May 16, 2011
13 mins read

የነርቭ እና ደም ፍሰት እክሎችን የሚፈውሰው አኩፓንቸር ህክምና ምን ያህል ውጤታማ ነው? ለየትኛው የጤና ችግር ይረዳል?

ኤዥያውያን በተለያዩ ተፈጥሯዊ የህክምና አሰጣጥ የሚታወቁ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አኩፓንቸር በመላው ዓለም ከፍተኛ ተቀባይነትን አስገኝቶላቸዋል፡፡ ከኤዥያ አገራት አኩፓንቸር ህክምና አንዱ በእጅ ላይ የሚሰጥ ሲሆን የመዳፍ ላይ በሚነሱ ሀሳባዊ መስመሮች የሚያያዘው /የሚወክለው/ የሰውነት ክፍል አለ፡፡ ይህን መስመር እየተከተሉ በመርፌ የሚወጋው እና የተለያየ ተጨማሪ ክብካቤዎች የሚደረግለት ክፍል ፈውስ እንደሚያገኝ ይታወቃል፡፡
ታሪካዊ አመጣጡን ስንመለከት ጥንት በንጉስ ፓስደን ዘመን መፍሬን ከድንጋይ፣ ከብርና ከመዳብ በመሳልና በማሾል ይየሰሩ ነበር፡፡ ይህንንም መገልገያ በደረቅ መርፌ ህክምና ላይ ይጠቀሙበት እንደነበር ይነገራል፡፡ የስነ ህክምናው አመጣጥ ይህ ሲሆን ኮሪያውያን የራሳቸውን ማሻሻያ ያደርጉበታል፡፡ በመላው አካል የሚወጋ (የሚቀመጠውን) መርፌ በእጅ ላይ በማድረግ እንዲሰጥ ያዛሉ፡፡ ለትግበራውም አምስት አይነት መንገድ ይከተላሉ፡፡
1. ኒውሮትራንስሚተር ቲዎሪ አዕምሮንና ህብለ ሰረሰረን ያነቃቃል
2. አውቶማቲክ የነርቭ ሲስተም የነርቭ ስርዓትን ያስተካክላል በተጨማሪም ስቃይን /ህመምን/ ያሰታግሳል፡፡
3. ጌት ኮንትሮል ሲሆን ናይሮክቲቤቲቭ ሪሴፕተር ለከፍተኛ ህመም ማስታገሻ ነው፡፡
4. ቫስኩላር ኢንተርስቲያልን ስንመለከት ኤሌትሪካዊ የሰውነት አቅም ላይ ያተኩራል
5. የብለድ ኬሚስትሪ ፖስቹሌት ሲሆን ደግሞ በደም ውስጥ የሚገኘው ቅባት ይመለከታል
ከመዳፍ የሚነሱ መስመሮች አስራ አራት ሲሆኑ ወደ አካል በሚወክሉት ስርዓት ውስጥ ወደ ሶስት መቶ ነጥቦች አሉ፡፡ በነዚህ ነጥቦችና መስመሮች ዙሪያ የሚሰጠው ህክምና ፍቱንነ ት በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ ከእስያ ወደ መላው ዓለም በመሰራጨት ከሳይንሳዊ ህክምና እና መድኃኒቶች ጎል ለጎን አካሄዳቸውን ጠብቀው ይሰጣሉ፡፡ የዓለም አቀፋዊ ተቀባይ ነቱ በየአገራቱ ስነ ህክምናው መስፋፋት ማረጋገጫ ነው፡፡
