(የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ) ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት!!

ከኢትዮ ተዋሕዶ

ህሊናዬ ያለእረፍት ይናጣል በሃሳብ ቅብልብሎሽ አድማስ ይሻገራል፡፡መቸም ህሊናችን አንድ ግዜ ክፉውን ሌላ ጊዜ በጎውን ማውጠንጠኑ የተለመደ ገቢር ቢሆንም ህሊናዬን በቁጣና በቁጭት ያደነቆረኝን ነገር በልቤ አብሰልስዬ በአንደበቴ መስክሬ የእርካታ ጣሪያ ላይ መድረስ አልተሳነኝምና ቁጭት ያቀረረ ብእሬን አንስቼ በጦማር ልፋለመው ገባሁ፡፡በቅድሚያ ክቡር ንዑድ የሆነ ሰለምታዬ ይድረሳችሁ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለዘመናት በሊቃውንት አባቶች ከታላቁ መፃህፍ ከመፅሐፍ ቅዱስ በተጨማሪ ህገ መንፈሳዊ በሆኑት ፍትሃ ነገስት(The Law of the Kings)፣ቃለዓዋዲ፣ ሐይማኖተ አበው እና ሌሎችም አዋልደ መፃህፍት በመታገዝ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን ቅዱሳን አባቶች ስለ እውነት ብለው እንደ ስንዴ ተቆልተው እንደ አክርማ ተሰንጥቀው በዱር በገደል እንዲሁም በበረሀ ተቅበዝብዘው ቅጠል በልተው አፈር ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው የቤተክርስቲያንን ህልውና ከፀና ሰርዓቷ ጠብቀው አኖረዋል፡፡

የጉድ ሃገር ገንፎ እያርደ ይፋጃል” እንዲሉ አለማዊ ክብርና ዝናን ለመላበስ በመሻት ከሙሽራው ክርስቶስ ውዳሴ በላይ የኔ ስምና ክብር ይቅደም በማለት በበዓለ ሆሳዕና ቅዳሴ የተስተጓገለበትን የሚኖሶታው ደብረ ሰላም መድሐኒያለም በአርምሞ ማለፍ ከህሊና ጋር መቃቃር እንዲሁም የልቦና መባከን ስለሆነብኝ ትንሽ የግሌን የአስተሳሰብ ልኬት እና ግንዛቤ ከመንፈሳዊ ህግ ጋር በማዋሃድ ላወጋችሁ ወደድኩ ፡፡ሆሳዕና በልዩ ሁኔታ የሚከበር ጌታችንን ክርስቶስ በእየሩሳሌም ከሚጠቡ ህፃናት አንደበት አንስቶ እሰከ ቤተፋጌ ድንጋዩች ድረስ “ሆሳዕና በዓርያም በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ አርሱ ብሩክ ነው″ ብለው ያመሰገኑበት ተዓምራታዊ እለት እና አንደኛው አበይት በዓል ነው፡፡ እናም በዚህ እለት ኢትዮጳያ ካለው ቅዱስ ሲዲኖዶስ ለኒዮርክና አካባቢዋ የተላኩት አቡነ ዘካሪያስ በስርዓተ ቅዳሴው የእኔን ስም በመግለፅ ሊቀደስ ይገባል ካለሆነ ቅዳሴው ተስተጓግሎ ቤተክርስቲያኒቷ እንድትዘጋ የሚል ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ለሃያ አመታት በዚህ ስርዓት ሲተዳደሩ የነበሩ ህገ እግዚአብሄርን የሚያከብሩ ካህናትና ዲያቆናት ከህዝበ ክርስቲያኑ ጋር ጌታን ሲያመሰግኑ ዋሉ፡፡ የነገስታቱ ምድራዊ ጥንካሬና ጉልበት ያስፈራቸው ካህናት ቅዳሴውን ትተው ምድራዊውን ንጉስ ሊያመስግኑ ከሆሳዕና ተለዩ ከፈሪሳዊያንም ጋር አበሩ፡፡ከሙሽራው በላይ መድመቅና መክበር የፈለጉ ሚዜዎች መሆን ፈልገው እንጂ ከማያልፈው የክርስቶስ ክብር የእነሱን ዘለቄታ የለሽ ዝና ማስቀደም አልነበረባቸውም(የመንግስት ቀኝ ክንፍ ካለሆኑ በቀር) ደግሞም ቤተክርስቲያን ስለአለም ሁሉ የምትማልድ እንጂ ለህዝብና አህዛብ፣ ለቤተክርስቲያን ኃላፊዎችና ለቤተመንግስት ባለስልጣን አልያም ላለው ለሌለው ብላ እግዚኦታ የምታስብል አይደለችም፡፡ ለቤተክርስቲያን አገልጋይም በተለየ መልኩ በማዕረግ ፀሎት መደረግ አለበት ከተባለ በስርዓተ ቅዳሴው “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ቀሳቀወስት ወዲያቆናት” በሚል ሀረግ ይማልዳል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንድም ሶስትም ፡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የ 2012 ዓ.ም የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚው የዐብይ አህመድ ሰለስቱ ማንነቶች {ዐብይ ሰባኪው ፤ ዐብይ ተዋኒው እና ዐብይ አጼ በጉልበቱ}

ስለውግዘት መፅሐፍ ቅዱስ (መፅሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ 36 ቁጥር 15) እንዲህ ይላል፡- “የማይገባ ግዝትን ለምትፈፅሙ ለናንተ ወዮላችሁ ስለ ኃጢያታችሁ ድህነት ከናንተ ይራቀ እንደስራችሁ መጠን ፍዳውን ትቀበላላችሁና ለባልንጀራችሁ ክፉ ምላሽ ልምትመሱ ለናንተ ወዮላችሁ”፡፡ በፍትሃ ነገስትም ላይ እንዲህ የሚል ኃያል ቃል እናገኛለን “አለቃው ህዝቡን የሚመክራቸው በውግዘት ያይደል በመስቀል የሚያስራቸው ይሁን በማይገባ አያውግዝ፡፡ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለት ፈልጎ በማይገባቢያወግዝ እርሱ ከእግዚአብሐየር ዘንድ የታሰረ የተወገዘ ይሁን፡፡ ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት ይላል፡፡ በተፃራሪ ለግል ክብርና ዝና ውግዘት ማድረግ ተገቢ አይደለም ተደጋጋሚ ምክር ሳይደረግ ሊቃውንተ ቤተክረስቲያን ጉባዔ ሳይቀመጡ ውጉዝ ከመዓርዮስ ማለት ወፈ ገዝት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ሰለስቱ ምዕት(318ቱ ሊቃውንተ ቤተክርሰቲያን) አርዮስን በተደጋጋሚ መክረውና ዘክረው በነቂያ ጉባዔ እንዳወገዙት ልብ ይሏል ይህም የሆነው ለግል ክብርና ዝና ሳይሆን ከባድ ሐይማኖታዊ ክህደት በመፈፀሙ ነው፡፡ደግሞም እኮ በድርጊት እንጂ በስም ሰማዕትነትን የተቀበለ የሰው ዘር የለም (መብራቱን እስከ ዘይቱ የያዘም አይደል ከሙሽራው ጋር ሰርጉን የሚታደም?)፡፡

ከታሪክ የማይማር ታሪክን ይደግማል እንዲሉ ፈሪሳውያንና ሰዱቃዊያን በሆሳዕና እለት ህዝቡ የዘንባባ ዝንፃፊ እና የለበሱትን ልብስ በማንጠፍ ጌታ በውርንጭላይቱ ላይ ሆኖ እንዲያልፍ በማድረግ “ሆሳዕና በዓርያም በእግዚበሔር ስም የሚመጣ አርሱ ብሩክ ነው″ ብለው ሲያመስግኑ ለእነሱ አልተዋጠላቸውምና መምህር ሆይ ለምን ዝም በሉ አትላቸውም አሉት ምስጋና የባህሪ ገንዘቡ ነበርና እነሱ ዝም ቢሉ የቢታኒያ ድንጋዮች ያመሰግኑኛል አላቸው፡፡ እውነትም ድንቅ ነበር የቤተ ፋጌ አለቶች ድምፅ አውጥተው አመሰገኑት ዛሬም ይሄ ነው የተፈፀመው ፈሪሳውያንና ሰዱቃዊያን አናመሰገንም ሲሉ በበዓለ ሆሳእና በደብረ ሰላም መድሐኒያለም የቤተ ፋጌ አለቶች ድመፅ አውጥተው አመሰገኑት (ከቢታኒያ ድንጋይ ከማነስ ይሰውረን)፡፡ አቡነ ዘካሪያስም መፅሐፍ ቅዱስ በማይፈቅደው ከቤተክርስቲያን የህግ መፅሐፍ ከሆነው ከፍትሃ ነገስት ጋር በሚጣረስ መልኩ የግዝት ትዕዛዝ አስተላለፉ (እንደማስተባበያ ሥልጣነ ክህነታቸው ተያዘ እንጂ አልተወገዙም የሚል ጉንጭ አልፋ ምክንያት እንደ ምክኒያት ቢቀርብም &እዚች ጋር አንድ ቀልድ ቢጤ ትዝ አለችኝ ሰዎቹ በሰውዬው ሀብትና አውቀት እጅጉን ይቀኑና ህይወቱን እስከማጥፋ የሚደረስ ቅናት ያድርባቸዋል እናም በሚመላለስበት ቦታ አዘውትረው ይጠብቁት ነበርና አንደ ቀን አድፍጠው በሚጠብቁበት ሰዓት የሰውየው የበኩር ልጅ ያገኛቸዋል ወትሮውንም አባቱን ሊያጠፉት እንደሚፈልጉ ይሰማ ነበርና የያዙትን ስለት በማየት አባቴን ልትገሉት ነው አይደል ሲላቸው አንደኛው ፈጠን ብሎ አይደለም ባክህ የእናትህን ባል ነው አለው፡፡ግዝትና ክህነትን መያዝ ምን አለያየው ሁለቱም ግልጋሎትን የሚከለክሉ አይደሉም እንዴ ቂቂቂቂቂ)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአቦይ ስብሐት ነጋ ‹‹ይሰቀሉ፣ ሞት ይገባቸዋል!›› የሚል የበቀል መንፈስ ከወዴየት ነው!?

ግዝት በቤተክርስቲያን ሃይማኖትን ለካዱ እና በነውር ለተገኙ ሰዎች በተለይም በካህናት ላይ የሚተላለፍ የመጨረሻው የፍርድ ውሳኔ ነው።ይህ አንድን ካህን(ሰው) ከማኅበረ ክርስቲያን የመለያ ውሳኔ የሚተላለፈው ደግሞ ተጨባጭ የሆኑ የኃይማኖት ክህደትና የምግባር ብልሹነት ሲቀርቡ ብቻ ነው።
ስለውግዘት መፅሐፍ ቅዱስ (መፅሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ 36 ቁጥር 15) እንዲህ ይላል፡- “የማይገባ ግዝትን ለምትፈፅሙ ለናንተ ወዮላችሁ ስለ ኃጢያታችሁ ድህነት ከናንተ ይራቀ እንደስራችሁ መጠን ፍዳውን ትቀበላላችሁና ለባልንጀራችሁ ክፉ ምላሽ ልምትመሱ ለናንተ ወዮላችሁ”፡፡ በፍትሃ ነገስትም ላይ እንዲህ የሚል ኃያል ቃል እናገኛለን “አለቃው ህዝቡን የሚመክራቸው በውግዘት ያይደል በመስቀል የሚያስራቸው ይሁን በማይገባ አያውግዝ፡፡ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለት ፈልጎ በማይገባቢያወግዝ እርሱ ከእግዚአብሐየር ዘንድ የታሰረ የተወገዘ ይሁን፡፡ ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት ይላል፡፡ በተፃራሪ ለግል ክብርና ዝና ውግዘት ማድረግ ተገቢ አይደለም ተደጋጋሚ ምክር ሳይደረግ ሊቃውንተ ቤተክረስቲያን ጉባዔ ሳይቀመጡ ውጉዝ ከመዓርዮስ ማለት ወፈ ገዝት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ሰለስቱ ምዕት(318ቱ ሊቃውንተ ቤተክርሰቲያን) አርዮስን በተደጋጋሚ መክረውና ዘክረው በነቂያ ጉባዔ እንዳወገዙት ልብ ይሏል ይህም የሆነው ለግል ክብርና ዝና ሳይሆን ከባድ ሐይማኖታዊ ክህደት በመፈፀሙ ነው፡፡

መቸም ዲያብሎስ በእድሜ እንጂ በተንኮል የማይበልጠን ተመፃዳቂ ለምድ ለባሽ ተኩላዎች ስለሆንን እንጂ ከእውቀትና ከመንፈሳዊ ብስለት ጋር የማይስማማ ቅዱሳን በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ከፃፏቸው የህግ መፅሕፍት ጋር በሚጣረስ መልኩ ባልተባረከነ በአራቱም የቤተክርስቲያኑ አቅጣጫ በቅብዓ ሜሮን ባልተባረከበት ብዙ ተገቢ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ባለተፈፀመበት አዲስ ቤተክርስቲያን ከሶስት ሳምንት በላይ ስርዓተ ቅዳሴ መፈፀም ምን ይባላል? ደግሞስ ለብዙ ዘመናት የጌታ ስጋና ደም ሲፈተትባት የነበረችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ይሄንን በረት አሳማ አርቡበት ብሎ ናቡከደነፆራዊ ድፍረት የተሞላበት ስድብ መሳደብ መቸም ሚኒሊክ ቤተመንግሰት ካሉት ነገስታት የተላከ እንጂ ከሰማዩ አባት የተወረሰ መንፈሳዊ ብስለት አይደለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰሚ ያላገኘው የአባ ባሕርይ ምክር - አቻምየለህ ታምሩ

ሌላው አስነዋሪ ክስተት አላዋቂ መካር የፍዳ ማከማቻ መሆኑ ያልተረዱት የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የበላይ አሰተዳዳሪ አባ ዘርዓ ዳዊት በትንሳኤ ሌሊት አለም ከአመተ ፍዳ ወደ አመተ ምህረት በተሸጋገረበት አዳም ከዲያብሎስ እስራት ወጥቶ በክርስቶስ እቅፍ በዋለበት በዚያች የድህነት ብስራት በሚበሰርበት የምህረት እምቢልታ በሚለፈፍበት የነፃነት ነጋሪት በሚጎሰምበት ትንሳኤ ክርስቶስ በሚዘመርበበት እለት የአስታራቂነት ሚና ከሚጠበቅበት መንፈሳዊ አባት ቤተክርሲቲያኗ ግልፅ ያልሆነ በጉባዔ ባለተወሰነ የካህናቱና ዲያቆናቱ ምግባር ፅድቅ ይሁን ኩነኔ ባልተለየበት ለማህበረ ምዕመኑ የካህናቱንና የዲያቆናቱን ውግዘትና የስልጣነ ክህነት እስር መለፈፍ ምን ይሉታል? (እስራት የባህሪ ገንዘቡ ከሆነው የኢትዮጵያ መንግሰት ካልተላኩ በቀር)፡፡ እናም ቅዱስ አባታችን የቀደመውን አስቡ እግዚአብሔር ለሁለት አምላክ መገዛት አትችሉም በማለት ቀናተኛ አምላክ መሆኑን በአውደ ምህረቱ ትሰብኩልን የለ እናንተም ወይ ምድራዊ ክብራችሁን አልያም በመስቀል ላይ የዋለውን አምልኩ አልያ ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት ሆኖ በቤተክርስቲያን መክበር አይቻልም፡፡
ናቡከደነፆራዊ ድፍረታችሁን ትታችሁ የቀደመውን አስቡ!!!

እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያናችን ህብረትን ፍቅርን አንድነትም ይስጥልን!!!

10 Comments

  1. Hello Anbabiyan hulu,
    We are being challenged to bring out all the facts at hand as to how the merigeta of DSMA is degraded from his status until he admits and corrects him self to abide by the faith he sworn in to get in to the chambers of holy holies.
    Does this person deserve to serve as an individual let alone as a priests.
    We all know a lot about what he has done to people here and there and do we have to bring it out? Is it hurts to do so? Is this a bad idea? Is this helps to get to know all about his personal behavior and acts out side?
    We are members that are hurt and want to speak up, as exactly he put out that he is concerned. You want to hear it? Asking your honest suggestions.
    Please teach and convince us if we don’t have to do it, and not off driving us creazy more.

    • Helo brother, don’t full the people. You guys are woyane messengers. You guys distrurbed , messed up our church. You ignited fire between brotherhoods. You splitted our church in to two parts. You separated our children and spreads the seeds of hatred. Even you don’t regrets. Please if you are christians kneel down and pray. God will give you wisdom and peace.

  2. ባካችው ይህ ሁሉ አተታ ለምን አስፈለገ በዝህ ዙርያ ብዙ አላችው ይህ ሁሉ በድምጽ ለመላቅ ነው አይዞአችው አትፍሩ ችግር አለ ወይ ፈራችው ብዙ አወራችው ለምን አትተውንም አምሮብን ደምቀን ስታዩ ቀናችው ወይ ትገርም ከአሁን በዋላ ወደ ዋላ የለም ታያላችው ግዚው ቅርብ ነው ምንም በሉ ከድያቢሎ ስራ በ አምላክ ተአምር አምልተናል የስራዊት አምላክ ማደሪያውን ይሰራዋል ክርስትናን ማስተማር በትህትና ነው ከአባቶቻችን ተማሩ ስትስድቦአቸው ባረክ ህዝብከ አሉ ምንይሆን ለልጆቻችው ያምታስተምሩት ትውልዱን ተሳዳቡ ብላችው አታሳድጉ በናን ይብቃ ትውልድ ይዳን የሰራዊት አምላክ ይክበር ይመስገን::

  3. We are good with Merigeta, just live him alone, we don’t care about Gizet we heard a lot. You guys need maybe some Gizet, to hold you mouth shut,and move on including your Priest. Just live us a lone you look like you lonely you need some one to talk. talk with those kids.

  4. እኔም የ “ግዝት ይገባል”ን ሃሳብ እጋራለው። እባካችሁ መርጌታውን ከወደዳችሁት ዝምታ እራሱ እኮ አንድ ነገር ነው። ምን አልባት የሚፈታለትን ነገር፡ ንሰሃ የሚገባበት ነገር አመቻቹ እንጂ እንዲህ አይነት ጨዋታ ለእሱ አያዋጠውም። ብዙ ሰው ክርስትናው ይዞት እኮ ነው በልግናውን የደብቁለት። ለእሱ ብለው ሳይሆን፡ ቤተክርስቲያን እንዳይበጠበጥ፡ ገመና ወቶ ቤተክርስቲያን እንዳትሰደብ ማለት ነው። አሁን ግን የሰውን ብሶት ካላወጣኽው!!! እያላችሁት ነው! ቆም ብላችሁ አስቡ ሰውየው ስልጣነ ክህነቱ መያዝ በእውነት ሲያንሰው ነው! አሁን ግን የሚብስበት ወይም እናንተ የምታብሱበት እንዲህ አይነት ነገር እየጻፋችሁ ሕዝቡን የባሰ እንዲናገር ታደርጉታላችሁ። ዛሬ ስልጣነ ክህነቱ ተያዘ ነገ ደግሞ የሰራቸው ስራዎች ሁሉ ቀስ በቀስ እስከነ መረጃ ሲወጡ ወደ ውግዘት (ፈጽሞ ከቤተክርስቲያን) ይተላለፋል። እስቲ አስቡ!….. በዚህ ሁሉ የሚጎዳው እኮ አቶ ጌታሁን ነው። እስቲ የምትወዱት አልቅሱለት!

  5. Hi Mequanninet,

    Girum Tsihuf new. It has been a while since I read your article
    (birih nafikogn neber). Keep the good work.

  6. በስመ አብ በስመ ወልድ በስመ መንፈስቅዱስ አመን በመጀመርያ ትዛዙን አንተላለፍ ይህም ወደፍትሀነገስቱ ከመሂዳችን በፍት የትናው
    የመጽሀፍ ቃል ነው አባትህን አዋርድ የሚል አባቶችን በአደባይ ሰድባችው ሲያበቃ ይህንን አይነት የክህደት ቃል ትናገራላችው ለመሆኑ ቃሉን ትዛዙን መተላለፍችሁንስ አውቃችዋል ከ10ቱ ትዛዛት አንዱን ያለማክበራችውስ ምነው ተዘነጋችው አይናችውን ምን ጋረደው ወንድሞች ከአንድ ሁለት ግዚ በላይ አባትችን ለመርግየታ ነግረዋቸዋል ይህ ሁሉ የመድሀንያለምን ንብረት ለመውሰድ ከሆነ አይዙአችው ለና አሱ
    ምናችንም አይደለም አላማችን ሰውን ከተሳሳተ መንገድ መመለስ ነው ገዘብ መውረስ አይደለም ምክንይቱም ንብረቱ የአምላክን ትዛዝ ከሚያውቅ ወገን ስለተገና ነገ ይተካል የና አላማ አናንተን ከስህተት ማዳን ነው ::

  7. well. we heard a lot about gizet. after sundays vote they are done.let them move from place to place and worship dabilos. for sure they will come back without the prists

    gashaw

  8. ከ ሃያ አመታት በላይ መስዋእትነት የተከፈለበትን ታላቅ ደብር ያሳማና ያህያ መዋያ አድርጉት የሚሉ ጳጳስ ነን ባዮች ተከትላችሁ በህማማት የመድሀኔአለምን ቅዳሴ ረግጣችሁ ክርስትያን ነን እያላችሁ አትመጻደቁ። እኛን ተዉን ይልቁንስ ካሴት እየቸበቸቡ በእግዚአብሔር ስም የሚነግዱ አዝማሪዎች እያመጠችሁ ገንዘብ የተረፈው ይመስል በምትከራዩት የሆቴል አዳራሽ እሽክም እናኑን ቀጥሉበት። የናንተ መጨረሻ ከዚህ አያልፍም።

  9. I heard the three artist music band at the Air port hotel was good. they also sale a lot of CD. What a Gobae. Next i don’t know what the gonna bring.

Comments are closed.

Share