እኛና አ መላ   (ገበየሁ ባልቻ)

 
ባለፈዉ ሰሞን ኢትዮጵያዉያን መንደር ስፍር ቁጥር የሌለዉ የወገን ተቆርቋሪ አባ መላን አስመልክቶ ቁጭቱን ብስጭቱን መታለሉን ሲገለጽ እኔም አቧራዉ እስኪበርድ ከጦርነቱ አዉድማ ራቅ በማለት አገር አማን ሲሆን ብእር መዝዤ ወረቀት በጥሼ ብቅ ብያለሁ። እዚህ ላይ ገና ከጅምሩ አንባቢ አልበዛም እንዴ ይሄ ነገር ብሎ እንዳይበሳጭብጭ የዚህ ጽሁፍ አላማ አባ መላ በእሱነቱ  ወይም ደግሞ በተክለ ሰዉነቱ አለመሆኑን ማሰገንዘብ እወዳለሁ ይሁን እንጂ የነገሩ አዉራ አባ መላ ስለሆነ ለመንደርደሪያነት ለማብራሪያነት ለመቋጫነት እሱን መጥቀሱ ግድ ይላል።

ስለ ብረሀኑ ዳምጤ በተከታታይ ጽሁፎቹ እንደተገለጸዉ ቀልጠፍ ያለ የከተማ ልጅ መሀል አራዳ ተወልዶ መሀል አራዳ ያደገ ከመሆኑም በላይ ሰያፍ አንደበት ያለዉ መሆኑን አብሮ አደጎቹ ቢገልጹም ይህን ችሎታዉን እኛም በፓልቶክ ታዳሚነት ሳንገነዘበዉ አልቀረንም። እንደ ዛሬዉ ሳይሆን አቶ መለስ ከአዲስ አበባ አንድ መግለጫ ሲሰጡ ዝርዝሩ አባ መላ ዘንድ ስለሚገኝ የሱን ትንታኔ ማዳመጥ የአቶ መለስን አካሄድ ያመላክት ነበር። በወቅቱ አባ መላ ስጋዬም ህይወቴም ከህወኣት ነዉ የተሰራዉ በማለት የወያኔ ተቃዋሚ ናቸዉ ወይም ሊሆኑ ይችላሉ ብሎ የገመታቸዉን ሁሉ ክፉኛ እየነደፈ የአንድነት ሀይሉን ቢያስቆጣም በህወአት አካባቢ ግን ይህ ስራዉ ትልቅ ፍስሃና ደስታን ፈጥሮ ነበር።

ነገር ግን ለማንም ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ አባ መና (ተሳስቼ ነዉ) ሰፈር ቀይሮ የአንድነቱን ጎራ ለማስደነስ ወደ አንድነት ሰፈር መጥቶ ባንድራወን በማዉለብለብ የኛን ቀልብ ለመግዛት ጊዜም አልፈጀበትም። ትላንት የህዋአት ጋሻ ጃግሬ እንዳልነበረ ሁሉ በህወአት አካባቢ ያሉትን የቀድሞ ጌቶቹን እንዳልነበሩ አድርጎ ሲያብጠለጥላቸዉ የአንድነት ሐይሉ እጁን ዘርግቶ አባ መላን ጓዳዉ ድርስ ዘልቆ እንዲገባ በመፍቀድ አባ መላ ጸጸት ሳይገባዉ ትያትሩን እንዲቀጥል ሁኗል ። ብቻ በሗላ  እሱም እንዳለዉ እስከ ጓዳቸዉ ዘልቄ ገብቻለሁ ባዶ ናቸዉ ብሏል። ይበለን ደግ አደረገ።

አባ በላ (አሁንም ተሳስቼ ነዉ) የአንድነት ሐይሉን ተቀላቅያለሁ ብሎ መግለጫ ሲሰጥ ህወአት ምድር እንደተደፋበት ሁሉ ቤቱን ዘግቶ ሲላቀስ ነበር። ዛሬ እኛ እሱ ላይ ካደረግነዉ በላይ ቤተሰቡ ላይ ያጠነጠነ አስነዋሪ ትችትም በፓልቶክ መገናቻ መስመሮች አስተላልፈዉም ነበር ።አባ መላ ቂም ስለማይቋጥር ይበሉኝ እስከ ከፈሉኝ ድረስ በማለት ወደ ቀድሞ ጌቶቹ መመለሱን ስንሰማ ለጊዜዉ ማመን ቢያስቸግረንም ሁኔታዉ እዉን መሆኑ ተረጋገጠ በእርግጥ ሃሳብ ከአፍ ሳይሆን ከልብ መመንጨቱን የዛሬ የደረቀ ንግግሩን መስማት በራሱ ምስክር ነዉ ። በእርግጥ አባ መላ ወደ ህወአት ከተመለሰ በሗላ በአንድነት ጎራዉ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤን  ፈጠረ ሁሉም ያለዉን ወረወረ አባመናም ተብጠረጠረ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አያ ጅቦ ሳታመሃኝ ብላኝ!!  (በአገሬ አዲስ)    

