብዎት ይናገሩ
  • መድሃኒት እንዳይወስዱ የሚከለክልዎ ሁኔታም ካለ ይግለፁ
  • ነፍሰጡር ከሆኑ ወይም እያጠቡ ከሆነ ይጠንቀቁ
  • የተሰጠዎትን መድሃኒት መልኩን፣ መጠኑን ወዘተ. . . ጠንቅቀው ይወቁ
  • መድሃኒት አይቀላቅሉ
  • ግጭቶችን ለማስወገድ ሲባል ከምግብና ከመጠጥ እንዲሁም ከሌሎች መድሃኒቶች ተቀላቅሎ መወሰድ አለመወሰዱን ይጠይቁ
  • ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ይጠይቁ፡፡ ችግሩንም ለመከላከል ያለውን መፍትሄ መረዳት መልካም ነው፡፡
  • መድሃኒቱን ከወሰዱ በኋላ ምን እንደሚሰማዎት ያጢኑ፡፡ ለውቶችን ያስተውሉ፣ ትንሽም ይሁን ትልቅ ችግር ቢያጋጥምዎ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ይወቁ፡፡ ባለሙያ ለማማከር አያወላዱ፡፡

የባህል መድሃኒቶች ከእለት እለት በዓለም ሁሉ ተጠቃሚያቸው እየጨመረ ሄዷል፡፡ የጥራት ቁጥጥሩ ትኩረት እነዚህን የባህል መድሃኒቶች መውሰድ፣ ለጤና የሚያበረክተው ጥቅም ወይም የሚስከትለው ጉዳት ምን እንደሆነ ማወቅ ነው፡፡ የተፈጥሮ ምርት ማለትና ጤናማ ይዘት ያለው መድሃኒት የተለያየ ትርጉም እንዳላቸው ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡

የባህል መድሃኒቶችን ጥቅም ከፍ ለማድረግ፣  ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት ለመቀነስ እንዲሁም ነባር እውቀትን ለማቆየት የሁሉንም ሰው አስተዋፅኦ ይጠይቃል፡፡

ምንጭ፡- እንቁ መጽሔት

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop