የኢትዮጵያውያን አንድነት ለሰላምና ለዕድገት ለኢትዮጵያ መግልጫ 

የኢትዮጵያውያን አንድነት ለሰላምና ለዕድገት ለኢትዮጵያ

UNITED ETHIOPIANS FOR PEACE AND DEVELOPMENT FOR ETHIOPIA

 

የአላማ መግልጫ (CONCEPT NOTE)

 

ከሁሉ በፊት ከመጀመሪያ ጀምሮ ይህ አገራዊ ህብረት ተጸንሶ እንዲወለድና እዚህ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላደረጉት ለፕሮፈሰር ሲሳይ አሰፋ፣ ለፕሮፈፈር ብርሃኑ መንግስቱና ለአቶ ብርሃኑ ውርሰኖ ትልቅ አድናቆትና ምስጋና እናቀርባለን፡፡

 

ሰለሕብረቱና ስለመሪዎቹ፡

 

  • ይህ ሕብረት የፖለቲካ ፓርቲ አይደልም፡፤ ወይም ፕሮፈሽናል ሕብረት(Association) አይደልም፡፡፤ ማንኛውንም የፖለቲካ ፖርቲ አይውክልም፣፤ በመደገፍም አይቆምም፤ አቋሙ ለአገራችን ለኢትዮጵና ለሕዝቡዋ የሚጠቅመውን ለመሥራት መርሆ ላይ ብቻ ተመሠርተ ነው፡፡

 

  • ይህ ሕብረት ማንም ኢትዮጵያዊ የዚህን ሕብረት አላማ ለማሳካት በበጎ ፈቃድ የሚሳተፍበትና ገምቢ ሃሳብ የሚሰጥበት ነው።

 

  • የዚህ ሕብረት አባላት ክየትኛውም ሙያ ዘርፍ ሲሆኑ የአገራችንን የጎሳ ግጭት ለመፍታትና በልማትም ለመሳተፍ በማሰብ የተሰባሰብን ሲሆን ሁሉም አባላት የሕብረቱን አላማ ለማሳካት ይጥራሉ።

 

  • የሕብረቱ አላማና ግቦች ሶስት ናቸው፡

 

ሀ) ኢትዮጵያውያንን በተለይም በውጭ አገር የሚኖሩትን ለአገራቸው ኢትዮጵያ በሙያቸውና አቅም በሚፈቅደው መሰረት አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ማስባስብና ማረጋገጥ፣

ለ) ባገራችን ውስጥ ግጭቶች ያሉበትን አካባቢዎች ተክታትሎ በጦርነት ሳይሆን በሰላማዊ መንገድ በማሥታረቅ ባገረቱዋ ሰላም እንዲመጣ ማድረግና መክታትል፣

ሐ) አገራችንን አሁን ካለችበት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ችግሮች ለማላቀቅ በየጊዜው ስልጣን ላይ ካለው መንግሥት ጋር በመነጋገር ክዚህ በታች በ(መ) በተገለጹት ትምሪታዊ ልምድ መሰረት በአገሪቷና በሕዝቧ ላይ ለዘምናት የደረሰው በደል እንዳይደገም ለማረጋገጥ ከመንግስትና ክሕዝቡ ጋር መሥራት።

 

ለእነዚህ ዓላማዎች እንድንሰባሰብ ያደረጉን ምክንያቶች የሚከትሉት ናቸው።

 

ልንማር የሚገባቸዉ የታሪክ ማስረጃዎችና የወደፊት ተግባራት ጠቋሚነት

 

መግቢያ፡ አገራችን ኢትዮጵያ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አስትዋጽዖ ያላትና ነጻነቷን ለዘመናት ያላስደፈረች አገር ስትሆን በዚህም ለሁሉም ጥቁር ሕዝብ መኩሪያ ስትሆን በተለይ ለገዛ ልጆቿ ለኢትዮጵያውያን ይህ ዕውነት ነው፡፤ ይሁን እንጂ ሕዝባችን ለዘመናት በጎሳ በሃይማኖት በቋንቋ በመከፋፈል መጨረሻም በዘር አካባቢውን በመካፈፍል ላይ ያተኮረ የፖለቲካና የአገር አስተዳደር ሥርዓት በመመሰሩትና ህዝብ በነጻነት የአገር መሪዎችን የሚመርጥበትና የተመረጡትም ጥፋት ክሠሩ በህግ የሚጠየቁበት ሥርዓት ለዘመናት በኣገራችን ያልነበረ በመሆኑ ለዘመናት ጉቦኝነት ስርቆት ማጭበርበር ስሮአት ዓልበኛነት ነግሶ ሕዝብ ሲሰቃይ ንብረት ሲወድም የሕዝቡን ሃዘንና ብሶት ምክያት በማድረግ ስልጣን ፈላጊዎች ሰላማዊ የአገዛዝ ስልጣን ሽግግርና የስረዓት ለውጥ ሳያደርጉ በጦር መሳሪያ ሃይል በሥልጣን ላይ የነበሩት ክሥልጣን እየተባረሩ እየታሰሩና እየተገደሉ ንብረቶቻቸውም እየተዘረፈ ለሰላምና ለሃገር እድገት ሳይውል መቅረቱ ማንም ኢትዮጵያዊ የሚያቀዉ ነው። ለዚህም የሚከተሉት ማስረጃዎች ናቸው፡፡

 

) ንጉሱ ኃይለ ሥላስ አገዛዝ ዘምን፡ እ አ አ 1908 እስከ 1974

 

ንጉሳችን ኃይለ ስላሴ በጊዘው በነበራቸው ንቃተ ህሊና ለህገራችን ዕድገት በትምህርት ለማህበራዊ ዕድገትና ለኢኮኖሚው ዕድገት ክፍተኛ አስተዋጥጽዖ አድርገው እንደነበር የሚካድ አይደለም። ይህ ሆኖ እያለ ምንም እንኳን በጊዜው ሕዝብ የምክር ቤት አባላትን የሚመርጥ የነበረ ቢሆንም የሴነት አባላት በራሳቸው በንጉሡ ይመረጡ ነበር፤ ካብነኔት አባሎቻቸውም እንዲሁ፡፡ ለምከር ቤት በሕዝብ ለመመረጥ ዕጩ ሆኖ ለመቅረብ $850 ኣሜሪካ ዶላር የመሬት ይዞታ ወይም $1,700 የአሜሪካ ዶላር ተንቀሳቃሽ ንብረት ያለው ሰው መሆን ነበረበት፡፡ ለማንም ኢትዮጵዊ አልነበረም ማለት ነው፡፡ ስለሆንም፡

 

  • ስልጣናቸው የጊዜ ገደብ አልነበረውም። የሚሾሟቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ሴነተሮችና ሚኒስትሮቻቸው የስልጣን ጊዜ ገደብ አልነበረውም። በንጉሡ የሚመሩጡት ለኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ለንጉሡ ተጠሪ ነብሩ። ክዚህ የተነሳ ሕዝቡም መሪውን ለመቀየር ነጻነት አልነበረውም፡፡ ስልሆነም ባለስልጣናትና ከእነርሱ ጋር ቅርበት ላላቸው ህዝቡን ለመበዝበዝ ምቹ ሁኔታንና ጊዜን ፈጠረላቸው።

 

  • ከተመረጡት ውስጥ ህግን የሚጥስ ወንጀለኛን ህዝቡ ተጠያቂ የሚያደርገበት ሰርአት አለነበረም።

 

  • ጠቅላይ ሚኒስትሩና ምክትከል ጠ/ሚኒስትሩም በህዝብ የሚመረጡ አልነበሩም ለሕዝብም ተጠያቂ ያሚሆኑበት ስራት አልነበረም፡፡

 

  • እነዚህ የመንግስት ተሿሚዎች ባለስልጣናትና ተመራጮች ከባለሃብቶች ጋር በህዝቡ ላይ በሚያደርሱት የአስተዳደር በደልና የአርሶ አደሩን መሬት በመዝረፍ በሕዝቡ ላይ ባደረሱት ሰቆቃ ምክያት መሬት ለአራሹ ንቅናቄ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተነስቶ እ ኢ አ የካቲት1974 ንቅናቄ ደርግ ስልጣን ለመያዘ ሁኔታውን ተጠቀመ። ለዚህ ምክንያቶቹ ሲጠቃለሉ ሦስት ናቸው።
ተጨማሪ ያንብቡ:  "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" አማራ ወጣቶች ማህበር

 

አንደኛው እንደ ኢንግሊዝ መንግስትና ሌሎችም ተመሳሳይ አገሮች የንጉሡ ስልጣን ገደብና የሌሎች ባለልሥልጣናት የስልጣን ዘመን በጊዜ የተወሰነ አለመሆኑ።

ሁለተኛው ሕዝብ በነጻነት መሪዎቹን የሚመርጥበት ስርዓት አልመኖሩ ሦስተኛው የተመረጡት ሲያጠፉ በህግ የሚጠየቁበትና ከስልጣን የሚባረሩበት ስርዓት አለመኖሩ ናቸው።

 

) የደርግ አገዛዝ ዘመን፡ (የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዲሞክራትክ ርፓብሊክ (Peoples’ Democratic Republic Ethiopian)

 

  • እ ኢ አ ሰኔ1974 እስከ ሚያዝያ 1991 ዓ ም።

 

ደርግ መሬት ይዘትን በአዋጅ ለአርሶ አደሩ ቢያስረክብም፤ የመንግስት አስተዳደሩን ክሲቪል አስተዳደር ወደ ወታደራዊ አገዛዝ ቢለውጥም፤ በንጉሡ ዘመን ለብዝበዛውና ለጭቆናው ምክንያት ናቸው ያላችውን ባለስልጣናትንና በሃሳቡ የማስማማውን ሁሉ ቢገልም ከላየ የተጠቀሱትን ሶስት የንጉሡ ዉድቀት ምክንያት በሆኑት ላይ ለአገርና ለሕዝቡ በሚጠቅመው መንገድ እርምጃ አልወስደባቸውም። ግን ቀጠለበት፡፡ ይህ ደግሞ በህዝቡ ላይ እንደ ንጉሡ ዘመን ጭቆናንና ብዝበዛን አበዛ። በዚህም ላይ ማርክስዚም ለኒንዚም ፍልስፍና ለአገርቱዋ አስተዳደር ስልት በማድረግ በፍርሃ እግዚአብሐር ላይ በተምሰሠተ ግብረ ገብ እርስ በእርሱ በመተሳሰብ የሚኖረውን ህዝብ እርስ በርሱ እንድጠራጠርና ወደ ስራዓተ አልብኝነት መራው።

 

በዚህም ላይ ሃገራችን ኢትዮጵያ በኢርትሪያ ጦርነት በተወጠረችበት ዉጥረት ላይ የትግራይ ነጣ አውጭ (TLF) ተፈጠረ፤ በወታድሩም ውስጥ መክፋፈል መጣ፡፡ ጦር ኃሉመ ተዳክመ፤ ቲለፍ ኢትዮጵያን ነጻ አወጣለሁ ባለው ፕሮፓንዳ ተታሎ ከወታደሮቹም ገሚሶቹ ወታደሮች ቲለፍን ተቀላቀለ፤ ከጦርነቱ ከኑሮ ውድነትና ክጭቆናው የተነሳ ህዝቡም ተማረረ፤ የመንግስት ለውጥንመ ፈልገ። አገራችን እንደዝህ ሆና በነበረችበት ጊዜ ነበር ኢሕአዲግ ደርግን በጦርነት አሽንፎ ገዚ የሆነው። በጦርነቱ ብዙ ሕዝብ አለቀ፡ የአገራችን ዕድገትም በሁሉም አቅጣጫ ወድ ኃላ ሃደ።

 

) የኢሕአዲግ) (የኢትዮጵያ ሕዝቦችህ አብዮታዊ ዲሞክራሳዊ ግንባር ፟Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front=EPRDF) 1991-2018

  • ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ እ ኤ አ1991 እስከ 2018 (ፓርቲ፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ድሞክራሳዊ ግንባር ፟(ኢሓአዲግ፟) Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front=EPRDF)

 

ኢሒአዲግ፟በጦር መሳሪያ ኃይል ስልጣን ይያዝ ኢንጂ የህዝቡን የልብ ትርታ ማዳምጥ እርሱም አልፈልገም;፤ በንጉሡ ኃይሌ ሥላስሴ ጊዜ የነበሩትን ሶስቱን የመንግስት ድክመትና ለአገር ዕድገት መርዝ የሆኑትን ምክንያቶች ለማስተካከል እርምጃ አልወተሰደም። ሕገ መንግስት ለራሱ አገዛዝ በሚመች መልኩ ቀረጸ። ደርግ እንደ አደረገው ስልጣን ላይ የነበሩትን ባለስለጣናትን ግማሹን ገደለ ግማሹንም ዕስር ቤት አጎራቸው ጦር ኃይሉንም በተነ የሚገድለውንም ገደለ፤ የአገርቱዋን አስተዳደር ሁሉም ኢትዮጵያውያን በነጻነት የአገር መሪዎችን የሚመርጥበትን ስርዓት ሳይሆን በመሳፍንት ዘመን እንደነበረው ስልጣን ለመያዝ የሚፍልግ የራሱን ዘር በሌላው ላይ በበላይነት እንዲነሳሳ የሚያደርግ አስተዳደሩን በዘር ከፋፈለ። የስልጣን ዘመኑ ያልተወሰነ በማድረጉ ስልጣልን ላይ የሆኑ ግለ ሰቦች የማይነኩ እየመሰላቸው እንደ ንጉሱና እንደ ደርግ ዘመን ሕዝቡን በተለያየ መንገዶች አስጨነቁት፡፡ እንደ ደርግ ጊዘ በኢሕ አደግ ዘምን የረዥም ጊዜ ጦርነት ባይኖርም የአገራችን እድገት በመጠኑ መሻሻል ቢያሳይም በንጉሡ ኃይሌ ሥላስሴ ጊዜ የነበሩትን ሶስቱን የመንግስት ድክመትና ለአገር ዕድገት መርዝ የሆኑትን ምክንያቶች ለማስተካከል እርምጃ ባልመውሰዱ አሁንም ህዝቡ ተጨንቆ በነበረበት ሰዓት ነበር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ስልጣን ላይ የወጡት።

 

  • ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አቢይ አህመድ፡ የካቲት2018 እስከ ዛሬ

 

እኔ እስክማስታሰው እስከ ትግራይ ጦርነት ድረስ ዶ/ር አቢይ አህምድ የሰላም ቃል የዕርቅ ቃል የመደመር እንጂ የመቀነስ ቃል አይናግገሩም ነበር፡፡ አገሪቱዋን ከዚህ በኋላ የሚገዙ ገዥዎች በጦር መሣሪያ ሳይሆን ሕዝብ በነጻነት የዲሞክራሲ ስርዓት ተክትሎ በሕግ የአገሩን መሪ የሚመርጥበትን ስርዓት ለአገሪትዋ አመጣለሁ አሉ፡ ጥቂቶች በጦር መሣሪያ ስልጣን ላይ ለመውጣት

 

