የፋኖና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ስምምነት፥ የዘመቻ ሰማዕታት ተጋድሎና ሌሎችም፥ ለፊልድ ማርሻሉ የቀረበው ሰነድ፥ የምክክር ኮሚሽኑ August 27, 2025 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email የፋኖና የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ስምምነት፥ የዘመቻ ሰማዕታት ተጋድሎና ሌሎችም፥ ለፊልድ ማርሻሉ የቀረበው ሰነድ፥ የምክክር ኮሚሽኑ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email 2 Comments Leave a Reply መቼም የግድ ግድ ከሆነበት በተወሰነ ደረጃ የአማራ ፋኖ ከጤነኛ የኦሮሞ ሰራዊት ጋር ቢያብር በተመጠነ ደረጃ አግባብነት ይኖረዋል ነገር ግን ለጥፋቱ ሁሉ ምክንያት ከሆኑት ትግሬዎቹ ጋር አብሮ መስራቱ በምንም ሁኔታ ተቀባይነት አይኖረውም። Reply የተሳከረው የሃበሻ ፓለቲካ አሁን ደግሞ ብሎ ብሎ ፋኖ ከወያኔ አልፎ ተርፎም ከሻቢያና ከኦነግ ሸኔ ጋር አብሮ ሊሰራ ነው ተብለናል። ይህ በዘር የተሳከረው የብሄርተኞች ስብስብ ከየትም ጎን ይሁን ከየት ሃገርና ህዝብን ማዳን አይቻለውም። በኢትዮጵያ የፓለቲካ ታሪክ ውስጥ ሁሉን አቀፍ የሆነ ድርጅት ከኢህአፓ በላይ አልነበረም ዛሬም የለም። ፍጻሜአቸው ግን የሮም አወዳደቅ ነው የሆነው። በከተማ ሰው መግደልና ቤትና ንብረታቸውን ቤተሰብ ጥለው አብረዋቸው የተሰለፉትን አንጃ በሚል ሰበብ መግደል ሲጀምሩ ውድቀታቸው ከሌሎች አያሌ የፓለቲካ ውስብስብ ጉዳዪች ጋር ተያይዞ ግባዕተ መሬታቸውን አፋጠነው። አሁን ላይ በየድህረገጽ የሚለጠፈውና የሚወራው ሁሉ 100% የፈጠራ ወሬ ነው። ውሸቱን የሚነዙት መንግስትም በዚህም በዚያም የታጠቁ ሃይሎች ጭምር ናቸው። ማረክን፤ በተነው፤ አፈረስነው፤ ከተማ ያዝን ይሉናል … ቱልቱላ ሁሉ ህዝብ አሸበርን፤ ዘርፈን ወጣን፤ በምትኩ ደግሞ ወታደር ገብቶ በወረፋው አሸበረ ቢሉን ዜናው ወደ እውነት ይጠጋል። በቅርብ ቀን አንድ ትንሽ ነካ የሚያደርገው የሚመስል ሰው ሃበሻ ነህ አለኝ። አዎን በማለት በትህትና መለስኩለት። ከየትኛው ብሄር ነህ ሲለኝ… አልፌው ሄድኩና ጥያቄው ከነከነኝ። ብሄሬን ማወቁ ሰው ከመሆኔ በላይ ለዚህ ሰው የሚጠቅመው ምን ነገር አለ እያልኩ እያሰላሰልኩ መንገዴን ስቀጥል። ይህች ስንኝ ወደ ጭንቅላቴ መጣች። ዘርህ ከወዴት ነው ብሎ ቢጠይቀኝ የወፍ ዘር ነኝ አልኩት ጥያቄው ቢገርመኝ… በአንድ ሃሳብ በአንድ አላማ ሃበሻ ተጠቃሎ የኖረበት የታሪክ ምዕራፍ የለም። ሾላኮችና የጠላት ፊርማቶሪዎች ያኔም ነበሩ ዛሬም አሉ። ግብጽ የሃገራችን አንድነትና ህብረት ትሻ ይመስል ከግብጽ ጋር አብረን እንሰራለን ይሉናል። የእኛ ችግር አንድ እና አንድ ነው። የወንድምና የእህቶቻችን ደም ፈሶ ካላዬን በስተቀር የበላይነት አይሰማንም። የሚሞተውም የሚገድለውም ወገን ወገኑን ነው። ለዚህ ነው ምንም መልክ ይኑረው ምንም የሃበሻ የትጥቅ ትግል የቆሻሻ ክምር ነው የምንለው። ዞር ብሎ የአጭር ጊዜ የሃገሪቱን ታሪክ ላገናዘበ የመሳሪያ ጋጋታ ለህዝብና ለሃገር ጠቅሞ አያውቅም። 70 ዓመት ሙሉ በጣሊያን የተገዛችው ኤርትራ ዛሬ ላይ ቅኝ ግዛት አድርጋን እያሉ የሚያላዝኑት ኢትዮጵያን ነው። ታሪክን ወደ ኋላ ተመልሶ ለተመለከተ ግን ነገሪየው ሌላ ነው። ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ በጣሊያኖች/በእንግሊዞች/በሃበሾች የተጻፉ መጽሃፍትን ለቅሞ ማንበብ አሁን ወያኔና ሻቢያ ሌሎችም ከሚዘረግፉት የውሸት ፕሮፓጋንዳ ራስን ለማጽዳት ይጠቅማል። የዓይን ምስክሮች በጊዜው ኑረው የጻፉት አያሌ መጽሃፍቶች አሉና! ታዲያ ከላይ መሳይ መኮነን የሚነግረን ወሬ መመዘን ያለበት እርስ በእርሱ አንድ መሆን ያቃተው ፋኖ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው በሃሳብ እጅግ ከራቀው የኦሮሞ ታጣቂ ጋር አንድ ሆኖ መስራት የሚቻለው? የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር ይባላል። ግን ነገር ለማጦዝ ወሬ ለማስፋፋት ይጠቅማል። እንዲያው ይሁን ቢባልና ሁለቱ ሃይሎች አብረው መስራት ቢጀምሩም ነገሩ አይዘልቅም። ይህ ደግሞ የሃበሻ ፓለቲከኞች ዋና መለያ ነው። ተስማማን ባሉን ማግስት አንድ አፈንግጦ ሌላውን ያስበላል ወይም ራሱ ይበላል። ያለፍንበት መንገድ የሚያሳየው ይህኑ ታሪክ ነው። ለዚህ ነው ከመታኮስና/ሃገርን ወደ ድንጋይ ዘመን ከመለወጥ በሃሳብ ልዪነት ተስማምቶ አብሮ በሰላም መኖር ቀዳሚ አማራጭ የሚሆነው። ጊዜው ተለውጧል። በድር በገደል ገብቶ በመሸጎጥ የሚፈጸም ፍልሚያ የህዝብን ሰቆቃ ከማባዛት ያለፈ ሌላ ለውጥ አያመጣም። ወያኔን ለማውረድ ስንቱ ታገለ? ግን ወያኔ ከስልጣን የወረደው በሰላም እንጂ በጦር መሳሪያ አይደለም። ብልጽግናም የሚወርደው በምርጫ እንጂ በጦር መሳሪያ አይሆንም። ይህ ጦርነትን እንደ ቋሚ አማራጭ የመውሰድ የፓለቲካ አቋም ሊፈተሽና ሊቀየር ይገባል። በዚህ በፋኖና በሌሎች ታጣቂዎች ሰበብ ያለ ትምህርትና የጤና ተቋማት በር ተዘግቶባቸው ያሉትን ወገኖቻችን እናስብ። የግብጽም ድጋፍ፤ የሻቢያም አይዞአችሁ ባይነት፤ የወያኔም ሴራ ለህዝባችን አይጠቅምም። በኢትዮጵያ ውስጥና ውጭ ያላችሁ ሁሉ በግልጽ ተነጋግራችሁ ሰላም አስፍኑ.. የትጥቅ ትግል ዘመን የሻረው፤ መጨረሻ የሌለው አረንቋ ነውና ለሰላም ስሩ! Reply Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ
መቼም የግድ ግድ ከሆነበት በተወሰነ ደረጃ የአማራ ፋኖ ከጤነኛ የኦሮሞ ሰራዊት ጋር ቢያብር በተመጠነ ደረጃ አግባብነት ይኖረዋል ነገር ግን ለጥፋቱ ሁሉ ምክንያት ከሆኑት ትግሬዎቹ ጋር አብሮ መስራቱ በምንም ሁኔታ ተቀባይነት አይኖረውም። Reply
የተሳከረው የሃበሻ ፓለቲካ አሁን ደግሞ ብሎ ብሎ ፋኖ ከወያኔ አልፎ ተርፎም ከሻቢያና ከኦነግ ሸኔ ጋር አብሮ ሊሰራ ነው ተብለናል። ይህ በዘር የተሳከረው የብሄርተኞች ስብስብ ከየትም ጎን ይሁን ከየት ሃገርና ህዝብን ማዳን አይቻለውም። በኢትዮጵያ የፓለቲካ ታሪክ ውስጥ ሁሉን አቀፍ የሆነ ድርጅት ከኢህአፓ በላይ አልነበረም ዛሬም የለም። ፍጻሜአቸው ግን የሮም አወዳደቅ ነው የሆነው። በከተማ ሰው መግደልና ቤትና ንብረታቸውን ቤተሰብ ጥለው አብረዋቸው የተሰለፉትን አንጃ በሚል ሰበብ መግደል ሲጀምሩ ውድቀታቸው ከሌሎች አያሌ የፓለቲካ ውስብስብ ጉዳዪች ጋር ተያይዞ ግባዕተ መሬታቸውን አፋጠነው። አሁን ላይ በየድህረገጽ የሚለጠፈውና የሚወራው ሁሉ 100% የፈጠራ ወሬ ነው። ውሸቱን የሚነዙት መንግስትም በዚህም በዚያም የታጠቁ ሃይሎች ጭምር ናቸው። ማረክን፤ በተነው፤ አፈረስነው፤ ከተማ ያዝን ይሉናል … ቱልቱላ ሁሉ ህዝብ አሸበርን፤ ዘርፈን ወጣን፤ በምትኩ ደግሞ ወታደር ገብቶ በወረፋው አሸበረ ቢሉን ዜናው ወደ እውነት ይጠጋል። በቅርብ ቀን አንድ ትንሽ ነካ የሚያደርገው የሚመስል ሰው ሃበሻ ነህ አለኝ። አዎን በማለት በትህትና መለስኩለት። ከየትኛው ብሄር ነህ ሲለኝ… አልፌው ሄድኩና ጥያቄው ከነከነኝ። ብሄሬን ማወቁ ሰው ከመሆኔ በላይ ለዚህ ሰው የሚጠቅመው ምን ነገር አለ እያልኩ እያሰላሰልኩ መንገዴን ስቀጥል። ይህች ስንኝ ወደ ጭንቅላቴ መጣች። ዘርህ ከወዴት ነው ብሎ ቢጠይቀኝ የወፍ ዘር ነኝ አልኩት ጥያቄው ቢገርመኝ… በአንድ ሃሳብ በአንድ አላማ ሃበሻ ተጠቃሎ የኖረበት የታሪክ ምዕራፍ የለም። ሾላኮችና የጠላት ፊርማቶሪዎች ያኔም ነበሩ ዛሬም አሉ። ግብጽ የሃገራችን አንድነትና ህብረት ትሻ ይመስል ከግብጽ ጋር አብረን እንሰራለን ይሉናል። የእኛ ችግር አንድ እና አንድ ነው። የወንድምና የእህቶቻችን ደም ፈሶ ካላዬን በስተቀር የበላይነት አይሰማንም። የሚሞተውም የሚገድለውም ወገን ወገኑን ነው። ለዚህ ነው ምንም መልክ ይኑረው ምንም የሃበሻ የትጥቅ ትግል የቆሻሻ ክምር ነው የምንለው። ዞር ብሎ የአጭር ጊዜ የሃገሪቱን ታሪክ ላገናዘበ የመሳሪያ ጋጋታ ለህዝብና ለሃገር ጠቅሞ አያውቅም። 70 ዓመት ሙሉ በጣሊያን የተገዛችው ኤርትራ ዛሬ ላይ ቅኝ ግዛት አድርጋን እያሉ የሚያላዝኑት ኢትዮጵያን ነው። ታሪክን ወደ ኋላ ተመልሶ ለተመለከተ ግን ነገሪየው ሌላ ነው። ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ በጣሊያኖች/በእንግሊዞች/በሃበሾች የተጻፉ መጽሃፍትን ለቅሞ ማንበብ አሁን ወያኔና ሻቢያ ሌሎችም ከሚዘረግፉት የውሸት ፕሮፓጋንዳ ራስን ለማጽዳት ይጠቅማል። የዓይን ምስክሮች በጊዜው ኑረው የጻፉት አያሌ መጽሃፍቶች አሉና! ታዲያ ከላይ መሳይ መኮነን የሚነግረን ወሬ መመዘን ያለበት እርስ በእርሱ አንድ መሆን ያቃተው ፋኖ እንዴት ባለ ሂሳብ ነው በሃሳብ እጅግ ከራቀው የኦሮሞ ታጣቂ ጋር አንድ ሆኖ መስራት የሚቻለው? የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር ይባላል። ግን ነገር ለማጦዝ ወሬ ለማስፋፋት ይጠቅማል። እንዲያው ይሁን ቢባልና ሁለቱ ሃይሎች አብረው መስራት ቢጀምሩም ነገሩ አይዘልቅም። ይህ ደግሞ የሃበሻ ፓለቲከኞች ዋና መለያ ነው። ተስማማን ባሉን ማግስት አንድ አፈንግጦ ሌላውን ያስበላል ወይም ራሱ ይበላል። ያለፍንበት መንገድ የሚያሳየው ይህኑ ታሪክ ነው። ለዚህ ነው ከመታኮስና/ሃገርን ወደ ድንጋይ ዘመን ከመለወጥ በሃሳብ ልዪነት ተስማምቶ አብሮ በሰላም መኖር ቀዳሚ አማራጭ የሚሆነው። ጊዜው ተለውጧል። በድር በገደል ገብቶ በመሸጎጥ የሚፈጸም ፍልሚያ የህዝብን ሰቆቃ ከማባዛት ያለፈ ሌላ ለውጥ አያመጣም። ወያኔን ለማውረድ ስንቱ ታገለ? ግን ወያኔ ከስልጣን የወረደው በሰላም እንጂ በጦር መሳሪያ አይደለም። ብልጽግናም የሚወርደው በምርጫ እንጂ በጦር መሳሪያ አይሆንም። ይህ ጦርነትን እንደ ቋሚ አማራጭ የመውሰድ የፓለቲካ አቋም ሊፈተሽና ሊቀየር ይገባል። በዚህ በፋኖና በሌሎች ታጣቂዎች ሰበብ ያለ ትምህርትና የጤና ተቋማት በር ተዘግቶባቸው ያሉትን ወገኖቻችን እናስብ። የግብጽም ድጋፍ፤ የሻቢያም አይዞአችሁ ባይነት፤ የወያኔም ሴራ ለህዝባችን አይጠቅምም። በኢትዮጵያ ውስጥና ውጭ ያላችሁ ሁሉ በግልጽ ተነጋግራችሁ ሰላም አስፍኑ.. የትጥቅ ትግል ዘመን የሻረው፤ መጨረሻ የሌለው አረንቋ ነውና ለሰላም ስሩ! Reply