ይኄይስ አእምሮ
ጥቂት ከማይባሉ አሠርት ዓመታት በፊት ጀምሮ ስለምንገኝበት ዘመን ብዙ ሲባል እንሰማ ነበር፡፡ ከሰማነው ሁሉ የቀረው አንድ ነገር ብቻ ነው ቢባል እምብዛም አልተጋነነም፡፡ እሱን ወደመጨረሻየ አካባቢ አስቀምጣለሁ፡፡ ወደተነሳሁበት ልግባ፡፡
- አቢይ አህመድ – ይህን ሰው ለመግለጽ ከማውቃቸው ጥቂት ቋንቋዎች ውስጥ ብፈልግ ባስፈልግ አንድም ቃል ላገኝ አልቻልኩም፡፡ ይህን መሰል ጉግማንጉግ ፍጡር በዓለማችን ተፈጥሮም ስለማያውቅ አሁን ያሉት ከ7 ሽህ በላይ የሚገመቱ የዓለማችን ቋንቋዎች ይህንን “ሰው” – በሰው አምሳል የተፈጠረ ሸለምጥማጥም ቢሆን ያው ሰው መባሉ አልቀረምና ነው – ለመግለጽ ቃል የሚኖራቸው አይመስለኝም፡፡
እዚህ ላይ ነው የቋንቋዎች ደካማ ጎን የሚታወሰን፡፡ አንድ ቋንቋ – ማንኛውም ቋንቋ – ወደ አራት የሚደርሱ ደካማ ጎኖች እንዳሉት የሥነ ልሣን ድርሣናት ይጠቁማሉ፤ ከነዚህ ውስጥ አቢይ አህመድን በቃላት ለመግለጽ አለመቻሌን የሚያካትት አላገኘሁም፡፡ ስለዚህ እንደአምስተኛ አድርጌ በገዛ ሥልጣኔ አራቱ ላይ ጨምሬዋለሁ፡፡ ከአሁን በኋላ ቋንቋዎች አምስት ደካማ ጎኖች አሏቸው ብለን እንመን – ለኔ ሲባል፡፡ አንደኛውንና እኔ የጨመርኩትን ሁለቱን በአጭሩ ቀጥለን እንመልከት፡፡
አንደኛው የቋንቋ አቅመቢስነት (ችግር) ከፍተኛ ስሜትን መግለጽ አለመቻል ነው፡፡ ቋንቋን የምንጠቀመው እያሰብንና ማሰብ ስንችልም ነው፡፡ ከፍተኛ የሀዘን ወይም የደስታ ሲቃ ውስጥ ስንገባ ግን የቋንቋ ቅሽምና ይከሰትና እንደቀሪ እንስሳት ስሜታችንን በጩኸት እንገልጻለን፡፡ ለምሣሌ ከልጃችን ጋር ባቡር መንገድ እያቋጥን ሣለ አያድርግበትና ልጃችንን መኪና ቢገጨው ያኔ “ውይ ልጄን መኪና ገጭቶ ገደለው፤ አይቶ አይነዳም? ከውካዋ!” አንልም – ላንቃችን እስኪበጠስ እንጮሃለን እንጂ ቋንቋ የለም፤ ዕንባም ራሱ የሚመጣው ዘግይቶ ወደሰውነት ደረጃ ስንወርድ ነው፡፡ ከአእምሮ በላይ የሆነ መከራ ወይ ደስታ ሲመጣ ቋንቋ ይቅርና እኛ ራሣችንም ልንጠፋ እንችላለን – ልንሞት ማለቴ ነው፡፡ ልጁን ድንገት በሞት የሚያጣ ወይም “የአንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ ደርሶሃል” የሚባል የኔቢጤ ድሃ ወዲያው ቢሞቱ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ቋንቋ አገልግሎት ላይ የሚውለው መታሰብ የሚችልን ነገር ለመግለጽ እንጂ ከፍተኛ ስሜትን ለማውጣት አይደለም፡፡
ሌላኛው እኔ ያመጣሁት አቢይን በቋንቋ መግለጽ ያለመቻል ችግር ነው፡፡ እንደዚህ ያለ ክፉ “ሰው”፣ እንደዚህ ያለ ጭራቅ፣ እንደዚህ ያለ ዐረመኔ፣ እንደዚህ ያለ ሀሰተኛና አስመሳይ ዓለማችን አፍርታ ስለማታውቅ ይህን የብዙ ክፋቶች ምንጭ የሆነ “ሰው” ለመግለጽ አዲስ ቃል መፈጠር ይኖርበታል፡፡ አሁን ያሉን አይችሉም፡፡ “የናቁት ወንድ ያስረግዛል” እንዲሉ ‹አልተማረም አልሰለጠነም› እያልን ስንንቀውና ስናናንቀው እሱ ግን የተፈጠረበትን የማጥፋትና የማውደም አሉታዊ ተፈጥሮ አንድም ሳይዘነጋ ድራሻችንን እያጠፋ ነው – “የናቁት ያደርጋል ራቁት” ማለት አሁን ነው ታዲያ፡፡ አጋንንታዊ የጥፋት ተልእኮውን በተሟላ ሁኔታ እየተወጣ ነው፡፡ የጨለማው ንጉሥ ሣጥናኤልና ምድራዊ ምዕራባውያን ወኪሎቹ በአቢይ እንደተካሱ በማንም አልተካሱም፡፡ ሌላው ሁሉ ቀርቶ ሃምሣና ስድሣ ሚሊዮን አማራ በአንድ እዚህ ግባ በማይባል ወፈፌ ጎልማሣ እርስ በርሱ ሲባላና የዕልቂት ዐዋጁን መቀልበስ ሲያቅተው ስናይ የልጁ “ጉብዝና” ቁልጭ ብሎ ይታየናል፡፡ አቢይን በገዳይነትና በበቀለኝነት የሚስተካከል የለም፡፡ ለዚህም ነው እሱን ለመግለጽ ቃል የሌለኝና የማይኖረኝም፡፡
አዎ፣ ሙሶሊኒ ጨካኝ ነበር፡፡ ሂትለርም እጅግ ጨካኝ ነበር፡፡ መለስ ዜናዊ ሀገርን የካደ የፀረ-አማራነትና የፀረ-ኦርቶዶክስነት በጥቅሉ የፀረ-ኢትዮጵያነት ርዕዮተ ዓለም አቀንቃኝ መሠሪ ነበር፡፡ መንግሥቱ ሀገር ወዳድ ገዳይና ጨቋኝ ነበር – ግን ጥቅምና ጉዳቱ የሁላችንምና ለሁላችንም ነበር፡፡ ዚያድባሬና አፄ ቦካሣ ጨቋኞች ነበሩ፡፡ እነዚህና ሌሎች የምድራችን አምባገነኖች ሁሉ በተወሰነ ደረጃ ከመለስ ዜናዊ በስተቀር ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን በእኩል ለማለት ቢከብደን በተቀራራቢ ደረጃ ያስደሰቱ ወይም ያሳዘኑ አምባገነኖች ነበሩ፡፡ ስለሆነም እነሱን ለመግለጽ ቃል ተቸግረን አናውቅም፡፡
ወደአቢይ ስንመለስ ግን ለዬቅል ነው፡፡ አማራ ጋ ሄዶ “ኦሮሞ ጠላትህ ነውና አትማረው” የሚል፤ ኦሮሞ ጋ ሄዶ “አማራና ትግሬ እስካሉ ድረስ አያልፍልንምና ቆራርጠን እንጣላቸው” የሚል፣ ሶማሌ ክልል ሄዶ “አፋርን በሉት” የሚል፣ ቤንሻንጉል ሄዶ “ምን ትጠብቃላችሁ፤ አሁን እኔ በሥልጣን ሳለሁ ሠፋሪ አማራን ቆራርጣችሁ ጣሉ እንጂ!” የሚል፣ “የአማራና ትግራይ ክልሎች ከነሕዝባቸው ወድመው ካላየሁ እንቅልፍ አይዘኝም” የሚል፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች ልማት ማካሄድ ይቅርና አንድም የፍጆታ ዕቃና የህክምና ቁሣቁስ እንዳይሄድ፣ የነበሩትም እንዲደመሰሱ ጥብቅ ትዕዛዝ በማስተላለፍ ታኅታይ መዋቅሮች ሁሉ በድሮን እንዲወድሙ በማድረግ ላይ የሚገኝ፣ በባልና ሚስት መካከል ጭምር እየገባ ግለሰቦችን በማጣላት የሚጠመድ የአእምሮ ድውይ፣ ጥላውን ሳይቀር የሚጠራጠርና ሁሉንም ባለሥልጣናቱን በደኅንነት ክትትል ውስጥ አስገብቶ እያስጨነቀ የሚገኝ ቶማሳዊ ፍጡር፣ አፉን በከፈተ ቁጥር በሚወጣ የሀሰተኛ ንግግሩ የሰሚን ጆሮ የሚያደነቁርን ልዕለ-ዲያቢሎስ ፍጡር ለመግለጽ ቃል ቢጠፋ አይገርምም፤ ሁሌም እንደምለው ሣጥናኤል የሚቀናበት ብቸኛ ሰብኣዊ ፍጡር አቢይ ነው፡፡ አቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ካልጠፋች፣ አማራ ካላለቀ፣ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ካልወደመ እንቅልፍ በዐይኖቹ አይዞርም፡፡ ይህ ፍጡር አራት ኪሎን እስካለቀቀ ድረስ በየቀኑ እየሞትን እኛ ራሳችን እናልቃለን፡፡ እሱ እንደሆነ “ከአራት ኪሎ የሚወጣው ሬሣየ እንጂ በሕይወት እያለሁ እንዳታስቡት” ብሎ አስጠንቅቋል፡፡ ለዚህም ነው ሀብታችንንም እኛንም ቀድሞ የተቆጣጠረው፡፡
- ለኦሮሙማ የሚያሸረግደው ሆዳም አማራ፡፡ እነዚህን ጉዶች ለመግለጽም ቃል የለኝም፡፡ የጄኖሣይድ ዐዋጁ በሁሉም አማሮች ላይ ነው የታወጀው፡፡ ማንም አማራ አይቀርለትም፡፡ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ሁሉም ተራ በተራ ያልቃል፡፡ እነሽመልስ በዕቅዳቸው መሠረት እየሄዱ ነው፡፡ ለዚያም ነው በበደኖና በአሩሲ፣ በገለምሶና በሻሸመኔ፣ በወለጋና በባሌ የነበረውን አማራ ጨረስን ብለው ሲያምኑ በአማራው ክልል ሄደው አሁን እየፈነጩበት የሚገኙት፡፡ አይነጋ መስሏቸው ነው፤ ነገር ሲገለበጥ እነሱን አያድርገኝ፡፡ “ባንኩም ታንኩም በኛው ሥር ነው” ብለው ሆዳም አማራን ከከተማ እስከጫካ – ከብአዴን እስከፋኖ ውስጥ ድረስ አዝምተው አማራን በአማራ እያጨራረሱት ነው፡፡ ላይበሉት ገንዘብ፣ ነገ ለሚጸጸቱበት ክህደት ዛሬ አማሮች አማሮችን ሲያርዱና ሲያሳርዱ ማየት ትልቅ የታሪክ ምፀት ነው፡፡ የእነተመስገን ጥሩነህና አገኘሁ ተሻገር ወይም ዳንኤል ክብረትና ታዬ አፅቀ ሥላሤ ጉዳይ በሣጥናኤል ፍርድ ቤት የተያዘ በመሆኑ ለጊዜው በይደር ይቀመጥ፡፡ ነገር ግን በአድማ ብተናና በሚሊሽያ እንዲሁም በብልጽግና ካድሬ ስም ለሦስት ቀን በማትሆን የአንዲት ጉርሻ ምንዳ ተታለው ወገኖቻቸውን የሚጨርሱ አማሮች በቃላት ከመግለጽ በላይ ናቸው፡፡ ሆድ ልክ አለው፤ ሥጋዊ ፍላጎት ገደብ አለው፡፡ ዘርን እስከመሸጥ ካደረ ግን ከይሁዲነትም የዘለለ የእርኩስ መንፈስ ሎሌነት ነው፡፡ ነገ ራሱንም ለሚያጠፋው ዐረመኔ የኦሮሙማ ቡድን አድሮ ዛሬ የገዛ ወገኑን ቢፈጅና ቢያስፈጅ የውሻን ደም ሳይበቀል የማይተወው ቸሩ አምላክ ፊቱን ሲያዞር ይህ ባንዳ ዘሩ እንደማይተርፍ ግልጽ ነው፡፡ ለማንኛውም እነዚህን አጋሰሶች በጥቁር መዝገብ እየመዘገባችሁ አስቀምጡ፤ ቀኑ ቀርቧልና፡፡
- የኢትዮጵያ ሕዝብ፡፡ ምን እንደነካን ወይም ምን እንዳዞሩብን አላውቅም፡፡ የሰይጣን አምላኪዎቹ ቡድን በልጃቸው አቢይ በኩል አንድ ነገር እንዳደረጉብን መጠርጠር ከጀመርኩ ቆየሁ፡፡ የኛን የመሰለ መንግሥት በየትኛውም የዓለም ሀገር ቢኖር ወንበሩን ከተቀማ በትንሹ ሃምሣ ዓመታት ባለፉ፡፡ እኛ ግን የመጣውን ሁሉ ለመሸከም ትከሻችን ደንድኗል፡፡ ጦርነቱና ግድያው እንዳለ ሆኖ ኑሮው በየቀኑ ሽቅብ እየተወነጨፈ እኛ ግን የተመቸን መስለን አለን፡፡ የአምስት ሽህ ብር ደሞዝተኛ ሥራው ሜክሲኮ አካባቢ ሆኖ በአምስት ሽህ ብር የተከራያት ጠባብ ክፍል ኮተቤ ገብሬል አካባቢ ሆና ለትራንስፖርት የሚያወጣው በወር በአማካይ ሁለት ሽህ ብር ገደማ ሆኖ እየሣቀ ሲሄድ ማየት ብርቅ አይደለም – ይህ ዕንቆቅልሽ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ይገርማል፡፡ ብዙ ዶክተርና ፕሮፌሰር በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ እያበደ ወደሜቄዶንያና ወደሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እየገባ ነው – ሊያውም ዕድሉን ያገኘ፡፡ ብዙ ሰው ራሱን እያጠፋ ነው፡፡ ብዙ ሰው እየቀወሰ አዳሩ ድልድይ ሥርና በረንዳ ላይ ነው፡፡ አዲስ አበባ ግን በማስመሰያ ትያትር በመብራት አሸብርቃ በተለይ ለውጭ ታዛቢ በሕይወት ያለች ትመስላለች፡፡ በዚያ ላይ ቀማኛውና ሙሰኛው እንዲሁም አጭበርባሪውና አምታቹ የሚገዛው ዘመናዊ መኪና ሲርመሰመስ ማየት ሁለት ተቃራኒ ኢትዮጵያዎች ብዙዎቻችን ቀደም ካለ ጊዜ ጀምሮ በምናውቃት በአንዲቷ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ ያህል እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ እንጂ በእውነት ከሆነ ሞታለች፡፡ የግሪጎሪ መንደር በመባል የሚታወቀውን የአንድ ራሽያዊ አጭበርባሪ የተንኮል ሥራ የኮረጀው የሚመስለው አቢይ አዲስ አበባን የውጪውን ዓለም ለማታለያነት እየተጠቀመባት ነው፡፡ በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ግሪጎሪ ፖተምን የተባለ የታላቋ ንግሥት ካተሪን የአንድ ግዛት አስተዳዳሪ “ግሪጎሪ መንደር” (Grigory Village) ብሎ አንድ ሠፈር በመከለል አስጊጦና አስውቦ ለጎብኚዎች ያሣይ ነበር አሉ፡፡ ሌላው መንደር በድህነት ሲነፍር ያቺን ልዩ መንደር ግን አቆነጃጅቶና የሚበላና የሚጠጣም አቅርቦ ሰዎች ሲጎበኙ እነሱም እንዲደነቁና እሱም እንዲወደስ ያደርግ ነበር፡፡ ሌላው የግዛቱ ክፍል ግን ርሀብና ቸነፈር፣ ጉስቁልናና ድህነት የነገሠበት ነበር፡፡ ይህ የኛው ጉድም እኛን በመከራ ዶፍ እየመታ ዓለምን ያጭበረብራል፡፡ አስመሳዩ ዓለምም ሰውዬውን እያወቀው በኛ መከራና ስቃይ መዝናናቱን ቀጥሏል፡፡ ነግ በኔንም ረስቷል፡፡ እኛም ምቹ ሆነንለታል፡፡ እየሞትን የዚህን ዕብድ ቅዠትና ህልም እናሳካለን፡፡ በዚህ ሁኔታችን እሱን ከመታገል ይልቅ ሞትን መምረጣችን ለምን እንደሆነ ይደንቃል፡፡
በመጨረሻም፡-
“በዚያን ዘመን እንዲህ ይሆናል፡፡ ከሕዝቡ በኃጢኣት መርከስና በክፋት መሞላት የተነሣ አንድ እስላም ንጉሥ ለቅጣት ይነሳል፡፡ ያኔ መከራና ዋይታ ይበዛል፡፡ ርሀብና ጦርነት ይነግሣል፡፡ ሕዝቡ በኃጢኣቱ ተፀፅቶ ወደ ፈጣሪው ከተመለሰና ካለቀሰ ያ መጥፎ ንጉሥ ከሦስት ዓመታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ከንግሥናው ይወርዳል፡፡ ሕዝቡ ካልተመለሰ ግን ሰባት ዓመትና ከዚያም በላይ ይቆያል፡፡ መከራና ሰቆቃው ግን ተነግሮ አያልቅም፡፡ እህል በሸሃኔ ይሠፈራል፡፡ ርሀብና ጦርነት የሚፈጀው ሕዝብ ሥፍር ቁጥር የለውም፡፡ ለትንሣኤው ብርሃናማ ዘመን የሚተርፈው ጥቂት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ግን የአንዲት ላም ወተትና የአንድ ማሣ እህል ላገሩ ይበቃል፤ የሚጨርሰውም የለም፡፡”