የአማራ፣ የኦርቶዶክስና የኢትዮጵያ ጥላቻ ይቁም።

February 23, 2024

ዶ/ር በቀለ ገሠሠ
(drbekeleg@gmail.com)

1ኛ/  መግቢያ፣

ይህንን አርዕስት አድርጌ ስጽፍ እጅግ በጣም እያዘንኩ ነው። ነገር ግን ችግሮቹ
ስለተደጋገሙና እየተባባሱ በመምጣታቸው ነው የተገደድኩት። እነዚህን አካላት ነጥሎ የሚጠላ ግን የሰይጣንና የውጪ ባርያ ፈንጋዮችና ቅኝ ገዢዎች  መልእክተኛ ካልሆነ በስተቀር ለማንም ዜጋ የሚበጅ ጤናማ ሰው መሆን አይችልም።   ይህ ከቀጠለ ጉዳቱ የሁሉም ዜጋ ስለሚሆን በህብረት ቆመን ቶሎ ማስቆም ይኖርብናል።

2ኛ/  አሳፋሪው የአማራ ጥላቻ፣

የአማራን ህዝብ ነጥለው የማጥፋት ዒላማ ለምን እንዳደረጉ ፈጽሞ አይገባኝም ። በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎጃም፣ በጎንደርና በተቀሩት የአገሪቷ ክፍሎች የኖሩና የሚኖሩት አማራውያን በያሉበት ጥረው ግረው ከማደር በስተቀር ያገኙት የተለየ ጥቅም የለም፣ አልነበረምም። የባላባታዊ ሥርዓት ከሆነ ደግሞ የአማራ ብቻ ሳይሆን የትግሬውም፣ የኦሮሞም፣ የከፋም፣ የወላይታም፣ የአፋርም፣ ወዘተ፣  ነገዶች ሁሉ ባላባቶች ነበሩ። እርሱም ቢሆን ከተወገደ 50 ዓመታት አለፈው። ከርሱ በኋላ በተፈራረቁት ፋሺስታዊና ዘረኛ አምባገነን ሥርዓቶች ምክንያት ዲሞክራሲ ገንብተን እድገትና ሰላም ማምጣት አቅቶን እንጂ የተለየ የአማራ ነገድ ችግር ሆኖ አይደለም።

ይህ ከሆነ ዘንዳ አማራን ነጥለው የዘር ማጥፋት ዒላማ ማድረጋቸው ከቶ ሊገባኝ አይችልም። አማራውስ ቢሆን ዝም ብሎ ቁጭ ብሎ የሚያልቅላቸው ይመስላቸዋል? ጥሩ ሕሊና ያለው ሌላውስ ዜጋ ዝም ብሎ ቁጭ ብሎ የሚመለከታቸው ይመስላቸዋል? ከሆነ ትልቅ ስህተት እየደገሙ ናቸውና ቶሎ ቢያስቡበት ይበጃቸዋል።

3ኛ/  የኦርቶዶክስ ጥላቻ፣

ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የጋራ ጥቅም ከማምጣት በስተቀር ምን ባደረገች ነው አብያተ ክርስትያናትና ገዳማቷ የሚቃጠሉት? ቅዱስ ሲኖዶስዋን በጎሳ  የሚከፋፍሉባት? ሥልጣኔን፣ መልካም ሥነምግባርን፣ መቻቻልን፣ እንግዳ ተቀባይነትን፣ ከራስ በላይ ባልንጀሮችን መውደድን፣ አለመስረቅን፣ አለመግደልን፣ ወዘተ ሰብኮ አገር ከማቅናት በስተቀር ምን አደረጋቸው? ውድ አገራችን በውጪ ወራሪ ኃይሎች ስትወረር ከአርበኞቻችን ጎን ቆማ፣ ባርካና ቀድሳ ከባርነትና ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ያወጣችን ባለውለታችን መሆኗን መርሳቱ እጅግ በጣም ያሳፍራልና አስቡበት።

4ኛ/  የኢትዮጵያ ጥላቻ፣

ኢትዮጵያ ቸሩ አምላካችን ሁሉን አሟልቶ የፈጠራት ቅድስት አገር ናት። ያልዞርኩበት የዓለም ክፍል የለም። በቆዳ ስፋት፣ በልምላሜ፣ በተፈጥሮ ሃብቶች፣ በወንዞችና ኃይቆች ብዛት፣ ወዘተ ከኢትዮጵያ በላይ የታደለና የተጎናጸፈ ሌላ አገር እንደሌለ ስገልጽ በእብሪት ሳይሆን ሃቅን ተመርኩዤ ነው።

ኢትዮጵያ የነፃነት ተምሣሊት ናት። በዚህም ምክንያት ቂም የያዙብን ታሪካዊ ጠላቶች አሉ።

ዛሬ የኢትዮጵያ ገጽታ በኢጋድ፣ በአፍሪቃ ህብረት ድርጅትና በመላው ዓለማችን ፊት በጣም ወርዷል። በዚህ ከቀጠለ የአፍሪቃ ህብረት ድርጅትም ሆነ የዓለማቀፍ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ወደሌሎች አገሮች ሊዛወሩ ይችላሉ። ከገጽታም በላይ ብዙ የሥራና የኢኮኖሚ ዕድሎችን ሊዘጉብን ይችላሉ።

ስለዚህ የኢትዮጵያ መውደቅና መፍረስ ለማንም አይበጅምና በቶሎ እንጠንቀቅ ዘንድ ቅን ምክሬን እንድትሰሙኝ በትህትና እጠይቃችኋለሁ።

5ኛ/  ለውስጥ ኃይሎች አጭር መልእክት

አማራንና ኦርቶዶክስን በማጥቃት የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ ወዘተ መንግሥት ነጥሎ መመሥረት አይቻልም። አገሪቷ የሁሉም ስለሆነች የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ይገኛልና።   በመከፋፈልና በመጠፋፋት ሰላምና እድገት ማምጣት አይቻልም። ተያይዞ መጥፋትን ብቻ ነው የሚያስከትለው።

አማራው ዝም ብሎ ቅጭ ብሎ አያልቅላችሁም። የኦርቶዶክስም አምላክ አለ። ከየነገዱም ቅን የሚያስቡ ብዙ ዜጎች አሉ። ነግ በኔ ብሎ ማሰብም ያስፈልጋል።

በቤኒሻንጉል፣ በወለጋ፣ በአርሲ፣ በሸዋ፣ በማይካድራ፣ በመርዓዊ፣ ወዘተ በአማራ ህዝባችን ላይ የደረሰው ጭፍጨፋና ማፈናቀል ሁላችንንም እኩል መመልከት ይገባዋል። በአዲስ አበባ ብዙ ሺ ቤቶች በግፍ ፈርሰዋል። አማራ የኦሮሞም፣ የትግሬም፣ የማንም ጠላት ሆኖ አያውቅምና ሁሉም ያስብበት።

የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋውና ማፈናቀሉ ቶሎ ቆሞ ወደሰላምና እድገት እናቀና ዘንድ በህብረት ቆመን እንድንጸልይና እንድንታገል  በጥሞና ላሳስብ እወዳለሁ።
6ኛ/  ለውጪ ኃይሎች መልእክቶች እንላ

ኢትዮጵያ ሰላምና ወዳጅነት ብቻ ነው የምትፈልገው። ሰላም ካላት ራሷን በደንብ መመገብ የምትችል አገር ናት። ህዝቧ ከ120 ሚሊዮን በላይ ነው።
ዛሬ ዓለም በሙሉ በከባድ ውጥረት ውስጥ ይገኛል። በአካባቢው የአየር ንብረት ብክለት ምክንያት የዓለም ኢኮኖሚ እየወደመ ይገኛል።  በየቦታው በተደጋጋሚ በሚቀሰቀሱ  ጦርነቶች ምክንያት ኢኮኖሚዎች እየወደሙና ብዙ ሚሊዮኖች እየተሰደዱ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ መፍረስ ለማንም አይበጅም፣ ከባድ ችግር ይጨምራል በሏቸው። የሚሰሙ ብዙ ቅን ሰዎች አሉና በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ ወዘተ ለየፓርላማ አባሎቻችሁና ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በተደጋጋሚ መጻፉን አትርሱ።

ከሁሉም በላይ የጭቁኖች አምላክ አለና እርሱ ይጨመርበት።

3 Comments

  1. Genocide is not about hate. Genocide is about greed. Genocide is about dispossession. Genocide is about erasing the owners and inheriting their land. If Abiy Ahmed gets the monks of the monastery slaughtered, the aim is to take over Ziquala and turn it to a profitable resort. Meles Zenawi was making sugar plantations out of monasteries. Now, Abiy Ahmed is making resorts out of sacred sanctuaries and monasteries.
    The projects are partly funded by Arabs from across the sea. Hate is just an instrument. The driver is greed. Greed to dispossess and inherit all. As an agent and a broker, Oromumma gets its fat commission, but the ultimate benefactor is the foreign sponsor.

    • Internal genocides are evils who do not have any sustainable good vision for their people.
      Their external sponsors are slave masters and colonialists as well as those intoxicated by petrodollar seeking land for agriculture.

  2. ደማቸው በምድር ይመለሳል ለዚህ እልቂት አስተባባሪዎች ሬሳቸው ክብር ሳይሰጠው አድራጊዎቹ ተርበድብደው በፍርሃታቸው ይርዳሉ ይሞታሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Koree Nageenyaa Ethiopian News
Previous Story

የሉባ ገዳ፡  የጨፍጫፊወች ዕድር

188942
Next Story

የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አባቶች ግድያ

Go toTop