May 10, 2011
35 mins read

ናቲ ኃይሌ ከዘ-ሐበሻ ጋር

ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የጋዜጣችን አንባብያኖች ፤በዛሬው እለት ትንሽ ስለ ኪነጥበብ እና የኪነጥበብ ሙያተኞች ያላቸውን የሙያ ድርሻ እና የሂይወት ተሞከሮ ምን እንደሆነ ለማውጋት ደፋ ቀና ብለን ለእናንተ የሂይወት ልምዳቸው እና ተሞክሯቸው ያቀረቧቸው ሰራዎቻቸውን አስመልክቶ ምን ይመስል እንደሆነ እና እንዴት ሊመጥናችሁ ይችላል ለማካፈል እና እናንተስ በእነሱ ቦታ ሆናችሁ ይሳለፋችሁት ሂወት አለ ወይ ብሎ ለመነጋገር ያስችለን ዘንድ እና ያሳለፋችሁትን ሕይወት ወደ ሁዋላ ዞር ብለን እንድናስታውስ ይረዳን ዘንድ ቀድሞ የተሰሩ በፍቅርም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች የሰማናቸውን ዘፈኖች እንደ ትዝታ ማውጋታችን እና ትዝታችንን ይዘን መጓዛችንን ሳንሞክረው የቀረን አይመስልም ለዚህ ደግሞ የኪነጥበብ ሰዎች እና ስራዎቻቸው ተጠቃሽ ቦታ ይይዛሉ  ይህንን ቦታ እነሱ ከያዙት ለዛሬ በሂወቱ ዙሪያ እና በኪነጥበብ በቃቱ የማነጋግረው ወጣት ይኖረኛል ይህ ወጣት በቅርቡ አዲስ ሙሉ አልበም ለቆአል ይህ አልበም ከመለቀቁ በፊት ለረጂም ጊዜያት በኮፒ ራይት ምክንያት ምንም ካሴቶች ለገበያ ሊቀርቡ አልቻሉም ነበር ምክንያቱም በሃገራችን እየተስፋፋ የመጣው የቅጂ ስራ ንግድ  በሀገወጥ መልኩ መስፋፋት አደገኛ ሁኔታ መያዙን አስመልክቶ ስለነበር እና አሁን ትንሽ ክፍተት መፈጥሩን እና ይህ ሁኔታ ረገብ  ስላለ ያንን ሁኔታዎች በማመቻቸት አዲሱን አልበሙን “በቃ” በሎ ለእኛ አድማጮቹ  ጀባ ብሎናል ስለዚህ የዛሬው እንግዳችን ናትናኤል “ናቲ ሃይሌ “ የኪነ -ጥበብ አምዳችን እንግዳ ሲሆን ከእሱጋር ያሳለፍናቸውን ጊዜያቶች እኛም ለእናንተ ወጋችንን  እናካፍላችሁ …መልካም ምንባብ
በዘለአለም ገብሬ (የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ የቺካጎ እንደራሴ ጋዜጠኛ)
….ናቲ ሃይሌ እንደምን ዋልክ ?
ናቲ …እንዴት ነህ ዘሌ ?
ዘሃበሻ..እኛ ሰላም ነነ አንተ እንደምን አለህ እንግዲህ ሰላምታችንን በአንባብያኖቻችን ስም አደርስሃለሁ።
ናቲ ……..አመሰግናለሁ
ዘሃበሻ….በቅርቡ በገበያ ላይ ያወጣኸው “በቃ” የሚለው አልበምህ እንዴት እንደተሰራ እና ምን ይዘት እንደነበረው ለአንባቢያን እና ለአድናቂዎችህ ብትገልጽላቸው..?
ናቲ…ይህ ሁለተኛ አልበሜ ነው ያ ማለት የመጀመሪያዬን ከአምስት አመታት በፊት ነው የሰራሁት። ስለዚህ ይሄኛው ከመጀመሪያው ለየት የሚያደርገው ነገር አንደኛ እኔ እዚህ ቶሮንቶ ነው የምኖረው፤ ይህንንም ስራ ጀምሬ የጨረስኩት እዚህ ቶሮንቶ ውስጥ መሆኑ ነው፤ ሌላው ደግሞ ሙዚቃው ይዘቱ ሜሎዲው እና ሌላው ሙዚቃው ኳሊቲው እና ሙዚቃው ዌስተርናይዝድ የሆኑ ይዘቶች አሉት በደንብ እነሱን ያካተተ ነው ሂፕሆፕ አር አንድ ቢ እንደዚህ አይነት ነገሮች አሉት። ያ ማለት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ኢንደስትሪ ውስጥ እኔን በሚመስለኝ መልኩ ለየት ያለ ነገር አቅርቤአለሁ ብዬ ነው የማስበው። ግጥሙም በጣም ጥልቅ እና ጠንካራ ነው። እዚህ ካለኝ ልምድ ነው የሰራሁት። ያ ማለት ሌላ አገር መጥተህ ሌላ አገር ስትኖር እራስህን ለመኖር ስታስማማ ብዙ አይነት የሕይውት ልምድ ይኖርሃል እና እሱን ነው የጻፍኩት። እኔ እንደማስበው ሰው ሲሰማው ነው በበለጠ ሁኔታ የሚያ ውቀው እና በእኔ አመለካከት ለየት ይላል በዬ አስባለሁ ።
ዘሃበሻ……ስለዚህ በአዲሱ አልበም ስራህ ላይ ጥሩ ጥሩ የተዋጡ ስራዎች አሉ። በዚህም ስራህ ላይ አዳዲስ ይዘት ያላቸው የ አር ኤንድ ቢ ስታይል ያላቸው ዘፈኖች አሉ። እኔ ደግሞ በጣም ልቤ የጓጓለት አንድ ዘፈን አለ እስኪ ስለ እሱ ልጠይቅህ “ብላታዬ“ ብለህ ያቀነቀንከው  ዘፈን  የብላታልጅ አፍቅረህ ነው ወይስ የሰው ተሞከሮ በራስህ ውስጥ አድርገህ ሰርተኸው ነው?
ናቲ….ሳቅ……ይሕ እንግዲህ፡ ሓሳብ፡ነው፡ እኔ አሰብኩት። ግን አመለካከቴ የነበረው የቀድሞ ትልልቅ ሰዎች ልጆቻቸውን ሲታጩ እና በህብረተሰቡ ውስጥ ያለ ሰው ደግሞ እንደእነሱ ቦታ የማይሰጠው ሰው በዚህ ቦታ ላይ ቢወጣ ምንድን ነው? እንዴት? ብለህ ነው የምትጠይቀው የሚለውን ሃሳብ ነው የወሰድኩት። ሃሳቡን ለማንጸባረቅ እና የቀድሞ ንጉሳውያን ዘሮች ለህብረተሰባችን የሚሰጡት ግንዛ ቤ እና አመለካከት ምን ይመስላል የሚለውን ለመዳሰስ ሞከርኩ እንጂ እኔ ብላታም አላውቅም የብላታም ልጅ አላፈ ቀርኩም ግን ብላታ ሲባል እሰማለሁ ።ከዚያ ሃሳብ ተነስቼ ስለ ዱሮ ነገሮች የሚያውቅ  ነበር ይልማ ገ/አብ የሚባል የታወቀ ገጣሚ አለ እንዲጨርሰው አደረኩኝ ይህ ማለት ጥሩ ነው።
ዘሃበሻ…ምን ያህል ዘፈኖች ናቸው በአንተ የጥበብ ስራዎች ውስጥ የተካተቱት ወይንም የተሰሩት?
ናቲ… በአጠቃላይ ሁሉም ዘፈኖች ማለት ይቻላል፣ ምንድን ነው መሰለህ ያደረኩት እነዚህ ሶስት ዘፈኖች ብቻ ይልማ ገ/አብ እንዲረዳኝ አድርጌአለሁ። በይበልጥ  ብላታዬ የሚለው ዘፈንን እኔ ስሰራው እሱ እጁን አስገብቶበታል።  ያ የሆነው የእሱ የጥበብ ስራ በጣም ጥሩ እና የተዋጣ  ስራ ሲሆን እሱም የጠለቀ እውቀት አለው እና እሱን በስራዬ  ውስጥ ማስገባቴ በጣም አስደስቶኛል። ምክንያቱም ይልማ ማለት በኢትዮጵያ ውስጥ ስመ ጥር እና ጎበዝ ገጣሚ የሆነ እና በሳል ሰው ነው። ከእሱም ስራ በጣም ጥሩ ነገሮችን ተምሬአለሁ  ጥሩ ሆኖም እንዲወጣ ረድቶኛል። ሆኖም ግን ሁሉም ስራዎች የተሰሩት በእኔ ነው ማለት ይቻላል።
ዘሃበሻ…..የትኞቹ የትኞቹ ዘፈኖች ናቸው ሶስቱ ዘፈኖች የምትላቸው እነሱን ልትገልጽልኝ ትችላለህ?
ናቲ….ብላታዬ አንደኛው ነው ፤ ሁለተኛው አታምንም የሚለው ሲሆን እሱንም እራሴ ጀምሬ የሰጠሁት ዘፈን ነው ፤ ሶስተኛው ዘፈን ደግሞ ተለምኜ የሚለው ዘፈን ነው ይህንንም እንደዚሁ ሃሳቡን ግጥሙን ጀምሬው ነው በእሱ የተሰራው ።
ዘሃበሻ….ተለምኜ ስትል እንዴት ነው አንተ ተለምነህ እሷ ሸሽታ የደረስክበት ሁኔታ ነበር እንዴ በፍቅር አዙሪት ውስጥ?
ናቲ….ሳቅ….ብዙ ዘፈን ባንተ ሕይወት ላይ ላይፈጠር ይችላል። ብዙ ነገሮችን ልትገልጽ ትችላለህ ብዙ የሰዎችን ስሜት አንተም ሲሰማህ ታያለህ ለዚያ ነው እኔ የጻፍኩት.. በእርግጥ የሆነ ጊዜ አዎ በእርግጥ እንዲያውም አስታወስከኝ፤ አልመሰለኝም እንጂ ስትቀርብ በኋላ ላይ ግን ስትሸሽ ወደአንተ ይቀየራል …የአመለካከት ጉዳይ ሊሆን ይችላል ከአካልህ የጓደኛነት ሁኔታዎች ስትርቅ ወደአንተ ሊለወጥ ይችላል፤ ግን በአንተ በኩል ላይታወቅህ ይችላል። በወቅቱ ስለዚህ እንደዚህ አይነቱ ነገር በማንኛውም ሰው ላይ ሊፈጠ ር ይችላል እና እንዲህ አይነቱ ነግር ተፈጥሮብኝ ነበር ።
ዘሃበሻ……..ናቲ ይህንንን አልበም እንዳወጣህ በናሆም ሪከርድስ አማካይነት ከፍተኛ ሽልማት ተደርጎልሃል። ይህ የሽልማት ፕሮግራም ምን ይመስል ነበር፤ የናሆም ሪከርድስ ሽልማቱን ያቀረበልህ በምን አይነት መልኩ ነበር? ሌላው ደግሞ የአልበምህን መለቀቅ ምክንያት በማድረግ የሙዚቃ ምሽት ልዩ ፕሮግራም ነበረህ። ይህንን አስመልክተህ አጭር ገለጻ ብታደርግል?
ናቲ…..ናሆም ሪከርድስ እንግዲህ ቀደም ብሎ የኮፒ ራይት ህግን አስመልክቶ ላልተወሰነ ጊዜ የሙዚቃ ስራዎችን ላለመሸጥ ገደብ ላይ ነበር። በወቅቱም የሚወጡት ሙዚቃዎች ብዙም አልነበሩም ያም ሆኖ አብዛኞቹ የሚወጡት በነጠላ ዜማ አይነት ነገር ስለነበር ትንሽ ገበያውን አዳክሞት ነበር እና አሁን ግን ይህ ስራ ሲወጣ እነሱም በጣም ደስተኞች ነበሩ። በዚሁ አጋጣሚ ናሆም ሪከርድስን ሳላመሰግን  አላልፍም። እነሱው ፕሮሞት አደረጉልኝ፤ ለእንደዚህ አይነት ሥራ እነሱም ከልባቸው ነው የሚሰሩት እና የሰጡኝ ስጦታ በገንዘብ ነው። ያው መጠኑ እናዳለ ሆኖ እና እነሱ ለዚህ ስራ ደስተኛ ስለሆኑ እኔም በጣም ደስተኛ ነኝ። ምክንያቱም ስራህ ሰው ጋር ሲደርስ ሰው ሲያደምጥልህ አንተም ነህ ተጠቃሚ የምትሆነው ስለዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ ።
ዘሃበሻ….በጣም ደስ የሚል የሽልማት ስነስርአት ነው። እንግዲህ ወደፊትም በኪነጥበቡ ውስጥ ላሉ ባለሙያዎቻችን ስራዎቻቸው አስመልክቶ ለሚሰሩዋቸው ድንቅ ስራዎቻቸው እንደዚህ አይነት ሽልማቶች በየጊዜው ቢካሄዱ ጥሩ ነው ብለን ሃሳባችንን ሳንሰነዘር አናልፈም ምክንያቱም ብዙዎቹ አንጋፋ አርቲስቶች የሙዚቃ ሰዎች የመድረክ ተዋናዮች
