ጥንት፣
አይደለም ውጊያችን ከስጋና ከደም
ይልቅስ እንጂ ነው ከሰማይ ኃያላት፣
በመንፈስ ቅኝት
በሰው ውስጥ አድረው በሚወከሉበት፡፡
ኦ ኤርት-ራ!
ለፈረኦን የፀሐይ አምላክ
የአይኑ ብሌን የአምላክ ራ፤
የእግዜር ውሃ ፍርድ መገለጫ
ግፉአን የወደቁብሽ፣
የራማ ጩኸት ምላሽ
ቀንበር ሰባሪ አንቺ ነሸ፡፡
ቀይ ባህር፣
አፈ ታሪኩ ሲነገር
ደም የመምሰሉ ምስጥር
ነበር አሉ፣
ከሰማይ በወረደ የደም ጠብታ
ተንጸባረቆ ሲታይ ከባህር፡፡አሁን፣
የራስን ምስል ፍለጋ
ከጥቁር ውሃ መስታወት ስር፣
እንዲህ እንዲያ ነው እያሉ
ይጠቅሳሉ ከአፈ ታሪክ ስንክሳር፤
አማረህ አሉ ዘንድሮ
ልጎርፍበት ውቂያኖስ ባህሩን፣
ልትሰለቀጥ እንደሆን እንጂ
አትችለውም ግብረመልሱን፡፡
በምረቃና ፈረስ ጋላቢ
አንተ ጉራብቻ፣ጉራብቻ፣
የመከር ወራት ውቂያ
ትበላለህ ቀይ ኢሬቻ፡፡
ተፈጥሯዊ መቼት፣
አይ አዋሽ፤ምነው ጨነገፍክ
ሳትደርስ ከእናት ውሃ መህፀን፣
አባይን መምሰል አታስብ
አልቻልክም ዋቢሸበሌ፣ ገናሌን መሆን፡፡
ከእናት ምድር እንብርት ብትነሳም
ታጁራ እንደናፈቀህ፣አሰብም እንደራቀህ፣
የእትብት ገመድህ አጥሮ
አፋር አቤ ሃይቅ ላይ፣ እንደተቀበርክ ትኖራለህ፡፡
አስቻለው ከበደ አበበ
ሜትሮ ቫንኩቨር ካናዳ