March 13, 2024
12 mins read

የዮናስ ብሩ ቡፋ፤ አትንኩኝ የሹም ዶሮ ነኝ

Yonas
Dr. Yonas Biru

ዮናስ ብሩ ማለት የጭራቅ አሕመድ ተቃዋሚ መስሎ ለመቀረብ የሚሞክር ቀንደኛ የጭራቅ አሕመድ ደጋፊ፣ የኦሮሙማ ተቃዋሚ መስሎ ለመቀረብ የሚሞክር ቀንደኛ ኦሮሙሜመሆኑንና፣ ለማስመሰል የሚሞክረው ደግሞ በፋኖ ታጋዮችና አታጋዮች መካከልሠርሥሮ ገብቶ ለመከፋፈልየሚጣጣር (ይልቁንም ደግሞ ልዩ ተልዕኮየተሰጠው) ሸለመጥማጥበመሆኑ መሆኑን “ዮናስ ብሩ፤ የጭራቅ አሕመድ አዛኝ ቅቤ አንጓች” በሚል ርዕስ በጦመርኩት ጦማር ላይ በሰፌው ስላብራራሁኝ ዳግመኛ አልመለስበትም። ማየት ለሚፈለግ ሁሉ የዮናስ ብሩ ማንነት ከጽሑፎቹ ፍንተው ብሎ ስለሚታይ፣ አስተዋይነትን አይጠይቅም። በዚህ ጦማር ላይ የማተኩረው እኔን (ማለትም ዮናስ ብሩን) መተቸት የሚችሉት እኔን መሰሎች ብቻ እንጅ ሌሎቻችሁ ግን አትንኩኝ የሹም ዶሮ ነኝበማለት ቡፋ በነፋበት(ጉራ በጎረረበት) “Why is fanno stronger in Gojam compared to other Amhara regions” የሚል ከፋፋይ ርዕስ በሰጠው መሠሪ ጽሑፉ ላይ ነው።

ኦቦዮናስ ብሩ ዲባቶ(ዶክተር) ብሩክ ለማለጻፈለት ትችት ባግባቡ መመለስ ሲያቀተው፣ ስለ ፖለቲካ መናገር፣ መጻፍ፣ መተቸትና መተንተን የሚገባን እኔና እኔን መሰል ፖለቲካ የተማርን የፖለቲካ ሰወችእንጅ ፈላስፎች(philosophers)፣ መሐንዲሶች(engineers)፣ ሕክመተኞች(የሕክምና ምሁሮች)፣ ሳይንሰኞች(scientists) ወይም ሒሳበኞች(mathematicians) አይደሉም የሚል ውሃ የማይቋጥር ምክኒያት በማቅረብ፣ ለጦቢያ ሕልውና ወሳኝ የሆኑት ጉዳዮች ሁሉ ለሱና ለሱ መሰሎች ብቻ እንዲተውና፣ ፈላስፎቸ፣ መሐንዲሶቸ፣ ሕክመተኞች፣ ሳይንሰኞችና ሒሳበኞች ግን በሙያቸውና በሙያቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ትዛዝ የሚሰጥ ዓይነት ጥሑፍ ጣጥፏል። ዲባቶ ብሩክ ለማ ደግሞ ሳይንሰኛ ሆኖ ሳለ እሱን ፖለቲከኛውን ዮናስ ብሩን በመቃወሙሊሳለቅበት ሞክሯል።

“My curiosity prompted me to check his [Dr. Bruke’s] expertise. I found out he holds a PhD in biodiversity. This is the study of እንቁራሪት፣ እንሺላሊት፣ ጉሬዛ፤ ቢራቢሮ፣ ከርከሮ፣ ጊንጥ and ሸለ ምጥማጥ, among others. ዶክተር ብሩክ ለማ ዝም ብሎ እንሽላሊት እና እንቁራሪት ሲያባርር ቢውል ይሻለው ነበር። Politics is a complex topic outside the boundaries of his pay grade.” (ዮናስ ብሩ)

ፖለቲካ የተማርኩ ወይም የፖለቲካ ባለሙያ ስለሆንኩ ስለፖለቲካ ማውሳት ያለበኝ እኔና እኔን መስሎች ብቻ ናቸው የሚለው የዮናስ ብሩ የንቀት ጽሑፍ፣ “የፖለቲካ ተማሪወች ማን ናቸው?”የሚለውን ጥያቄ እንድንጠይቅ የግድ ይለናል። ማናቸውም የዩኒቨርስቲ መምህር በግልጽ እንደሚያውቀው የፖለቲካና የመሳሰሉትን ትምህርት የሚማሩ ተማሪወች ሒሳብነክ ትምህርቶችን መማር የማይችሉብቻ ሳይሆኑ እጅግ በጣም የሚፈሩ፣ የሲንሲን(የሰነ አመክንዮ፣ logic) ችሎታቸው ዝቅተኛ የሆነ ዝቅተኛ ተማሪወችናቸው። በሌላ አባባል ፖለቲካ ላንድ አገር ሕልውና እና እድገት ቁልፍ ቢሆንም፣ ባለመታደል ግን ፖለቲካና የመሳሰሉትን ትምህርቶች የሚማሩት ተማሪወች ጎበዞቹ ሳይሆኑ፣ ከዩኒቨርሲቲ ተማሪወች ውስጥ የውራወች ውራ የሆኑት ሰነፎቹ ብቻናቸው።

ለምሳሌ ያህል ዮናስ ብሩ የተማረው ፖለቲካ ከሆነና የፖለቲካ ትምህርቱ ስድስት ዓመትፈጅቶበት ከሆነ፣ እንደ ዲባቶ ብሩክለማ ያለ በሲንሲን(ስነአመክንዮ፣ logic) እና ሳይንሳዊ ዘዴ(scientific method) የተገነባ የፍልስፍና፣ የምሕንድስና፣የሳይንስ ወይም የሒሳብ ሰው፣ ስድስት ወርበማጥናት ብቻ ዮናስ ብሩ ስድስት ዓመት የፈጀበትን ከዮናስ ብሩ በላይ ሊያውቀውና ሊካንበት ይችላል። በተቃራኔው ግን ዮናስ ብሩ በፍልስፍና፣ በምሕንድስና፣ በሳይንስ ወይም በሒሳብ ልካን ቢል ፈጽሞ አይችልም፣ ከችሎታው በላይ ነውና ወይም ደግሞ በራሱ በዮናስ ብሩ አባባል above his pay gradeነውና፣ ፖለቲካ የተማረውም የችሎታውን አነስተኛነት ስለሚያውቅነውና።

አገሮች ችግር ላይ የሚወድቁት ዮናስ ብሩን የመሰሉ ስለ ሳይንስና ሒሳብ ኢምንት እውቅትያላቸው (ይልቁንም ደግሞ ምናምኒትም እውቀት የሌላቸው)፣ በሲንሲን(logic) እና ሳይንሳዊ ዘዴ(scientific method) ያልተገነቡ ዝቅተኛ የዩኒቨርስቲ ተማሪወች፣ ከተመረቁ በኋላ የፈላስፎች፣ የመሐንዲሶች፣ የሕክመተኞች፣ የሳይንሰኞችና የሒሳበኞች የበላይበመሆን የመንግስት አመራሩን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚቆጣጥሩበመሆናቸው ነው። በሌላ አነጋገር አገሮች ከፍተኛ ችግር ላይ የሚወድቁት፣ ያገርን ሕልውና እና እድገት የሚወሰነውን ከፍተኛ የሆነውን የፖለቲካን ጉዳይ የሚማሩት የመማር ችሎታቸው ዝቅትኛ የሆነ ተማሪወች በመሆናቸው ነው

ለምሳሌ ያህል አሜሪቃ እየተንኮታኮተች ያለችው፣ ያሜሪቃን መንግስት አመራር ከተቆጣጠሩት ውስጥ አብዛኛወቹ ምድር ጠፍጣፋ ናት፣ ሰማይ እንቅብ ነው፣ የሰው ልጅ የተፈጠረው ካምስት ሺ ዓመት በፊት ነው ብለው ከልባቸው የሚያምኑ፣ የሳይንስና የሎጅክ ማይሞችበመሆናቸው ነው። ይህን ለመገንዝበ ደግሞ የታወቁት ያሜሪቃ ሕገኛወች (senators) እና ሸንጎኛወች (congressmen) የሚናገሯቸውን አሳፋሪ ንግግሮች ማድመጥ ብቻ በቂ ነው። በተቃራኒው ደግሞ ቻይና ባጭር ጊዜ ውስጥ እንደ ጨሳፊ(rocket) ተጨስፋ ምዕራባውያንን ጣጥላቸው የሄደችው መሪወቿ ሲንሲን(logic) እና ሳይንሳዊ ዘዴ(scientific method) የታጠቁ መሐንዲሶች(engineers) ስለነበሩ ነው።

ያገራችንን የጦቢያን ችግር ምንጭ ብንመረመር ደግሞ አብዛኞቹ የትግሬና የኦሮሞ ጽንፈኞች(አሰፋ ጃለታ፣ ሙሐመድ ሐሰን፣ ጃዋር ሙሐመድ ወዘተ.) ፖለቲካና የመሳሰሉትን ትምህርቶች የተማሩ ዝቅትኛ የዩኒቨርሲቲ ተማሪወችሁነው እናገኛቸዋለን። የፖለቲካና የመሳሰሉት ዲፓርትመንቶች የሰነፍ ተማሪወች መሰባሰቢያወችናቸው። ሰነፍ ተማሪወች ደግሞ ሥራፈቶችስለሆኑ፣ ሥራቸው ሕዝብን ማፋታት(መለያየት) ነው፣ ሥራ ከምፈታ ልጀን ላፋታእንዲሉ፣ ሥራ የፈታ መንፈስ ዳቢሎስመሆኑን ሲያስገነዝቡ። በሲንሲን(logic) እና ሳይንሳዊ ዘዴ(scientific method) የታነፀ ጎበዝ የፍልስፍና፣ የሕክምና፣ የምሕንድስና፣ የሳይንስና የሒሳብ ተማሪ፣ የወያኔና የኦነግ ጎጠኞች በሚያስቡት ደረጃ ዘቅጦ የመንጋ አስተሳሰብሊያስብ አይችልም፣ ቢያስብም ህሊናው ይቆጠቁጠዋል።

ስለዚህም ያገራችንን የጦቢያን ችግር ለመፍታት ቁልፉ ያለው ዮናስ ብሩን የመሳሰሉ የዩኒቨርሲቲ ዝቅትኛ ተማሪወች የሚማሯቸውን ትምህርቶች የተማሩ ዝቀትኞችበከፍተኛ ቦታወች ላይ እንዳይቀመጡና ተደማጭነታቸው ዝቅትኛ እንዲሆን በማድረግ ነው። በተለይም ደግሞ እነዚህ ዝቅትኞች በከፍተኛ ጉዳዮች ላይ ገብተው እንዳይፈተፍቱ በማድረግ ነው። ለምሳሌ ያህል በሳይንሰኛው በዲባቶ ብሩክ ለማ ላይ የተሳለቀው ዮናስ ብሩ ያማራ ሕዝብ ስለሚያካሂደው የሕልውና ጦርነት ሲፈተፈት፣ ጦርነት ሳይንስ መሆኑንወይም ደግሞ ስለ ሰንሹ የጦርነት ጥበብ(Sun Tzu’s Art of War) ፍንጭ የሌለው መሆኑን እሱ ራሱ እየመሰከረ መሆኑን አያውቅም፣ ከእውቀት ችሎታው በላይ ነውና ወይም ደግሞ በሱ በራሱ አባባል above his pay grade ነውና።

ያገራችን የጦቢያ ዘረፈብዙ ችግር ባጭር ጊዜ ውስጥ ሊፈታ የሚችለው፣ አብዛኞቹ አመራሮቿ በተለይም ደግሞ ቁልፍ አመራሮቿ ዝቅተኛ ችሎታቸው የሚፈቅድላቸው እሱን ስለሆነ ብቻ ቃላት መጫወትንና ፀጉር መሰንጠቅን የተማሩት የዮናስ ብሩ ቢጤ እንቶ ፈንቶወችሳይሆኑ፣ በሲንሲን (logic) እና ሳይንሳዊ ዘዴ (scientific method) በጽኑ የተካኑና በጽኑ የሚያምኑ፣ ፈላስፎች፣ መሐንዲሶች፣ ሕክመተኞች፣ ሳይንሰኞችና ሒሳበኞች ሲሆኑ ብቻ ነው።

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop