በሱ ትዕዛዝ የስንት ኢትዮጵያዊ ህይወት ተቀጥፏል….?!
ስንቱ አካለ ጎዶሎ ሆኗል…?!
ስንቱ ከሀገር ተሰዷል….?!
ስንቱስ ተኮላሽቷል….?!
ከሱ የባሰ አውሬ መንበሩን እንደሚጨብጥ ሳናውቅ ቢያንስ ወይ አልቻልኩም ብሎ….ካልሆነም ግፍ በቃኝ….! የደም እንጀራ መብላት በቃኝ….! ብሎ ስልጣኑን በፍቃደኛነት ለቋል ብለን ይቅር ባንል ለዘብ ስንልለት ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ ቅዱስ ቅዱስ ያጫውተው ጀመር መቼም ተዓምር አያልቅ!!!
ስማኝ ቅዱስ ወንጀለኛው ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ በምትምልበት በኢፌዲሪ ህገ መንግስት እንኳን የሰራኸው ወንጀል ይቅርታም…ምህረትም የማያሰጥ ነውና በዚሁ በምድር ላይ ፍትህ የክብር ስፍራዋን አግኝታ ፀጉርህን ተላጭተህ ወህኒ እስክትወርድባት እስከዚያች ቀን ድረስ አንተም ፈንጭ!!!
ጊዜ ለኩሉ!!!
የምትዘባበትበት እግዚአብሔር መቼም ፍትህን ትቶ….ከግፏዐን እንባ አይኑን ሸሽጎና ከአመፀኞች ጋር ተባቡሮ ነው እንጂ በደም በጨቀየው ባንተ ስሙ ሲጠራ መዐት የማያወርደው….. የእውነትን ፀሀይ በሚያወጣ…..ፍትህ ክንዱ የሆነችው እግዚአብሔር ” አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው:: ንፁህ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው:: ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው” ሲል በያዕቆብ መልዕክት ምዕ.1÷26-27 በግልፅ አስቀምጦታል::
ኃይለ ማሪያም ደሳለኝ አምልኮ ዝላይ እና ጭፈራ….ልባዊ እምነት ደግሞ ተግባርን የሚጠይቅ መሆኑን እግረ መንገዱን “እንታነፃለን እንጂ አዲስ መሰረት አንመሰርትም” ባለው ቅዱሱ መፅሀፍ ባለውና ከተፃፈው አትለፍ ባለው መሰረት ላይ ታንፆ ወላጅ አልባ ያደረጋቸው በርካታ ህፃናትና ያለጧሪ ቀባሪ ያስቀራቸውን ስንት ባልቴቶችን ይቅርታ ሲጠይቅና ሲያስጠይቅ በኖረና ለዝላይና ጭፈራ ጊዜ በጠበበው ነበር!!!
“እምነት ይሸተኛል” ይላል ደግሞ ነውረኛ!!! እምነት የልብና የድርጊት ጉዳይ እንጂ የስሜት ህዋሳት አንዱ በሆነው በአፍንጫ የሚሸተት ነገር እንዳልሆነ የማያውቅ ያልዳነ አዳኝነት ነው!!!
“እምነት እምነት ይሰማኛል” የሚለው ሊሰማህ የሚገባው የንፁኃል ዋይታ….ራሄል ስለልጆቿ ያለቀሰችው ለቅሶና….ረሀብ አንጀታቸው አጥፎት “ዋይ…ዋይ” የሚሉ የረሀብን ጉንፋን የሚስሉ ህፃናትን ነበር ቢያድልህ ኖሮ!!!
ባይሆን የሚሸተው አፍስሷ ምድሪቷን ያከረፋው የንፁኃን ደም ነው!!!
ተላላኪ ነበርኩ የሚሉትን የመርሳት እና የመተው አባዜአችን አንዱ ችግር የረሳን መስሏቸው ደግሞ ተመልሰው ሲዘሉብን እና ሲጨፍሩብን ማየታችን ነው!!!
አንድ መታወስ ያለበት ሀቅ ላለፏት 10 አመታት ገዥዎቻችን ፓስተር ነን በሚሉ ቅዱስ ነብሰ ገዳዮች እንደሆነ ነው!!!
የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ፍርድ ደጃቸውን ማንኳኳቱ የማይቀር ነው!!!
ይኼው የሚዘባበቱበት መፅሐፍ “ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳል….ንፋስ የሚዘራ አውሎ ንፋስ ያጭዳል….! በስጋ የሚዘራ በመበስበስ ያጭዳል” ተብሎ ተፅፏልና እስከዛው ቅዱስ ነብሰ ገዳዮች በደም ሰክረው ይጨፍሩብን!!!
ጊዜ ለኩሉ!!!