
የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ምክትል የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊና የአጼ ዳዊት ክፍለ ጦር የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ፣ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡ ፋኖ አበባው ሰለሞን፡፡ ህይወቱ ያለፈው በጥይት ተመቶ ነው፡፡ ማንኛውም ፋኖ ሕይወቱ ሲያልፍ ልቤ ያዝናል፡፡ ይህ ወንድምም ነፍሱን ይማር፣ ለወዳጅ ዘመድ ቤተሰብም መጽናናት ይሁን እላለሁ፡፡
ፋኖ አበባው የሞተው ከአገዛዙ ጦር ጋር ሲዋጋ አይደለም፡፡ በፋኖዎች መካከክል ፣ ከእስክንድር ነጋ አፋህድ ጋር በተገናኘ በተፈጠረው ክፍፍል የተነሳ ነው፡፡ በርስ በርስ ግጭቶች በሸዋ ውስጥ በመቶዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ግጭቶቹ ደግሞ በሸዋ ጠቅላይ ግዛትና በአፋብሃ ፋኖዎች መካከል ብቻ ሳይሆን፣ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ውስጥ ግጭቶች ተከስተዋል፡፡
የቅርብ ጊዜውን ብንጠቅስ እንኳን፣ ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት የአስቻለው ደሴ ክፍለ ጦር የአፋብሃ የነግድጓድ ክፍለ ጦርን ባጠቃበት ወቅት፣ የክፍለ ጦሩ የዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ፋኖ ናትናኤል ጨምሮ ብዙዎች ሞተዋል፡፡ የራምቦ ክፍለ ጦር በመርሃቤቴ አውራጃ በሬማ ከአጼ ዳዊት ክፍለ ጦር ቀስተ ንዕብ ብርጌድ ጋር ፣ በዚያው በሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ውስጥ፣ ባደረጉት ውጊያ፣ ብዙ ፋኖዎች ሞተዋል፡፡ የብርጌዱ አዛዥ ፋኖ ግርማን ክፉኛ ቆስሎ አስረውት የነበረ ቢሆንም፣ በኋላ ህይወቱ አልፏል፡፡ ከቁስሉ የተነሳ ይሁን ይረሸን የሚታወቅ ነገር የለም፡፡
ሸዋ ያለው ነገር በጣም ያሳዝናል የምንል የነበረው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ በሸዋ ለተፈጠረው ክፍፍልና መናቆር መሃከል ላይ ያለው ደግሞ እስክንድር ነጋና በውጭ ያሉ የርሱ ጋንግሰተሮች ናቸው፡፡ ፋኖ አበባው ሰለሞን የዚህ የነ እስክንድር መርዝና ሴራ ሰለባ መሆኑ ያሳዝናል፡፡ ይህ ወንድም ለዚህ አልነበረም ወደ ዱር ገደል የወረደው፡፡
በዚህ ዙሪያ ላይ ሁለት መግለጫዎች ወጥተዋል፡፡ አንዱ ከሸዋ ጠቅላይ ግዛ እዝ፣ ሌላው ደግሞ ከአፋህድ፡፡ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ መሪዎች ለፋኖ አበባ ሰለሞን ትልቅ የቀብር ስነስርዓት እንዳደረጉለት፣ የሚያሳይ ምስል አይተናል፡፡ ጥሩ ነው፡፡
ሆኖም ግን ተመሳሳይ መግለጫዎች ከነጎድጓድ ክፍለ ጦር ሲዋጋ ለሞተው ለአስቻለው ደሴ ክፍለ ጦር የዘመቻ መምሪያ ሃላፊ አልወጣለትም፡፡ ለምን ? እሺ ግጭት መፈጠሩ እንዲወጣ ካልፈለጉ ደግሞ ከአገዛዙ ጋር ሲዋጋ በኤፍራታና ግድም ሕይወቱ ላለፈው ጀኛው ተስፋዬ ቦጌ፣ የሰባት ለሰባ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ለምን መግለጫ አላወጣለትም ? እንግዲህ አስቡት ለአንድ ክፍለ ጦር የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ መግለጫ ሲወጣ፣ ለሌላ ክፍለ ጦር ዋና አዝዥ መግለጫ አለመውጣቱ በራሱ አጠያያቂ ነው፡፡
በፋኖ አበባው ጉዳይ ላይ፣ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ፣ “ከተለያየ አቅጣጫ የሚቀርብልንን የአንድነት ጥያቄ ማዕበል ለማስተናገድ ዝቅ ብለን አንድነት እንዲመጣ እየሰራን በምንገኝበት ጊዜና አርበኛ አበባውም ለዚሁ ተልዕኮ በተሰማራበት በስምሪት ቀጠናው ከነበሩ ወዳጅ ዘመዶቹ ጋር አሳልፎ ወደ ዋርድያው ሲመለስ የጠላትን አጀንዳ በማስፈፀም ሸዋን የቀውስ ማዕከል እንዲሆን በሚሰሩ በፋኖነት ካባ ተደብቀው ምለው በሚገዘቱ ፀረ- ህዝብ ሀይሎች ተልዕኮ በተሰጣቸው ሰርጎ ገብ ከሐዲዎች ከኋላ በተተኮሰ ጥይት ሰኔ 24/2017 ዓ.ም በተወለደ በ38 አመቱ በክብር ተሰውቷል:” ይለናል፡፡በፋኖነት ካባ የተደበቁ ከጀርባው ተኩሰው ገደሉት ነው የሚሉን፡፡
አፋህድ መግለጫዎች በማሻሻል፣ “አርበኛ አበባው ሰለሞን የፋኖ የአንድነትን እውን ለማድረግ ድርጅታዊ ተልዕኮ ተቀብሎ በፍፁም ቅንነት እና እምነት እየተንቀሳቀሰ ባለበት ግዜ፣ የፋኖ አንድነት እውን እንዳይሆን ከውስጥም ከውጭም ሴራ እና ተንኮል ሲጎነጉኑ የሚውሉ አካላት ባሰማሯቸው ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ተመትቶ ህይወቱ አልፏል” ሲል፣ በፋኖነት ካባ የሚለው ቃል አውጥቶታል፡፡
በደቡብ ጎንደር አርበኛው ከፍያለው ደሴ ሲሞት፣ በነ ሻለቃ ሃብቴ በጉና ክፍለ ጦር፣ እስቴ ዶንሳ ብርጌድ ፋኖዎች ፣ ከጀርባ ተገደለ በሚል ነበር የእስክንድር ነጋ ጉጅሌዎች፣ ኢትዮ360ዎችና ሌሎች፣ የበለጠ ደም መፋሰስ እንዲኖር ፣ በ እሳት ላይ ነዳጅ ሲያርከፈክፉ የነበሩት፡፡ እውነታው ግን ያ አልነበረም፡፡ እውነታውን ያወቁት እነ ፋኖ ደረጄ በላይ እሳቱን አጥፍተው፣ እልቂት በጎንደር እንዲቀሰቀስ የሚፈልጉት ኩም ነው ያደረጉት፡፡
አሁንም የአበባው ሰለሞን ህልፈት ጋር በተገናኘ በፋኖዎች መካከል የበለጠ ደም መፋሰስ እንዲኖር፣ ምንም አይነት ማስረጃ ሳይሆን፣ እሳት ላይ ነዳጅ ለማርከፍከ የሚተጉትን በጋራ መታገል ያስፈልጋል፡፡
ፋኖ አበባው ሰለሞን የተገደለው በመዘዞ ነው፡፡ በዚያ በስፋት የሚንቀሳቀሰው የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ነው፡፡ መዘዞ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ዋና መቀመጫ ቦታ ነው፡፡ አፋብሃ በዚያ የለም፡፡ አፋብሃ የሚንቀሳቀባቸው አካባቢዎች ይታወቃሉ፡፡
ፋኖ አበባው የተገደለው በዚያው በሸዋ ተቅላይ ግዛት እዝ ውስጥ ከተፈጠሩት አለመግባባቶች የተነሳ ነው”” ውጭ ያሉት የ እስክንድር ሰዎች፣ አፋህድን አንደገፍም ብለው በይፋ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ከሸዋ ጠቅላይ ግዛትውስጥም እየደወሎ፣ ከሸዋ ጠቅላይ ግዛት እሽ ኃይል ገንጥለው፣ የአማራ ሕዝባዊ ሰራዊት የሚሉትን ለማቋቋም እየሰሩ ነው፡፡ከዚህ ጋር በተገናኘ በተፈጠረ ግጭት ይሆንል ይህ ወንድም ህይወይቲ ያለፈው፡፡
ከላይ እንደገለጽኩት ግን በዚህ ወንድም ህልፈት ላይ አፋብሃ የለበትም፡፡ ይህንን እንደ ሰበብ በመውሰድ ፣ በአፋብሃ ላይ የሰፈነውን የተኩስ አቁም በመተላለፍ፣ ወደ ግጭት ከተገባ፣ ሰዎቹ እጅግ በጣም ትልቅ ስህትተ ነው የሚሰሩት፡፡
በኔ እምነት አሁን በአስተማማኝ ሁኔታ የሸዋ ፋኖዎች አንድነት ካልመጣ፣ እንደ እስክንድር ነጋ ያሉና ውጭ ያሉት የርሱ ሰዎች የሚዘረጉትን እጆች መቁረጥ ካልተቻለ፣አንድ አይደለም፣ አስር አይደለም፣ መቶ አይደለም ሺሆች ያልቃሉ፡፡
መፍትሄ አንድነት ብቻ ነው !!!!