የአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን መተግበር ሌላ ኦሮምኛ ተናጋሪ ገበሬዎችን በግፍ ከመሬታቸው መንቀል ሌላ, ኦሮምኛ ተናጋሪ ገበሬዎችም ከኢትዮጵያ ሌላ ሀገር የላቸውም

አዲስ አበባ ዙርያ ገበሬዎች በእርሻ ላይ

አዲስ አበባ ከ 3.5 ሚልዮን ሕዝብ በላይ ውሎ ያድርባታል።ከተማዋ አሁን ካላት የህዝብ ብዛት በላይ እንደምትጨምር ሳይታለም የተፈታ ነው።ገጠር ወደ ከተማነት እየተቀየረ ይመጣል እንጂ ከተማ ወደ ገጠርነት ሊቀየር አይችልም።ዕድገት ባለፈ ታሪኩ ያስመሰከረው ይህንኑ ነው።

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማን ለማስፋፋት ከተያዘው ማስተር ፕላን አንፃር ከተማዋ በኢህአዲግ አከላለል መሰረት ከ ‘ኦሮምያ’ ክልል መሬት ለመውሰድ በነበረው ሂደት ውስጥ በርካታ ገበሬዎች መሬታቸውን እንደሚለቁ በመታወቁ ተቃውሞዎች በክልሉ ቢሮዎች እና ከዩንቨርስቲ ተማሪዎች ተሰምቷል።

በመሰረቱ ኦሮምኛ ተናጋሪ ገበሬዎች ሌላ ሀገር የላቸውም።ተወልደው ያደጉባት አፈር ፈጭተው ውሃ ተራጭተው ያደጉባት መሬት ኢትዮጵያ ነች።ከቀያቸው ”ተነሱ!” የሚል ቀጭን ትእዛዝ ማስተላለፍ በራሱ ሃሳፊነት የጎደለው ተግባር ነው።አንድ ሰው ከመሬቱ ለመነሳት ቢያንስ ከሁለት አንዱ መስፈርቶች መሟላት አለባቸው።አንደኛው በፈቃዱ ወደ ሚፈልገው ቦታ ሲሄድ እና ሌላው ከለመደው ቦታ ለመሄድ የበለጠ ጥቅም የሚያስገኘለት ክፍያ ሲሰጠው ነው።ከእዚህ ውጭ ሌላ በዜግነትም ሆነ ለሀገር በማሰብ በምንም በማይበልጠው ሃብታም ቦታው መወሰድ አለበት ማለት በእራሱ የአስተሳሰብ ድህነት ነው።ለኢትዮጵያ ሀብታምም ሆነ ድሃ እኩል አይን ሊታዩ ይገባል።ሀብታሙ መሬቱን ከፈለገ ድሃውን የሚያማልል ልዩ ጥቅም በህጋዊ ሰነድ አረጋግጦ መስጠት አለበት።በከተሞች የቀድሞ ይዞታ የሆኑ ቦታዎች ሲወሰዱ መሆን ያለበትም ይህ ነበር። እየሆነ ያለው ግን ሀብታሙ  ወደድሃው ሲመጣ የመንግስትን ጡንጫ ይዞ መሆኑ ነው ጉዳቱ።

በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችን ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ሊወረወሩ አይገባም።የሚነሱ ከሆነ በሚያማልል ጥቅም እነርሱም አምነውበት ከሆነ ብቻ መሆን ይገባዋል።በአንድ ወቅት ከከተማ እርቆ የነበረ ቦታቸው  ከተማው ሲለጠጥ ደረሰባቸው እና የመሬታቸውን ተፈላጊነት አናረው።ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።የመሬታቸው ዋጋ ሲጨምር ጉልበተኛ ተገቢውን ክፍያ በሚያማልል መልክ ሳይሰጣቸው ፈድራል ፖሊስ ይዞ እያስፈራሩ አርቆ ማስፈር ምን አይነት ፍትሃዊነት ሊሆን ይችላል? ይህንኑ ጉዳይ የተቃወሙ የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን መደብደብ እና ማሰርስ ምን ያህል የዜጎች የመጠየቅ መሰረታዊ መብትን መጋፋት ነው? ማናቸውም ፕሮጀክቶች በቅድምያ ከፕሮጀክቶቹ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ ማሳመን ይጠይቃል።ከእዚህ ውጭ ከጋምቤላ እስከ ቡራዩ  እና አምቦ መስመር የፕሮጀክቶች ግልፅነት የማነስ ጥያቄን እና በቂ ምላሽ የመስጠት አቅም ማነስን  በፌድራል ፖሊስ የመፍታት አባዜ እጅግ አደገኛ አካሂያድ ነው።

