August 1, 2023
5 mins read

አማራ ነቅተህ ጠብቅ!  የከሀዲዎች አንድነት ፓርቲ ጆቢራ አማራን አዘናግቶ ለማስጨረስ ዛሬም  እየዞረ ነው!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

Amhara 2 1

በመላእክትነት ተመርጦ የነበረው ሳጥናኤል እግዚአብሔርን ከድቶና ክርስቶስን ወደ ተራራ ወስዶ ከተማ እያሳዬ በንብረት ሊደልለው ሞከረ፡፡ የሳጥናኤል ተከታዮች ደግሞ ከዓለም በፊት እግዚአብሔርን እያመለከ የኖረውን አማራ አንድነት፣ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኢትዮጵያ ሱሴ ወዘተርፈ በሚሉ የቁማር ካርታዎች ሲያታልሉ ኖሩ፡፡  አማራ ክርስቶስን ስላለሆነ  ተታለለ፡፡

በቁማር መጫዋቻ ካርታ መደለሉ የሰለቸው አማራ ራሱን ለማዳን መሰባሰብ ሲጀምር ደሞ እንደተለመደው ከሀዲዎች የአንድነት ፓርቲ ያስፈልጋል የሚል ሌላ የክህደት ወጥመድ በማጥመድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሳጥናኤል አዙሮ የምያይበት አንገትና ይሉኝታ እንደሌለው ሁሉ እነዚህ የአንድነት ድስኩር አቀንቃኝ ከሀዲዎችም ትናንት የሰሩትን ዞር ብለው የሚያዩበት አንገት፣ እንደ አቡጀዲ የሸረከኩትን ውሽት የሚያፍሩበት ህሊናና ይሉኝታ የሳጥናኤል ያህል እንኳ የላቸውም፡፡

አማራ በእነዚህ ከሀዲዎች የአንድነት ድስኩር እየተታለለ ለሃምሳ ዓመታት ሳይደራጅ በምቅረቱ እየደረሰበት ያለውን የዘር ፍጅት ሰው ቀርቶ በደመ ነፍስ የሚንቀሳቀሱት እንሰሳትም ሊረዱት የሚችሉት ግፍ ነው፡፡

እነዚህ ድርጅት በማፍረስ ሰይጣን እንኳን የማይሰተካከላቸው ጉዶች ዛሬም እንደ ወትሮው አዙሮ የሚያዩበት አንገትና ሊያፍሩ የሚችሉበት ህሊና ወይም ይሉኝታ ስለሌላቸው ከምድር ላለመጥፋት በመዋደቅ ላይ ያለውን አማራ ሊያዘናጉ የአንድነት ፓርቲ የምትባል ቁማር እንደተለመደው ይዘው ብቅ አሉ፡፡ ዳሩ ዛሬም በዚህ ከሀዲዎች እንደገና ተጠልፎ የሚወደቅ  የአማራ የእንግዴህ ልጅ ምሁር ያጣሉ አይባልም፡፡ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ዓባይ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱሴ  አንድነት በሚሉ ይሁዳዊ ሰባኪያን የተንዘላዘሉና የተከንከረፈፉ ጅላጅል ምሁራን በዛሬው የአንድነት ፓርቲ ስብከትም እንደ ገለባ ተጠርገው የአማራ ማሳሳቱን አይቀጥሉም አይባልም፡፡

መጃጃል የማይሰለቻችሁ ምሁራን ሆይ! የወቅቱ የአማራ ትኩረት የመኖር ያለመኖር ትግል ነው፡፡ ህሊናና ይሉኝታ በሌላቸው ከሀዲዎች በአንድነት፣ በኢትዮጵያ፣ በአባይና በወደብ ስብከት መታለልና መጭበርበር በቃው!! አማራ ጊዜውን፣ እውቀቱን፣ ጉልበቱን፣ንብረቱንም ሆነ መንፈሱን ማዋል ያለበት ለራሱ ህልውና ብቻ ነው፡፡ አማራ እንደ ማርያም ጠላት በሚዋከብበት በዚህ ክፉ ዘመን የራሱ ልጅ እየተራበ ሌላውን አጎርሳለሁ የሚል፣ የራሱ እያረረበት የሌላውን የሚያማስል የእንግዴህ ልጅ ነው፡፡ ህዳሴ፣ ግድብ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱሴ፣ አንድነት እያሉ የአማራ ምሁራንን ሲያጃጅሉ የኖሩት ቁማርተኞች ዛሬ ደሞ ለሃምሳ ዓመታት ሲጠለፍበትና ሲታረድበት የኖረውን የአንድነት ማዘናጊያ ወጥመድ አጥምደው አማራን ለመጥለፍና ለማስጨረስ እየተቅበዘበዙ  ነው፡፡

አማራ ነቅተህ ጠብቅ!  የከሀዲዎች አንድነት ፓርቲ ጆቢራ አማራን አዘናግቶ ለማስጨረስና ለመብላት ዛሬም እየዞረ ነው!

ዓባይን ማን መቼ ይገድበው? https://amharic.zehabesha.com/archives/126545

ፈንድ ፈንዳጅ ዲያስጶራ እባክህ ስማ! ለዘራፊዎች የማይነጥፍ ጥገት መሆንህ ይብቃ!  https://amharic.zehabesha.com/archives/176751

https://zehabesha.com/the-genesis-of-ethiopian-problems-the-ghion-river-and-eyerusalem/

ነሐሴ ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

184620
Previous Story

በተኩስ እየተናጠች ነው! ቀጥታ ከደብረታቦር!| የአማራ ድምጽ ዜና

184633
Next Story

ሰበር ዜና ከጎንደር ከተማ! – ጀነራሉ ተገደለ- ትልልቅ ከተሞች በፋኖ እጅ ገቡ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop