December 20, 2023
20 mins read

የድሮን ጥቃትን ለመከላከል – ተግባር ቁጥር ፪

ተግባር ቁጥር ፪ – DOC-20231220-WA0011.

ፋኖ ድሮን አምካኝ ብርጌድ
Fano Drones Defence Squad

ታህሳስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

8779799oykየአብይ አህመድ አሊ የኦሮሙማ መንግስት ከሰሞኑ የታጠቀው ዘመናዊውን የቱርክ ድሮን Bayraktar TB3

መግቢያ

ድሮን ሰው አልባ በሰማይ ላይ የሚበር መንኮራኩር ነው ፣ ፈሩንጆች UAV – Unmanned Aerial Vehicle or UAS – Unmanned Aerial Systems ብለው ይጠሩታል ።

ድሮንን ለወታደራዊ ግልጋሎት በጦርነት ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀመችው አሜሪካ ከአፍጋኒስታን ጋር እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከ1999 እስከ 2021 ባደረገችው ጦርነት ሲሆን ፣ ዛሬ ደግሞ ራሽያና ዩክሬን በሚያደርጉት ጦርነት ላይ ሁለቱም ወገኖች በሰፊው እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ። እስራኤልም የፍልስጤም አማፅያንን ለማጥቃት ከፍተኛ የድሮን ጥቃት እየፈፀመች ይገኛል ።

ከእነዚህ ከፍ ብለው ከተዘረዘሩት ሀያላን አገራት ውጪ በኢትዮጵያ በአብይ አህመድ አሊ የሚመራው የኦሮሙማው ፈላጭ ቆራጭ መንግስት በዐማራው ህዝብ ላይ ሰፊ የድሮን ጭፍጨፋ እያካሄደ ይገኛል። በአፍሪካ ውስጥ በራሱ ሠላማዊ ህዝብ ላይ ወታደራዊ ድሮን የተጠቀመ የመጀመሪያው መሪ አብይ አህመድ አሊ ነው ። ኢትዮጵያም ወታደራዊ ድሮንን በጦርነት ላይ መጠቀም የያዘች ብቸኛዋ የአፍሪካ አገር ነች ።

አብይ አህመድ አሊ በአረብ አገሮች በአረብ ኤሚሬትስ ፣ በቱርክና በኢራን እየተደገፈ በሰላማዊው የዐማራ ህዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት እያደረሰ ከመሆኑም በላይ ኢትዮጽያን እያፈራረሰ ይገኛል ። እዚህ ላይ ልብ መባል የሚገባው ታሪክ እራሱን ይደግማል እንዲሉ ኢትዮጵያ በግራኝ አህመድ ጦርነት ስትወረር (1529 – 1543 እንደ አውሮፓ አቆጣጠር) ፣ የጦርነቱን የሀይል ሚዛን የቀየረው የቱርክ ወታደሮችና የሰለጠኑ ተዋጊ ፈረሰኞች (Turkish cavalry) ከግራኝ አህመድ ጦር ጋር ወግነው አብረው ከመሰለፋቸውም በላይ ፣ ይዘውት የመጡት ተጎታች መድፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር የተተኮሰው

በሸዋ የአማራ ህዝብ ላይ ነው ። ተከታትሎም ወራሪው የግራኝ አህመድና የቱርክ ጦር የተጠቀሙት የመድፍ ተኮስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ፣ ኢትዮጵያውያንም ይህንን የሚቋቃሙበት ተተኳሽ መድፍ በወቅቱ ስላልነበራቸው ፣ ወራሪው የጠላት ጦር በህብና በአገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል። ከ14 አመታት የስቃይና የእልቂት ጭፍጨፋዎች በሗላ የግራኝ አህመድ ጦር ቢሸነፍም ፣ ያስከተለው ጉዳት ከፍተኛ ስለነበር ፣ በተዳከመው የዐማራ ህዝብ ላይ የግራኝን ወረራ እግር ተግር ተከትሎ የመጣው የኦሮሞ ፍልሰት
እየተስፋፋ የዐማራውን አፅመርስት መሬቶችና ግዛቶች በመውረር ፣ ሌሎችንም ብሄረሰቦች በማጥፋት በወረራ ለያዛቸው አገሮች ስም እየቀየረ የራሱን ስያሜ እየሰጠ በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ የታሪክና የብሄረሰቦችን ማንነት የጨፈለቀ ክስተት ነበር ።

ዛሬ የአብይ አህመድ አሊ የኦሮሙማ መንግስት በዐማራው ላይ ከዛሬ 500 አመታት በፊት የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት ጦርነት ትምህርቶች ሳሳይነት ባለው መልኩ ከኢትዮጵያ  ቋሚ ጠላቶች የአረብ አገራት በሚያግበሰብሰው የጦር መሳሪያና የድሮን ክምችት የዐማራን ህዝብ ዘር ከምድረገፅ ለማጥፋት ቆርጦ ተነስቷል። እነዚህ ከታሪክ መማር ያልቻሉ ጠባብ ዘረኛ ቡድንተኞች ያልተገነዘቡት ነገር ቢኖር ህዝባዊ ሀይልን ምንም ወታደራዊ ትጥቅ ሊያቆመው አይችልም ። የቬትናም የነፃነትብታጋዮችን የአሜሪካ ዘመናዊ መሳሪያ ሊያቆማቸው አልቻለም ።

በቅርቡም አሜሪካ እና እንግሊዝ በአፍጋኑስታን ህዝብ ላይ የከፈቱት የድሮን ጥቃት የረባ ወታደራዊ ድል አላስገኘላቸውም ፣ ይልቅስ በውርደት ተሸንፈው አፍጋኒስታንን ለቀው መውጣት ችለዋል ።

የዐማራ ህዝብና የነፃነቱ ታጋይ ፋኖ ከአብይ አህመድ አሊ የወራሪ የኦሮሞ ጦር ከሚሰነዘርበት የድሮን ጥቃቶች ለመከላከል የሚከተሉትን ዝግጅቶችና ጥንቃቄዎች ማድረግ ይኖርበታል ፣

፩ኛ) ህዝባዊ ማህበራዊ ጥንቃቄዎች

፪ኛ) ድሮንን ለመከላከል መደረግ ያለባቸው የቴክኒክ ዝግጅቶችና አደረጃጀቶች

 

የዐማራ ማህበረሰብ በሲቭሎች ላይ ከሚተኮስ ድሮን ራሱን እንዴት መጠበቅ ይችላል?

  • ወታደራዊ ድሮን ምንድን ነው?በአጠቃላይ ብዙ የድሮን አይነቶች አሉ፤ ለማህበረሰብ ጠቀሜታ የሚያገለግሉና ለጦርነት የሚያገለግሉ ተብለው ይመደባሉ። ከዚህ በታች የሚገለጹት በህዝብ ላይ ጉዳት የሚያመጡት ወታደራዊ ድሮኖች ብቻ ናቸው።

ወታደራዊ ድሮን የአንስተኛ አውሮፕላን ቅርጽ ያለው ፣ ያለ አብራሪ ሰው (ፓይለት) በአየር ላይ በራሪ አካል ነው። ድሮን እንዲበር የኃይል ምንጭ ያስፈልገዋል። የድሮን አንቀሳቃሽ የኃይል ምንጮች እንደክብደቱ መጠን በሊቲየም ባትሪ ወይም በነዳጅ የሚሠራ አንጂን ናቸው። ድሮን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ (ካሚራ፣ ኮምፒውተር፣ ጂፒኢስ፣ የሬዲዮ ሞገድ መገናኛ፣ልዩ ልዩ መጠቋሚዎች (ሴንሰሮች) የተዋቀረ የዘመኑን ጦርነት የለወጠ በተለይም እግረኛ ወታደር አቅም ሲያጣ የሚያገለግል ዘመናዊ ወታደራዊ መሳሪያ ነው።

ድሮን በውስጡ የተቀመጠ ሰው አይኑረው እንጂ ሩቅ ጣቢያ ላይ ሆኖ የተቀመጠ የድሮን መቆጣጠርያ ጣቢያ ውስጥ የሚሠሩ የሰለጠኑ ሰዎች የሚቆጣጠሩት፣ ወደፈለጉት አቅጣጫ የሚዘውሩት፣ ጉዞውንና ፍጥነቱን የሚከታተሉት፣ እንዲሠራ ለሚፈልጉት ተልእኮ የሚያዙት የጦር መሳሪያ ተሸካሚና ተኳሽ ዘመናዊ

 

  • ድሮን ለምን አገልግሎት ይውላል?

ወታደራዊ ድሮን የሚሠራቸው ተግባሮች፡ ለጣቢያው የቅኝት መረጃዎችን ማስተላለፍ፣ የመልክአ ምደር አቀማምጥ ምስል ማንሳት፣

የከተማ አሰፋፈር፣ ኢንዱስትሪና መሰረተ ልማቶችን ቦታና አቀማመጥ ማጥናት፣ የገጠር ማህበረሰብ አሠፋፈርና እንቅስቃሴ ማጥናት፣ ቤተ እምነቶችን ፣ ብዙ ህዝብ የሚሰነሰብበትን አካባቢና የሁኒታ መረጃ ማስተላለፍ፣ የፋኖን እንቅስቃሴና መናኻሪያ፣ የትጥቅ አቋሙን አሰሳ ወዝተ ማድረግ ፣

የሚፈለጉ ቦታዎች ካርታ መገናኛ ነጥቦች (ኬንትሮስና ኬክሮስ መስቀልኛ አድራሻ) ምስል ጨምሮ ወደ ተቆጣጣሪ ጣቢያው ያስተላልፋል። የድሮን መቆጣጠሪያ ጣቢያ ውስጥ የሚሠሩ ባለሙያዎች መረጃዎቹን ተቀብለው ያቀነባብራሉ። የሚፈልጉትን መረጃ የኮሚውተር መርሀግብር ሰርተውለት ለትእዛዝ ያዘጋጁታል።

 

3)  ጥቃት ለመፈጸም የሚከናወኑ ሂደቶች እንዴት;

ከላይ የተጠቀሰት መረጃዎች ከተሰበሰቡና ከተቀነባበሩ በኋላ ኢላማው ይመረጣል፣ ኢላማው አካባቢ ጂፒኤስና መገናኛ የያዙ አስተኳሾች ተለኮ ተቀብለው አስቀድመው ይሰማራሉ፣ የጥቃት ዝግጂቱ ይጠናቀቃል፣ ሥልጣን ያለው ሀላፊ ጥቃት እንዲፈጸም ያጽድቃል። ትእዛዝም ያስተላልፋል፣ ወታደራዊ ድሮን ኢላማዎችን ለማጥቃት ከመሰማራቱ በፊት ቦምብ ወይም ሚሳኤል በክንፎቹ የታችኛው ከፍል ይጫኑለታል፣ የጥቃት ስምሪት በተፈለገ ጊዜ ማዘዣ ጣቢያ ላይ ያሉ ተቆጣጣርዎች እያዘዙት፣ ኢላማቸው ያለበት አካባቢ ጂፒኤስ የያዘ አስተኳሽ ሲግናል (ምልክት) እየሰጠ ጥቃት ያደርሳል።

በዚህ መንገድ አስቀድሞ በተጠና ቦታ፣ ለምሳሌ የሰው መኖርያ ቤት ለማጥቃት ከተፈለገ እየበረረ እንዲደርስና እንዲያጠቃ የትእዛዝ መርሀግብር እየተሰጠው፣ ፍጥነቱን እየተቆጣጠሩት አደጋ ለመፍጠር ይጠቀሙበታል።

 

  • ለጥቃት ምቹ የሆኑ ማህበራዊ ቦታዎች፣ ሁኔታዎችና እንቅስቃሴዎች፣

የድሮን ጥቃት የሚፈጸምባቸው ቦታዎችና ሁኔታዎች፣

  • ከለላ በሌለው መንገድ ተሰብስቦ መጓዝ፣
  • ወደቤተ እምነቶች በአንድነት መጓዝ፣
  • ወደገበያ በአንድ ላይ መጓዝ፣
  • ወደ እርሻ(ማሳ) ቦታ ተሰብስቦ መጓዝ፣
  • የታጨደና ለውቂያ የተሰበሰበ እህል በአንድ አካባቢ በብዛት ከምሮ ማቆየት፣
  • የቀብር ሽኝት ለማድረግ ተሰብስቦ መጓዝ፣
  • በብዛት በግልጽም ሆነ በተሸፈነ መኪና መጓዝ፣
  • ተማሪዎች በቡድን ተሰብስበው መጓዝ፣
  • በአንድ ቦታ ላይ በብዛት ተሰብስቦ መገኘት፣
  • ምእመናን በቤተ እምነት ቅጥር ወይም አካባቢ የአምልኮ ሥርአት ለመፈጸም በብዛት መሰብሰብ፣ ብዙ ጊዜ መቆየት፣
  • ገብያ በሚውልበት ቀን ብዙ ሀዝብ መሰብሰብ፣
  • ቀብር ሽኝት ለማድረግ ቀብር ቦት ላይ በብዛት መገኘት፣
  • የሰብል ማሳ ላይ ለእርሻ፣ ለአረም፣ ሰብል ለመሰብሰብ በብዛት መሰማራት፣
  • በትምሀርት ቤቶች፣ በሀኪም ቤቶች ተሰብስቦ መገኘት፣
  • ለሰርግ በብዛት ተሰብስቦ መገኘት፣
  • ከሩቅ የሚታዩ አልባሳት ለብሶ መሰብሰብ፣
  • ትምሀርት ቤት ውስጥ ተማሪዎች ተሰብስበው መገኘት፣
  • የህክምና ባለሙያዎች፣ ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው በጤና ተቋም ውስጥ ተሰብስቦ መገኘት፣
  • በጦርነት ቀጠና ውስጥ መገኘት፣
  • “መንግሥት”ነኝ የሚባለው ጠላት የዘር ማጥፋት ለማድረግ ቆርጦ መገኘቱ
  • ጅፒኤስ የያዙ አካባቢውን ተመሳስለው የሚኖሩ የጠላት ድሮን አስተኳሽች ወይም አማራ ሆነው በገንዘብ የተገዙ ባንዳዎች፣
  • ድሮን መቼ ጥቃት እንድሚጥል የመረጃ እጥረት ወይም ክፍተት
  • የድሮን ጥቃት ለመቀነስ የሚጠቅሙ ጥንቃቄዎች፣
  • ለስለላ የሚላኩትን ጽጉረ ልውጦች ሁልጊዜም ነቅቶ መከታተልና ለፋኖ ማስተላለፍ፣
  • በተለይ በቤተክርስቲያን ወይም መስጂድ አካባቢ ቄስ መስለው ደብተራ መስለው፣ ሙስሊም መስለው የሚመጡትን መለየት፣
  • በጦርነት ወቅት እንደድሮው በእንግድነት አለመቀበል፣
  • የተራበ ኮሳሳ ቢመስል እንኳ ሳይመረመር፣ አካሉ ወስጥ የተቀመጠ ጂፒኤስ፣ ወይም ከአልባሳቱ ውስጥ የተደበቀ መገናኛ፣ መሳሪያም ይሁን ጂፒኤስ፣ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ስልክ ወዘተ በጥብቅ መፈተሽ፣
  • የተለመዱ መሰበሰቢያ ቦታዎችን አለማዘውተር፣ አለመገኘት፣
  • በቡደን መጓዝ ማቆም፣ የግድ ከሆነ በጣም ተራርቆ መጓዝ፣
  • ነጭ ወይም ከሩቅ የሚታዩ ቀለም ያላቸውን ልብሶች አለመልበስ፣
  • የእምነት ስርአት የሚደርግባቸውን የተለመዱ ቦታዎች መለወጥ፣
  • የማይታወቁ ድብቅ የሆኑ የማደሪያ ቦትዎችን በስውር መጠቀም፣
  • ማሀበረሰቡ ውስጥ ማን እንደሚገባና እንደሚወጣ መቆጣጠር መግቢያ መውጫ በሮች ላይ ጠባቂዎች ማስቀመጥ፣
  • በመህር ጊዜ ሰብልን በፍጥነት ሰብስቦ ከጠላት እይታ ውጭ ማድረግ፣
  • የህክምና ባለሙያ እጥረት ቢኖርም በየአካባው ተጓጓዥ ሀኪሞችን ከጥበቃ ጋር ማሰማራት፣
  • ሰላም በሌለበት አካባቢ ትምህርት ቤቶች በሚስጥር የሚሰሩበት ዘዴ መፍጠር፣
  • የቤተሰብ ውድ እቃዎችንና ለምግብ የሚያገለግሉ የበስለም ይሁን ጥሬ ከቤት አርቆ በተሰወረ ቦታ እንዳይበላሽ አድርጎ በከርሰ ምድር ውስጥ ማስቀመጥ ፣
  • ድሮን ጥቃት ከማድረጉ በፊት ቅኝት ማድረጉን በንቃት መከታተል፣ መረጃውን ልሁሉም ማዳረስ፣

በኢትዮጵያ የአብይ አህመድ አሊ መንግስት የታጠቃቸው የድሮን አይነቶችና የድሮን መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች

8779799oykrrrIranian Mohajer-6 Drones Spotted In Ethiopia

ሞሀጀር – 6 በመባል የሚጠራው የኢራን ድሮን በአፋር ሳማራ ኤርፖርት ሜዳ ላይ አርፎ ይታያል ። በስተጎኑ የሚታየው መኪና (ትራክ) የድሮን መቆጣጠሪያና ማስተኮሻ መሳሪያዎችን የታጠቀ ነው።

Abiy at Samara airport ntitledeeee

አብይ አህመድ አሊ ፣ ማርሻል ብርሀን ጁላ ፣ የአፋር ክልሉ ፕሬዝዳንትና ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ሳማራ ኤርፖርት የሚገኘውን የድሮን መቆጣጠሪያ ጣቢያ(ግራውንድ ኮንትሮል ስቴሽን) በጉብኝት ላይ ሳሉ ፣

Abiy at Samara airport ntitledeeeeqq

ሳማራ ኤርፖርት  የሳተላይት ፎቶግራፍ (ኢሜጅ)

Abiy at Samara airport ntitledeeeeqqrr

በአፋር ሳማራ ኤርፖርት የሚገኘው የድሮን መቆጣሪያ በደረጃው ፪ኛ ሲሆን ፣ በ፩ኛ ደረጃ ያለው ደብረዘይት አየር ኃይል ውስጥ ሀረር ሜዳ የሚገኝው የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ነው። አብይ አህመድ አሊና ባለስልጣናቱ ተንቀሳቃሹን (ትራክ) የድሮን መቆጣጠሪያ Ground control station ከመጎብኘታቸው በፊትማብራሪያ ሲሰጣቸው ባለስልጣናቱ በተንቀሳቃሹ የድሮን መቆጣጠሪያው ጣቢያው (መኪናው) ውስጥ ያለውን የኮምፒዩተርና የኤሌክትሮኒክስ አደረጃጀቶችና ስለ አጠቃቀማቸው ማብራሪያ ሲሰጣቸው

ክፍል ፩

5utitittiti

ክፍል ፪

tu86uuyuyyu

ኢትዮጵያ ያሏት የወታደራዊ ድሮን አይነቶች ፣

List of Ethiopian military drones (UAV)

  • ዘመናዊውን የቱርክ ድሮንBayraktar TB3
  • Iranian-made Mohajer-6 UCAV
  • Turkish Bayraktar TB2
  • Chines Wing Loong drones
  • Israeli Aerostar UAS.
  • Boomerang catapult-launched UAV (Israel manufacturer
  • SpyLite tactical electric mini UAS (Cyient Solutions & Systems. Joint venture between Cyient and Israel based BlueBird Aero Systems, provides UAS- based intelligence)
  • WanderB mini-UAS (Israel)
  • CASC CH-4 drones (China)
  • TAI Aerostar (Israel)
  • TAI Anka-S. (Turkish)

 

ድሮንን ለማምከን የሚተገበር ቴክኖሎጂ በአራት መሰረታዊ ክፍሎች ይዋቀራል ፣

THE MANY WAYS TO KILL A DRONE

We can break counter-UAV technology into four broad categories:

  1. Tracking
  2. Jamming
  3. Kinetic
  4. Hybrid, hijacking, and cyber approaches

በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ተግባራዊ ቴክኒካል ሰነድ በሚቀጥለው ተግባር ቁጥር ፫ ላይ በሠፊው ይቀርባል ።

ድል ለፋኖ !

ድል ለዐማራ ህዝብ !

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/ ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ ላይ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
Go toTop