አሜሪካን ለጠሚ/ር አብይ በኤርትራ ጉዳይ ጠንካራ ማሳሰቢያ ላከች፥ በወልቃይት ውጥረት ነግሷል፥ የጸሀይ ሪል ስቴት ኦፕሬሽን

August 31, 2023

https://youtu.be/jfXg4KAq7oE?si=oyYJg1dDJBqPBomt

 

2 Comments

  1. ይህ ከእውነት የራቀ ወሬ ነው። አሜሪካ በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ሰርታ አታውቅም። ያው እንደሚታሰበው በአለም ላይ ከሚነዛው የሰበር ወሬ ጋጋታ ሩብ ያህሉ እንኳን እውነትነት የለውም። ነገር ሁሉ በአድርሱልኝና በስማ በለው በመሆኑ ከቦታው ተገኝቶ በአይን እማኝነት ይህንና ያን ለማለት ጭራሽ አልተቻለም። ናይሮቢ ላይ ተቀምጦ ስለ ናይጀሪያ ግጭት፤ ለንደን ላይ ሆኖ ስለ ዪክሬንና ስለ ራሽያ መጨራረስ በዚህም በዚያም ያገኘውን ወሬ በመቃረም ነገርን እያጋነኑ እስትንፋሽ እስኪያጥር መለፍለፍ የተለመደ የጊዜው ዜና ሆኗል።
    ዝንተ ዓለም ፍዳዋን በምትቆጥረው በሃበሻ ምድር ደግሞ ወሬ ሸቀጥ ሆኖ ሁሉም የኢንተርኔት ተጠቃሚና የቲክቶክ ንጉስና/ንግስት ለመሆን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይነዙት ወሬ የለም። አልፎ ተርፎም ስሜትን የሚጎዳ የሞተ ሰው ጋር ፎቶ መነሳት፤ እንስሳት ሲታረድ በሌላው ሲጠቁና ሲገደሉ መለጠፍና ሽርፍራፊ ሳንቲም ለቀማ ራቁትን መሄድ መሰልጠን ሆኗል። አሜሪካ ወያኔን ለማዳን ያለ የሌላትን ካርድ ተጫውታ ወያኔ በሶስት ጊዜ ወረራው ክፉኛ በመገሽለጡ አሜሪካኖቹ ዞረው ተገልብጠው የሰላም አደራዳሪ ሆነው መሰለፋቸውን ህዝባችን ከቅርብ ጊዜ ታሪኩ ይረዳል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ እንዲወጣም ሆነ እንዳይገባ የከለከሉት አሜሪካኖች ናቸው። ጠ/ሚሩ ታዛዥና አሜን ብሎ በመቀበሉ በዛም አነሰም ከዓለም ባንክ አንዳንድ ብድር እንዲያገኝ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ጫና እንዲቀል ያደረጉት ለዚያ ነው። አሁን ወያኔ በትግራይ ሴቶችን እየጎተተ መኪና በላያቸው ላይ ሲነዳ፤ ሲደፍር፤ ወንጀል በትግራ ምድር ሲበራከት ኡ ኡታ የሚያሰሙ የፓለቲካ ሙታኖች ሊረድ የሚገባቸው ጉዳይ በጦርነት ሁለት ሟቾች እንዳሉ ነው። የመጀመሪያዋ ሟች እውነት ራሷ ናት። ከዚያ ቀጥሎ ያለው ከጦርነቱ የተረፈው ወገን ነው። በተለይም ተፋላሚው ሃይል። ሟች አንዴ ተሰናብቷልና በዚህች ዓለም ስንክ ሳር መጠላለፉ አብቅቶለታል። ታዲያ በሶስት ጊዜ ወረራው ወያኔ ሴት የደፈሩ፤ ሰውን አንበርክከው የረሸኑ፤ እንስሳትን የገደሉ፤ ተርበናል ምግብ ብለው ምግቡን ከበሉ በህዋላ ያስተናገዷቸውን ሰዎች የረሸኑ ዛሬ መቀሌ ላይ ቢቀውሱና እርስ በእርሳቸው ቢጠዛጠዙ ምን ጉድ ያሰኛል? በሰው ደም የታጠበ በጊዜው የእርሱም ደም መፍሰሱ አይቀርም። የገደለም ሆነ ያስገደለ የዘንተ ዓለም የአዕምሮ ጠባሳ ተሸላሚዎች ናቸው። የሚያሳዝነው ዛሬም የሚገደሉትና እስር ቤት የሚወርድት፤ ለረሃብና ለመከራ የተጋለጡት ያው መከረኛ የትግራይ ህዝብ መሆኑ ነው። ወያኔና ዘመዶቻቸው በውጭ ሃገር ተንደላቀው፤ በሃገር ቤት ፎክረውና ሸልለው ነው የሚኖሩት። ይህ ነው የብሄር ነጻ አውጭዎች የስራ ስኬት። እልፎችን ማስለቀስ!። ታዲያ አሜሪካ ጠ/ሚሩን ተው ከኤርትራ ጋር በምንም ሂሳብ ቢሆን ጦርነንት አትግጠም ብለዋል መባሉ ለእኔ ትርጉሙ ተፋለሙ ነው። ሲጀመር አሜሪካ በኤርትራ ላይ ያላት አቋም ክፋትና ተንኮልን የተላበሰ ነው። ያኔ ሻቢያ በረሃ እያለ በዚህም በዚያም አይዞአችሁ ሲሉ የነበሩት አሜሪካኖች አሁን ላይ አፍቃሪ ወያኔ በመሆን የኢትዮጵያና የኤርትራን ጦርነት መግጠም ይፈልጉታል። ለምን፤ እንዴት ለሚለው ጥያቄ የዓለምን የቅርብ ጊዜ የፓለቲካና የኢኮኖሚ አሰላለፍ መመልከት በቂ ይሆናል። ስለሆነም በየሚዲያው የሚሰራጨውን ወሬ ሁሉ እንዳለ እየሰለቀጡ ወሬ አናፋሽና አቀባባይ ከመሆን ይልቅ ረጋ ብሎ ጊዜውንና ዘመኑን መፈተሽ አስፈላጊ ይሆናል።
    ኢትዮጵያ የማትወጣበት ማጥ ውስጥ ናት። የክልል ፓለቲካው፤ የቋንቋ ጦርነቱ፤ የብሄርተኞች የፓለቲካ ትኩሳት በዚህም በዚያም ሰንጎ ይዟታል። በኤትራም ሆነ በኢትዮጵያ ማንም ሰው ለሃገር፤ ለባህር በር፤ ለምናምን እየተባለ መገዳደሉ የጅልነት ምልክት እንጂ ፓለቲካዊ ብስለትን አያሳይም። ለነገሩ “መግደል መሸነፍ ነው” ያለን ጠ/ሚ አይደል አሁን የሚገድለንና በራሱ ጥላ የሚደነብረው? ባጭሩ እኔን ብቻ ምሰሉ በሚል የፓለቲካ ህሳቤ ውስጥ የተለየ ሃሳብ ማንሸራሸር የማይታሰብ ነው። ለዚህም ነው የሌለ ስም እየሰጡ እንደ ሲሳይ አጌና ያሉ ምጡቅ ጋዜጠኞችን ከድህረ ገጽ ላይ ያጠፏቸው። መሰንጠቅ፤ መከፋፈል፤ በዚህም በዚያም አዲስ የፓለቲካ ፓርቲ/ቡድን መፍጠር የተለመደ የሃበሻ የፓለቲካ ስሌት ነው። ለዚህ ነው አባቶች “የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል” ያሉት። ትርፍ የለሽ ፓለቲካ፤ አፍራሽን አፍራሽ እየተካው ህዝባችን ዛሬም ያነባል፤ ይራባል፤ እኛ ግን በዘርና በቋንቋ እንዲሁም በክልል ፓለቲካ ሳቢያ ዛሬም በቅርብና በሩቅ ሆነን በለው እንላለን። ጾማቸውን ውለው ለሚያድሩት እናቶችና አባቶች፤ ቤታቸው በላያቸው ላይ ለፈረሰባቸው ወገኖች ማን ድምጽ ይሆናቸው? ይህ የሃበሻ የዘመን የፓለቲካ መጨራረስ መቼ ይሆን የሚያባራውና ህዝባችን እፎይ የሚለው? ያ ጊዜ ይመጣ ይሆን? በቃኝ!

  2. እውነትም ከሆነ በርቱ መሰለኝ የምትለው በዚህ ግርግር ፋኖ የመሳሪያ አቅሙን ያሳድግ ነበር። የሃገሪቱ መዳኛ በፋኖ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published.

oromo 2 1 1
Previous Story

ኢትዮጵያዊነት ማንነት በማይከበርበት ስለ ብሄራዊ አንድነት እና ሠላም እንዴት ?

537
Next Story

ከመካነሰላም! “ሞርተር ተማረከ፣537 ወታደር ተደምስሷል”| ደብረ ዘቢጥ፣ ጋይንት፣ እስቴ! “ከነ ፓትሮሉ ወደሙ” | የአማራ ድምጽ ዜና

Go toTop