ተግባር ቁጥር ፩- DOC-20231220-WA0012.
Fano Drones Defence Squad
ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም
ለፋኖ ታጋዮች ጥንቃቄ ይረዳ ዘንድ
ማህተም ፣ የማይነበብ
ወታደራዊ ድሮን ለመከላከልና ለማምከን ብዙ የተለያዩ በቴክኖሎጂ የተደገፉ ዘዴዎች አሉ ፣ ሆኖም በቴክኖሎጂ እየታገዙ ድሮንን ለመጣል ወይም ተልእኮዋን ለማምከን የሚረዱ መሳሪያዎች በፋኖ እጅ እስከሚደርሱ ድረስ በዩክሬንና በአፍጋኒስታን የነፃነት ታጋዮች እራሳቸውን ከድሮን ጥቃት ለመከላከል እና የጠላትንም ሀይል ለማዳከም የሚያስችል የሚከተሉትን ሚስጥራዊ የማሳሳቻ ዘዴዎች ተጠቅመው ከጠላት የሚሰነዘሩ የድሮን ጥቃቶችን አምክነውበታል ፣
፩) የሚሰሩ የሞባይል ስልኮችን በመሰብሰብ ፣ በተለይም ከዚህ በፊት ለጠላት መረጃ የተጋለጡ ሲም ካርዶችን ወይም ጠላት (መንግስት) የፋኖ ናቸው ብሎ የሚጠረጥራቸው የስልክ ቁጥሮችን (ሲም ካርዶችን) የያዙ የስልክ ቀፎዎችን በዛ ባለ ቁጥር ማዘጋጀት ፣
፪) እነዚህ ለዚህ ተግባር እንዲውል የተሰበሰቡት ስልኮች ባትሪዎቻቸው ሙሉ ሆነው ቻርጅ መደረግ አለባቸው ፣
፫) ጠላት (መንግስት) ቀደም ሲል ፋኖዎች ይኖሩበታል ብሎ በአየር እና በምድር ጭምር የስለላ አሰሳ በሚፈፅምባቸው አካባቢ ወይም በተደጋጋሚ ጠላት በምድርም በመሬትም ጥቃት የሚፈፅምባቸው የፋኖ ወረዳዎች ፣ መንደሮች ወይም አካባቢዎች ለይቶ ለዚህ ግዳጅ እንዲውሉ ማድረግ ፣
፬) የፋኖ ምሽጎች ሊመስሉ በሚችሉ የቋጥኝ ስፍራዎች አካባቢ ከዛፍ የተቆረጡ በሰው ቁመት አካባቢ እርዝመት ያላቸው የግንድ ቁራጮችን በማዘጋጀት የፋኖ ዩኒፎርሞችን በማልበስ ምሽግ፭) ውስጥ የተቀመጡ ፋኖዎች አስመስሎ ማስቀመጥ ፣ በሌላ አነጋገር እውነተኛ የፋኖ ወረዳ ምሽጎች ማስመሰል ፣
፮) ከጥቅም ውጭ የሆኑ ግልጋሎት የሌላቸው መሳሪያዎችን በተዘጋጁት የማሳሳቻ ምሽጎች ውስጥ “ፋኖ ተመስለው” ለተዘጋጁት የግንድ ቁራጭ አሳቻዎች መሳሪያውን አስይዞ በምሽጉ የተዘጋጁ አስመስሎ ማቀናበር ፣
፯) ከፍ ብሎ በተራ ቁጥር ፩ እና ፪ ላይ የተጠቀሱትን ስልኮች ላይ ሞልተው ቻርጅ የተደረጉትን ባትሪዎቻቸውን ከየስልክ ቀፎዎቻቸው ውስጥ መግጠም ። በተራ ቁጥር ፩ ላይ የተገለፁት ስም ካርዶችም በእያንዳንዱ ስልክ ውስጥ መኖራቸውን ማረጋገጥ ፣ የጂ ፒ ኤስ መተግበሪያ መስራቱን (GPS Feature ON) ማረጋገጥ ፣ ቀጥሎም ለአሳቻነት በተሰራው ምሽግ ውስጥ እና አካባቢ ምንም የስልክ ሲግናል ብሎክ መሆን በማይችልበት ስፍራ እየመረጡ ስልኮቹን በተሰባጠረና ዘርዘር ባሉ ስፍረዎች ላይ ማኖር ፣
፱) ከዚህ በሗላ ይህንን ዝግጅት ያደረጉት ፋኖዎች በአስቸኳይ ስፍራውን በፍጥነት ለቀው በርቀት ወደሚገኘው የወገን ወታደራዊ ወረዳና ምሽጎች መሄድ ይኖርባቸዋል ።
ይህንን ተከትሎ ጠላት (መንግስት) በሁለት አይነት መንገድ በሚያደርገው የድሮን አሰሳ ትክክለኛ የፋኖ ተዋጊዎችን የስልክ መስመር ግንኙነት ያገኘ መስሎት ተክለፍልፎ ወደ ተዘጋጀለት ወጥመድ ሊገባ ይችላል ። ድሮኑ የጂ ፒኤስ GPS እና የስልኩን ሲግናል ማሰስ ይችላል ።
በዚህም ረገድ ጠላት አሳቻ በሆነ ኢላማ ላይ በከንቱ የድሮን ተተኳሾቹን ክማባከኑም በላይ ፣ በርቀት ምሽግ ውስጥ የተዘጋጁ የርቀት ተተኳሽ መሳሪያ ያላቸው ድሮኗን ከአየር ላይ መተው ሊጥሏት ይችላሉ ።
ከፍተኛ ጥንቃቄ ፣
በዚህ ፋኖ ባዘጋጀው አሳቻ ምሽግም ሆነ አካባቢ አንድም ፋኖ ወይም የአካባቢው ነዋሪ መገኘት የለበትም ምክነያቱም የደሮን ጥቃት ከኢላማው ውጭ ስቶ ሊያጠቃ ስለሚችል፣ ከዚህ አካባቢ ፈጥኖ ርቆ መሄድ ቸል የማይባል የወታደራዊ ደህንነት ግዴታ ይሆናል ።
ድል ለዐማራ ፋኖ !