ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ዋንጫ ውጭ ሆነ

May 6, 2013

(ኢትዮፉትቦል እንደዘገበው) በአፍሪካ ክለቦች በሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ ከግብፁ ዛማዜክ ጋር ዛሬ አዲስ አበባ ላይ የመልስ ጨዋታውን ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-2 በመለያቱ ከሻምፒዮናው ውጪ ሆነ፡፡ ዛማሌክ ወደቀጣዩ ዙር ማለፍ የቻለው ከሃገሩ ውጪ ቡዙ ባገባ በሚለው ህግ ነው፡፡ ሁለቱ ቡድኖች ካይሮ ላይ ከ15 ቀን በፊት አንድ ለአንድ ነበር የተለያት ፡፡በዛሬው ጨዋታ ዛማሌኮች ጨዋታው በተጀመረ በመጀመሪያው ደቂቃ ላይ ነበር የመሪነቱን ግብ በአብዱላሂ ሴሲ ግብ ማስቆጠር የቻሉት፡፡ከግቧ መቆጠር በኋላ ጫኛ ፈጥረው የተጫወቱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በ14ኛው ደቂቃ አቻ የምታደርጋቸውን ጎል በሽመልስ በቀለ ማስቆጠር ችለዋል፡፡ከግቧ መቆጠር በኋላ በተደጋጋሚ የግብ እድል የፈጠሩት ጊዮርጊሶች የመጀመሪየው ግማሽ የጨዋታ ጊዜ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩ ሁለተኛውን ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡
በአንድ የግብ ልዩነት እየመሩ የሁለተኛውን ግማሽ የጀመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በመጀመሪያው ግማሽ የነበራቸውን በማጥቃት ላይ ያዘነበለውን አጨዋወት በመቀየር በመከላከልላይ ያዘነበለ አጨዋወት ተከትለዋል፡፡የጌዮርጊስ አጨዋወት መከላከል መሆኑን የተረዱት  ዛማሌኮች ጫና ፈጠረው በመጫወት በ69ኛው ደቂቀቃ አደገኛ የግብ ሙከራ ማደረግ ችለው ነበር፡፡ጊዮርጊሶች የያዙትን ውጠት አስጠብቆ ለመውጣት መከላከሉን በመምረጣቸው ጨዋታው ሊጠናቀቅ ሶስት ደቂቃዎች ሲቀሩ በተቆጠረባቸው ግብ ከአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ውጪ ለመሆን ተገደዋል፡፡አቡዱለሂ ሴሲ ከክንፍ የተሻገሩለትን ኳሶች በጭንቅላቱ ገጭቶ ከመረብ በማገኛኘት ለዛማሌክ ጣፋጭ ድል አሰገኝቷል፡፡ በደርሶ መለስ ጨዋታዎቹ ዛማዜክ ጊዮርጊስ ላይ ያስቆጠራቸውን ሶስቱንም ጎሎች ከመረብ ያገናኘው ቡኪናፋሶዊው አብዱላሂ ሴሲ ነው ፡፡
የግብፁ ዛማሌክ ጠንካራ ከሚባሉት የሰሜን አፍሪካ ክለቦች እንዱ ነው፤ክለቡ በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና የአምስት ጊዜ አሸናፊ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫውን ያነሳው በ2002 ነበር፡፡ዛማሌክ በታሪኩ ከኢትዮጵ ክለቦች ለመጀመሪያ ጊዜ የገጠመው መቻል ሲሆን በ1997ዓ.ም ቅዱስ ጊዮርጊስን፤በ2000ዓ.ም ከኢትዮጵ ቡና ጋር ተገናኝቷል፡፡

 

photo0977 001
Previous Story

የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አንዷለም አራጌን እንዳይጠይቁ በልዩ ሀይል ተባረሩ

UDJ Unite
Next Story

ሁለቱን በጣምራ/በአንድነት ማስኬድ አይቻልም?

Latest from Blog

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የውጪ ግንኙነት የቤተክርስቲያኒቱን የሺሕ ዘመናት ታሪክ እና እሤቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርባታል!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) (ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) እንደመንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ- ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአንድ ቀን የተካሄደው፤ ‹‹የአፍሪካ  መንፈሳዊ ቀን/The African Spiritual

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |
Go toTop