ሰማእት ሁን ካህን!

January 23, 2024

3455545454መጣፉ ያዝዛል እንድትገጥም ሰይጣንን፣
ተሕዝብ እንድትነቅለው ነግንገህ ቁንጮውን፣
ለእምነትህ ለአገርህ ሰማእት ሁን ካህን!

ቀጥ ብለህ ተከል ጴጥሮስን አድማሱን፣
ፈለገ ሚካኤል የቴዎፍሎስ ዱካን፣
ቤተክሲያን የሚንድ ጨፍጫፊ ምእመናን፣
የከፋ አምስት ዘመን ዳግም ሲመጣብን፡፡

እንኳንና ሕዝቡ እንዳትገዛ ምድር፣
በግዝት መሀላ በጸሎት ውል እሰር፣
ጭራቅ አገር ወሮ ተኝተህ ላታድር፡፡

ከበሮ ደልቀህ እምቢልታውን ነፍተህ፣
ፀናጽል አፋጭተህ መቋሚያህን ሰብቀህ፣
አዋጅ! አዋጅ! ብለህ ሞረሽ ክተት ጠርተህ፣
ክላ ዲያብሎስ በል ተአገር ሳያጠፋህ!

ሰሜን እስተ ደቡብ ቀጥ ብለህ ቆመህ፣
ተምስራቅ ምዕራብም አግድም ተያይዘህ፣
የወልድን ምልክት መስቀል በአንገት አስረህ፣
እንደ ጉም አብነው ሳጥናኤልን ገፈህ፣
ተመልካች አትሁን ሲጨስ ሲነድ ሕዝብህ፡፡

ዜማውን አዚመህ ቅኔን ተቀኝተህ፣
ጸበልን እረጭተህ በመስቀል ደልዘህ፣
አስወጣ ዲያብሎስ ዛሩን አስጎርተህ፡፡

እግዜር ተሳጥናኤል እንዳልታረቀ አውቀህ፣
ማተብ ታላሰረ ሽምግልና አቁመህ፣
ቃል አባይ ከሀዲን ዳግም ማመን ትተህ፣
መንን ወደ ጫቃ ጥራኝ ፋኖ ብለህ፡፡

ለምተዋት ዓለም ነገ ለማትኖር፣
ሥጋህ አሸንፎ ነፍስ አትግባ ሲኦል፡፡

እግዜርና ታሪክ ጥሪ ሲያቀርቡልህ፣
አደጋ ሲወድቁ አገርና ሕዝብህ፣
እንድታድናቸው በሥጋ በደምህ፣
ሰማእት ሁን ካሀን እንደ ቅድመ አያትህ፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
ታህሳስ ሁለት ሺ አስራ ስድስት ዓ.ም.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

188298
Previous Story

ጳጳሳቱ መንግስት ላይ ”ሆ” ብለው ተነሱ”አሁንስ በጣም አበዛኸው”

188316
Next Story

የዋግኽምራ ሰቆጣ ፋኖዎች አምርረዋል! | ብልጽግና በመርዝ ጋዝ ህዝብ እየገደለ ነው | የጀግናው ፋኖ ቀብር በዚህ መልኩ ደመቀ | ሌላ ድሮን ተከሰከሰ ይልማ የቁም እስረኛ |

Latest from Blog

አትዮጵያ ያን ዕለት

ግም ሞት 20’ 1983 .ዓ.ም. ለህወሀት /ኢህአዴግ ልደት ለኢትዮጵያ እና ለብዙዉ ኢትዮጵያዉያን የዉድቀት ፣ጥልመት እና ሞት ዕለት መሆኑን ያ ለሁለት አሰርተ ዓመታት ከፍተኛ ዕልቂት እና ደም መፋሰስ የነበረበት ጦርነት አዲስ አበባ በደም
Go toTop