በጣም ጥሩ ስራዎቻቸውን አቅርበው ከህዝባቸው ምንም ምስጋና ሳይቸራቸው አልፈዋል። ይህ ማለት ደግሞ ምንም ነገር አልሰራችሁም ይቀራችሗል ብሎ ምስጋናቸውን እንደመንሳት ይቆጠራል። ስለዚህ ምንም ነገር በስራቸው ሳይወደሱ ሳይደነቁ ብዙዎቹ አልፈዋል። እንደ አብነት ብንጠቅስ  አለባቸው ተካ፣ ምኒሊክ ወስናቸው፣ ኮረኔል ሳህሌ ደጋጎ ፣ ጥላሁን ገሰሰ… እንደ ምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። በህልፈተ ሕወታቸው ታሪካቸውን ከማንበብ ይልቅ ጥሩ ነገርን ቢያበረክቱላቸው በሕይወታቸው ቀና  እና ደስተኛ ሆነው ለህዝባቸውና ለስራቸው ፍቅር ኖሮአቸው ይዘልቃሉ ለማለት ወደን ነው። ስለዚህ ናሆም ሪከርድስ ያደረገው የሽልማት ስነስርአት የሚወደስ ስራ ሲሆን ለወደፊቱ ለሌሎቹም ጥሩ እመርታ ያሳያል ብለን እንገመታለን።
ዘሃበሻ….ናቲ አንተ ያለኽው በውጭ ነው። ስለዚህ ህይወትህ ምን ይመስላል? አሁንስ ሙያህን ይዘህ ለመጓዝ ይመቻል ብለህ ታስባለህ ካለው ኑሮ እና ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር?
ናቲ….ትልቅ ጥያቄ ነው። ውጭ ሃገር ቅድም እንደገለጽኩልህ በጣም ይከብዳል እንኳን ለአርቲስት አይደለም ለማንኛውም ሰው ቢሆን ህይወቱን ለማሻሻል ቤተሰቡን ለመርዳት እራስን አሻሽላለሁ ብሎ በተለይ ከኢትዮጵያ ለመጣ ሰው ይከብዳል ; በዚህ ውስጥ ሆኖ ደግሞ ሙያህን መስራት ደግሞ በጣም በጣም ከባድ ነው ምንድነው የሚሆነው መሰለህ በተመሳሳይ ሰአት ሌላ ስራ መስራት አለብህ። ስለዚህ ሙያዬን ብለህ ስትል እዚህ ጋር የተለያዩ ቢሎች ይጠብቁሃል። ኢትዮጵያ ቢሆን የእናትህ ቤት የዘመድ አዝማድ ቤት አለ ተረዳድተህ ትኖራለህ። እንደዚህ አይነት ነገሮች ላይ ብዙ ጊዜ አታስብም። በተለይ ለኑሮ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች ላይ ማለት ነው። እዚህ አገር ግን ስትኖር መስራት አለብህ። ካልሰራህ አትበላም። መኖሪያ አይኖርህም። እነሱን ነገሮች ካላደረገህ ደግሞ ለሙያ ቦታ መስጠት በጣም በጣም ከባድ ነው። እና በዚያ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ነው ይህንን የሙዚቃ ስራ ሰርቼ የጨረስኩት ማለት ነው። እንዳልኩህ አሁን እኔ እንደዚያ ሆኛለሁ። ያም ማለት አሁን ሰው ሆኛለሁ የተለያዩ ልምዶችን አግኝቻለሁ። እነሱ ደግሞ የተሻለ ስራ እንድታመጣ ያደርጉሃል። ይህ ደግሞ አሁን መጥፎ የሚሆንብኝ አይመስለኝም። ጥሩ ሁኔታዎች ላይ ነኝ ያለሁት ።
ዘሃበሻ…በነገራችን ላይ የአንተን ሙሉ አልበም በደንብ እና በሚገባ ሁኔታ አዳምጬዋለሁኝ። ነገር ግን ከአንድ የሙዚቃ ባለሙያ ጋር ተመሳሳይነት ያለው አንድ ስራ አለህ። ይህ ስራህ ከዚያኛው የሙዚቃ ባለሙያ ጋር ሪትሙን ተወራርሳችኋል ወይስ ምንድን ነው? ዘፈኑ የችክችካ እና የወሎ የአዘፋፈን ስልት ወይንም  ስታይል ያለው ሲሆን በሁለታችሁም በኩል ምንም አይነት ልዩነት የለውም። እንደዚህ አይነት ስራዎች ደግሞ በአሁን ሰአት እየበረከቱ ነው የመጡት አብዛኞቹ የሰውን ሪትም (የሙዚቃ ቅንብር)፣ዜማ ፤የአዘፋፈን ስታይል ፣ አጠቃላይ ይዘቶች ተመሳስለው ይሰራሉ  ስለዚህ የአንተን ስራ እንዴት ታየዋለህ ?
ናቲ….ኦውውውው አሁን ያልከኝን ነገር አስቤውም አላውቅም። ማንም ሰው ነግሮኝ አያውቅም። በእውነት የምነግርህ ይህንን ዘፈን የሰራሁት የዛሬ ሶስት አመታት ገደማ ነው እውነቱን ልግለጽልህ የዳዊት ጽጌ ያልከኝን ዘፈን አልሰማሁትም። ምክንያቱም እኔ የነበርኩባቸው ሁኔታዎች ሌላ ዘፈኖች የምሰማባቸው አጋጣሚዎች አልነበሩም፣ ሙሉ በሙሉ አልሰማም ማለቴ ሳይሆን ሙሉውን ጊዜዬን እራሴ ስራ ላይ ነበር ትኩረት አድርጌ የምሰራው ለማለት ፈልጌ ነው እንጂ በወቅቱ እንደኔ ያሉትን የኢትዮጵያኖች አርቲስቶች ስራዎቻቸው ሲወጣ አዳምጣለሁ፤ አድንቄ አልፋለሁ እንጂ እስካሁን የምትለኝን ዘፈን  አልሰማሁትም፤ አላውቀውም።  ምናልባት የእኛ አገር ቅኝቶች እና ቅንብሮች ተመሳሳይ ስለሆኑ ሊመሳሰሉብህ ይችላሉ። በተለይ እንኳን አንተ ሌላም ሰው ካለ በደንብ ማዳመጥ አለብኝ። ነገር ግን እኔ እንደዚህ ሰምቼ ከሰው የወሰድኩት ምንም አይነት ነገር የለም ።
ዘሃበሻ…. ናቲ በአሁን ሰአት በአዲሱ አልበምህ ከህብረተሰባ ችን ጋር ተቀላቅለሃል። ወደፊትስ በምን አይነት ዝግጅት እና ኮን ሰርቶችንም ሆነ የሙዚቃ ስራዎችህን በተመለከት ተዘጋጅተሃል ?
ናቲ…… እንግዲህ አሁንም ይቀጥላል።  የእኔ የዚህ አዲስ አልበም ዋነኛው ህዝብን ለማስደሰት መሞከር ነው። ወደፊትም በአዲስ መልክ አዲስ ነገር ይዞ ለመቅረብ መሞከር ነው። እዚህ አገር አሁን በአለፉት ጥቂት አመታት ብዙ ዘፈኖች ወጥተዋል እና ሁሉንም ስናያቸው በቢታቸው ሜሎዲያቸው የአዘፋፈን ቅላጼአቸውም ሆነ ሌሎቹም ነገሮች ፈጽሞ አይገናኙም። ስለዚህ እነሱ ሁልጊዜ ሙዚቃውን እያሰደጉት ነው ያሉት። ያ ማለት ለህብረተሰቡ አዳዲስ ሰራዎች ያሳይዋቸዋል። አዲስ ስራዎች ይዘውላቸው ይቀርባሉ ለሙዚቃው ትልቅ ለውጥ ያሳዩታል እና እኔም ያንን ነው እያሰብኩ ያለሁት። ህብረተሰባችንም ቢሆን አዲዲስ ነገር መስማት አይጠላበትም መስራትም ያለብን  ሁለጊዜ ሊደመጥ የሚችል ስራ እና ለየት ያለ አንድ አይነት ያልሆነ ነገር መሆን ይገባዋል ብዬ አምናለሁ። እንደዚያም ሲሆን ሙዚቃው ያድጋል። ደግሞም አዳዲስ ሙዚቃዎችን የሚፈጥሩ ሰዎች ይኖራሉ እና በአሁን ሰአት ከሌሎች አርቲስቶች ጋር በጋራ በመሆን ጥሩ ስራ ለመስራት ላይ ነው ያለሁት።
ዘሃበሻ ….ይህ በእንዲህ እያለ በአሁን ሰአት የተለያዩ የሙዚቃ ባለሙያዎች የሙዚቃን ብቃት እና ጥራት ወይንም ጥሩ መልእክት እንዳለው የተለያዩ ክሊፖች በመስራት ጥረት ያደርጋሉ። ምክንያቱም የሙዚቃን ህይወት ስለሚገልጹበት ሊሆን ይችላል።  ስለዚህ  እኛ አገር ደግሞ እንደዚህ አይነት ስራዎች አይስተዋሉም። ቢሰሩም ጥራት እና ብቃታቸው በጣም ዝቅተኛ ነው ዳንሰኞችም ሆኑ በጥሩ ኬሪዮግራፈር ኖሮአቸው አይሰለጥኑም። ቪዲዮግራፈሮችም ጥሩ ሙያው እና ብቃቱ ኖሮአቸው አይሰሩም። እንደዚሁም ሙዚቀኞችም ስራችን ነው ብለው የሙዚቃ ክሊፕ ሲሰሩ የዳንስ ትምህርትም ሆነ የቮካል ሌሰን አይወስዱም። አንተ ግን የስራህን ውጤት እንዴት አድርገህ በምስል አስደግፈህ ለመስራት ታስባለህ? በሙዚቃ ውስጥ ሊኖርህ የሚችለው ሚና ምንድን ነው?
ናቲ….ልክ ነህ። በተሻለ ነገር ሁለጊዜም መምጣት አለብን ብዬ አምናለሁ። በሁሉም አቅጣጫ የተሻለ ነገር መስራት ይጠ በቅብናል ፊልም ወይንም ቪዲዮ ስትሰራ መጨነቅ አለብህ።
ዘሃበሻ፦ በኪነጥበብ ውስጥ እያሉ ሰለ ኪነ-ጥበብ ሰዎች እና የስም ስያሜአቸው ስናስብ በአጠቃላይ ለባለሙያዎቹ የሚሰጥው የስም ስያሜ ለሁሉም አንድ አይነት ነው። ይህም ስያሜ ብዙዎቹን አጠያያቂ  ሆኖ እናገኘዋለን።  ሁሉም ሰዎች የተሰጣቸው ስያሜ አንድ መሆኑ ግራ ያጋባል። ስለዚህ በአንተ አመለካከት አርቲስት የሚባለው ሰው ማነው?
ናቲ፦ አርቲስት የሚባል ሰው ዋው…..አርቲስት የሚባለው ሰው በእኔ አመለካከት ለሰው የሚኖር ሰው ነው። ሰውን የሚያከብር መሆን አለበት። ምክንያቱም የሚያቀርበውን  ሰው አይቶ መርህ የሚሆን ማለት ነው፤ ምሳሌ መሆን አለብህ ማለት ነው። ካንተ ህይወት ሰው መማር አለበት፤ ያንን ካላደረገህ አንተ ካላደረግህ የሰው መርህ መሆኑ ይቀራል ማለት ነው። ከአንተ ህይወት ጋር እነዚህ ህይወቶች የሚመጡ ናቸው ስለዚህ መርህ ወይንም አስተማሪ መሆንህ የሚጀምረው ከአንተ ስራ ባህርይ እና ከአንተ የስራህ ገላጭነት ዋና ሚና ይጫወታል እና ከአንተ ንግግር ሰዎች ይማራሉ። እዚህ አገር አይተህ ከሆነ ትልልቅ አርቲስቶች  ለህዝቦቻቸው ትልቅ አስተማሪዎች እና ዋና ገላጮች ናቸው። ያ ደግሞ ማለት የአርቲስቶች ፋሽን የዘፈን ወይንም የጸጉር ስታይል ነው የሚታየው ስለዚህ እና እነዚህ ሰዎች ትልቅ እይታ ናቸው። አርቲስት የሚባለው ጥሩ የሚሰራ እና በጎ አድራጎት ውስጥ የሚገባ መሆን አለበት። እሱን የሚያደርግ ነው ለእኔ አርቲስት የሚባለው። እንዲህ ሲሆን ለህብረተሰብህ ታሪክ ትሰራለህ ለሚያድጉትም ሆነ ለትልልቆቹ ትልቅ የሆነ ክብር ይኖርሃል። እነሱም ለአንተ ትልቅ ቦታ ይሰጡሀል እና ያንን ደግሞ ከልብህ የምታደርግ አርቲስት መሆን አለብህ። እኔ እንደማስበው ይሄ ይመስለኛል አርቲስት የሚባለው…ከሰብአዊ እርዳታ ጋር ህይወቱ የተቆራኘ ሰው ለእኔ አርቲስት ነው!!
ዘሃበሻ ….እስኪ የዚህ አዲሱ አልበምህ የቅኔ ዘረፋ የግጥሙ አወራረድ እና የአዘፋፈን ህይወት በአንተ እንዴት ይገለጻል ? አንተ ከምትወደው አንዱን ዘፈንህን ብታቀነቅንልን?
ናቲ……እኔ እንግዲህ ገና አሁን ነው የተነሳሁት ማታ ስራ ስለነበረብኝ ድምጼ ጥሩ ላይሆን ይችላል ነገር ግን አንዱን እሞክርላችኋለሁ  እሞክራለሁ ….ዘፈኑ ብዙ ነገሮች አሉት አንድ ዘፈን እንዳወጣህ ብቻ አይደለም የምታየው። ብዙ አስተማሪ የሆኑ ነገሮች አሉት አዳዲስ ነገር አለው ይህንን ለማወቅ መስማት ያስፈልገዋል። ዘፈኑን ለማጣጣም ጊዜ ያስፈልጋል።  እንግዲህ ብዙዎቹን ነገር ደጋግመን ብለናል ስለዚህ ዘፈኔን ሰምታችሁ ለወደዳችሁትም ሆነ ለምታደምጡት በጣም አመሰግናለሁ። እናንተንም እድሉን ስለሰጣችሁኝ ሳላመሰግን አላልፈም። በዚህ አጋጣሚ ወደፊት ደግሞ ከዚህ የተሻለ ይዤ ለመቅረብ እሞክራለሁ …እንግዲህ ዘላለም ዝፈን ካለከኝ “በቃ” የሚለውን ዘፈን እዘፈንልሃለሁ ለእኔ ትልቅ መልእክት አለው ስለዚህ እሞክረዋለሁ
   ዛሬ ትኖር ነገ አታውቅም
   ለምንድነው የምትጨነቀው
  ሁሉ ወረት የዚች አለም
መች ይዘልቃል ለዘላለም       
 በቃ ብቃ በቃ ዛሬን  ኑር በቃ
በሰላም ኑር  ከሁሉም ጋራ
እንግዲህ ይህ አልበም በቅርቡ ታትሞ ለገበያ ቢቀርብም በህዝብ ዘንድ ዘልቆ ገብቷል። ይህ ማለት ደግሞ የዘፈኑን ጥልቅ ስሜት ያዳመጠው ያውቀዋል። በጣም ቆንጆ እና በሳል የሆነ መልዕክት ያለው ስራ ነው። በዚህ አጋጣሚ እኛም እድሉን ካገኘን መግለጽ የሚገባን ነገር ቢኖር የአርቲስቶቻችንን የግል የፈጠራ ስራ በህገ ወጥ መንገድ አባዝቶ ከመጠቀም እና ከመሸጥ ተቆጥበን በትክክለኛው ቅጅ ጥራት ያለው ሙዚቃ እንደናደምጥ እና አርቲስቶቻችንንም ስራዎቻቸውን እና ውጤቶቻቸውን ብንደግፍላቸው መልካም ነው እንላለን። በሌላም በኩል ደግሞ ለአርቲስቶቻቸን እርስ በእራሳችሁ የምታደርጉት የሙዚቃ ግጥም፣ዜማ ፣እንዲሁም የቅንብር ስራ ቀርቶ በትክክለና የእራሳችሁን የሆነ አዳዲስ የፈጠራ ስራ ብታቀርቡ የሙዚቃ እድገቱን ታፋጥኑታላችሁ እንጂ አትገድሉትም  አድማጮቻችሁንም ከመሰልቸት ወደ አድማጭነት ለመሳብ ሞክሩ ለሁላችሁም መልእክታችን ነው።
ዘሃበሻ…….ናቲ ይህንን ዘፈን ለህዝብ ስታቀርብ ለአንተ የሰጠህ ስሜት ምንድን ነው? አንዳንድ የሙዚቃ ባለሙያዎች የሚሰሩት የሃዘናቸውን መግለጫ እሮሮ ሊሆን ይችላል ወይንም የፍቅር የደስታ… ስለዚህ ያንተስ በየትኛው ሁኔታዎች ሊመደብ ይችላል?
ናቲ …..የስራህን ፍሬ ስታይ በጣም ደስ ይልሃል ማንም ሰው የስራውን ስኬት ወጤቱን ሰምሮለት ምን ያህል ደስ እንደሚለው ታውቃለህ። እና የአርት ስራ በተለይ በተለይ.. ከማንም ይበልጥ አንተን ነው የሚያስደስትህ። ምክንያቱም በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ ስለምታልፍ ከዚያ ሁሉ ነገር አልፈህ ዛሬ የስራህ ውጤት ፍሬ ሲያፈራ እንዴት እንደምትገልጸው እና እንደምትወደው ልነግርህ አልችልም። ያ ደሞ አንተን የሚገልጽ ነው። ሁሉም ተጠናቆ ለህዝብ ሲወጣ ደግሞ እና እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ በዙ ድካም እና ልፋት አለው ስለዚህ  እግዚአብሄርንም አመሰግናለሁ ሌሎችም በቅርብ ሆነው የሚረዱኝ ሰዎች አሉ እነሱንም ሳላመሰግን አላልፍም ።
ዘሃበሻ….. በመጨረሻም የምንሰጥህ እድል ማስተላለፍ የምትፈልገው መልእክት ካለ እና ስራዬን በተቀላጠፈ ሁኔታ ረድተውኛል የምትላቸውንም ሆነ ከጎነህ ሳይለዩህ የስራህን ውጤት እንዲሰምር ላደረጉልህ ዘመድ ወዳጅ ጓደና እንዲሁም የሙዚቃ ባለሙያዎች የምታስተላለፈውን የምስጋና መልእክት ካለህ እድሉን ልስጥህ እና በዚሁ እሰናበትሃለሁ ለአሳለፍናቸው ወርቃማ ጊዜያቶች ከልብ እያመሰገንኩኝ ወደ አንተ እመለስሃለሁኝ ?
ናቲ ….በጣም በጣም  ከልብ ለዘሃበሻ አዘጋጆች እና ለአንተም ለዘላለም ገብሬ ጊዜህን ሰውተህ ከእኔ ጋር ቆይታህን ስላደረግህ በጣም አመሰግናችኋለሁ። ይህንንም ቃለ ምልልስ ለምታነቡትም ሁሉ እጅግ አድርጌ አመሰግናችኋለሁ። በተለይ ገዝታችሁ ላደመጣችሁም ሆነ ገና ለምትገዙት ማንኛውም ዘፈን ቀስ ብሎ ስለሆነ ውስጠሚስጥሩ የሚገባችሁ እና ጊዜአችሁን ለስራችን እንደትሰጡት እጠይቃችኋለሁ።  አድምጡት አዳዲስ ነገር ግዙ። ሁሉም ነገር ቀስ ብሎ ነው የሚገባው። በዚህ ዘፈንም ላይ ለረዳችሁኝ ወንድሞቼን፣ እናቴን፣ ጓደኞቼን፣ ቤተሰቦቼን እንዲሁም ናሆም ሪከርድስን፣ ኤልያስ ፍቅሩን እና ገመቹን ደገፋን ከልብ በመነጨ ምስጋና ከልብ አመሰግናለሁ።መልካም ጊዜ ለሁላችሁም
ዘሃበሻ….እኛም ከልብ እናመሰግናለን መልካም ቆይታ!!!!!µ

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop