April 29, 2014
25 mins read

Health: የደናግላን ቁጥር ለምን ቀነሰ?

ድንግልና ወይም ክብረ ንፅህና (Virginity) የሴትነት ወሲባዊ ተአቅቦታና የጨዋነት ሚዛን እንደሆነ በሀገራችንም በሌሎች ሀገራትም ይታመንበታል፡፡ ይሄን ተከትሎ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሀገራችን ደናግላን ለመድረክ ወብቅ እያሉና እየተሰባሰቡ የዘመን ጥንካሬያቸውን እያሳዩ ነው፡፡ ዛሬ ፅሑፋችን የደናግላኑን ሰብዕናና በተቀሩት ሀገሮች ላይ የተደረጉ ጥናቶችን ዋቢ አድርጎ የድንግልናን (Virginity) ምስጢር እና ድንግልና በወንዶች ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ ይተነትናል፡፡

‹‹ኬላው ተሰበረ
ኬላው ተሰበረ
በእናት ባባቱ ቤት
ተከብሮ የኖረ…
ኬላው ተሰበረ››
የሚለውን ህዝባዊ መዝሙር (ዘፈን) የሚያስታውስ ይኖር ይሆን? ያውም ከነዜማው የሚያስታውስ ይኖራል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ የወንድ ሚዜዎች የሙሽራውን የአባወራነትና የወንድነት ጥንካሬ ለመግለፅ፡-
‹‹እንክትከት አደረጋት
ስብርብር አደረጋት
አሆሆ…

የኛ ወጣት…›› እያሉ የጫጉላውን ምሽት ሲያደምቁ… የሴት ቤተሰብ ደግሞ የልጅቱን ጨዋ አስተዳደግ ከጋብቻ በፊት ወሲብ አለመፈፀሟን ለመግለፅ ‹‹ኬላው ተሰበረ…›› ይላሉ፡፡ ‹‹እንክትክት አደረጋት›› የሚሉት ሚዜና የሠርጉ አድማቂዎች ክብረ ንፅህናን በመገርሰስ ሂደቱ አልጋ በአልጋ እንዳልሆነ አድካሚ እንደሆነ ማስረዳታቸው ይመስላል፡፡ ‹‹ኬላው ተሰበረ›› ሲሉም በቀላሉ የማይደፈር የማንነት ድንበር መሆኑንና ክብሩን ከፍ ከፍ ለማድረግ የሚገልፁት ነው ማለት ይቻላል፡፡

ይህ የልጃገረዶች እስከ ጋብቻ ክብርን ጠብቆ የመቆየት የውዳሴ አጀባ በሀገራችን ድምፁ እየሰለለ… ሞገሱ እየኮሰሰ የሄደ ይመስላል፡፡ ጨርሶ ባይጠፋም፡፡ የውዳሴ ዜማው ሆታ በጭብጨባና በጫጉላ ምሽት ከበርቻቻ… ባይገለጥም ወጉ በጥንዶች የፍቅር ሹክሹክታ ውስጥ የራስን ክብር (ድንግልና) አሳልፎ መስጠት አሁንም ያለ ተግባር ነው፡፡ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ይሄ ድንግልናን እስከ ጋብቻ አቆይቶ በጋብቻ ወቅት የክብረንፅህናን ሙሉነት በመሃረብ በተቀባ የክብር ደም ማሳየቱ አሁንም የሚታይበት ሁኔታ እንዳለ ይታሰባል፡፡ አብዛኛው አስተያየት ሰጪ ግን የወቅቱ የጋብቻ ሁኔታ በዘመናዊ ዘፈን ተሸርቦ ‹‹ክብረ ንፅህና ድሮ ቀረ›› የሚለውን በድምፃዊው ማይክ ባይሆንም ‹‹በግልፅ ዝምታ›› ያንፀባርቃሉ ብለው ያስባሉ፡፡ ክብረ ንፅህናን እሰከ ጋብቻ ያለማቆየት ልማድ እየተስፋፋ በመጣበት ሁኔታ ውስጥ ግን ያውም ከመዲናችን አዲስ አበባ ደናግላን መድረክ ላይ ወጥተዋል፡፡ ራሳቸውን ለመድረክ ያላበቁ እህቶቻችንም እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡ ‹‹የእኚህ ደናግላን ወደ መድረክ መውጣት አቻዎቻቸውን የመቀላቀል ኃይል ይፈጥራል›› ይላሉ የስነ ልቦና ባለሙያው አቶ ዳንኤል ተሻለ፡፡ ‹‹እስከ ጋብቻ ተጠብቆ የመቆየት ወኔንም ያላብሳል›› ብለዋል፡፡

ድንግልና ምንድን ነው?

ወሲባዊ ተሞክሮ በፍፁም የሌላት ‹‹ድንግል›› ተብላ እንደምትጠራ ጥናቶች ይገልፃሉ፡፡ ድንግላዊነት ማለት ድንግል ሆኖ መገኘት ማለት ነው፡፡ የቃሉ መሰረት ቪርጎ (Virgo) ከሚለው የላቲን ቃል የመነጨ ሲሆን ትርጓሜውም ‹‹ወሲባዊ ተሞክሮ የሌላት ሴት›› ማለት ነው፡፡
ልክ እንደ ላቲኑ ሁሉ የእንግሊዝኛውም ቃል ዕድሜን ፆታንና ወሲባዊነትን ሰፋ አድርጎ የሚገልፅ ቃል ነው፡፡ በዚህም መሰረት የጎለመሱ ሴቶችም ድንግሎች ወይም ደናግላት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ወንዶች እና የተለያዩ እምነቶችና መስህቦች ውስጥ በአዲስ አባልነት የሚመለመሉ ሰዎችም ድንግል ሊባሉ ይችላሉ፡፡ አንስታይ የእንስሳ ቤተሰቦችም ወሲባዊ ተራክቦን እስካልፈፀሙ ድረስ ድንግል ናቸው ይባላል፡፡ እስካሁን የታወቀው የእንግሊዝኛው ቃል የመጀመሪያው አጠቃቀም የዋለው ካምበሪጅ ዩኒቨርሲቲ ትሪንቲ ኮሌጅ የሚገኘው የአንግሎ ሳክስን የብራና ፅሑፍ ውስጥ ነው፡፡
በኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ውስጥ የሰፈሩት 18 አይነት የድንግል መገለጫዎች በአብዛኛው ተመሳሳይ ቢሆኑም በ1923 ፍራንክ ሃሪስ ግን በአንድ ሌክቸሩ ላይ ድንግል የሚለውን ቃ ቀልደኛ በሆነ ማብራሪያ ሲተረጉመው ‹‹ቪር Vir›› ሁሉም ሰው እንደሚያውቀው በላቲን ‹‹ሰው›› ማለት ሲሆን ‹‹ጂን-Gin›› ደግሞ በቆየ እንግሊዝኛ ‹‹ወጥመድ›› ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹ድንግል-Virgin›› ማለት ታዳሚዎችን አስቋል፡፡

‹‹Vir- Gin››

መምህሩ ፍራንክ ሃሪስ ‹‹Vir- Gin›› በሚል ክፍልፋይ ትርጓሜዎች ቀልዱን መወርወሩ በሀገራችን እንደ ቀልድ የሚታይ አይመስልም፡፡ በእርግጥም ድንግልና የወንድ ወጥመድ ይመስላል፡፡ ድንግል የሆኑ ሴቶችን መርጦ ለጋብቻ ማጨት… ድንግልን የሆነችን ሴት ለማቅበጥ አጮልቆ ማየት በተለይ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የደፈጣ ውጊያ ያህል ይታያል፡፡ አንዲት ሴት ድንግል መሆኗን ያወቀ ወንድ ወይም ማህበረሰብ ለሴቲቱ ከሚሰጠው ክብር ባሻገር ለመውደድ መንሰፍሰፍም የሚታይ ሁኔታ ነው፡፡
በ2001 ‹‹የሚስ ቨርጂን›› አሸናፊ የነበረችው ኤልሳቤት ይሄንን ታረጋግጥልናለች፡፡ ‹‹ድንግልናዬን ሰዎች አይተውኝ የሚያውቁበት መንገድ የለም፡፡ በቅርብ የሆኑ ጓደኞቼ ግን ያውቃሉ፡፡ እነሱ ዘንድ ከፍተኛ አክብሮት እንዳለኝ አረጋግጫለሁ›› የምትለን ኤልሳ፤ ነገር ግን የወንዶች ወጥመድ እንደሆነም ታምናለች፡፡

ክብረ ንፅህናዋን /ድንግልናዋን/ በህክምና አረጋግጣና ከደናግላን አቻዎቿ (ከ17 ልጃገረዶች) ጋር ተወዳድራ በውስጣዊ መመዘኛዎች ጭምር በአንደኝነት ተሸናፊ የሆነችው ኤልሳ ወንዶች ለድንግልና የሚሰጡት ክብርና ትኩረት ቢገለጥላትም ‹‹ድንግል ወንድ›› ያጋጥመኛል? ብላ ስታስብ ሳቋ ይቀድማል፡፡ ሆኖም ‹‹ጥሩ ስብዕና ያለው አላማዬንና ጥንካሬዬን የሚከተል ጥሩ ባል በጊዜው አገኛለሁ›› ትላለች- አሁን አላማዋን የማሳካት ሂደት ላይ ናት፡፡

‹‹… እጃችን ገባች ሳይውልም ሳይነጋ!…››

…የፈረንሳይ ብሔራዊ ስነ ህዝብ ተቋም ተመራማሪ ሚካኤል ቦዘን በ2003 ዓ.ም ባወጣው ጥናታዊ መግለጫው የተለያዩ ባህሎች ውስጥ የሚደረጉ ጋብቻዎችን በ3 ጎራ ፈርጀውታል፡፡ በመጀመሪያ ምድብ ውስጥ የተካተተው ለአቅመ ሄዋን የደረሰችን ልጃገረድና የጎልማሶች ጋብቻ በወላጆች ወይም በቤተሰብ የሚዘጋጅበትን ሲሆን በእነዚህ ማህበረሰቦች ውስጥ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች በዕድሜ ከገፉ በኋላ ከወሲብ ጋር እንዲተዋወቁ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም ወሲብ የሚፈፀመው በተቃራኒ ፆታዎች መሃል ብቻ ነው፡፡ በዚህ ምድብ ውስጥ ከተካተቱት ውስጥ ከሰሃራ በታች የሚገኙ ሀገሮች ማሊ፣ ሴኔጋልና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ የህንድ ንፍቀ ክበባት (Indian Subcontinent) በዚህ ምድብ ውስጥ ተካትተዋል፡፡

በሁለተኛው ምድብ የተካተቱት ባህሎች (ሀገሮች) ደግሞ ቤተሰቦች ሴት ልጆቻቸውን ጋብቻን እንዲያዘገዩ ወይንም እንዲያቆዩ፣ ግን ጋብቻን እስኪፈፅሙ ድረስ ከወሲባዊ ተራክቦ እንዲታቀቡ የሚያደፋፍሩ (Families encouraged daughters to delay marriage, but to abstain from sexual activity prior to it) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ወንዶች ልጆቻቸው ከጋብቻ በፊት ከትልልቅ ሴቶች ወይም ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር ወሲብን እንዲፈፅሙና ተሞክሮአቸውን እንዲያዳብሩ ያደርጓቸዋል፡፡ የዚህ ምድብ አባላትም ከደቡባዊ አውሮፓ ፖርቹጋል፣ ግሪክና፣ ሩማንያ እንዲሁም ከላቲን ሀገሮች ውስጥ ብራዚል፣ ቺሊና ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ይገኙበታል፡፡

በሶስተኛው ምድብ የተቀመጠ ባህሎች ውስጥ የሚገኙት ህዝቦች ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ወሲባዊ ግንኙነትን ለመፈፀም በተቻለ መጠን ዕድሜያቸው ተቀራራቢ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ከእነዚህ ሌላ ንዑስ ምድቦች ሲኖሩ የወሲብ መፈፀሚያ ዕድሜዎችም ከፍ ዝቅ ይላሉ፡፡ ለምሳሌ በሰሜንና ምስራቅ አውሮፓ ቬርቤን፣ ቼክሪፐብሊክና ሲውዘርላንድ ውስጥ ወንዶችና ሴቶች ወሲባዊ ትውውቅን የሚያደርጉበት ዕድሜ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡

በታላቋ ብሪታኒያ በተደረገ የፆታ ትምህርት ዳሰሳ እንዳሳየው ከሆነ ዕድሜያቸው ከ14-17 ዓመት መሃል ከሚገኙ ወጣቶች ውሳኔ 6 በመቶ ብቻ ከጋብቻ በፊት ወሲብን ያለመፈፀም (መታቀብ) ዝንባሌ እንዳላቸው ታውቋል፡፡

የሴት ድንግልና (Family virginity) በብዙ ባህሎች ውስጥ ከግለሰባዊና ቤተሰባዊ ክብር ጋር የተገናኘም ነው፡፡ እነዚህ ‹‹የሀፍረት ማህበረሰቦች›› (Shame Societies) ተብለው በሚታወቁ ህዝቦች ውስጥ አንዲት ሴት ከጋብቻ በፊት ድንግሏን ብታጣ ለቤተሰቡ ከፍተኛ ሀፍረትና ውርደት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ለምሳሌ በደቡብ አፍሪካው የጋንቱ ማህበረሰብ ውስጥ ድንግል መፈተሽ እና ብልትን መስፋት በስፋት የተለመደ ተግባር ሲሆን፣ የሱዳን ኬንዙ ልጃገረዶችም ለአቅመ ሄዋን ከመድረሳቸው በፊት በአዋቂ ወንዶች የድንግላቸው መኖር ከተፈተሸ በኋላ ያገቧቸዋል፡፡ በዚሁ የኬንዙ ማህበረሰብ ውስጥ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሱ ልጃገረዶችን መግረዝና ንፁህ ሆነው እንዲቆዩ ብልታቸውን መስፋትም ባህላዊ ተግባር ነው፡፡

አንዳንድ ሀገሮች ውስጥ ደግሞ አንድ ወንድ አንዲት ልጃገረድን አስገድዶ ቢደፍር ወይንም ክበረ ንፅህናዋን ቢገስ እንዲያገባት ወይንም ለወላጅ አባቷ ካሳ እንዲከፍል የሚያስገድዱ ህጎችና ደንቦች ተደንግገዋል፡፡ እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ማብቂያ ድረስ በአንዳንድ ሀገሮች ውስጥ አንደ ወንድ አስገድዶ በመድፈር ድንግሏን ከወሰደና ሊያገባት ፍቃደኛ ካልሆነ ተጠቂዋ የገንዘብ ካሳ ለመጠየቅ የመክሰስ መብት ተሰጥቷታል፡፡ የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ደግሞ በዚህ የአስገድዶ መድፈርና የክብረ ንፅህና መገሰስ/ያለ ፈቃድ ላይ ፈጣንና ዳጎስ ያለ ቅጣት ያስቀምጣል፡፡

ድንግልናቸውን ለሽያጭ ያቀረቡ ልጃገረዶች

ድንግልና የላቀ ክብር ብቻ ሳይሆን የላቀ ዋጋ ያለው ጥሬ ዕቃ ይመስላል፡፡ ‹‹ድንግል ሴት ንፁህ ናት ተብሎ ስለሚታመን ከንፅህናዋ አክሊል በላይ ንፁህ ሰብዕናዋ በዜጎች ዘንድ የላቀ ዋጋ ያሰጠዋል›› ይላሉ- የስነ ልቦና ባለሙያው፡፡ ‹‹ይሄ እንደ ብርቅ የሚታየው የጨዋነት ሚዛን በሀገራችን በተለየ ሁኔታ በተለይ በአሁን ወቅት ደናግላን በልዩ መነፅር እንዲታዩ አድርጓቸዋል›› ብለዋል- ሳይኮሎጂስቱ፡፡

ድንግልናቸውን ለሽያጭ ያቀረቡ ልጃገረዶችን ማንሳት ይቻላል፡፡ በ2004 ዓ.ም የብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ (እንግሊዝ) ተማሪ የሆነች ግብረሰዶማዊት (Lesbian) ልጃገረድ በኢንተርኔት አማካኝነት ድንግሏን በ8,400 ፓውንድ መሸጧ ተነግሯል፡፡ የለንደን ከተማ ነዋሪና የ18 ዓመት ወጣቷ ሮዚ ሬይድ የ44 ዓመት ጎልማሳ ለሆነ ኢንጂነር ሂውስተን ሆቴል የመኝታ ክፍል ውስጥ ድንግሏን ሸጣለት እንደተኛችው ታውቋል፡፡ በ2008 ዓ.ም ኢጣሊያዊቷ የ28 ዓመት ሞዴሊስት ራፋኤል ፈቶ ድንግልናዋን በ1 ሚሊዮን ዩሮ ለጨረታ አቅርባለች፡፡ በዚሁ ዓመት የታሊ ዋይሊን በሚል ተለዋጭ ስም ራሷን የጠራች አሜሪካዊት ኒቫን ግዛት (State) በሚገኝ አንድ የዝሙት አገልግሎት ሰጪ ድርጅት (Brothel) አማካኝነት ድንግሏን ለጨረታ አብቅታለች፡፡

ለድንግልና ከፍተኛ ዋጋ (ክብር) የሚሰጡ ማህበረሰቦች ከጋብቻ በፊት ግብረ ስጋ ግንኙነትን ያላካተተ በርካታ ወሲባዊ ተግባራትን እንደሚፈፅሙ አረጋግጠዋል፡፡ ለምሳሌ በአፍ ንክኪ (መጥባት፣ መላስ) እና ወንድና ሴት በጋራ ሆነው የማሸት (ሴጋ) ወሲብን ይፈጽማሉ፡፡ ይህ አይነቱ ወሲባዊ እንቅስቃሴ የሴትን ብልት የማይጠልቅ በመሆኑ ‹‹ቴክኒካዊ ድንግልና›› (technical virginity) ተብሎ ይጠራል፡፡ በ1999 ዓ.ም በ29 የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ በ599 የኮሌጅ ተማሪዎች ላይ ወሲባዊ ጥናት ያደረገው የአሜሪካ ሜዲካል አሶሴሽን (ማህበር) ባወጣው ዘገባ መሰረት ዕድሜያቸው በአስራዎቹ ውስጥ በሚገኙ ወጣቶች ዘንድ ‹‹ቴክኒካዊ ድንግልና›› እጅግ ተወዳጅ እየሆነ መምጣቱን አሳውቋል፡፡

በተለይም የሴቷን ብልት በወንዱ ብልት በመንካት የሚደረግ ወሲባዊ ግንኙነት ‹‹የደረጃ ለውጥ›› ወይንም የማይመለስ የድንግልና ማጣት ተደርጎ የሚወሰድበት አንትሮፖሎጂካዊ ምክንያቶች እንዳሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

የስነ ልቦና ባለሙያው አቶ ዳንኤል ‹‹ቴክኒካዊ ድንግልና››ን ከነፃነት ማጣት ሰቀቀን ጋር አያይዘው ይመለከቱታል፡፡ ወሲባዊ ነፃነትና ግልፅነት ጨርሶ በጠፋበት ሁኔታ ልጃገረዶች በወላጆች ነፃነትና አስተምህሮ ውስጥ ክፉ ደጉን እንዲለዩ ማድረግ እንጂ ድብብቆሽ አካሄድ የተዘዋዋሪ ቀዳዳ ሊከፍት ይችላል ብለው ያስባሉ፡፡ ከላይ የጠቀስኩት ጥናት የሚያሳየውም ይሄንኑ ነው፡፡ ወጣት ልጃገረዶች ድንግልናቸውን በራሳቸው ጨዋነትና ጥንካሬ እንዲያቆዩት ከማድረግና ከማስተማር ይልቅ ድፍን ባለ ግለሰባዊ ወይም ቡድናዊ አመለካከት ተጠፍሮ እንዲቆይ ማስጨነቁ ወጣቶቹን ቤተሰብ አክባሪ ያደረጋቸው ቢሆን እንኳ ስነ ልቦናዊ ጫናው (Physiological impact) ወደ ቴክኒካዊ ድንግልና አሻግሯቸዋል፡፡