ከሚፈልጉት በስተቀር የኢትዮጵያ ሕዝብ በእኔ መረዳት ከሰማንያ አምስት (85%) በላይ የዕርፍት ጊዜዬ መጣልኝ ብሎ በደስታ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ይቀበሏቸው ነበር። ከኤርትራ ጋርም አገራችን ሰላም ፈጥረች። ከዚህም የተነሳ ላገራችንም ከብር የሆነውን የኖብል ሽልማት ተሽለሙ። በጦርነት ስልጣን እንይዛለን የሚሉትንም በነጻነት ተወዳድረን ስልጣን እንያዘ በጦርነት አይሁን ብለው ለዕርቅ እጃቸውን ዘረጉ። የተጣሉትን አስታረቁ። በኢሒአዲግ ዘመን ለእስር ቤት ተዳርገው የነበሩትን በመፍታትና ካገራችንም ተባረረው ወደ ገዛ አገራቸው እንዳይገቡ ኢሒአዲግ የክለክላቸውንም ወደ አገራችሁ ገብታችሁ ለስልጣን በነጻነት ተወዳደሩ ብለው አስገቡ። እንደገቡ ማንም አልታሰረም አልተገደለምም። በትግራይ ጦርነት ጊዜም ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስተሩ ጦር ሜዳ ድረስ ሄደው ተዋጉ። ምንም እንኳን ከተለያዩ ክልሎች ክልሎች የተሰባሰቡ የኢትዪዮጵያ ጦር ኃይል በፋኖ እገዛም የትግራይን ጦር ወደ ማሽነፍ የተቃረቡ ቢሆንም በጦርነት ማሽንፍ ቂምን መፋቅ እንደማይችል በማስተዋልና ተጨማሪ ከትግራይ ኃይልም ሆነ ከጋራው ጦር ኃይል ከፋኖውም ጭምር የሚሞት ወታድርም ሆነ ወታደር ያልሆነውም ኢትዮጵያዊ ሰው መሆኑን በማስተዋል ሰው እንዳይሞት ጦርነቱን እ ኤ አ ግንቦት 20 ቀን 2023 ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በእርቅ እንዲያልቅ አደርጉ። ይህንን የሚያነብ ሰው የእርቁን ዜና በሰማ ጊዘ ምን እንደተሰማው ባናውቅም ብዙዎቻችን እፎይ ብለን ነበር። በሁላችን ላይ የደረሰ ላይሆን ይችላል ነገር ግን ከኮሚቲ አባሎች የአንዱ ወንድም ልጅ ካገራችን ጦር ኃይልና ክፋኖ ጎን ሆኖ በትግራይ ጦርነት ሲዋጋ አንድ እጁን በ22 ዓመቱ አጥቷል፡፡ ይህ ወጣት አማራ አይደለም ነገር ግን የአመራው ክልል በተወረረበት ወቅት ብዙ ወጣቶች ከተለያዩ ክልሎች እንደዘመቱና እንደተጎዱት ዘምቶ አንድ እጁን በሃያ ሁለት ዓመቱ ያጣ ወጣት ነው። ይህንን ጽሑፍ የሚያነብ ይህ ጦርነት በቤተ ሰቡ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ቤቱ ይቁጠረው;፡ የሰላም እርቁ ተፈርሞ ጦርነቱ ሲቆም በብዙዎቻችን በኩል የአገሬ ሕዝብ አረፈ ብለን ነበር፡፡ ግን አልሆነም፤ በፋኖና በመንግስት መካከል ሌላ ጦርነት ከስምምነቱ ከአንድ ወር በኋላ ተጀመረ። በዚህም ጦርነት እስካሁን ብዙ ወጣቶች ሞቶአል ብዙ አባቶች እናትችና ወጣቶች የጦርነቱ ሰለባ ሆነዋል፡፡ ሁላችንም ልናዝን የሚገባን ማጣት ነው ያጣነው። እነዚህ የማን ናቸው? ምን ይሁን መልሳችን? ዛረ ምናልባት መንግትን በመደግፍ ክፋኖ ይህን ያህል ሞተ ሲባል ደስ እየተሰኘን ይሁን? ወይም ክመንግስት ይህን ያህል ሞተ ወይም ቆሰለ ሲባል ደስ እያለን ይሁን? የሚሞትና አካለ ስንኩል እይሆኑ ያሉት ለኛ ወንድሞቻችን እህቶቻችን ናቸው። እነዚህ ለአገራችን ኢኮኖሚው እድገትና ለውጭ ጥቃት መካላከያ ኃሎችና መከታዎች ናቸው እንጂ እርስ በርስ በመዋጋት ሊያልቁ የሚገባቸው አልነብሩም፡፡ ሰለዚህ ነው በህብረት ሁላችንም በአንድነት መንግስትንም በመለመን ፋኖዎችንም በመለመን የኦሮሞ ነጻ አውጭዎችንም በመለመን ጦርነቶች ቆሞው ዕርቀ ሰላም እንዲመጣ ለማድረግ አስተዋጽዖ ለማድረግ መሰባሰብ የጀመረነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዐማራ ሕዝብ ድርጅት (ዐሕድ) መግለጫ

 

መ) የተልያዩ ዘጎች ኖሮአቸው የሕዝብ ሰላም ያላቸው በእድገት ክመነጠቁ አገሮች ልንማር የሚገባን ትምህርቶች፡ እኤአ በግንቦት 2021 ሕዝብ ለሕዝብ (P2P)  በሚባለው ድርጅት ውስጥ ለሚሳተፉ የሚክተለው ጹሑፍ በኢሜል ከኮሚተው አባሎች በአንዱ ተልኮ ነበር፤ (ያጠረ)

 

……፟ለመሆኑ እንዲህ እይነቱ ችግር በአሜሪካ በዩኬ (UK) በሌሎች አውሮፓ አገሮች ወይም ዲሞክራሲ እራማጅ ሀገሮች ለምን አልተከሰተም የሚል ጥያቄ በእዕምሮችን ተፈጥሮ ያውቅ ይሁን? እነርሱ የጎሳችግር ስሌለባቸው ነውን? ከነዚህ ሀገሮች ምን እንማራለን የኛስ ሀገር ኢትዮጵያ ልክ አንደነዚህ ሀገሮች ለምን አትመራም? ለምንስ ይህንን ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት አገራችን ኢትዮጵያ እንድ ትከፋፈል ሳይሆን አንድነትዋ እንዲጠበቅ፡ ልጆችዋ ለጦርነት ማገዶ ክመሆን ለራሳቸውና ለአገራቸው እድገት አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ አይደረግም? የንጉሡ ኃይሌ ስላሴም ሆነ የደርግ መንግስት አሁን ደግሞ ኢሒአዲግ መንግሥት በውርደት የወደቀው ለምን ይመስልሃል ? ዛሬም ለሀገራችን ይህንኑ ውርደት የተሞላው ሽግግር መንግስት እንዲኖር ነው የምንፈቅደው?

 

በዚህ ኮሚቲ መረዳት ከላይ የጠቀሱት አገሮች ሕዝቦቻችው በነጻነት የአገር መሪዎችን መርጠው የተመርጡትም ስልጣንን መከታ በማድረግ ጥፋት ቢያጠፉ በህግ የሚቀጡበት ስርዓት ለአገሮቻችው ተግባራው በማድርግ የጎሳና የዘር ጉዳይ አገሮቻቸውን እንዳውክ ያደርጉት ስራዓት ለአገራችን ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ ያስፈልጋታል፡፡

 

) ይህ ሕብረት ሊያደርግ ያቀዳቸው ተግባሮች፤

 

  • ኢትዮጵያውያንን ማሰባሰብ

 

ኢትዮጵያውያንን በተለይም በውጭ አገር የሚኖሩትን ለአገሩ ለኢትዮጵያ በሙያውና አቅሙ በሚፈቅደው አስተዋጸዖ እንዲያደርግ ማስባስብና ማረጋገጥ። ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ አሁን በጀመረው መሰረት የዙም ስብስባ ቢያንስ በወር አንድ ጊዘ ያደርጋል፤ በግልጥነትም በየጊዜው ባገሪቷ ባጋጠሙ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ሰላማዊ መብፍትሄ ለመፈለግ ከመንግስትና ከሕዝቡ ጋር ይሠራል;

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጠላቶቻችንን በደማቅ የአሸናፊነት ታሪካችን ብቻ ሳይሆን በብሩህ ተስፋችንም ጭምር ፊታቸው ጠቁሯል₋ኢዜማ

 

  • የአሁኑ አንገብጋቢ ችግር ፟፟ጦርነትን ማቆም፡

 

ጦርነት ጦርነትን ይወልዳል፡ ሰላም በጦርነት አይመጣም አብሮ በመነጋገር እንጂ; እድገት በጦርነት አይመጣም አብሮ በመሥራት እንጂ; ጦርነትን ማስውገድ የምንችለው ለጋራ ህይወታችን፤ ለጋራ እድገታችን የሚያስፈልጉን ነገሮች ለግል ሕይወታችንም ሰላምና እድገት አስፈላጊ መሆኑን አውቀን ልዩነታችን ላይ ሳይሆን በጋራ ጥቅማችን ላይ አብረን ለመሥራት ቆርጠን ስንነሳ ብቻ ነው፡፡

 

የጦርነት አስክፍነት እጅግ ክፉ ነው፤ ይህ ጥሑፍ ሲዘጋጅ በትግራይ ጦርነት ከ800000 በላይ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንድሞቱ ከነዚህ ዉስጥ 600000 የሚሆኑት ወታድር ያልሆኑ ተራ ሕዝብ እንድሆኑ ተደርሶበታል፡፡ ክዚህ በላይ እንድተጠቀስው የዛሬ ወር በፊት በአንድ ዜና ማሰራጫ ራድዮ ጣቢያ መሰረት በመንግስትና በፋኖ መካከል ጦርነት ከተጃመረበት ከሃምሌ ወር እስክ ነሃሴ (አውገስት) 27 2023 ድረስ 180000 ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ተገድለዋል፤ ወንድሞቻችንን አጥተናል እህቶቻችንን አጥተናል አባቶቻችውን ወይም እናቶቻቸውን ያጡ ስንት እንዳሉ የደረሰበት ይቁጠረው፡፡ እንደዚህ ተጎድተው በየበቱ ያሉትን አባቶቻችን እናቶቻችን ወንድሞቻችና እህቶቻችን ናቸው፤ እነዚህ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ናችው እንዚህ የውጭ ወራሪ ኃልን ተከላክለው የኢትጵያን አንድነት የሚያስጠብቁ ነበሩ፤ ለአገሪቱዋ ሰላም አስተዋጽዖ የሚያደርጉ ነብሩ፤ ለወላጆቻቸውና ለዘምዶቻቸው ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ መኩሪያ ነበሩ፤ ዛረ ግን የሉም ወላጅ አያገኛቸውም ዘምድ አያገኛቸውም አገራቸውም አታገኛቸውም በስልጣን ፈላግዎች ምክንያት ሌላውን ያለ ስራዓት እንገዛለን ባዮች ምክያት የጋራ ጥቅምን የጋራ ዕድገት ሳይሆን ለኔ ብቻ ወይም ለእኔና ለወገነ ብቻ ብለው ጦርነት በሚይስነሱት ምክን ያት፡፡ አሁን ጥያቀው እኔ ምን ላደርግ ይህንን ለማስቆም? እኛስ? የሚለው ነው፡ የዚህ ሕብረት ሰብሳቢዎች ዝምታ መልስ እንደማይሆን ተገንዝበው የሚከተለውን አቅደዋል፡፡

 

መንግስት ክፋኖና ካኦነግ ጋር ያለው ጦርነት፡ ጦርነቱን ስለማስቆም፡ ዉጭ ክሚኖሩት ስድስት እስከ ዘጠኝ ሰዎችን መምርጥ፡ ሥራቸው እንድሚከተለው ይሆናል

 

ቡድን 1) ወደ ፋኖ ይሚላኩ – ሁለት(ሶስት) ሰዎች

ቡድን 2) ወደ ዖነግ የሚላኩ ፟ሁለት(ሶስት) ሰዎች

ቡድን 3) ወድ መንግሥት የሚላኩ ፟ሁለት(ሶስት) ሰዎች

 

እነዚ ከአገር ውስጥ በተለይም ክበ/ክርስቲያአንና ክሙስሊሙ ሕብረተ ሰብ ኢንዲሁም ከተመረቱ አገር /ስማግለዎች ጋር ይሠራሉ;፤ ስብጥራቸውም ለሽምግልናው መልካም ውጠት ሊያመጣ በሚችለው መንገድ ይሆናል፤ ዝርዝር አስራሩ በምክክር የሚሆን ሲሆን አስችኮአይ ነው፤

 

  • ባህልንና የፈጣሪን በላይነት ሳይጣረረ አገርቱዋን ሰው በጠመንጃ ኃይል ጉልበት ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዕኩል ደረጃ በሕግ ኃይል የሚገዛበት ስርዓት እንዲኖር መሥራትና ማረጋገጥ

 

ፈጣሪያችን እግዚኦአብሔር በመጽሐፍ ቅድሱ ውስጥ “ራዕይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል ሕግን የሚጠብቅ ግን የትመሰገነ ነው” ብሎ መክረን፡፡ ቤት ያለ ንድፍ (ብሉ ፕርንት) ሊሠራ አይችልም; ቤቱ በሁሉ ነገር የተሟላ እንዲሆን ንድፍን በክፍተኛ ጥንቃቄ መከትል የግድ ነው፤ ቤተሰብም ሰላም የሚኖረው የወደፊት ዓላማውም የተሳካ የሚሆነው በቤተሰቡ ውስጥ አድሎ የማያደርግ ስርዓት ሲተገበር ነው፡ አገርም እንዲሁ ነው፤ በአገራችን ውስጥ ለዘመናት ለሁሉም እኩል የሚሠራና ሕዝቡም መብቱንና ግደዴታውን አውቆ በነጻነት የአገር መሪዎችን መርጦ የተመርጡትም ሲያጠፉ ተጠያቂ የሚሆኑበት ያለአድሎ ተግባር ላይ የዋለ ሥርዓት አለመኖሩ ነበር ለዘመናት አንዱ ብሐረ ሰብ በሌላው ላይ የበላይ እንደሆነ እንዲቆጥርና እርስ በርስም እኔ ልብላ እኔ ልብለጥ ፉክክር ምክንያት ነው አገራችን የጦር አውድማ የሆነችው፤ ሕዝብም ያለቀው ንብረትም የወደመው ወደ ላይ በማደግ ፋንታ ወደ ታች የወረድነው ወደ ፊት በመሄድ ፋንታ ወደ ኋላ የሄድነው በመክበር ፋንታ በውርደት ስማችን የሚታወቀው፡፡ በዓለም ድሃ ክከሚባሉት አገሮች ኢትዮጵያ አንዱዋ ነበረች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ፡፡

 

ታድያ የኛ ዝምታ መፍት ልሆን ይችላል? ይህ ኮሚቲ ኢትዮጵያውንን በሙሉ የሚለምነው ከላፈው ተምርን ያለፈውንም ትተን ይቅር ተባብለን ለልጆቻችን መልካም አገርን መልካም ባሕሪን ክሁልም በላይ እግዚአብሔርን መፍራትን ለአብሮነት ለሰላም ለዕድገት አብረን ሠርተን አብረን ኖረን ለምጭው ትውልድ ክፉ ሳይሆን መልካም ሁኔዎችን ትተን እንድንልፍ ነው።

 

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ አንድነትዋንም ይጠብቅ ለሕዝቡም እርሱን የመታዘዝና በመተሳሰብ አብሮ የመኖርን ማስተዋል ይስጥ፣

 

September 9/2/23

Written by Berhanu Ayele Wurseno Edited by Munach Mulualem Mersha

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share