ኢትዮጵያዊነት ማንነት በማይከበርበት ስለ ብሄራዊ አንድነት እና ሠላም እንዴት ?

 

በኢትዮጵያ የትህነግን የ1968 ዓ.ም. ፀረ -ኢትዮጵያዊነትን የፀነሰዉን የጥላቻ እና የጭካኔ መመሪያ የወለደዉ 1987 .ዓ.ም ህገ-ኢህአዴግ ኢትዮጵያም ሆነ ኢትዮጵያዊነት በስጋት ተመልክተዋል ፡፡

ፀረ- ኢትዮጵያዊነት፣ ፅዮናዊነት፣ ዓማራ ለኢትዮጵያዊነት ዕዉቅናን የሚነፍግ ፣የዓማራን ህዝብ በፖለቲካ ፣ ሠርቶ የማግኘት እናየመኖር (ኢኮኖሚ) ፣ በዕምነት እና ማንነት በግልፅ በማግለል የሚደነግግ ህገ- ፓርቲ ከተወለደበት አስካሁን ሁሉንም የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት እና የዘመናት ታላቅነት ታሪክ የሚንድ፣ የዓማራ ህዝብ ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በደም እና አጥንት በመሰረታት አገር በባይታዋርነት እና በመጣትነት በመፈረጂ ላለፉት ሶስት አስርተ ዓመታት የበይ ተመልካች አድርጎታል፡፡

የትግራይ ህዝብ ነፃ አዉጭ ድርጂት(ት.ህ.ነ.ኣ.ድ) በበረኃ የቋጠረዉን ቂም በህገ- ፓርቲዉ አሳድጎ በመዉለድ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮጵያዊነትን እና የዓማራ ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ የአንድን አገር ህዝብ ጠላትነት ወዳጂ ማድረጉ በበረሃዉ ሴራ ጨቋኟዋ የዓማራ ብሄረሰብ የምታደርገዉ የኢኮኖሚ እና ፓለቲካ ብዝበዛ እና ጭቆና አስካለቆመ ህብረተሰባዊ ዕረፍት እንነሳለን የሚለዉን ከጥላቻ እና የበታችነት ስሜት የሚመነጭ ብቀላ ከዚያ አስካሁን እየሰራበት ይገኛል ፡፡

ከዚህም በላይ የ፫ ሽ ዓመታት ታሪክ እና ባህል ተዘርፈናል የሚል የዚያን ዘመን ቁጭት ዛሬም ላይ በዓማራ ህዝብ እና ማንነት ላይ ያለዉን ጥላቻ ማሳየት መቀጠሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ያለዉን ዕዉነተኛ ታሪክ እና የዘመናት ብሄራዊ ማንነት ከነልዩነት ለመቀበል አለመፈለግ ነዉ ፡፡

ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ በተለይም በዓማራ ህዝብ የማንነት እና የፖለቲካ ጫና ህዝብ ሲያነሳ የተለያየ መጠሪያ ዕየሰጡ በጥላቻ እና በቂም በቀል ዕዉነትን እና የህዝቦችን ማንነት መካድ ለማንም የሚጨምረዉ ፋይዳ የለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ ያልታሰበ እድል አግኝታለች--ይህንን ወርቃማ እድል ደግሞ እናባክነው ይሆን? (አክሎግ ቢራራ (ዶር))

ትህነግ የኢትዮጵያን የዘመን ቆይታ በ ፻ ዓማታት ቀንብቦ የሶስት ሽ ዓመታት ታሪክ እና ባህል ተቀምተናል ሲል እኛ ኢትዮጵያን ደግም ከዳማት ስርወ መንግስት ጀምሮ ሲቆጠር የ፭ ሽ ፭፻ ዘመን ያላት የታላቋ ኢትዮጵያ አገር ህዝቦች መሆናችንን አለመናገራችን “ከሞኝ ደጂ …….” ሆኗል፡፡

ለመሆኑ አንድ ድርጂት አንድን አገር እና ህዝብ በዚህ ልክ ሲመለከት በተለይ የዓማራ ህዝብ እና የዓማራ የአገረ መንግስት ምስረታ እና ባለዉለታ መሆን በዚህ ልክ ሲካድ የዓማራ ህዝብ ራሱን እና አገሩን ከዉጭ እና ከዉስጥ ጥቃት ያደረገዉን የዘመናት ታጋድሎ ፋና ወጊነት ምልክት እና ስያሜ የሆነዉን ህዝባዊ አደረጃጀት “ፋኖ ” በድንገት የተፈጠረ እና ከምንም ያልነበር አድርጎ መረዳትም ሆነ መገመት ፍረደ ገምድልነት እና የታሪክ ባዶነት ነዉ ፡፡

አዚህ ጋ ሁላችንም ልናሰምርበት የሚገባ ዛሬም ላይ ዜጎች በፖለቲካ እና በሰባዊ መብት ዕጦት እና መገለል ለሚያቀርቡት ጥያቄ ዛሬም ከልካይና ሰጪ ትክነግ ሆኖ ማየት የሶስት ሽ ዓመት ባላታሪክነቱን ሳይሆን ታሪክ አልባ ህዝብ እና አገር ለመፍጠር ሊረካ የማይችል ነዉ ፡፡

ማሳያችን የፖለቲካ መገገለል እና መድሎ ደርሷል ብሎ በጥላቻ ሲነሳ በህዝብ መስዋዕትነት ስልጣን ላይ ወጥቶም ሆነ አሁን ከጭቆና አስተሳሰብ ባለመዉጣት ለበቀል እና በደል በዓማራ ህዝብ ላይ አሁንም በነበረበት መሆኑ ነዉ ፡፡

በመማል ከሆነ ኢትዮጵያ የዕኛ ናት ኢትዮጵያም የብዙ ሽ ዘመናት የዕድሜ ባለፀጋ ናት ፡፡ የዓማራ ህዝብ የባላገርነት፣ የአርበኝነት እና የብሄራዊ ኩራት ተምሳሌነት ዓለም የሚመሰክረዉን እኛ ብንክደዉ ዕዉነትን መቀየር ከቶ ድካም ፡፡

ስለ ኢትዮጵያም ሆነ ስለ ዓማራ አገር ወዳድነት እና አርቆ አሳቢነት አንናገርም ከዚህ በላይ በተግባር ተፍትኖ በታሪክ ተሰንዶ የሚገኝ ከነቦታ ስያሜ እና ሁነት ጋራ ሸንተረሩ የሚመሰክረዉ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይሄ ሰውዬ በርግጥም በሽተኛ ነው፤ “አትግደሉኝ” ማለት በየትኛው ሒሣብ ነው የሥልጣን መያዣ አቋራጭ መንገድ የሚሆነው? ይነጋል በላቸው

አበዉ ቂም (ጥላቻ) በ፻ ዓመቱ የወተት ጥርስ ነዉ እንዲሉ የኢትዮጵያ እና የኣማራ ህዝብ ጠሎች በፖለቲካ ጭቆና ላይ ሆነዉ ዛሬም ወደ ፊቱም እየጨቆኑ ለመኖር የሚገዳቸዉ በጥላቻ ምክነያት እንጂ በጭቆና የኖረ ጨቐኝ ሆኖ እንዲኖር የሚያደርግ ጥላቻ እና የበታነት ስሜት መሆኑ ዛሬም የሚታይ ነዉ፡፡

የሚያሳዝነዉ ይህን የመሰለ ለአገር እና ህዝብ አደጋ የሆነዉን ዕንቀፋት እና የሞት ወጥመድ ተሸክሞ ስለ ሠላም፣ አንድነት ፣ ብሄራዊነት፣ ዕኩልነት …….ስለሚያወራ ሁሉ ነዉ ፡፡ እናዝናለን የመታንን እንቅፋት፣ የጠለፈንን ወጥመድ፤ የካደንን ጠላት ሳናዉቅ ወደ ፊት ለመራመድ ወደ ኋላ እያየን ወደ ፊት ለመራመድ አለመቻላችን አለማወቃችን ነዉ፡፡
እያወቀ ላላወቀ ይሆን ዘንድ ከተ.ህ.ነ.ድ 1968 ዓ.ም. መመሪያ እና የዓማራ ህዝብ ለዘመናት በጠላትነት የብዙ መከራ ዘመናት ገፊ እንዲሆን የተጫነበት የጭቆና ቀንበር ማስተግበሪያ በከፊል የሚከተለዉን ለሚያይ ይኸዉ ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

Allen

 

 

1 Comment

  1. እውነትም ሽመልስ እብዱሳ አሉህ ሁሉም አበደ አዳነ አበበም የሴት ስነ ምግባር ታጣባት የጠቅላዩ ነገር ፕሮፌሰር መራራና አያቶላ ጁዋር እንዳሉት የጊዜ ጉዳይ ይሆናል እንጅ ኦሮሞ ይበላዋል ብለዋል፡፡ እስቲ ሰላም ፍጠሩ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share