December 26, 2024
5 mins read

መንግስት ኢሰመጉ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን አገደ፤ የታገዱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቁጥር አራት ደረሷል

GfrmfkvXMAASJ6Lየሲቪል ማህበረስብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልን (EHRDC) “ገለልተኛ ባለመሆን ከተቋቋሙበት ዓላማ ውጭ ተንቀሳቅሰዋል” በሚል ምክንያት ማገዱ ገለጸ።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC) ከባለሥልጣኑ ታኅሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በተላከለት ደብዳቤ መታገዱን ዛሬ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ አረጋግጧል።

ማዕከሉ ለመታገድ የተሰጠው ምክንያት ” ባለስልጣኑ ድርጅቱ ከተቋቋመበት አላማ ውጭ መንቀሳቀስ፣ ገለልተኛ አለመሆንና ግልጽ የሆነ የአደረጃጀት መዋቅር የሌለው መሆኑን በተደረገ ክትትል እና ግምገማ ተረጋግጧል” የሚል መሆኑን አስታውቋል።

ድርጅቱ በባለስልጣኑ አደረኩት ባለው ምርመራ ስለመከናወኑ እንደማያውቅ እና በእግድ ደብዳቤው የተጠቀሱት ውንጀላዎች ማዕከሉን የማይመለከቱ እንደሆኑ በመግለጫ ገልጿል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በዛሬው ዕለት ባወጣው አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫም ስራዎቹን “በፍጹም ገለልተኝነት”፣ “ኃላፊነት በተሞላበት ጥንቃቄ” እና “የድርጅቱን መርሆዎች በተከተለ መልኩ ብቻ ሲያከናወን” መቆየቱን ገልጿል።

በተጨማሪም ድርጅቱ ግልፅ የአደረጃጀት መዋቅር ኖሮት ለአመታት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ያለ መሆኑ እየታወቀ ከባለሥልጣኑ “ግልጽ የሆነ የአደረጃጀት መዋቅር የሌለው” በሚል የተሰጠው አስተያየት “ግልጽ ባለመሆኑ ለባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ባቀረብነው የማብራሪያ መጠየቂያ ደብዳቤ ላይ መግለጻችንን ለማሳወቅ እንወዳለን” ብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን መታገዱንም የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ኢሰመጉን “ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል” በሚል ባለሥልጣኑ መታገዱን ገለጿል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጀቱ በተደጋጋሚ ከመንግስት አካላት በሚደርስበት ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች ምክንያት ስራውን በአግባቡ ለመስራት መቸገሩን ማስታወቁ ይታወሳል።

የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚፈጸሙበት የገለጸው ድርጅቱ ዋና ዳይሬክተሩ ዳን ይርጋ በዚኹ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳቢያ ከአገር ለመሰደድ እንደተገደዱ መግለጡ ይታወቃል።

በቅርቡ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከልን (ካርድ) እና የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች የተሰኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በድጋሚ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣኑ መታገዳቸው ይታወቃል።

በዚህም አጠቃልይ በመንግስት የታገዱ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አራት ደርሰዋል።

ካርድ በድጋሚ ለመታገድ ያደረሰው ምክንያት ቀደም ሲል ተጥሎ የነበረው እገዳ ሲነሳ “የተገለጸለትን የእርምት እርምጃዎች ባለመውሰድ“ እንዲሁም “ለተሰጠው ማስጠንቀቂያ ትኩረት መንፈግ/አለመስጠት” በሚል መሆኑን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

በተመሳሳይ መልኩ ባለስልጣኑ ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ (AHRE) ላይ ጥሎ የነበረውን አግድ ማንሳቱ ይታወሳል። አስ

 

ዘገባው የአዲስ ስታንዳርድ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop