አብይ አህመድ ከየብሔሩ የተመረጡ እንደ አበደ ውሻ የሚያጠቁ ታማኝ አገልጋይ ሰዎችን መልምሏል። ስም የሚያጠፉ፣ ጣፉርዲ ተሳዳቢዎችን በጋዜጠኝነት፣ በአማካሪነትና በወዳጅነት መልምሎና አሰልጥኖ፤ ጠላቾች የሚላቸውን የሚረግሙ፣ አሉቧልታ የሚተርኩ ተሳዳቢዎችን አዘጋጅቷል። እነዚህ ምልምሎች ከመንግስታዊ መዋቅር ውጭ በውጭ አገርና በአገር ውስጥ እንዲሰሩ ከፍተኛ በጀት መድቦላቸዋል።
ለምሳሌ ያህል የስዩም ተሾመን ተልዕኮና ሚና መጥቀስ ይቻላል። ስዩም ተሾመ ጋዜጠኛ ወይም አክቲቪስት ሳይሆን፤ ከዳንኤል ክብረትን የሚወዳደር የአብይ አህመድ ድብቅ ተዋጊ ሀይል ነው። በውስኪ፣ በጫትና በአደንዛዥ እፅ እየተጀነጀነ፤ በሚያቀርበው ዝግጅት ላይ ህልውናውን እኪያጣ ድረስ እያጓራ መላው ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ በሰዎች ላይ እየተሳለቀ ይሳደባል።
ስዩም ተሾመ እንደ ዳንኤል ክብረት የቤተመንግስት ባለሟል ባይሆንም፤ በማነኛውም ጊዜ አብይ አህመድን የማግኘት መብት አለው። ከጀነራሎችና ከሚኒስትሮች የበለጠ 4ኪሎ ያለጥያቄ የመግባትና የመውጣት ሙሉ መብትና ልዩ ፍቃድ ተሰጥቶታል።
ስዩም ተሾመ፤ የሚያርምና የሚገስፅ ከልካይ የሌለው ባለጌ ልጅ ሆኖ ያደገ በሚመስል መንገድ፤ በአስቀያሚ የብልግና ቃላት የአብይ አህመድ ጠላቶች የሚባሉትን መሳደብ ሙያው አድርጎታል። የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የትግሬ፣ ወዘተ.. የአብይ አህመድ ጠላቶች የሚባሉትን ሳይሳቀቅ ሲዘልፍ ሲሳደብና ሲያበሻቅጥ የሚውለው ከጌታው በሚያገኘው ከለላ በመተማመን ነው።
በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ምን አይነት ፕሮግራም መስራት እንዳለበት ከአብይ አህመድ ጋር በቀጥታ ይወያያል። የግለሰቦችን ስም እየጠቀሰ ማንቋሽና መሳደብ የሚያስፈልግበት ጊዜና ሁኔታ ሲፈጠር፤ ከጠ/ሚኒስትሩ በቀጥታ ምን ማለት እንዳለበት ቃል በቃል ተነግሮት ፕሮግራሞችን አዘጋጅቶ እንዲያቀርብ ይታዘዛል።
አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ ሲደርስም ይነገረውና፤ ተቃዋሚዎችን፣ ታዋቂና ተደማጭ ጋዜጠኞችን፣ የህብረተሰብ አንቂዎችን፣ ሚኒስትሮችን፣ ጀነራሎችን፣ የደህንነት ሹሞችንና፣ የክልል ፕሬዜደንቶችን ፣ ዳኞችን ወዘተ… የመተቸትና የመስደብ ትዕዛዝ ከሙሉ መብት ጋር ይሰጠዋል።
የሚሰደቡት የአብይ አህመድ ሹማምንቶች የስዩም ተሾመን ስድብ ሲሰሙ ተቃውሞ አያሰሙም። ትዕዛዙ የሚመጣውም በቀጥታ ከአብይ አህመድ መሆኑ ሁሉም ስለሚታወቁ፤ የተተቹት ወይም የተሰደቡት ባለስልጣናት ስዩም ተሾመን ደውለው ምን መስራትና ማስተካከል እንዳለባቸው ምክር ከመጠየቅ ሌላ በሱ ላይ ምንም አይነት የበቀል እርምጃ ለመውሰድ አይቃጡም።
ስዩም ተሾመ እንዳበደ ውሻ ለሀጩን እያዝረከረከ፤ በውጭ የሚኖሩ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ላይም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሳደብ ከጌታው አብይ አህመድ ልዩ እቅድና ትዕዛዝ ተሰጥቶት ከሚሰሩ ሰዎች አንዱ ነው።
የአብይ አህመድ አስተዳደር ህገመንግስትንና ህግን የሚከተል ሳይሆን የማፍያ ቅርፅ ያለው አደረጃጀት በመንግስት ውስጥና ከመንግስት ውጭ አቋቁሟል። የተለያዩ የአፈናና የግድያ እስኳዶች እንዳሉት ሁሉ የሚዲያ ተሳዳቢና ስም የሚያጠፉ ቡችሎች አሉት። እነዚህን በመጠቀም በማስፈራራት፣ በማሰርና በመግደል የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም የሚረዳ አሰራር የዘረጋ ስርዓት ከልሆነ ቆይቷል።
አብይ አህመድ ማፍያ አገዛዙን ለማራዘም የሚረዱ አሉቧልታ የሚያሰራጩ ተሳዳቢዎችን አዘጋጅቶ በጀት ሰጥቶ አሰማርቶ ሽንጣቸው ገትረው በታማኝነት ያገለግሉታል።
ነማ ነቀምቶ