ዋናዉ ጉዳዬ ከዚህ ይጀምራል። በተደጋጋሚ እንደታየዉ ከጠላት ጎራ ወደ አንድነቱ ተቀላቅለናል ብለዉ የሚመጡትን እንደ አባ መላ አዉሩልን ሳይሆን ምሩን ብለን ከሚገባቸዉ በላይ ከበሬታን ሰጥተናቸዋል ከብዙ በጥቂቱ ዝርዝራቸዉን ከዚህ በታች አትታለሁ ለቅምሻ ያህል።  ትላንት አጼ ሐይለ ስላሴ በኤርትራ የባንዳዉን ልብ አማልላሁ በማለት ከአንድነት ሐይሉ ይልቅ ለባንዳዉ ክብር፤ድጎማ፤ሹመት በመስጠታቸዉ የአንድነት ሐይሉ አዝኖ ተበሳጭቶ ጀርባዉን በእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ በማዞሩ ይህ ትዉልድ ጠንቅቆ የሚያዉቅ ይመስለኛል። በእርግጥ አጼ ሐይለ ስላሴ የኢትዮጵያን አንድነት ለማጠናከር እንጂ የባንዳ ፍቅር እንደሌላቸዉ ልገልጽ እወዳለሁ እራሳቸዉን መከላከል በማይችሉበት ሁኔታም ልከሳቸዉ አልፈልግም። ባለፈዉ አንድ መጻጽፌ እንዳመላከትኩት ትላንት ኢትዮጵያን ለማጥፋት ተግተዉ የሰሩት ኤርትራዉያን ዛሬም በተለያየ ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ የሀገሪቱን አንጡራ ሀብት መጠቀም ብቻ ሳይሆን እንደገና ጥልፍልፍ በመስራት የሚጠሉትን ህዝብ እንዴት እንደሚቀጡት በማዉጠንጠን ላይ መሆናቸዉ ከማንም የተሰወረ አይደለም። ታዲያ ሁኔታዉ ይህ ሁኖ ሳለ አባ መላ ላይ ሲደርስ እንደባነንን ሁሉ መጠነ ሰፊ ዉርጅብኝ በዚህ ፐሮፌሺናል ካድሬ ላይ ሲዘንብበት መክረሙ ከምክንያት አንጻር ሲታይ ሚዛን የሚደፋ አይሆንም ከስሜት አንጻር ሲታይ ግን ሰሜትን ሊያረካ ይችላል። እንደእዉነቱ ከሆነ እኛ ተሸከምናቸዉ ምሩን እያልን ከምንሰግድላቸዉ የህወአት አባሎች መሀል አባ መላ ሚዛን ያማያነሳ ትንሽ ቡችላ ነዉ ብዬ ብዘግብ ሀሰትም ክብረ ነክም አይሆንም። እንዲህ አይነቱ ቁጭት ሀገርን ከጠላት ለማዳን ለምንስ በነሱ ጊዜ አልተሞከረም ብሎ መጠየቅ ግድም ይላል።

እስቲ እነዚህ ግለሰቦች እነማን ናቸዉ ስራቸዉ እና ስማቸዉ ለሰሩት ስራ ቢዘከር ክፋት የለዉም እነሱም ቅር አይላቸዉም ያልሆኑትን ስላልተባሉ።

 1. ተስፋዬ ገ/አብ የሻቢያ ሰላይ በህወአት ዉስጥ ከፍተኛ ስልጣን የተሰጠዉ በሗላም በአንበሳዉ አለማየሁ መሰል ገመናዉ የተጋለጠዉ (ልብ ይበሉ አባ መላ ወደ አንድነቱ ጎራ ተቀላቅያለሁ ባለበት ጊዜ ተስፋዬ ገ/አብ  እንዳይጎዳ ከዳኛ ወልደ ሚካኤል ጋር የተደረገዉን ዉይይት አቅጣጫዉን እያስቀየረ በተነሳዉ ህዝባዊ ቁጣ ዉሀ ከመቸለሱም በላይ ለዚህ ወንጀለኛ  ሽፋን ሲሰጠዉ ነበር። ይህም ከኤርትራ ጋር ግንኙነት የነበራቸዉን ድርጅቶች ወይም የነሱን አቀንቃኞች ለማስደሰትም ጭምር ነዉ)።
 2. አረጋዊ በርሄ የህወአት መስራች በተለያዩ ጸረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎች በሀላፊነት የሰራ ከተገለለም በሗላ መለስን እንጂ ይህን አፋኝ ድርጂት ያላጋለጠ ያልኮነነ። ከዚህ ወንጀለኛ ሰዉ አንጻር ክቡር ገ/መድህን አርያን በንጽጽር ማየት ይጠቅማል እሳቸዉን ግን ኢትዮጵያም ኢትዮጵያዉያንም የሚገባቸዉን ክብር ሰጥተናል።
 3. ታምራት ላይኔ ድርጅቱን መርቶ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት የሰነዘረ በሀይማኖት ሰም ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ ኢትዮጵያዊ የሚመራ።
 4. ሰየ አብረሀ ህወአት ዉስጥ ከፍተኛ አመራር የነበረ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተኮሰ ባደረገዉ ጥፋት ያልተጸጸተ የጥፋት ጓዶቹን ያላጋለጠ።
 5. ነጋሶ ጊዳዳ የህወአት ፕሬዚዳንት የነበረ ህወአት የሰጠዉን የጥፋት ስራ በተሰጠዉ ወምበር ተጠቅሞ ተግባራዊ ያደረገ።
 6. ገብሩ አስራት የህወአተ ከፍተኛ አመራር የነበረ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የተኮሰ አሁንም ከዛ የማይተናነስ የእብሪት የህወአት እህት ድርጂት  በመምራት የሚንቀሳቀስ ድርጅቱ አረና ትግራይ እንጂ አረና ኢትዮጵያ አይደለም ከዚህ የአንድነት ሀይሉ ምን ይላል?
 7. አንዳርጋቸዉ ጽጌ የሀወአት የፕሮፓጋንዳ ሀላፊ/በህወአተ የማዘጋጃ ቤት ሹም ሁኖ የሰራ።ይህ ግለሰብ ህወአት ሲደናበር እጅና እግር ነብስ ቀጥሎለት በሰላም ግባ ተብሎ የተሸኘ በህወአት ቤት የተሰጠዉ ከፍተኛ ሃለፊነት  ለአድዋ ተወላጅ እንኳን ለመስጠት መጠነ ሰፊ አስተዋጽኦ  የሚያሰፍለግ ከመሆኑም በላይ በእጅጉ ታማኝነትን የሚጠይቅ ።
 8. ጁዋር መሀመድ  የኢስላሚክ አሮሚያ አክቲቪስት ይህ ግለሰብ በተለያየ ጊዜ በአንደበቱ እንደገለጸዉ ኢትዮጵያዊነት የሚያመዉ ሰዉ ከመሆኑም በላይ ሀጂ ናጂብ ባዘጋጁት በእስላሞች ዝግ ስብሰባ እስላም ያልሆነዉ ኢትዮጵያዊ በሜንጫ እንዲመታ ጂሀዳዊ መመሪያ የሰጠ
ተጨማሪ ያንብቡ:  የጃዋር መሃመድ ቅኝቶች | ከክንፉ አሰፋ

ከዚህ ባነሰ ደግሞ በተቃዋሚ ስም የህወአትን ስራ ህጋዊነት የሰጡ እነ መራራ ጉዲና፤ቡልቻ ደመቅሳ፤በየነ ጴጥሮስን የመሳሰሉ ሰዎች በተለያየ ደረጃ ምሩን እያልን አባ መላን የመሰለ ተራ ካድሬ ከሚገባዉ በላይ ክብርን ሰጥቶ የመወያያ አርስት አድርጎ ማቅረብ ባልተገባ ነበር።

ለማጠቃለል ኢትዮጵያ በታሪኳ ጠላቶቿን የማባበል ባህሪዋን ብዙ መጥቀስ ይቻላል ሀዲስ አለማየሁ ነብሳቸዉን ይማረዉና በአንዱ መጻፋቸዉ ነጻነት ከተመለሰ በሗላ አንዱ ባንዳ ዜጋዉን  ሲያንገላተዉ የተመለከተ ጀግና በሺመል እንዴት እንዳንጎራደደዉ የሀገር ፍቅር ሰሜት ባለዉ ቃና ዘግበዉታል።  አጼ ተዎድሮስም ጠላቶችን ከማጥፋት ብለዉ እራሳቸዉ ማጥፋትን መርጠዋል በአጼ ሐይለ ስላሴ ዘመንም ጣሊያኖቹ እንኳንም ተማረክን ብለዉ እስኪሉ በኢትዮጵያ የምድር መንግሰተ ሰማያትን ኑረዋል ታዲያ ይህ ባህል ሲንከባለል ከርሞ አባ በላንና መሰሎቹን (ከላይ የጠቀስኳቸዉን) በሰሩት ስራ ሳያፍሩ ሳይሸማቀቁ እጃችንን ዘርግተን ተቀበልናቸዉ እነሱም በደሉን ዘንግተዉ የችግሩ ምንጭ እነሱ መሆናቸዉን እረስተዉ ፖለቲካዉን ከተጎዳዉ ህዝብ ጋር በመሆን አዳከሩት አልፎ እንዳይሄድም አቅጣጫዉን በስልት አሳቱት።

እዚህ ላይ የፖለቲካ ስራ የጥቅል ስራ ነዉ አንድ ግልሰብ  የኒዉክለር ቁልፍ እጁ እንደያዘ ሁሉ ያን ያክል መረበሽም መጨነቅም ቁልፍ ቦታም መስጠትም አግባብ አልነበረበም የግለሰቦች መምጣትና መቅረትም በአማካይ አንድ ግለሰብ ከሚሰጠዉ ጠቀሜታ በላይ ሊኖረዉም አይችልም።

በአጠቃለይ ከላይ ለማመልከት እንደሞከርኩት ሁሉ ለእንደዚህ አይነቱ የፖለቲካ ስራ ሚዛኑ ሀቅ እና ጽናት በመሆኑ በየጊዜዉ ከጣላት ጎራ መጣን ተቀበሉን የሚሉትን ጊዜ ሰጥተን ማየት ተገቢ መሰለኝ። አቶ በረከት ሰሞኑ አክራሪ የትግራይ ተወላጆች አላስቀምጥ አሉኝ ብሎ ወደኛ ቢመጣ የአንዱ ድርጂት መሪ ማድረጋችን ያማይቀር ይመስለኛል ካለን ተሞክሮ። በዚህ አይነት በዳይና ጥፋተኛን መቅጣቱ ቢቀር በስራዉ እንኳን እንዲጸጸት ማድረግ የመንግስትም የመንፈሳዊም ህግ መመሪያ ይመስለኛል። ስለዚህ እንደነዚህ አይነት ከጥቅማቸዉ በላይ ጉዳታቸዉ የሚያመዝን ሰዎች ወደ አንድነቱ ጎራ በመምጣት ትግሉን ይበልጥ ዉስብስብ ያደርጉታል እንጅ መፍትሄ ስለማይሰጡ ከመጡም አነስ ያለ ወምበር ተሰጥቷቸዉ የሚያዉቁትን ለቅርብ አለቆቻቸዉ እንዲያቃብሉ ቢደረግ ጠቀሜታ ያለዉ ይመስለኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  መንግሥትም ሆነ እኛ ከልብ ልንጸጸትበት እና ይቅርታ ልንጠይቅበት የሚገባን የ2ቱ ዓመት የእርስ በርስ ጦርነት!! - በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)

እንግዲህ ሀሳቤ ያልተመቸዉ ሀሳቤን ይቀጥቅጠዉ ለሁሉም መድረስ ካለባችሁ በዚህ ድረሱኝ gebeyhubalcha@yahoo.com

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

3 Comments

 1. የሃበሻው ፓለቲካ በሳህን ላይ እንዳለ ውሃ ነው። አቅጣጫ የሚቀይረው ቦይ ሳይቀደድለት ሲሆን ፍሳሹም ለምንም አይጠቅምም። የውጭም ሆነ የሃገር ቤቱ የፓለቲካ አሰላለፍም “እኔን ምሰሉ” እንጂ በራስ አስቦ መስመር ያለው ብልሃት ያፈለቀን እንደ ጠላት የሚመለከት ወልጋዳ አረማመድ አሽመድምዶታል። ገበየሁ ባልቻ አባ መላን ተገን አርጎ ያለከፈው ሰው የለም። አቶ ብርሃኑና ሌሎች ተጠቃሽ ወገኖች ያጠፉት ነገር ምንድን ነው? ሰው ትላንት በነበረበት የፓለቲካ እይታ ዛሬም ይኖራል ብሎ በመገመት አሉባልታዊ የፓለቲካ ጭቃ ሰውን መቀባት ተገቢ አይደለም። አባ መላን፤ ተስፋዬ ገ/አብን፤ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን፤ ሰዬ አብርሃን፤ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን በተለያዩ መድረኮችና አጋጣሚዎች የሚሉትን አንዳምጠናል። በእኔ እምነት እይታቸው የኢትዮጵያ ህዝብ በህብረትና በአንድነት ረሃብና በሽታን እንዲዋጋ እንጂ ፀሃፊው እንደሚለው ሃገር ለማፍረስ ወይም ወያኔ መላእክ ነው ያሉበት ጊዜ የለም። አባ መላም ሆነ ሌሎች የሚሉን (give credit where credit is due). ወያኔ ያጠፋቸው ዓእላፍ ነግሮች እንዳሉ ሆነው አፍርሶ የሰራቸውም ጥቂት በጎ ነገሮች አሉ ነው የሚሉን። እንዲሁ ሁሉን በአንድነት መወንጀል ለእርቅና ለሰላም አይበጅም። የሃበሻው ፓለቲካ ሰው በራሱ ማሰብን እስካለተቀበለ ድረስ የጅምላ የፓለቲካ የትም አያደርሰንም። ዘጠና ዘጠኝ መርፌ አንድ ማረሻ አይወጣውምና!

 2. ዉድ አቶ ተስፋ የተሰጠ ምላሺ
  1. “ወያኔ ያጠፋቸዉ አእላፍ ነገሮች እንዳሉ ሁነዉ አፍርሶ የሰራቸዉም ጥቂት ነገሮች አሉ ነዉ የሚሉን”
  2. “የሀበሻዉ ፖለቲካ ሰዉ በራሱ ማሰብን እስካልተቀበለ ድረስ የጅምላ ፖለቲካ የትም አያደርስም። ዘጠና ዘጠኝ መርፌ አንድ ማረሻ አይወጣዉምና”
  ዉድ ተቺዬ በተራ ቁጥር 1 የጠቀስኩትን የሚያመላክት አንድ አረፍተ ነገር ኮፒ ፔስት ቢያደርጉልኝ።
  በተራ ቁጥር 2 የዘገቡት ሀበሻ ሲሉ ምን ማለቶ እንደሆነ አልገባኝም ይህንን አባባል የሚጠቀሙት ኢትዮጵያን የሚጠሉ ሁነዉ ሳለ በዚሁ አረፍተ ነገሮ ሰዉ በራሱ ማሰብን እስካልተቀበለ የጅምላ ፖለቲካ ብለዋል ይህንን የሚቃወም ነገር በተለያየ ጽሁፌ ላይ የነቀፍኩበት የለም ነገር ግን በዚሁ በእርሶ ጽሁፍ እራሶን የሚቃወም ነገር ገልጸዋል 99 መርፌ አንድ ማረሻ አይወጣዉም ብለዋል ይህም የመተባበርን አላስፈላጊነት የሚገልጽ መሰለኝ እኛ ግን አንድነት ሀይል ነዉ እንላለን ። ስማቸዉን ካነሳሗቸዉ ሰዎች ዉስጥ አንዱ እስካልሆኑ ድረስ ኢተዮጵያ የሰዉ ሀይል እጥረት ያላት አገር ስላልሆነች ወንጀለኛን በወንጀለኝነቱ መፈረጂ አግባብ ይመስለኛል መረጃዉንም እርሶ የሚያዉቁትን ጠቅሻለሁ። ፈራ ተባ ብለዉ ነዉ እንጂ አባ መላንም ሊከላከሉት ሳያስቡ አልቀሩም።
  አመሰግናለሁ ስለ ትችቶ

Comments are closed.

Share