እዚህ ላይ የማስተር ፕላኑን ትግበራ ከንፁሃን ገበሬዎች መፈናቀል ጋር በተያየዘ እንጂ አዲስ አበባ እራሷ ”የምንስትሶ” ነች እና ማስተር ፕላኑ የማስፋፋት ትግበራ ሊያዝ አይገባም የሚሉት የተሳሳተ እና ደካማ አስተሳሰብ እንደሆነ እረዳለሁ።”ገብረ ጉራቻ የምንትስ ደብረብርሃን የእገሌ” ስለሆነ በሚል ስሌት የገበረዎቹን መፈናቀል የሚቃወሙ በራሳቸው የተሳሳተ ተምኔት ገብተው የምስኪን የኦሮምኛ ተናጋሪ ወገኖቻችንን ችግር ለሕዝቡ እንዳይደርስ ያደረጉበት ብሎም ከቀሪው ሕብረተሰብ ጋር በመጋጨት እና በማጋጨት የሚደክሙ መኖራቸው ይታወቃል።ይህ እንግዲህ ቀላሉን ጉዳይ  በአጉሊ መነፀር ለማየት እስከሚያዳግት ድረስ ያጠበቡበት የጥበት ደረጃ ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም።

ጉዳዩን ያነሱ ተማሪዎችም ይፈቱ! ፕሮጀክቶችም ህዝብን አሳታፊ እና የህዝቡን ይሁንታ ሳያገኙ አይተግበሩ።

ጉዳያችን
ሚያዝያ 19/2006 ዓም

ተጨማሪ ያንብቡ:  እነ ሺመልስ አብዲሳ ተመረጡ፣  አፓርታይድ ይቀጥላል (ግርማ ካሳ)

2 Comments

  1. As far as I know, the cries of a few Oromo students from Wellega and Arsi is not to stand for the Farmers around Addis, it is to snatch lands in the name of Oromo nationality. Muktar was not born in Shewa and had never seen Addis until he became an OPDO member. Now, he has houses at several places in Addis and surrounding towns. Why should he and his likes get a land in Addis, Nazareth, Debre Zeit and other cities while the people who were born in these cities are denied the same right for a reason that they don’t speak Oromgna. Why should Oromgna be a criteria for one to have a property in these towns or elsewhere in that country? Oromos came to the region just 200 years ago while the original people (Amara, Gurage, Hadya) were there for nearly 6 centuries. Who is saying Shewa is for Oromos? The region’s (Shewa) destination must be decided by people who were born and raised in that region, not by Muktar and Jawar nor by Gidada and Bulcha, still not by Meles and Sebhat. Muktar and co. want use the farmers as a cover to loot the land endlessly; they have already sold Burayou, Gelan and Lege Tafo for Tigray weyanes. So, a few confused and brainwashed Oromo students should shut up, study the science of living together, and rise against Weyane. That is the way forward, not Anole nor boycotting Bedele.

    Thans

  2. >>>”በአንድ ቀንበር ሁለት በሬ ሁለት ገበሬ…. በሻቢያ ፈጣሪነት “በእንገንጠል ራዕይ” ህወአት እና ኦነግ “በኢትዮጵያ! የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ሆይ ከ፲፱፹፯ ጀምሮ በመፈቃቀድ ላይ በተመሠረተችሁ ሀገር ላይ ሁሉም በአንድ ፖለቲካ ጥላ ሥር ሆነው አማራን በማጥፋት በጋራ ሊኖሩ ተስማምተዋል። የዚህ ሥምምነታቸው ሰነድ ‘በአመለካከት’ በሚወክሏቸው ዘንድ ቀርቦ ፀድቋል። አንዱ ሰጪ ሌላው ተቀባይ አንዱ ባለሥልጣን ሌላው ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነው በኅብረት (በደቦ) አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ሙስና መር! ልማታዊ መንግስት መስርተው ሲሿሿሙ ሲወዳደሱ ባህላዊ ለቅሶ አብረው በእንባ ሲራጩ የዘረኝነትና ጎጠኝንት አስፋፍተው ታሪክ ሲነዙ፣ አብረው ዘርፈው፣ አብረው በባዶ ሆድ፣ በባዶ ቂጥ፣ በባዶ ሆድ፣ ባዶ ሜዳ ላይ ተከታዮቻቸውን በአንገት ልብስ፣ በካኒቴራ፣ በባርኔጣ ጠቅልለው ሲያስጨፍሩ ሰላም ነበሩ፡! አሁን ምን አዲስ ነገር ተገኘ?!
    __________————————-_________________—————-_
    (፩) የኦነግ ሙስሊም የሜንጫ ፖለቲካ ትንተና ከዲያስፖራ ኢህአዴግ መዋቅር ውስጥ ዘለቀ? (፪) ለመሆኑ ፳፪ ዓመት ድምፃቸው የጠፋው ኦሮሞና የትግራይ አብዮተኖች ዛሬ የምሬት መሳይ የማትሰማ የተሸራረፈች ቅላጼ ድምጽ ለምን ማሰማት ጀመሩ? (፫) በእርግጥ ሕገመንግስቱ ከተማ አይሰፋ ይላልን ? በጋራ ማስተዳደር ማለት እነሱም ታላቁን መሪ ቃል ሊተገብሩ ይሆን!?አሃ…”ሱዳኖችን ባለፉት በኢትዮጵያ መንግስት ሥርዓቶች ሁሉ የእኛን አትንካ ያንተን እንካፈል ሲባሉ ችለው ኖረዋል” ብለው ነበር? አሁን ደሞ የእኛን አትንኩ የእናንተን እንኑርበት ልንባል ይሆን!? ወይንስ እኛ ያለንበት ሁሉ የእኛ ብቻ…የእናንተን በጋራ በጋብቻ ማለት ይሆን? (፬) ለመሆኑ የኦሮሞ ሊሂቃንና የውስጥ አዋቂና ለወያኔ ቃል አሳላፊ እነ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ..በየነ ጴጥሮስ…ቡልቻ ደመቅሳ የአለፉት ወራት ቃለመጠይቆች ሁሉ በአንድነት.. በመኢአድና በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ያጠነጠነው ሰብቅና ውንጃላ ከምን የመጣ ፍራቻ ነበር? ” የእነኝህ ሶስት ፓርዎች “በሀገር ሉዓላዊነትና በሕዝብ ጥቅም ላይ አንደራደርም!” የሚለው አቋም ለምን አስፈራቸው?ይህንንስ አቋም ለምን የአማራነት መገለጫ አድርገው በተራና በአድማ ለምን ፈረጠጡ !? ለምንስ በጋራ የግድ እንዲሰባሰቡና በውስጣቸው ተሰግስገው ለማዳከም ፈለጉ!? (፬) ድሃ የሀገሪቱን ገበሬዎች ያለ በቂ ካሳ ማፈናቀል ወንጀል እነደሆነና የዜግነት መብት እንደመጋፋት ቢቆጠርም..በጨዋ ደንብ አሳብን መግለፅ ሲቻል…ያለ ሕጋዊ ፍቃድ አድማ ጠርቶ ሰላም ማደፍረስ ለምን አስፈለገ? (፭) በጣም ተጠቅመናል..ተደስተናል የትግላችን ውጤት አማራን እንዳያንሰራራ የቀበርንበት ድንቅ ሥርዓት ብለው የሚወራጩበት ቋንቋና ዘርን ያማከለው ፌደራላዊ መዋቅር…እንሱን ያልመሰለውን እንዳውሬ ቆጥረው ሲደፍሩ..ሲገርፉ..ሲያቃጥሉ..ሲሰቅሉ…ሲገድሉ… ሲያፈናቅሉ ደስተኛ ነበሩ፡፡ ዛሬ ለሁለት ገበሬ ቦታ የተሰማው ጩኸት ግን ሙስሊም ወገኖቻችን ከጮሁበት የሁለት ዓመት ሰላማዊ ሰልፍና መልካም ሥነምግባር የታየበት ሰልፍ ሲከለከል ሲታሰሩ ሲገረፉ የኦሮሞን ተማሪዎች ጩኽት ልዩ የሚያደርገው ምንድነው? (፮) ለሀገር ዕድገትና አብሮ መኖር በመሳሪያም ኀይል ተጠቅሞም የትግራይ ክልል ወልቃይት ተገዴን ሁመራን ከልሎ ሲይዝና የትግራይ ክልል ከሱዳን በደረቅ ወደብ ሲገጥም እኛ ሞቱ ጠ/ሚ “ጎንደር ከሸዋ ከሚጋባ ከትግራይ ይቀለዋል ብለው ነበር (ታጋይቷስ ወልቃይት አደለችምን!? …ከወሎ ክፍለሀገር ኮረምንና አላማጣን ወደ ትግራይ ሲጠቃለል..ቀጥሎ..ማንዳ ፣ኤሊዳር፣ዶቢን ሰብሮ ከጅቡቲ የባቡር መሥመር መዘርጋቱና አሰብን ቆርጦ ለመያዝ ያለው ሰፊ እቅድ ማንም ያልተናገረለትና ዩኒቨርሲቲዎች አድማ አልመቱበትም! ለእሱም ፈቃጁ የኢህአዴግ ግራ ክንፍ የኦነግ ኦብነግና ሻቢያ በጋራ፣ቡድን በኅብረት ሀገር መርተው ስሚያፈርሱ አደለምን!? ግን ጥቂት አማራ ክልል ነዋሪዎች መበሳሪያ ፍራቻ አንድነትና ሰላም ወደው ሌሎች በፈለጉት ሰዓት የሚያተራምሱት በሀገርና ሕዝብ የኢኮኖሚ ገቢ ላይ “ቦይ ኮት” የሚያደርጉት የተለየ ዜግነት አለ ይሆን? ወይስ ህወአት ለጥቅሙ ጥቅመኞችን ያከብራል ይፈራል!? (፯) ያለ አድልዎ ዘረኝነትና ለጋራ እደገት ሲታሰብ ቹኽትም በጋራ ሲሆን ኢደመታል ለመሆኑ ለጋንቤላ ወገኖቻችን ከቤንሻንጉል ግሙዝ ለተፈናቀሉ መሬታቸው ያለአግባብ ለተነጠቁና ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ መሬታቸው ለተሸጠባቸው ሌላው ብሄርና ምሁራን ለምን አድማ አልመቱም… የእነሱ ልጆች ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሉም ማለት ነውን? ጭራሽም ቀደምት የህወአት ታጋዮች ዛሬ ኢንቨስተር ሆነው ሲሰፍሩ ጋንቤላ ለጋምቤላ ብቻ አላሉም!? የሚናገሩበት ቋንቋ የላቸውም ወይንስ የብሄር ብሄረሰቦች ሶስተኛ ዜጋ ናቸው የምንለው እውነት ሆነ!? ለሱዳን ለተሰጠው መሬት ህወአት እና…የኦሮሞ ሙስሊም ሜንጫ አብዮተኞች የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት ለማደናቀፍ የተሯሯጡትን ያህል ይህንን ጥቂት አጅግ በጣም ጥቂት መልካም ሀገራዊና ሰብዓዊ አመለካካት ካላቸው የትግሬና ኦሮሞ ልጆች በቀር በአብዛኛው በደስታ ለምን ፈነጠዘ? (፰) በእርግጥ የምታስተዳድሩት መሬት የእናንተ ለእናንተ ብቻ ነው ሲል የሚጠቅሰው የህገመንግስቱ አንቀፅ የት ይሆን? ኦሮሚያ ከአዲስ አባባ መስተዳድር ትቅማ ጥቅሞችን ያገኛል ሲል ኦሮሚያ ለሌሎች ክልሎችና ለአዲስ አባባ መስተዳድር ነዋሪዎች ጥቅም እንዳያገኙ ይረብሻል የከተማ ዕድገትና ልማት እንዳይኖር ይከላክላል የሚል አንቀፅ አለን!? በእርግጥ አዲስ አባባ የኦሮሞዎች ነው ወይንስ በኦሮሚያ ክልል ነው ይላል?ለመሆኑ አዲስ አባባ የሸዋ ዋና ከተማ እንጂ ኦሮሞ የሚል ማን ፈጠረው ሻቢያህወአት ? ኦሮሞ ከባሌ ተራራ ወደ ሰሜን ወይንስ ከአዲስ አባባ ወደ ደቡብ? ኦሮሞ ዘርፎ፣ ሰልቦ፣ገድሎ ሲሰፍር ለምግብ ፍለጋ ተሰደደ ሲባል ምንይልክ ሀገር አንድ ሊያደርግ ሲሄድ ወረረ ገደለ ቆረጠ !? ቀድሞ ያልነበረ ይወረራልን!? ቀደም ሲል በሙስሊም ወገኖች ሰላማዊ ትግል ላይ አሁን በደቡብ ብሔር ብሔረሰብ ትከሻ ላይ መንተላጠልና ትውልድ ማምከንና ማባከን ያስኬዳልን? ተጠቃሚው ማነው? (፱) በእርግጥ ኤርትራ ተፀጽታ ወደ እናት ሀገሯ ኢትዮጵያዬ ማሪኝ ብዬሻለሁ ብላ ብትመለስ !!? ከብተናው በፊት በአዲስ አባባ ሀብት፣ ንብረትና ትዳር መሥርተው ከተለያዩ ብሔር ዘሮች ልጆች ያፈሩ ሁሉ በግድ ኦሮሞ ይሆናሉ ማለት ነው!? (፲) የኦሮሞ ልሂቃንና ጩጬ ተማሪዎች..የገበሬውን መሬት ሕንድ..ቻይና.. ዓረብ… ቱርክ..ከ፵-፺ዓመት ሲከራይና ከእነ ሰፋሪው ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ ሲገዛ ምነው አልተቃወሙም …ከአማራ በግርግር የተገኘ መሬት ባንበላውም አንድፋው ብለው አልነበረምን!? ያ ሁሉ ለሻቢያህወአት ሙገሳና ደረት ድለቃ የት ገባ!? *****ለመሆኑ ይህ በማተራመስና እርስ በእርስ በማሸበር የተቧደነው መንግስት መሳይ…በጠ/ሚ ማዕረግና …በም/ጠ/ሚ ማዕረጎች …በተለያዩ አማካሪዎች ድጋፍ የቆመው፡ ለሚወደውና ለፈለገው የራሱን የሥልጣን እድሜ ለማራዘም ሀብትና ንብረት እደዱላ ቅብብል ለትውልዱ ለማስተላለፍ ስለፈለገ ብቻ አማራን ለማጥፋት የክልል ካርታ ቀርጾ…መሬት ሸንሽኖ በማደል…በሙስና መር ኢኮኖሚ፣ በድራጎትና በብድር በቆመ ህንጻ ያበደ ከተማ….አመፅና ሽብር፣ አፈናና ወከባ፣ እስራትና እንግልት፣የዜጎች ሽያጭ.. በሞት ቀለበት አጠላልፎ ፣ በአሳላጭ መንገድ የሚከበርበት ብላ ተባላ የተለጠጠ ዕቅድ…በተለያዩ የገንዘብ ማሸሺያ መጋቢ መንገዶች…በፈጣን ጎዳና ሲሄድ ጥቅማ –ጥቅሞቻቸው የተነካባቸው ሁሉ ዙሪያውን ይጮሃሉ። ግን ጩኽቱም የቁራ እንባውም የአዞ ነው። ድምፃችሁን ሰምተናል ህገመንግስቱ ይከበር ድሃው ኦሮሞ የውጭ አሸባሪ ኀይሎች መጠቀሚያ አይሆንም!! የውሸት “መሬት ለአራሹ ብላችሁ አስፈጃችሁት “መሬት ለመራሹ ሻቢያህወአት!” አስረክባችኋል። እናንተ የድሃው ገበሬ ልጆች ሆይ፣ ትምህርታችሁን ቀጥሉ ለድሃ ቤተሰቦቻችሁ ጧሪ ቀባሪ አኩሪ ትውልድ ሁኑ፣ የፖለቲካ ተንታኞች ድንፋታ ሆዳችሁን አይሞላም! ዓለም የደረሰበትን በሰላም፣ በጋራ፣ ሠርቶ በጋራ መለወጥና ማደግ መቻሉን ተማሩ፣ የጥቂት ቡና ቤትና ፓልቶክ አርበኞች አዳራሽ ውስጥ ድንፋታና ጭብጫቦ እንደበቀቀን መድገም አይጠቅማችሁም! በቀን አንድ ግዜ የሚበላና በፋስት ፉድ(በሞቀ ውሻ) በሆት ዶግ ሙሉ ቀን እያመነዠከ የጠገበ አንድ ናችውን? ጠግበው የሚደፉ ሀገራት ዜጎች ወሬና ተርበው የሚደፉ የድሃ ሀገራት ብሔርተኞች ድንፋታ አንድ አደለም! ሠላም ለሁሉም በቸር ይግጠመን<<<<

Comments are closed.

Share