Hiber Radio: ኃይለመድህን አበራ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው፤ * ክርስቲያን በመሆኗ ሞት የተፈረደባት ትውልደ ኢትዮጵያዊት ልትፈታ ነው

/

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ግንቦት 24 ቀን 2006 ፕሮግራም

<<... ኢትዮጵያውያን የዲሞክራሲ ሀይሎች መነቃቀፍ ትተው በአንድ ላይ ለጋራ ግብ መስራት ያለባቸው ወሳኝ ወቅት ላይ ነው ያለነው ...ህወሃት የወጠነልንን የከፋፍለህ ሴራ ትተን ለአገራችን የጋራ መፍትሄ ማበጀት አለብን ...>> ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የቀድሞ የዓለም ባንክ አማካሪ እና ተመራማሪ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሸንጎ በሲያትል ላዘጋጀው ስብሰባ የሚያቀርቡትን የመፍትሄ ሀሳብ መሰረት አድርጎ ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ኢትዮጵያውያን በምግባረ ሰናይ ተግባራቸው የሚዘክሯቸው የሰዎች ለሰዎች መስራች ካርል ሲዘከሩ (ልዩ ዝግጅት)

ግንቦት ሃያ ይዞት የመጣው ምስቅልቅል እና ሰብዓዊ ውርደታችን በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሪፖርት ሲዳሰስ( ልዩ ዘገባ አለን ሙሉውን ያዳምጡት)

<<...ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ ለኢትዮጵያው አገዛዝ አሳልፎ አይሰጥም ከተባለ በሁዋላ በቅርቡ በይፋ በተከሰሰበት ጉዳይ ፍርድ ቤት ይቀርባል...>>

አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ የረዳት አብራሪውን ጉዳይ ከሚከታተሉት አንዱ ከሲዊዝ ጄኔቫ ለህብር ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ውይይት እንደገና ዩኒየን እንደገና መደራጀት ?

ዜናዎቻችን

– በትግራይ አለመረጋጋት መኖሩ ተገለጸ

* የአረናን ልሳን ያደሉ ተደብድበው ሄስፒታል ገብተዋል

– ከአውስትራሊያ የሶማሌ ክልል ተወላጆች አዜብ መስፍን ከውጭ ኩባንያ ጋር ሆነው ከክልሉ ለተወሰደ መሬት ተጠያቂ መሆናቸውን ገለጹ

– ጅቡቲ አጥፍቶ መጥፋት በአገሬ ፈጸሙ ካለቻቸው ሁለቱ አንዱ ከኢትዮጵያ የሄደ መሆኑን ገለጸች

– የክርስትና እምነት ተከታይ በመሆኗ በሱዳን ሞት የተፈረደባት ትውልደ ኢትዮጵያዊትን የአገሪቱ ባለስልጣናት ልንለቅ ነው አሉ

– ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡትን ጦማሪያን ፖሊስ መንግስት ሊገለብጡ ነበር ሲል ቀጠሮ ጠይቆ ተፈቀደለት

_ ፍርድ ቤቱ ከሁለት ሳምንት በፊት ሽብር የለም ሲል ውድቅ ያደረገውን የ28 ቀን ቀጠሮ መቀበሉ ህጋዊ መሰረት እንደሌለው ታውቋል

_ ኤርትራ ወጣት ዜጎቼ በህገወጥ ደላሎች ሳቢያ ከአገር እየወጡብኝ ነው አለች

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጎጃም አማራ እግዚአብሔር ይወድሀል ብአዴን ያለ ትጥቅ ሊያሳርድህ ቢያሴርም እግዚአብሔር ቤትህ ድረስ ያመጣልህን እያስወለቅህ ታጠቅና አርበኛ ፋኖ ሁን

3 Comments

  1. satgadem feswa kedem alu abew . gena bedenb sattaweku haymanotn behaymanot le magachet krstian bemehonwa mot yeteferedebat stlu tnsha aykefachum . ezh sudan weym bemelaw areb ager sint milion crstyanoch beselam endeminnor tawkalachu ?? lemin ewnt lemawrat atmokrum . ahun bezh wshetachu tekebaynetn atachu .wshetamoch .

  2. Hi Hiber radio the sound is very bad interview with Ato Petros Ashenafi .
    How can I listen clear I have very interesting to lesten again .Thank you
    very much!!!!!

Comments are closed.

Share