ይህ የህክምና ጥበብ በኢትዮፕያም የሚሰጥ ሲሆን የኮሪያውያኑ የህክምና አሰጣጥ ከሃያ ዓመት በፊት በፖሊሶች ህክምና ክፍል የአኩፓንቸር ስፔሻሊት ዶክተሮቹ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በጳውሎስ መክበብ ኢንተርናሽናል ከፍተኛ ክሊኒክ ይህንኑ አገልግሎት እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡
የአኩፓንቸርና የሳይንሳዊው ህክምና አንድነትና ትብብር
ዘመናዊው (ሳይንሳዊው) ህክምና በላብራቶሪ ቅድመ ህክምና የደም፣ የሽንትና ሰገራ የአክታ እና የመሳሰሉት ምርመራ የሚደረግ ሲሆን በተጨማሪም የተለያዩ ኬሚካላዊ መድኃኒቶችን በአፍ በሚዋጥ በመርፌ በሚወጋ መልኩ ይሰጣል፡፡ በሌላው በኩል ይህ ህክምና የሚሰጠው በተለያዩ ባክቴሪያዎች፣ ቫይረሶች፣ ጀርሞችና ፈንገሶች ሳቢያ ለሚከሰቱ ህመሞች ሲሆን መድኃኒቶቹ እነዚህን ፀረ ሰውነት (አንቲ ቦዲዎች በማጥፋት ህመሙ እንዲድን ያደርጋሉ) ከዚህ በተለየ መንገድ የሚሰጠው የአኩፓንቸር አገልግሎት ከሳይንሳዊው ህክምና በኋላ ተከስተው የነበሩ ህመሞች አጥቅተውት (ጎድተውት) የነበረው ሰውነትን ወደ ቀድሞ አቋም የመመለስ አቅምን ለማዳበር የሚረዱ ናቸው፡፡ ከላይ እንደተገለፀው ድክመት (ችግር) የተፈጠረበትን አካባቢ ከመዳፍ በመነሳት በሚሰጠው አገልግሎት በደረቅ መርፌ እየታገዘ ምንም አይነት ተጨማሪ መድኃኒቶችን ሳይጠቀሙ የሰውነትን የአሰራር ስርዓት ያስተካክላል፡፡ ምንም እንኳ (በሳይንሳዊ) በዘመናዊ ህክምናዊ ማስረጃ ባይረጋገጥም የተለያዩ በሽታዎችን ፈውስ በመስጠት ስኬታማነቱ እየታየ እንደሆነ ለማረጋገጥ ይህ አገልግሎት እንደ ስፔሻሊስቱ ዶክተር ገለፃ በተለያየ ምክንያት የሰውነት ፓራሊስስ ናህ ህመም ይኖራል ለዚህም መነሻው
መንስኤ
– እስፖርታዊ እንቅስቃሴ (ስፖርት ትሩማ)
– በእርግዝናና ከወሊድ ጋር በተያያዘ (የፕሪግናንሲ ትሩማ)
– በተለያዩ ኢንፌክሽኖች እንደ ኤች.አይ.ቪና የመሳሰሉት
– የደም ግፊት ስኳር፣ ኩላሊትና የመሳሰሉት የረጅም ጊዜ ህመሞች የሚያስከትሏቸው የደም መርጋት /መጓጎል/ የደም ስር በመፈንዳቱ የደም መፍሰስና የደም መርጋት ሰውነት ውስጥ በሚገኙት የደም ስር ዝውውሮች ላይ እክልን በመፍጠር የደም ዝውውርን በመግታት ህዋሳችን እንዲሞት የሰውነታችን አቋም እንዲዛባና በተለይም እንቅስቃሴ እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ የአኩፓንቸር አገልግሎት አላማ እነዚህንና መሰል ችግሮችን መፍታት ነው፡፡
የአኩፓቸር አገልግሎት የሚያስፈልጋቸው እነማን ናቸው?
ፓራላይዝ የሆኑ ሰዎች
1. በጭንቅላት ውስጥ ከደም መፍሰስ በኋላ
2. የጭንቅላት የደም መፍሰስ
3. ከሌሎች የነርቭ ችግሮችና ከዕድሜ መግፋት ጋር
4. የወገብ የመገጣጠሚያ የአንገት አጥንት ችግሮች
5. የደነዘዙና የሰነፉ ጡንቻዎች
6. ከስፖርታዊ እንቅስቃሴና እርግዝና ጋር የሚመጡ ችግሮችና የመሳሰሉት የአኩፓቸር ህክምና ያስፈልጋቸዋል፡፡
የህክምናው አሰጣጥ
ከሳይንሳዊ ህክምናው በኋላ ማንኛውም ታካሚ በአኩፓንቸር የዘመናዊ ዋግምት (ብለድ ቴክ አውት) በጭስ ስቲሙሌሽን ከመካሄዱ አስቀድሞ የሜዲካል ምርመራ (የጤና ምርመራ) ይደረጋል፡፡ ምክንያቱም የሚያስፈልጋቸ ውና የማያስፈልጋቸውን አስቀድሞ ለመለየት ይረዳል፡፡ ታካ ሚዎቹን ወይም ህክምናው የማይሰጣቸው እንደ ከፍተኛ የደም ግፊት፣ የልብ ህሙማን፣ በስትሮክ እና ኮማ ውስጥ ያሉ ፣ ሲወለዱ ጀምሮ ሽባ የሆኑ፣ ትኩስ ስብራት ወይም ከፍተኛ አደጋ (truma) ላይ ያሉ አገልግሎቱን አይጠቀሙም፡፡
ጥንቃቄዎች
ዶክተሮቹና እረዳታቸው ሚስ ሀን ኢትዮጵያ ውስጥ ህክምናውን በሚሰጥበት ወቅት የታዘቡትን ሲያጫውቱን
ኢትዮጵያውያን የአመጋገብ ዘይቤ ከጤና አኳያ ብዙም ተቀባይነት የለውም፡፡ ምክንያቱም ያፓራሊስስ አደጋ በደም ዝውውር ችግር የሚመጣ ነው፡፡ ለደም ዝውውር ስርዓት ምግብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ እናም ኢትዮጵያውያን ፀረ ሰውነት ተብለው የሚጠሩትን ስኳር፣ ቅባትና ጨው የበዛባቸው ምግቦችን ያዘወትራሉ፡፡ ይህም ለከፍተኛ የጤና ችግር ያጋልጣቸዋል፡፡ ውሃ አብዝቶ መጠጣት እና ምግብ ላይ መጠቀም ብዙም አይስተዋልም፡፡
በመሆኑም ትኩስ ፍራፍሬና አትክልቶችን ለመመገብ ቅባታማ ስኳርና ጨው የበዛባቸው ምግቦች መተው ወይም በጣም መቀነስ ከጥንቃቄዎቹ ዋነኛው ሲሆን በተጨማሪም እራስን ከድንገተኛ አደጋ መጠበቅ የጤና ክትትል ማድረግ ስፖርት ማዘውተር ማንኛውንም ኢንፌሽክን በጊዜው መታከም ከመርዛማ ነገሮች ራስን መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
የአኩፓንቸር ህክምና በመስጠት ከሚታወቀው ጳውሎስ መክብብ ኢንተርናሽናል ከፍተኛ ክሊኒክ ስፔሻሊስቶች ሚስተር ቹ እና ሚስ ሀን የሚያክሟቸው ሰዎችን ተመልክተን በአገልግሎቱ ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት በጠየቅናቸው መሰረት እንዲህ አጫውተውናል፡፡
ስማቸው መምህር ፋሲል አብርሃ ይባላል፡፡ ወደ ጳውሎስ መክብብ የመጡበት ምክንያት መጋቢት 13 በስራ ላይ እያሉ በደም ግፊት ምክንያት የግራ አካላቸው ላይ ባደረሰው ጉዳት ሰውነታቸው ፓራላይዝድ በመሆኑ ወደ አራት የህክምና ቦታዎች ሄደው ህክምናዊ መፍትሄ ስላላመጡ በጥቆማ መጥተው የአኩፓንቸር አገልግሎት መከታተል በጀመሩ ከአራተኛው ቀን በኋላ መቀመጥና መቆም እንደጀመሩ አሁንም በክትትል ላይ መሆናቸውን ገልፀው በአስራ አንደኛው ቀን ለመራመድ እየጀመሩ መሆኑን ገለፀውልናል፡፡ ሲመጡ የነበራቸውን ሁኔታ ሲገልፁ እራሳቸውን ለመቆጣጠር ካለመቻላቸው የተነሳ ለመንቀሳቀስ በዊልቸር ይጠቀሙ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ እንደየደረጃው የዋግምት ቫይብሬት የመታሸትና ሌሎችም ህክምናዎች በማግኘታቸው ለዚህ እንደበቁ ገልፀዋል፡፡ ብዙዎቹ ሰዎችን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ፓራላይዝ (ዝለት) በሚያጋጥማቸው ጊዜ የተለያዩ ህክምናዎች ጋር ቢሄዱም ለውጥ እንዳላገኙ የአኩፓንቸር ህክምናው በሰው በሰው ሲሰሙ መጥተው እንደሚጠቀሙ በ ውጤቱም ብዙዎች ደስተኞች መሆናቸውን ገልፀውልናል፡፡µ

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop