የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓት ዳግም ህጋዊ እውቅና ሊያገኝ የሚችልበትን ማሻሻያ አዋጅ አጸደቀ

June 4, 2024
447779387 994627278949326 3603304511526386812 n
ማክሰኞ ግንቦት 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) በድጋሚ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ እንዲሆን የሚያስችለው አዋጅ ጸደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህወሓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚፈቅድ አዋጅ አፅድቆታል፡፡
በ2011 ዓ.ም. የወጣውን “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን” የሚያሻሽለው የህግ ረቂቅ የጸደቀው በሁለት የፓርላማ አባላት ተቃውሞ፣ በአንድ ድምጸ ተዐቅቦ፣ በአብላጫ ድምጽ ነው።
“በአመጽ እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበሩ” የፖለቲካ ፓርቲዎችን “በልዩ ሁኔታ” እንዲመዘገቡ የሚያስችለው የህግ ማሻሻያ፤ የፖለቲካ ቡድኖቹ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን እና የምርጫ ቦርድን ኃላፊነት የዘርዘረ ነው። ይህ የአዋጅ ማሻሻያ፤ “ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል” በሚል “ህጋዊ ሰውነቱ እንዲሰረዝ” የተደረገው ህወሓት በድጋሚ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ አንቀጾችን በውስጡ ይዟል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዓርብ ግንቦት 23 ቀን 2016 ባካሄደው ስብሰባ ‘የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ’ እንዲሻሻል ወስኖ ለፓርላማው ማስተላለፉን አዲስ ማለዳ ዘግባ ነበር።
በተጨማሪም የህ.ወ.ሓ.ት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሉ ጌታቸው ረዳ በዕለቱ “የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሰላምን ለማጠናከር ወደ ትክክለኛው አቅጣጫ አንድ እርምጃ የተራመደ ነው” ማለታቸው ይታወሳል።

አዲስ ማለዳ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

190806
Previous Story

አዛዡ ተሸኘ | የዘመነ ካሴ ጦር ሰብሮ ወደ ከተማ ገባ | ፋኖ ሀይሎችን የተቀላቀለው የቤተመንግስቱ ጠባቂ | የአብይ አህመድ ሴራ ተጋለጠ “ፋኖን እንመርዘው” | የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ሁሉም አ-ል-ቋ-ል

190869
Next Story

ለስልጠና የታፈሱ ከአስር ሺህ በላይ ወጣቶች ከብርሸለቆ ካምፕ ጥሰው ወጡ:: | አበባው ታደሰ እና አረጋ ከበደ በደብረብርሃን በፋኖ ተከበቡ | አርበኛ ዘመነ ካሴን ለመግደል የመጣው ደህንነት ተያዘ | ህወሃት ራያን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠረ

Go toTop