May 17, 2024
2 mins read

“አብይ አህመድ ባህር ዳር ሄደ” በሚል የአማራን ትግልና የፋኖን ተጋድሎ ለማጣጣል ብዙ ርቀት የተጓዙ ደነዞችን ከዚህም ከጠላት ካምፕም በስፋት እያየን ነው

Killer facist Aby Ahmedዴቭ ዳዊት

ሲጀመር፥ ከእስከዛሬው ድላችን መካከል ትልቁ የሚባለው፥ አብይ አህመድ የሚባል ፋሽስት አውሬን ዳግም ከልቡ ጓዳ ሊያኖር የማይችል አማራዊ ህዝብ መፍጠራችን ሲሆን፥ በከተሞች ሹልክ ብሎ ታይቶ መውጣትን እንደ ድል ለሚቆጥሩ የቀነጨረ አዕምሮ ላላቸው ሰዎች ማስታወስ የምንፈልገው ነገር ቢኖር ግን፥ ደርግ ምንም እንኳ በኤርትራ ውስጥ ከተሸነፈ የቆየ ቢሆንም፥ ሻዕቢያ አስመራን የተቆጣጠረው መንግስቱ ኃይለማርያም ሀገር ጥሎ በሸሸ በሶስተኛው ቀን መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል።

መንግስቱ ሀገር ሊለቅ ቀናት ሲቀሩትና ሀገር በለቀቀበት ጊዜ የወቅቱ የመከላከያ ሚንስትር ሀዲስ ተድላን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣናት አስመራ ደርሰው ይመለሱ የነበር ሲሆን የእነሱ በአስመራ መታየት፥ የሻዕቢያን ሽንፈት አልያም የደርግን ድል አመላካች አልነበረም።

እናም ዘገምተኞች ሆይ! እንኳን ሃያ ደቂቃ ለማይሞላ ጊዜ ባህር ዳር ታይቶ ለተመለሰው አብይ አህመድ ቀርቶ፥ ከዚህ በኋላ ማንም ምድራዊ ኃይል የአማራን ትግል ማስቆም፣ ፋኖንም መበተን አይችልም!!!

Legitimate Grievance እና Noble Cause የወለደውን የአማራ ህዝብ ትግል፥ በእንቶ ፈንቶ የማጣጣል ፕሮፓጋንዳ መድፈቅም መቀልበስም አይቻልም!!!

ድል ለአማራ ህዝብ !!!

1 Comment

  1. ፉከራው ያለፈውን ትዝ ያሰኘኛል። ” አንድ ሰውና አንድ ጥይት እስኪቀር” ይሉ ነበር የያኔው ጅሎች። ጉራ፤ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት የእውቀት ብልጭታ አይደለም። ረጋ ባለ ሂሳብ በፋኖና በብልጽግና መካከል ያለውን ግብግብ ለተረዳ ትርፍ የለሽ ነው። በውጊያው የሚጎዳው ነጻ እናወጣሃለን የሚባለው የአማራው ህዝብ ነው። ጠ/ሚሩ ሃያ ደቂቃ ባህርዳር ቆየ አልቆዬ ዋጋ ይብሉን። ግን ማብቂያ የሌለው በሚመስለው በዚህ ፍልሚያ ላይ የሚወድመው ሃብትና ንበረት፤ የተቋረጡት የህዝብ መገልገያ ተቋሞችና ት/ቤቶች፤ እንበለ ፍርድ በፋኖም ሆነ በብልጽግና ይህን ደግፋችኋል ያን ሰርታችሁሃል እየተባሉ የሚጨፈጨፉት ነጻ ይወጣሉ የሚባሉት ወገኖች ናቸው። ጦርነት እውነትን አያውቅም። ጦርነት ብቀላን ብቀላ እየተካው የመገዳደልና የስርዓት የለሽ ፊልሚያ ነው። ያለፈው በደም የተነከረ ታሪካችንም የሚያሳየው ይህን እውነት ነው።
    የዶ/ር አብይ መሞትም ሆነ ከስልጣን መውረድ የሃገሪቱን ችግር አይፈታም። በአንድ ግለ ሰብ ሞት ሃገር አይድንም። ይህን ስል መንግስት በጎ ነገር እያረገ ነው ማለቴ አይደለም። እልፎችን እንበለ ፍርድ በማጎሪያ የከተተውና በየጥሻው ሞተው የሚገኙት ሰዎች ቁጥር ለመንግስት የማፊያ አሰራር አመልካች ተግባር ነው። የእኔ ዋናው ሃሳብ ጦርነት ይቁም ነው። ፋኖም ሆነ ሌሎች ታጣቂ ሃይሎች በመደራደር ነገሮችን መስመር እንዲይዙ ያድርጉ ነው። ህዝብ ተጎዳ፤ ሰው ተራበ፤ ተሰደደ፤ ሃገር ተተራመሰ ይብቃ ነው የምለው። አውቃለሁ ጦርነቱ እንዲቀጥል የሚሹ ሃይሎች ደግሞ የራሳቸው እይታ ይኖራቸዋል። ጦርነት ለወያኔም አልሆነ እንኳን ለኦነግና ለፋኖ። አሁን ካለው የከፋ መከራ እንዳይመጣ በድርድር የታሰሩ ተፈተው የተጎድ ተክሰው ነገሮች መስተካከል ያለባቸውና ጦርነቱ መቆም ያለበት አሁን ነው። መገዳደላችን ያብቃ!
    የዛሬ 61 ዓመት ገደማ በጄ/ አብይ አበበ “አውቀን እንታረም” ከተባለው መጽሃፍ ዓለም በሚለው ግጥም ስር አንድ ስንኝ ልዋስና ነገሬን ላብቃ
    ዓለም ገና ልጅ ናት አውራጃዋም ደግሞ
    አርጅቶ እሚሞተው ሰው ብቻ ነው ቀድሞ
    ብዙ አሳልፋለች ብዙዎች ተክታ
    የሁሉንም ምግባር በየተራው አይታ።
    ለዚህ ነው ያኔ አንድ ሰውና አንድ ጥይት እስኪቀር እንፋለማለን ሲባል አንድ ሰው ብቻ ከቀረ ጥይቱ ለሰውዬው ሰውየው ለሃገሪቱ አስፈላጊ አይሆንም ይባል የነበረው። ግን ያ ሁሉ ቱልቱላ ጊዜ ሲንደው የሆነውን ቋሚ አይቷል። ልብ ይስጠን። የተራዘመ ጦርነት ህዝብና ሃገርን ይጎዳል። ይታሰብበት!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

2
Previous Story

መከላከያ በአስቸኳይ ይውጣ” ብአዴን ለ2 ተከፈለ | ባህርዳር አዋጊው ተገደለ ጎጃም ውጊያ |

zeme
Next Story

“መፍን-ቅ-ለ መንግስት ሊያደርጉብኝ ነው” | ሰራዊቱ ተበተነ – ሁሉም ፋኖን ተቀላቀሉ “ፊታችንን ወደ አብይ አዙረናል” | አዲስአበባ ከባድ ፍንዳታ ተፈጸመ | የከንቲባው ቤት ተመታ | የሸዋ ፋኖ ታላቅ ድል አበሰረ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop