አድዋ ትርጉም አልባ ድል ቢሆንስ? በኢትዮጵያ እየሆነ ያለውን እያየ ይህን ጥያቄ የማያነሳ ግብዝ ብቻ ነው?

What significance does the victory Ethiopians achieved against the invading Italian forces in the Battle of Adwa in 1896 hold today if the descendants of Adwa’s heroes are treated worse than animals in their own land?

በ1888 ኢትዮጵያውያን በጣሊያን ላይ የተቀዳጁት አኩሪ ድል፣ ዛሬ በገዛ ሃገራቸው የሰውነት ክብር ተነፍገው በባርነት ለሚማቅቁት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የአድዋ ጀግኖች ልጆች ትርጉሙ ምንድነው?

What significance does Adwa hold for the parents, siblings, and loved ones of a young man whose dignity is violated (through genital mutilation ), by soldiers under Abiy Ahmed’s command, his suffering broadcasted across social media? (for those who have the nerve video is available on this telegram page) https://t.me/+UNLX8ZQKVJw0Y2Fk

የአብይ አህመድ ወታደሮች ቪዲዮ እያነሱ በቢላዎ ብልቱን ሲተለትሉት የተቀዳውንና በማህበራዊ ሚድያ የተሰራጨውን ቪድዮ ለሚመለከቱ የወጣቱ እናት፣ አባት፣ ወንድም፣ እህትና ዘመዶች የአድዋ ድል ትርጉሙ ምንድንነው? (ይህን ለማየት የሚቀፍ ግፍ በዚህ ቴሌግራም ፔጅ ታኙታላችሁ https://t.me/+UNLX8ZQKVJw0Y2Fk

What significance does Adwa have for a family mourning the loss of 16 members, victims of Abiy Ahmed’s drones while returning from a joyful christening event?

በሰሜን ሸዋ የህጻን ልጃቸውን ክርስትና አስነስተው በደስታ ሲመለሱ፣ የአብይ አህመድ ድሮን 16 የአንድ ቤተሰብ አባላት ለጨፈጨፈባቸው የተጨፍጫፊዎቹ ወገኖች የአድዋ ድል ትርጉሙ ምንድን ነው?

What significance does Adwa hold for those facing mass slaughter in the Amhara and Oromia regions, targeted by Ahmed’s war jets, drones, artillery, and other heavy weaponry?

ተጨማሪ ያንብቡ:   የዐብይ አሕመድ መሰወርና የወያኔ ፕሮፓጋንዳ - መስፍን አረጋ

በአብይ አህመድ የጦር ጀቶች ድሮኖች መድፎችና ሌሎች ከባድ የጦር መሳሪያዎች ቀን እና ማታ በጅምላ ለሚጨፈጭፈው የአማራ የኦሮሞና ለተቀረወም የኢትዮጵያ ህዝብ የአድዋ ድል ትርጉሙ ምንድን ነው?

What significance does Adwa have for those spending the day of victory in concentration camps or overcrowded prisons, denied access to justice?

በአብይ አህመድ ማጎሪያ ጣቢያዎችና የተጨናነቁ እስር ቤቶች ሆነው፣ ፍትህ እንደሰማይ እርቆባቸው መፈጠራቸው እየተራገሙ እለቱን ለሚያሳልፉ፣ በመቶ ሽዎች ለሚቆጠሩ የሃገሪቱ ዜጎች የአድዋ ድል ትርጉሙ ምንድን ነው?

What significance does Adwa hold for the masses of Ethiopians whose dreams of a brighter future are repeatedly shattered by cruel, corrupt regimes and leaders driven by ignorance, caprice and greed?

በየጊዜው የሚመጡ መንግስታት እና መሪዎች የተሻለ ህይወት የመኖር ተስፋውን የሚያጨልሙበት፣ በጨካኞች፣ በደንቆሮዎች በስግብቦች ከስክስ ጫማ እየተከሰከሰ ለሚኖረው፣ በአለም አደባባይ መዋረድ ምሱ ለሆነው የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ የአድዋ በአል ትርጉሙ ምንድን ነው?

Andargachew Tsege

4 Comments

  1. ወንድሜ አንዳርጋቸው ኸረ ጭፍን የኢትዮጵያ አምላኪዎች እንዳይቦጫጭኩህ ተጠንቀቅ። የበራ ጭንቅላት ለታደለና በምድር ላይ ዛሬም ሆነ ያለፈውን የሃገሪቱን መከራ ለመረዳት ፈቃደኛ ለሆነ የአድዋ ድል ለኢትዮጵያ ካስገኘው ጥቅም ይልቅ በዚያ ድል ምክንያት ነጻነታቸውን ለተነፈጉ የአፍሪቃ ሃገሮች የፈነጠቀው ጮራ ይበልጣል። የእኛው ነገር እማ እያደሩ ወደ ኋላ ከሆነ ቆይቷል። ይህ አሁን የምናየው መሸራከት ይዘትና መጠኑ ብሎም ቋንቋና ብሄርን ተገን አርጎ በጊዜው ጠበንጃ አንጋቾች የሚደርስ የከፋ ፈተና ይሁን እንጂ ድሮም ተንኮልና ያዘው ጥለፈው ማለታችን የታወቀና ተመዝግቦ የተያዘ ነው። የ 3 ሺህ ዘመን ነጻነት አላት እያልን መደንፋት ምድር ላይ ሲፈለግ የማይገኝ ጉዳይ ነው። ዘመኑ ራቀ እንጂ ንጉሱ ከተሰደድበት ገብተው ንጉስ ነኝ ሲሉ የሾሟቸው ብዙዎቹ ኢትዮጵያን ሲያደሙና ሲያፈርሱ የነበሩ ናቸው። ለዚህ የታሪክ መዛግብትን መመርመር ተገቢ ይሆናል። በበረሃና በጫካ ለምድሪቱ ነጻነት የታገሉት ደግሞ በአደባባይ ተሰቅለዋል። ከእነዚህም መካከል እውቁ ተፋላሚ በላይ ዘለቀና ወንድሙ እጅጉ ዘለቀ የተንጠለጠሉት በአንድ ቀን ፊትና ኋላ ሆነው ነው። ያኔ ቆሞ ሲንጠለጠሉ የተመለከተው መንግስቱ ንዋይ ደግሞ ከግርማሜ ጋር በጠነሰሱት ሴራ ወደ 14 የሚደርሱ ባለስልጣኖችን ረሽነው ግርማሜ በተኩስ ልውውጥ ሲገደል፤ መንግስቱ ለገመድ በቅቷል። መንግስቱ ንዋይ እንዲገደልና ሌላም ነገር ከሥር ሥር ሲገፉ የነበሩትን ደግሞ ደርግ የሚባል ጉድ መጣና 60 ዎቹን በአንድ ጉድጓድ ከተታቸው። በንጉሱ ባለስልጣኖችና በሌሎች የሃገሪቱ ምሁሮች ላይ ሰማይ ጠቀስ ግፍን ያደረሰው ደርግ ደግሞ ወያኔና ሻቢያን ልኮበት ንፋው የነካው ደመና ሆነና ከሰመ፤ ለመነ፤ ተራበ፤ ተሳቀበት። ወያኔና ሻቢያ ፍቅራቸው አልቆ በባድሜ አሳበው ተባሉ። አሁንም በደም ይፋለጋሉ! ታዲያ ይህ የነጻ ህዝብ ባህሪ ነው ቢሉ ጅልነት ነው። የአንዲት ምድር የነጻነት መለኪያው ምንድን ነው? አሁን ማን ይሙት ኤርትራ ነጻ ሃገር ናት? አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ አለና ሰላም አለ? መልሱ በጭራሽ ነው።
    መቀየር ያለበት እይታና አስተሳሰባችን ነው። አዲስ አበባ ላይ እትብቱ ተቀብሮ ለሻቢያ ቁጭ ብሎ የሚያለቅስ፤ የትግራይ መሬትን እግሩ ሳይረግጥ በአራተኛ ትውልድ ለትግራይ ቆሜአለሁ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚል። ምንም መረጃ በሌለው ጉዳይ ንጽህ አማራ፤ ንጽህ ኦሮሞ ነኝ እያሉ በብሄር ስካር ሌላውን ወደ ጎን የሚያደርጉ እኩዪች ባሉበት ምድር ላይ የአድዋ ድል ለከበሮ ድለቃ ካልሆነ በስተቀር ዋጋ ይብሉን። በቀልን እያሰላሰሉ ያደጉ ሰውን በሰውነቱ ብቻ ከመመልከት ይልቅ ቋንቋና ብሄሩን ቀዳሚ የሚያደርጉ እነዚህ አረመኔዎች እስካልጠፉ ድረስ ምድሪቱ በዚህም በዚያም ሰበብ ሰንደቋን ማውለብለቧ የነጻነቷ ምልክት አይሆንም። የሃገሮች መለኪያ ሚዛኑ ከመቶ ዓመት በፊት በተደረገ ገድል ወይም እንደ ኤርትራው ባርነት ወይም ነጻነት በማለት አስመርጦ መልሶ ባርነትን በህዝቦች ላይ የሚጭን፤ ወይም እንደ ብሄርተኞቹ ታጣቂዎች የእህል ክምር እያቃጠሉ፤ የቁም ከብቶችን እየገደሉ፤ የሃይል ማመንጫና የመገናኛ አውታሮችን እየናድ በብሄር መመጻደቅ ቀንዳም መሆን ነው። ኢትዮጵያ የዘርና የቋንቋ የአፓርታይድ የክልል ፓለቲካን ከሥሩ ፈንግላ በሥፍራው ሁሉም ለሁሉም በሁሉም የሆነ ጠንካራ ስርዓት እስካልገነባች ድረስ አንድ አንድን ሲበላው የተበላውን አዲሱ ቆፍሮ እያስወጣ ቋሚን ሲያስለቅስ ዝንተ ዓለም መኖራችን አይቀሬ ነው።
    ንጉሱም ግፈኛ ጡርን የማይፈሩ
    ደርግም ተንኮለኛ ትውልድን የፈጀ
    ወያኔም መናጢ ሽንክ ነው ዲያብሎስ
    ብልጽግናም ክፉ ቃሉ እማይጨበጥ
    ወይ አንቺ ሃገሬ ከቶ ምን ይበጅሽ
    የሄደ የመጣው አምሶ ሲቆላሽ።

  2. The significance of the Adwa Victory has been lost on us most Ethiopians. The victory was not an end-point, but a landmark in the freedom voyage. The enemy we defeated at the front gate, has succeeded in entering via the back-door (an alien educational system, an alien political system etc) and nullifying the gallant sacrifices of our ancestors. And we have been caught unawares, sleeping. The atrocities we see today, are results of a concerted effort to uproot us and it started as a poison fed to so-called freedom fighters and Great X dreamers in the fringes of the Ethiopian state. That is what spread to the university and guised itself as a progressive movement of university students. The struggle to remove the age-old institutions (the monarchy, the church and the military) using iconoclastic foreign imported ideologies, dismantled much more than just these institutions. Now we are seeing the fruits of a mentally colonized people that is in conflict with its identity.

    ሜንኒጃይትስ
    የመከተው ጠላት ምኒልክ በጋሻ
    አሸንፎ ገብቷል በቀለም በጉርሻ።
    እኛ ስንፎክር እሱ ቁስሉን ልሶ
    መንፈስ ሆኖ መጥቶ ቀስፎናል መልሶ።
    እንደ ሜኒንጃይትስ አንጎል ውስጥ ተጸንሶ።

  3. Yes, indeed! The deposits that our ancestors left for us at Adwa Bank have been embezzled.
    How did we arrive here? What are the sins of omission or commission of post-Adwa generations in failing to preserve the independence and freedom obtained through the gallant sacrifices of our ancestors? Were generations of Ethiopians “asleep as the enemy came and sowed weeds among the wheat and slipped away”? (Matthew 13:25)

    Of course we have to study and celebrate Adwa because therein lies our redemption once again. It is by forgetting how we got from Zemene Mesfint to Adwa that we have allowed history to repeat itself. Nations like people have their highs and lows. The value of Adwa for us would be, once we understood that we have hit a low, to serve us as an inspiration and a road map to rise again.

    የአድዋ ባንክ ተዘርፏል
    ኧረ ምኑ ተርፏል!
    ያድዋ ባንክ ተዘርፏል።
    አባቶች ያኖሩት የአንድነት እቁብ
    እናቶች ያኖሩት የአርነት ቋጠሮ
    ከኢትዮጵያ አልፎ ላፍሪካ እንዲተርፍ
    በአድዋ ካዝና ውስጥ ያኖሩት ሀብት ሁሉ
    የባንኩ ዘበኛ የባንኩ አስተዳደር
    የሂሳብ ሹሞቹ የገንዘብ ቆጣሪ
    ከሽፍታ ከሌባ ተባብረው በሙሉ
    ጠራርገው ዘረፉት ከቶ ምኑ ተርፏል
    አድዋ አድዋ ስንል ያድዋ ባንክ ተዘርፏል።
    አዲስ ሠራተኞች አዲስ ትውልድ ቀርጸን
    የባንኩን ቀዳሚ ዓላማ አስርጸን
    ታማኝ ጠባቂዎች ዘበኛና ውሻም
    ተቀማጭ የሚሆን ለመንቀሳቀሻም
    ሁላችን አዋጥተን እስካልጨመርንበት
    ለትውልድ የሚተርፍ ሙጣጭም የለበት።

    (ይህ ግጥም አባቶቻችን ለልጅ ልጆቻቸው ብቻ ሳይሆን ለዓለም ጭቁን ሕዝቦች ሁሉ የሚተርፍ የአንድነት፣ የነጻነት፣ በራስ የመተማመን ስሜት የሚለግሥ ድል በአድዋ ያስመዘገቡልን ቢሆንም ድሉን ግን ስላላስጠበቅነው፣ ስላልዘከርነው፣ ስላልጨመርንበት፣ ስላልሰራንበት ከቶውንም በጠላት ተመዝብሮ ዛሬ ጥሪቱ ተመናምኗል ይለናል። ጠላት የአንድነትን፣ የኅብረትን፥ የነጻነትን ዋጋ ቀስ በቀስ ሸርሽሮ ከውስጣችን አውጥቶታል። ለልጆቻችን እነዚህን ዋጋዎች ለማቆየት እኛ አድዋዊ ተጋድሎ ልንጨምርበት ይገባል የሚል ማሳሰቢያ ነው። )

  4. አይ አንዳርጋቸው፣ ሁለተኛዋን ጩቤ በአድዋ ላይ ለመሰካት መሞከርህ ይገርማል።
    ይቺ ለእንግሊዝ ዜግነትህ የተከፈለች ሁለተኛዋ የባንድነት ወሮታ መሆን አለባት።
    ፊት ያንተው ቢጤ ጸረ ኢትዮጵያ እንግሊዛዊ የጻፈውን መርዘኛና ተንኮለኛ ቀጣፊ ድርሰት ጠቅሰህ አድዋ ላይ የእስላም ሬሳ ተለይቶ አልተቀበረም ነበር ብለህ ነጭ ውሸት በመጻፍ አሳተምክ።
    ዛሬ ደግሞ በዚህ ታላቅ ድል መታሰቢያ አድዋን ጠብቀህ በአዛኝ ቅቤ አንጓችነት ጥላሸት ስትቀባ ይገርማል። ማን ያነገሠው ሥርዐት ሆነና!
    ለመሆኑ ሁለት ጊዜ ለጎሳ ፋሺዝም አንበሎች ለመለስና ለአቢይ ጋሻ ጃግሬ ሆነህ የተከልከው የልዩነትና የጥላቻ ሥርዐት ወዴት እንዲያመራ ጠብቀህ ነበር? ወደ አድዋ ከፍታ? ሥርዐቱ ኅሊና ላለው ለሚያመዛዝን ሁሉ በከባድ ፍጥነት ወደ ሩዋንዳ ጭፍጭፋ የሚገስግስ ሥርዐት ነው። ይህንን የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ጄኖሳይዳዊ ግስጋሴውን ሊያስቆመው ፋኖ ተነስቷል። አንተ ደግሞ እድሜ ልክ የለፋህበት የጌቶችህ ሕልም እንዳይጨናገፍ ፋኖን ለመከፋፈልና ለመጥለፍ ተልእኮ ተሰጥቶህ ትተጋለህ።
    የአድዋ ዋልታና ማገር በሆኑት በእምነት፣ በቋንቋ፣ በሰንደቅ ዓላማ፣ በዘውድ ሥርዐት ላይ ስልሣ አመት ዘምታችሁ መልሳችሁ ደግሞ የሥራችሁን ውጢት አድዋን ለማጠልሻማ አትጠቀሙ።
    ልጥህ የተራሰ ጉድጓድህ የተማሰ ሰው
    ይልቅ ይቺን አጋጣሚ ለንሥሐ ብትጠቀምባትና “በኛ ያላሰለሰ ተሳትፎ ኢትዮጵያን ለዚህ ውርደት አበቃናት” ብትል አይሻልም ነበር?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share