ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ተጠናቀቀ፤ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ “ውሃ ጠማን” አለ

April 27, 2014

(ዘ-ሐበሻ) ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የጠራውን ‘የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ” ሰላማዊ ሰልፍ በብዙ አፈና ታጅቦ ማጠናቀቁን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ። በተደጋጋሚ በዚህ ሳምን በድረገጻችን ላይ እንደዘገብነው የዛሬውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማሳካት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት እስር እና እንግልት ሲደርስባቸው ቆይቷል።

ዛሬም መነሻውን ከፓርቲው ጽ/ቤት ተነስቶ በአዋሬ፣ አድዋ ድልድይ፣ ባልደራስ አድርጎ መድረሻው ወረዳ 8 ሜዳ የካ ሚካኤል ታቦት ማደርያ ባደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፖሊስ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የማንገላታትና የማሸማቀቅ ሥራዎችን ሲሰራ እንደነበር የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል።

በአዲስ አበባ ያለውን የመብራት እጦት፣ የትራንስፖርት፣ የውሃ እጦት፣ የኔትወርክ እጥረትና ሌሎች የማህበራዊ ቀውሶችን ያስተጋባው የዛሬው የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከተሰሙት መፈክሮች መካከል
“ውሃ ጠማን ውሃ ጠማን”
“ፍትህ ናፈቀን ፍትህ ናፈቀን”
“ውሽት ሰለቸን ውሽት ሰለቸን”
“የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ባስቸኳይ ይፈቱ”
“በቀለ ገርባ አሽባሪ አይደለም”
“ኦልባና ለሌሳ አሽባሪ አይደለም”
“አቡበክር አሸባሪ አይደለም”
“አንዷለም አራጌ አሽባሪ አይደለም”
“እስክንድር ነጋ አሽባሪ አይደለም”
“ናትናኤል መኮንን አሽባሪ አይደለም”
“ርዮት አለሙ ጋዜጠና እንጂ አሽባሪ አይደለችም” የሚሉና ሌሎችም ድምጾች ከሰልፉ ተሳታፊዎች ተደምጠዋል።

በተለይም ተሰላፊው “እኛ ኢትዮጵያኖች አንለያይም፤ እኛ ኢትዮጵያኖች አንድ ነን” የሚሉና “የተነጠቁ መብቶቻችን ይመለሱልን” ሲሉ ጩኸታቸውን ያሰሙ ሲሆን መንግስት የለም ወይ? እያሉም ሲጮኹ ነበር።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉትና በቅስቀሳው ወቅት ታስረው ባለፈው አርብ ማምሻውን የተለቀቁት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለሰልፈኛው “ወደ ሰልፉ የመጡትን እና ስልፉን ያስተባበሩትን ወጣቶች እና መላውን ባለ መብት ተሳታፊ አመሰግናለሁ። ስርዓቱ በሙስና ተጨማልቋል፡፡ አገራችን አደጋ ላይ ወድቃለች፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ሆነን እጣ ፈንታችን እንወስን። በየትኛውም አገር አምባገነን እንዲሁ ለሕዝቡ መብት አይሰጥም። አስፈላጊውን መስዕዋትነት መክፈል አለብን” ብለዋል።

ሊቀመንበሩ ቀጥለውም “ከ19 አመት ጀምሮ እስከ 63 አመት ያሉት አባላትና አመራሮቻችን ታስረዋል፡፡ ክርስቲያኖች፣ ሙስሎሞች ወጣቶች፣ ኢንጅነሮች፣ ሌሎቹም ታስረውብናል። ይህም የኢህአዴግ አምባገነንነት ያሳያል፡፡ ሰማያዊ ለሁሉም የህዝብ ክፍል እንደሚቆምም በዚህ ሰልፍ የታሰሩት አባላትና አመራሮቻችን ማሳያ ናቸው ነው። ክብርና ፍርሃት፣ ማጎብደድ የኢትዮጵያውያን ባህል አይደለም፡፡ ማሸነፍን ያስተማርን ህዝቦች ነን፡፡ ሙስሊም ክርስቲያኑ በጨዋነት አብሮ የሚኖርባት አገር ናት፡፡ እነሱ ግን ይከፋፍሉናል፡፡ አሁን በአዋራጅ ሁኔታ ላይ እንገኛለን። ይህን ለማስቆም ከእነአስፈላጊው መስዋትነት ሌት ተቀን እንሰራለን” በማለት ንግግራቸውን አስመተዋል።

የሰልፉን ሁኔታ የሚያሳውን ፎቶዎች ይመልከቱ

11 Comments

  1. Mitashenfut be mircha bicha new inji be ames aydelem egypt nim alitekemem dedeboch….akkkkkkkk

    • Muluken, Lemebtu selamawi tigil yemiyadegewun DEDEB yemitil, end hiwehat lemin betemenja altagelum maletihi newu ? Ye gibtsi hizbawi abyot siletetelfe yelelawu hulu endeziya yihonal bilehi demedemki? Berasihi Quwankuwa DEDEBis antenna yante bitewoch.

  2. ብራቦ ሰማያዊ አስሩን ፣ማዋከቡን ፣ድብደባዉን በትእግስት አልፋችሁ ብሶታችንን እንድንተነፍስ ስላረጋሁ እናመሰግናለን ።

  3. Yeweshet tekawami enna yeweshet self.weyane yazegajew yeweshet tekawami semayawei party.

  4. Bravo blue party! continue your pressure on this Ethnic based TPlF/EPRDF system and exapand your area of struggle both in the town and rural area.

  5. Bravo blue party! continue your pressure on this Ethnic based TPlF/EPRDF system and expand your area of struggle both in the town and rural area.

  6. በአንድ ቤት አጠገብ አንድ ያረጀ ዛፍ አለ። ይህ ዛፍ በቤቱ ላይ እንዳይወድቅ ይፈራል። መውደቁ ደግሞ እንደማይቀር በዛፉ ስር ያሉ ሰዎች እርግጠኞች ናቸው። ታዲያ ዛፉን መቁረጥና በሚፈልጉበት አቅጣጫ ጉዳት ሳያደርስ መጣል በመፈለጋቸው በመጥረቢያ መቁረጥ ጀመሩ። ዛፉ ወፍራም በመሆኑ በመጥረቢያው ቢመቱትም ሊወድቅ ግን አልሞከረም። ግን የቤቱ ባለመቤቶች ይህን ግዙፍ ዛፍ ባለቻቸው አነስተኛ መጥረቢያ አየቆረጡት ነው። አንድ ቀን… አንድ ቀን… በቅርቡ የመጨረሻዋ የመጥረቢያ ምት ስታርፍበት ያ ብዙ ጊዜ ሲቆረጥ ያልወደቀው ያረጀና በበሽታ የሞተ ዛፍ መውደቁ አይቀርም።

    ዘመድ፣ ደኑ ተመንጥሮ ዛፍ በጠፋበት ዘመን ይህን መንግስት በዛፍ መመሰሌ እንደአጥሪነት ቢሰማኝም አሁን የሚደረገው ትግል ለውጥ ያላመጣ ቢመስልም አንድ ቀን (በቅርቡ) ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ብየ አምናለሁ። አንዲት ጠብታ ውሃ ግድብ ትንዳለች እንደሚባለው። ወይ ጉድ አሁንም ጠቃሚውን ግድብ ለመጥፎ ተጠቀምሁበት። ይቅርታ!

Comments are closed.

29508
Previous Story

የጃኪ ጎሲ የሕግ አማካሪ ተናገሩ፡ “ሸዋ ከዚህ ቀደም ቴዲ አፍሮን፣ ሔኖክ አበበንና ጆኒ ራጋን ከሷል”፤ በሸዋ ላይ የ$400,000 ካሳ ክስ አቅርበናል

Next Story

“እኛም ከሚሊዮኖቹ ውስጥ ነን” (የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop