ጭራቅ አሕመድ፣ ለማ መገርሳና ሽመልስ አብዲሳ፤ የጭራቅ አሕመድ መፃኢ ዕጣ

February 2, 2024
14 mins read

ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ በልቶ ለመጨረስ ቆርጦ የተነሳ የኦሮሙማ አውሬ ቢሆንም፣ አውሬውን እንደ እንዝርት የሚያሾረውና ባማራ ሕዝብ ላይ የሚያሰማራው ግን ‹‹ቀድሞ የይፋ አሁን የሕቡዕ አለቃየ›› እያለ አለቅጥ የሚሽቆጠቆጥለት፣ በመሠሪነቱ ወደር የሌለው ሸለመጥማጡ ለማ መገርሳ ነው፡፡  አሁን ላይ ግን ጭራቅ አሕመድ ለለማ መገርሳ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ ስለመጣ፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ረሽኖ ያስወግደዋል፡፡  ለምን እና እንዴት የሚለውን ደግሞ ባጭሩ እንመልከት፡፡

በፖለቲካ ብስለታቸው አንቱ የሚባሉትን ጨምሮ አያሌ ጉምቱ ሰወች ጭራቅ አሕመድ ለማ መገርሳን ከስልጣን አስወግዶ፣ ከሀገር አስወጥቶ ከጨዋታ ውጭ አርጎታል እያሉ እጅጉን ሲሳሳቱ ይደመጣሉ፡፡  ይህን ትልቅ ስህተት የሚፈጽሙት ደግሞ የለማ መገርሳን የመሠሪነት ጥልቅት ባለመረዳትና፣ ዐላማውን በምን መንገድ እንደሚያስፈጽምና ማስፈጸም እንደሚፈልግ ባለማወቅ ነው፡፡ ጭራቅ አሕመድ ጃዋርን አሰረው የተባለው፣ እስክንድርን ለማሰር ጭራቅ አሕመድና ጃዋር ሙሐመድ የተጫወቱት ቀልድ እንደነበረ ሁሉ፣ ጭራቅ አሕመድ ለማ መገርሳን አባርረው የሚባለው ደግሞ አማራን ለማታለል ጭራቅ አሕመድና ለማ መገርሳ የተጫወቱት ቀልድ ነበር፡፡

ጭራቅ አሕመድን ጨምሮ ሁሉንም ኦሮሙሜወች በየመደበላቸው የሥራ ድርሻቸው የሚያሰማራቸውና የሚከታተላቸው የኦሮሙማ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆነው ኦቦ ለማ መገርሳ ነው፡፡  የኦሮሙማ ፕሮጅከት ሊሳካ የሚችለው ደግሞ በኦነግ ጥንካሬ ሳይሆን ባማራ ድክመት እንደሆነ ከለማ መገርሳ በላይ የሚያቅ የለም፡፡  ያማራ ድክመት ደግሞ ካማራነቱ በላይ ኢትዮጵያን ማፍቀሩ ነው፡፡   ስለዚህም፣ ለማ መገርሳ የኦሮሙማ ፕሮጀክቱን ማስፈጸም ይችል የነበረው ኢትዮጵያን የሚያፈቅር መስሎ በመቅረብ ነበር፡፡  የወያኔ የደህንነት ኃላፊ ሆኖ ኢትዮጵያን ሲያጠፋ እንዳልነበር፣ ወያኔ ሊወድቅ ሲንገዳገድ በድንገት ተነስቶ ኢትዮጵያ ሱሴ ያለውም ኢትዮጵያ ሱሱ ሁናበት ሳይሆን በኢትዮጵያ ፍቅር የወደቀውን አማራን ለማነሁለል ሲል ብቻ ነበር፡፡

ያዲሳባ የዲሞግራፊ ቅይራ ንግግሩ ይፋ ከወጣበት በኋላ ግን ለማ መገርሳ አማራን ማታለል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡  የነ ዲባቶ (ዶክተር) አምባቸው የባሕርዳር ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ ጭፍጨፋውን ያካሄደውን መከላከያን ይመራ የነበረው እሱ መሆኑ ደግሞ የለማ መገርሳን ማንነት ይበልጥ ይፋ አደረገው፡፡  ስለዚህም አማራን እያዳከመለት የኦሮሙማን ፕሮጀክት ለመፈጸም እስካስቻለው ድረስ፣ ጭራቅ አሕመድን ከፊት አድርጎ ከኋላ ሁኖ ከመምራት ውጭ ምርጫ አጣ፡፡

አሁን ላይ ግን ጭራቅ አሕመድ አማራን የሚያታልልባቸውን ትሪኮቹን (tricks) ተጠቅሞ ጨርሷል፡፡  ካሁን በኋላ ጭራቅ አሕመድ በኃይል ካልሆነ በስተቀር አማራን በማታለል ሊፈጽም የሚችለው አንዳችም ነገር የለም፡፡  ባማራ ሕዝብ ላይ ይፋ ጦርነት የከፈተውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ አማራን ማታለል ካልቻለ ደግሞ ለለማ መገርሳ የኦሮሙማ ፕሮጀክት ምንም ጥቅም የለውም፡፡  እንዲያውም ጉዳቱ ያመዝናል፡፡  ስለዚህም ባስቸኳይ ያስወግደዋል፡፡

ጭራቅ አሕመድ ስለነጻነት ምንነት ምንም ባማያውቅበት ዕድሜው፣ ኦሮሞን ካማራ ነጻ ለማውጣት ጫካ የገባ የኦነግ የሕፃን ወታደር (child soldier) ነበር፡፡  የኦነግ የሕፃን ወታደር የነበረ በመሆኑ ደግሞ በኦነግ አለቅጥ የተነወረ (ነውር የተፈጸመበት abused) የነውር በሽተኛ (abused child) ነው፡፡  የኦነግ የሕፃን ወታደር የነበረ ከመሆኑ በላይ አናቱ አማራ ናቸው መባሉ፣ ያባቱ ማንነት ደግሞ በውል አለመታውቁ በኦነግ የተፈጸመበትን ነውር ይበልጥ የከፋ አድርጎታል፡፡  የተማረ ነው ይባል የነበርው ሃይሌ ፊዳ፣ አባቱ የመናዊ በመሆናቸው ምክኒያት በማንነቱ ያን ያህል ተሰቃይቶ ኦሮሞነቱ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገባ ሲል ብቻ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ልሁን ካለ፣ አናቱ አማራ ናቸው የሚባሉት ምንም ትምህርት የሌለው ጭራቅ አሕመድ ደግሞ አሮሞነቱ እንዳይጠርጠር ሲል ብቻ አማራን ከምድረግጽ ሊያጠፋ ቢነሳ ምንም አያስገርምም፡፡

እንደ ጭራቅ አሕመድ ያለ፣ ከሕፃንነቱ ጀምሮ አለቅጥ የተነወረ የነውር በሽተኛ/ነዋሪወቹን/ (ነውር የፈጸሙበትን) ለማስደሰት ሲል ምንም ከማድርግ አይመለስም፡፡  መዱስ (መጽሐፍ ቅዱስ) እንደሚያስተምረን አብርሃም ለጌታው /ያለውን/ ታማኝነት ለማስመስከር ልጁን ይስሐቅን ለእርድ እንዳቀረበ፣ ጭራቅ አሕመድ ደግሞ ‹‹ቀድሞ የይፋ አሁን የሕቡዕ አለቃየ››  ለሚለው ለጌታው ለለማ መገርሳ ያለውን ታማኝነት ለማስመስከር አማራን ማረድ ሳይሆን ልጆችህን እረድ ቢለው በደስታ ያርዳል፡፡

ያንድ ብሔር አባል አለመሆኑ የሚጠረጠር ግለሰብ ወዶም ሆነ በነውር ተገዶ የዚያ ብሔር ብሔርተኛ ከሆነ፣  ጥርጣሬውን ለማስወገድ ሲል ብቻ ማናቸውንም አረመኔያዊ ድርጊት ለመፈጸም ቅንጣት አያቅማማም፡፡  ሂትለር ይሁዳወችን ያለ ርኅራኄ የጨፈጨፈበት አንዱ ምክኒያት፣ የይሁዳ ደም አለበት የሚባለውን ጭምጭምታ ለማስተባበል ነበር፡፡  ምሥራቅ አውሮጳውያን (ቸኮች፣ ፖሊሾች፣ ዩክሬኖች፣ ክሮአቶች…) ካንግሎ ሳክሶኖች በከፋ ሁኔታ ዘረኛ መስለው ለመታየት የሚጥሩት፣  ከነጭ አይቆጥሩንም ለሚሏቸው ለምዕራብ አውሮጳውያን ነጮች መሆናቸውን ለማስመስክር ሲሉ ነው፡፡  ያሜሪቃ ጥቁር ፖሊስ ከነጭ ፖሊስ የበለጠ በጥቁር ላይ የሚጨክነው፣ ታማኝነቱን ለነጭ አለቆቹ ለማሳየት ነው፡፡  ባባቱ አማራ ነው የሚባለው ጌታቸው አሰፋ ያማራ ሳጥናኤል የሆነው፣ ትግሬነቱን ለማስመስከር ነበር፡፡

ጭራቅ አሕመድ ደግሞ በናቱ አማራ ነው ከመባሉ በላይ የተጋባው ጎንደሬ ናት ከምትባል ሴት ጋር ነው፡፡  ስለዚህም በጎጠኝነት የሰከሩት የኦሮሞ ጽንፈኞች ጭራቅ አሕመድን ከአሮሞ አይቆጥሩትም፡፡  እንደማይቆጥሩት ደግሞ እሱ ራሱ በደንብ ማወቅ ብቻ ሳይሆን አልቅጥ ያስጭንቀዋል፡፡  ኦሮሞነቴን ማንም አይሰጠኝም፣ ማንም አይነፍገኝም፣ እናቴ አማርኛ አትችልም እያለ ሳይጠይቁት የባጥ የቆጡን የሚቅባጥረው ይሄን ጭንቅቱን ለማለዘብ ነው፡፡

ጭራቅ አሕመድ በኦሮሞነቱ ስለማይታመን ባይነ ቁራኛ እንደሚጠበቅና እያንዳንዷ ድርጊቱ ባጉሊ መነጽር እንደምትመረመር አሳምሮ ያውቃል፡፡  ትንሽ ቢሳሳ ግዙፍ ውለታው መና ቀርቶ ከሃዲ እንደሚባ ነጋሪ አያስፈልገውም፡፡  እስከጣፈ ድረስ ተላም የሚተፉ አገዳ መሆኑን በደንብ ያውቃል፡፡  ስለዚህም ጥፍጥናውን ላለማጣት ሲል ብቻ ማናቸውንም ፀራማራ ድርጊት ለመፈጸም ቅንጣት አያቅማማም፡፡  የሱ ጽኑ ፍላጎት ደሞ ኦነጋውያን ትናንት ከሚያምኑት የበለጠ ዛሬ እንዲያምኑት ስለሆነ፣ ትናንት ከጣፈጠው የበለጥ ዛሬ መጣፈጥ ነው፡፡  ስለዚህም ጥፍጥናውን ለመጨመር ሲል፣ ትናንት ቶሌ ላይ ያማራን ሕጻናት ግዳይ እንደ ጣለ፣ ነገ ጉለሌ ላይ፣ ከነገ ወዲያ ደግሞ ቦሌ ላይ ግዳይ ለመጣል ሙሉ ዝግጁ ነው፡፡

በለማ መገርሳ እይታ ግን፣ የጭራቅ አሕመድ ጥፍጥና አማራን ማታልለና ማዘናጋት መቻሉ ሲሆን፣ ይህን ጥፍጥናውን ደግሞ ሙሉ በሙሉ በማጣት ታኝኮ የተጨረሰ አገዳ ሁኗል፡፡  ስለዚህም ለማ መገርሳ በቅርቡ ይተፋዋል፡፡  ጭራቅ አሕመድን ተፈቶ ሲጠለው ደግሞ፣ ቱሲወች (Tutsi) የሁቱወችን (Hutu) መሪ ሃብያሪማናን (Habyarimana) እንደገደሉት አማሮች የኦሮሞወችን መሪ ዐብይ አሕመድን ገደሉት በማለት እልፍ አእላፍ አማሮችን ባንድ ጀምበር በመጨፍጨፍ የኦሮሙማ ፕሮጀክቱን ከግብ ለማድረስ ይጠቅምበታል፡፡  ጭራቅ አሕመድ በለማ መገርሳ ቀጭን ትዕዛዝ ግርማ የሺጥላ ላይ የፈጸመውን፣ ለማ መገርሳ ደግሞ በራሱ በጭራቅ አሕመድ ላይ ይፈጽምበታል፡፡  የጭራቅ አሕመድ መፃኢ ዕጣ በለማ መገርሳ ቀጭን ትእዛዝ በሽመልስ አብዲሳ መረሸን ነው፡፡

ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ሆይ፣ ጭራቅ አሕመድ ግርማ የሺጠላን አስወግዶ ይፋ ጦርነት እንደጀመረብህ፣ ለማ መገርሳም ጭራቅ አሕመድን አስወገዶ ይፋ ጭፍጨፋ ሊጀምርብህ መሆኑን አውቅህ፣ ራስህን ከጭፍጨፋ ለማዳን ማድረግ ያለብህን ሁሉ ከወዲሁ አድርግ፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

2 Comments

  1. ሲጀመር ጭራቅ የሚባል ነገር በዓለም ላይ የለም። ያለው የሰው አውሬ እንጂ! በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1961 ዓ. ም ዪሃንስ አድማሱ ” ጸጥ እንበል” በሚል ግጥሙ የጊዜውን ሰቆቃ ያላዘንላት ያቺ ውድ ሃገር እንደገና በዚሁ ዘመን በ 1961 እውቁ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ” ዝም እንበል” በሚለው ግጥሙ በሚጥሙና በሚስጢራዊ ቃሉ ያነባላት የሃበሻ ምድር ዛሬም ያው ናት። ኸረ ምን ያው ናት የግፈኞች መናህሪያ ሆናለች እንጂ! ችግራችን ሁልጊዜም ትሻልን ትተን ትብስን መቀበላችን ነው። አዎን ወያኔ ከብልጽግና ይሻላል ወይ የሚሉ ይኖራሉ። እሱን የመከራው ገፈታ ቀማሽ ለሆነው ለኢትዮጵያ ህዝብ እተዋለሁ። በእኔ እይታ ግን ሁለቱ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው።
    አንድ የቅርብ ጓደኛዬ ያለውን ሽጦ፤ እቃውን ጠቅሎ ሃገር ቤት ከገባ እንሆ 7 ዓመት ሆነው። አሁን በቅርብ ስንጫወት አይ ምነው ያኔ የመከርከኝን በሰማሁ አሁንስ በቃኝ ልመለስ ነው ቢለኝ እንዴ ይህን ያህል ዘመን ተቀምጠህ ለምን ስለው ለጥቂት ሴኮንዶች ጸጥ ካለ በህዋላ ስማ ወንድሜ አለ ” ከሰው ክፋት የተነሳ ሃገሩን ጠላሁት” በማለት ሌላም ጉዳይ አጫወተኝና በያዝነው ወር ማለቂያ ላይመለስ እንደሚመለስ አጫወተኝ። ይህ የዘርና የክልል ውታፍ ፓለቲካ ውሃ የማይቋጥር ለእኔ እንጂ ለእኛ የማይል የጠባብ ብሄርተኞች የጥቅም ማስጠበቂያ ስልት ነው። ሰፊው ህዝብ ለእነርሱ የገበጣ መጫወቻ ገበታ ነው። ዛሬም ትላንትም የሆነው ይህ ነው። ጠበንጃ አንግቶ ሰርቶ የሚበላና የሚያበላን ህዝብ እየገደሉና እያፈናቀሉ ተራብን ማለት ተንጋሎ መትፋት ነው። ዛሬ በሰሜኑ ህዝባችን ላይ የምናየው መከራ እኛው ያመነጨነው የመከራ ዝናብ ነው። በኢትዮጵያ ምድር የተበደለው የሰው ፍጡር ብቻ ሳይሆን ግዑዟ መሬትና ያቀፈቻቸው እጻዋት፤ ዛፎችና እንስሳዎች ሁሉ ናቸው። በምድሪቱ ጠበንጃ አምላኪዎች እስካልሰከኑ ድረስ ሰላም አይኖርም። መግደል መገዳደል እንደ ጀግንነት ሳይሆን እንደ ውርደት የሚቆጠርበት ጊዜ ካልመጣ ፋታ አናገኝም። በለው ያዘው ጥለፈው አታሳልፈው አባረው እያልን ዝንተ ዓለም ሰው እያስለቀስንና እያስራብን መኖራችን አይቀሬ ነው።
    ብልጽግና አብዷል። ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንደሚሉት ልክ እንደ ነጯ ደ/አፍሪቃ በአዲስ አበባና በሌሎች ክልሎች ” ልዪ ጥቅም” በሚል ሰበብ አፓርታይድን እያስፋፋ ይገኛል። የፓለቲካ መሳከር እንዲህ ነው። በአደባባይ ስለ ሰላምና አንድነት እያወሩ አንድ የሚያረገንን ነገር መናድና ማፍረስ፤ ሰላምን መበጥበጥ። አይ ፓለቲካ! አሁን በአማራ ክልል የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከወያኔ መከራ የተረፈውን ይህን ህዝብ የበለጠ ለማሸማቀቅ ታስቦና ታልሞ በተግባር የዋለ የፓለቲካ ሴራ ነው። እልፎችን በዘርና በቋንቋቸው ዘብጥያ አውርዶ በእንበለ ፍርድ እያሰቃዬ በመድረክ ላይ አጨብጫቢ ፓለቲከኞችና ፍርፋሪ ለቃሚዎች ሲሸነጋገሉ ማየት ያማል። በዚህ ሁሉ ግን የሚጎዳው ነጻ እናወጣሃለን፤ ክልልህ ላንተ ብቻ ነው። ዘርህ ንጽህ ነው። ቋንቋህ ወሸኔ ነው እየተባለ የሚሸነገለው ህዝብ ነው። ዓለም አንድ እየሆነች በመጣችበት በዚህ ዘመን በድንጋይ ዘመን ላይ ቆመው ስለ ዘርና ቋንቋቸው ወይም ስለ እምነታቸው ልዕልና ሌላውን እያጥላሉ የሚናገሩ ሁሉ ድንጋዪች ናቸው። ዛሬ ላይ ልክ ነኝ ብለህ ሰውን የምታመሳቅልበት ነገር ሁሉ ቆይቶ የሚያስለቅስህ ነገር ይሆናል። ለዚያውም በመከራው ጎርፍ ቀድመህ ካልተወሰድክ ነው። እንኳን ይህ ተልካሻው የጠባብ ብሄርተኞች ፓለቲካ ይቅርና 70 ዓመቱ ሙሉ የተለፋበት የያኔው ሶቪየት ህብረት ቁሳዊ ፓለቲካም እሳት የበላው ገለባ ሆኗል። ልብ ያለው የሰው አውሬነቱን በመተው ወደ ራሱ ይመለስ። ለህዝባችን መልካም ለማድረግ ይጣር። ሌላው ሁሉ አሻሮ ፓለቲካ ነው!
    32ኛው የአሜሪካ ፕሬዝደንት Franklin D. Roosevelt በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር። “Lost ground can be regained – lost Time never.” ጊዜን ተመልሶ መገልገል አይቻልም። ጊዜን ተገን አርገን ደሃና መጠጊያ የሌላቸውን መጨፍጨፋችን ይቁም። ያ ካልሆነ ዛሬ በትግራይ በጎንደር በወሎ በምስራቅ ኢትዮጵያ የምናየው ረሃብ ሃገር አቀፍ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም። ሰው አምርቶ ካልኖረ ምን ይበላል? የእህል ክምር የሚያቃጥሉ እብዶች ባሉበት ሃገር እንዴት ረሃብ አይግባ? የቆመ የቀንድ ከብት በጥይት የሚደበድቡ የክልል ሰካራሞች በሚራወጡበት ምድር እንዴት አራሽ አይጠፋ? ሰው ዝም ብሎ በማይኖርበት ሃይማኖት ከመመጻደቅ ይልቅ በምድር ላይ ያለውን እውነት ተመልክቶ ለሌላው አዞኖ ያለውን አካፍሎ በሰላም በመኖር ሌላው በሰላም እንዲኖር መምከርና ማስተማር አስፈላጊ ነው። ከዚህ ውጭ አማራ ተኮር የሆነውን ጥላቻ ወንድሜ መስፍን አረጋ በዝርዝር ያስቀመጠው በመሆኑ መደጋገሙ አስፈላጊ አይሆንም። ግን ብጽግና ሰውን እያጎሳቆለና የኦሮሞን ጠባብ ብሄርተኞች ሰይፍ አስይዞ ሌላውን እያስጨፈጨፈ እኖራለሁ ማለቱ ከታሪክ አለመማር ነው። ሰንብቶ ላየው አወዳደቃቸው የሮም ነው የሚሆነው። በቃኝ!

  2. ይሄ ነገር ለእውነት እየቀረበ መሰለኝ ሽመልስ አብዲሳ አብይን አንገቱን ሊለው ዝግጅት የጨረሰ ይመስላል።
    ቄሮን ማን ሊመራው ነው የሚለው ያስጨንቃል ጁዋር እግሩ ኢትዮጵያን ከረገጠ ኦነግ በጥይት ይፈልጠዋል ሽመልስ አብዲሳም የሸዋ ወጣት ኦሮሞ ቢያገኘው አሳልፎ ለታየ ደንዳ ይሰጠዋል። እነ ሌንጮዎች ዲማ ነገዎ አዲሱ ትውልድ ምን እንደሚያወሩም አይገባቸውም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ፓርላማ ለምን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አራዘመ | የአብኑ አበባው ደሳለው ፓርላማውን አስጨነቀው | አብይ በቀጥታ 200 በላይ ሰዎችን አስገደለ

Next Story

ከምርኮኞች አንደበት – ጎጃም | እጅ የሰጡ አመራሮች ሚስጥሩን አጋለጡ | የአማራ ህዝባዊ ሃይል ፋኖ |

Latest from Blog

እስክንድርን ለማውገዝ በፋኖ ስም የወጣ የመረጃ ቲቪ መግለጫ – መስፍን አረጋ

“በአራቱ ግዛቶች ያሉ የአማራ ፋኖዎች የጋራ አደረጃጀት እየመሰረቱ መሆኑ ይታወቃል” እያሉ፣ “ከአማራ ፋኖ በጎጃም፣ ከአማራ ፋኖ በጎንደር፣ ከአማራ ፋኖ በሸዋና ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ የጋራ መግለጫ” ማለትን ምን ይሉታል? ገና ያልተመሰረተ የጋራ ድርጀት የጋራ መግለጫ እንዴት ያወጣል? መግለጫው በጋራ ወጥቶ ከሆነስ፣ መግለጫውን በጋራ አወጡት የተባሉት ፋኖወች አዛዦች ስማቸውን በመግለጫው ሥር ያልዘረዘሩት ማንን ፈርተው ነው? ባለቤቱ ሾላ በድፍን የሆነ መግለጫ

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም

አቢይ አህመድ ታላቁን አሜሪካንና የተቀሩትን የምዕራብ ካፒታሊስት አገሮችን ማታለል ይችላል ወይ? የአሜሪካ “ብሄራዊ ጥቅምስ ኢትዮጵያ ውስጥ“ እንዴት ይጠበቃል? የአሜሪካ እሴቶችስ(Values) ምንድን ናቸው?

ለመሳይ መኮንና ለተጋባዡ የቀድሞ “ከፍተኛ  ኢትዮጵያዊ ዲፕሎማት” በአሁኑ ወቅት በአሜሪካን የስቴት ዴፓርትሜንት ውስጥ ተቀጥሮ ለሚስራው ኢትዮጵያዊ ሰው የተሰጠ ምላሽ!   ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ግንቦት 19፣ 2016(ግንቦት 27፣ 2024) መሳይ መኮንን በአ.አ በ17.05.2024 ዓ.ም አንድ እሱ  የቀድሞው “ከፍተኛ የኢትዮጵያ

ጎንደር ሞርታሩን እስከ ጄነራሉ ተማረከ | ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | ብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን

ይልማ ምስጢሩን አወጣ “ብርሃኑ ከሸ-ኔ ጋር በድብቅ ይሰራል” | “ፋኖ ከተማውን ቢቆ-ጣ-ጠር ይሻላል” ከንቲባው |“አብይ ክዶናል ለፋኖ እጅ ለመስጠት ዝግጁ ነን” ኮ/ሉ |“በድ-ሮን እንመ-ታችኋለን እጅ እንዳትሰጡ” ጄ/ሉ
Go toTop