የ2001 የሚስርጂን አዲስ አበባ አሸናፊ የሆነችው ኤልሳቤጥ ያሬድ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ትሆናለች፡፡ ኤልሳቤጥ ያሬድ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ትሆናለች፡፡ ኤልሳቤጥ እንደነገረችን በቤተሰብ ውስጥ ፍፁም ነፃነት አላት፡፡ ቤተሰቦቿ ለዚህ ለመብቃቷ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳበረከቱላት አልሸሸገችም፡፡ ‹‹በቤተሰብ ውስጥ ያለው ግልፅነትና ውይይት ነሮችን እንዳውቅና ራሴን በደስተኝነት እንድጠብቅ አድርጎኛል›› ትላለች- ኤልሳ፡፡

ኤልሳ በትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቿ ራሷን እንደሚመስሉም ትናገራለች፡፡ ሰው ማንን ይመስላል ሰብዕና ያላቸው ጓደኞች ብቻ ሳይሆን የወንድ ጓደኛ ያላቸው ሴቶችንም ትጎዳኛለች፡፡ ‹‹መወስወስና መሳብ ግን የለም›› ትላለች- ለራሷ የሰጠችውን የላቀ ግምት በንግግሯ እየገለፀች፡፡

ድንግልናን ማጣት

ድንግልናን ማጣት በብዙ ባህሎች ውስጥ ወሳኝ የሆነ የህይወት ሽግግር ተደርጎ የሚወሰድ የመጀመሪያው ወሲባዊ ተሞክሮ ነው፡፡ በአብዛኛው የአንዲት ልጃገረድ ድንግል በወንድ ብልት የሚወሰድ (የሚቀደድ) መሆኑ ቢታወቅም የህክምና ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ግን አንዲት ልጃገረድ ብስክሌት በመንዳት፣ በፈረስ ግልቢያና በጅምናስቲክ እንቅስቃሴም ድንግልናዋን ልታጣ ትችላለች፡፡

በአንዳንድ ሴቶች ላይም ከተለመደው ውጭ የሆነ የብልት ሽፋን (ድንግል) ይከሰታል፡፡ ይህም በተፈጥሮ በጣም ጠንካራ በቀላሉ የማይቀደድ ከመሆኑም ሌላ የወር አበባን መውጫ በመዝጋት ህመም ስለሚያስከትል ይህንን ችግር ለማስወገድ ቀላል የቀዶ ጥገና ህክምና ያስፈልጋል፡፡

የድንግልና ነገር ባህላዊ ስነ ልቦናዊና አንትሮፖሎጂካዊ ግንኙነት እንዳሉት ይታወቃል፡፡ የባህል ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡት የተለያዩ ማህብረተሰቦች ውስጥ በፍቅር፣ በወሲብና በድንግል ላይ የተመሰረቱ ‹‹ቅናቶች›› ዓለም አቀፉ የሰው ልጅ መገለጫዎች ናቸው፡፡

ከስነ ልቦና አኳያ በ1985 ዓ.ም በአሜሪካ የተደረገ ጥናት እንዳሳየው ከጋብቻ በፊት ወሲብ የፈፀሙ ሴቶች ብዙዎቹ የትዳር መፍረስ አደጋ እንዳደረሰባቸው ታውቋል፡፡ ድንግልናን እስከ ጋብቻ ድረስ መጠበቅ የጥሩ አስተዳደግና የጨዋነት ምልክት ተደርጎ በሚወሰድበት ማህበረሰብ ውስጥም ከጋብቻ በፊት ወሲባዊ ተራክቦን የፈፀሙ ሴቶች ከድንግሎች የበለጠ ለትዳር መፍረስ የተጋለጡ ሆነው ተገኝተዋል፡፡

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop