April 12, 2013
3 mins read

ቄስ፣ ወታደርና ነጋዴ፤ መስቀል፣ ጠመንጃና ብር – ሶስቱ ምስጢራዊ የወረራና የብዝበዛ መሣሪያዎች

(The three secret weapons for colonialist invasion and Exploitation)

 
ከአገሬ አዲስ
በመካከለኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓውያን ትልልቅ የመርከብ ግንባታን እውቀት በተቀዳጁና ከከባቢያቸው እርቀው በመሄድ፣ውቅያኖስን ተሻግረው አንዳንድ ክፍለ ዓለማትንና አገሮችን በገለጡበት ጊዜ ከኑዋሪው ሕዝብ ጋር ለመቀራረብ አንዳንድ ገጸበረከቶችን በመስጠት ወዳጅ መስለው ይቀርቡ እንደነበር፣ከዚያም ከከባቢው ያገኟቸውን ግኝቶች ይዘው በመመለስ ለአገራቸው የምርትና ገበያ እንቅስቃሴ ምንጭ ማድረግ እንደቻሉ ታሪክ ይነግረናል።የመጀመሪያውን እግራቸውን ተከትሎ የተደረገው ጉዞ ወደ አገር መያዙና መስፈሩ ከመሸጋገሩ በፊት የሃይማኖት መነኮሳት በቅድሚያ ተልከው በመቀላቀል ኑዋሪ ሕዝቡን በዕምነት ረገድ ማጥመቅና በሰላም ተቀብሎ እንዲያስተናግዳቸው የማድረግ ሂደት መከተል ነበር።እነዚሁ የሃይማኖት ካባ የለበሱ መነኮሳትና ቀሳውስት በሚሲዮን ስም ከመስቀል ዘመቻው በስተጀርባ ለቅኝ ግዛት ወረራ የሚያመቻቹና መንገድ ከፋቾች፣ሰላዮች ነበሩ።በዚህም ሂደት የደቡብና ሰሜን አሜሪካ፣ካናዳ፣ የእስያና አፍሪካ፣የካሪቢያንና ሌሎችም ታላላቅ ደሴታማ አገሮች አውስትራሊያና ኒውዚላንድ ጭምር በአውሮፓውያን ተይዘው ስማቸው ሳይቀር በመጤው ለመሰየም በቁ።ነባር ሕዝቡም በባርነት፣በገዛ አገሩ ባይተዋር ሆኖ፣ አልፎ ተርፎም እየተነቀለ በባርነት በያገሩ የሰፋፊ እርሻዎች የጉልበት ሰራተኛ እንዲሆን ተገደደ።ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት እየመጣ ጉልበት እየፈረጠመ ሲሄድ በአውሮፕያውያኑ ወራሪዎች መካከል የጥቅም ግጭት እየተነሳ አንዴም በሰላምና በመስማማት በሌላም ጊዜ በጦርነት አንዱ ሌላውን እያንበረከከ ጥቅማቸውን ማስከበር ቻሉ። በዚህ ሁኔታ ለዘመናት ቆይተው የስግብግብ ጸባያቸው አርፎ ለመቀመጥ ስላልፈቀደላቸው ፉክክሩና ውድድሩ ወደ ትልቅ ጦርነት አምርቶ የመጀመሪያውንና የሁለተኛውን የዓለም ጦርነቶች ወለደ።ብዙ ሕዝብ አለቀ፣ንብረት ወደመ።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

554159 547719028612791 429265140 n
Previous Story

የጊዜው የኢትዮጵያ ጬኸት፤ የተመስገን ደሳለኝ ዕይታና የከበደ ሚካኤል”ጽጌረዳና ደመና”

Next Story

በብአዴን ወለድ አግድ ስር ያለ የአማራ ህዝብ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop