በሽምግልናና ድርድር ማደናገሪያ የአማራውን የህልውናና ነፃነት ትግል መቀልበስ አይቻልም! የአማራ ፋኖ የህልውና ትግል መዳረሻው የስርዓት ለውጥ ብቻ ነው!
በኢትዮጵያ ጥንተ ጠላቶች ከፍተኛ ሴራ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንቅፋት ናቸው ብለው የለዩአቸውን የዘውዱን ሥርዓት ማፍረስ፣ ከህዝብ አማራን ማዳከም እንዲሁም ኢትዮጵያውያንን በአንድነት አስተሳስራ የያዘችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ማጥፋት አይነተኛ መንገዶች መሆናቸው ታምኖበትና ብዙ አመታት ተሰርቶበት የውስጥ ባንዳወችንና የተወናበደውን የተማሪወችን ንቅናቄ በመጠቀም የዘውዱን ሥርዓት እንዳልሆነ ሆኖ እንዲፈርስ ለማድረግ ችለዋል። ከዚያም ምንም ጊዜ ሳያጠፉ የብሄር ድርጅቶችን እንዲመሰረቱ በማድረግ በአማራው ላይና ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ዘመቻቸውን ቀጥለው ህወሓትና ኦነግ በአማራው ህዝብ ላይና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ ያደረሱትን ግፍ መዘርዘሩ ለቀባሪ እንደማርዳት ነው።
በተለይም በዚህ አምስት አመታት በኦነጋዊው የአብይ አህመድ ፋሺስታዊ የአፓርታይድ አገዛዝ ዘመን በአማራውና በኦርቶዶክስ ምዕመናን፣ ካህናት፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማትና መስጊዶች ላይ የደረሰው መጠነ ሰፊ ውድመት መቼውንም ጊዜ ደርሶ ከነበረው
ጥፋት ሁሉ ተወዳዳሪ የሌለው ነው። ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ለማጥፋትና በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ሁለት አዲስ አገሮችን ለማዋለድ የብሄር ተዋፅኦን መሰረት ያደረገ ሲኖዶስ በማዋቀር ላይ ይገኛሉ። በተለይም በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ድርድር የማያውቀውን አማራ በወለጋ፣ በመተከል፣ በምዕራብና ሰሜን ሸዋ የዘር ማጥፋት ወንጀል (genocide) እንዲፈጸምበት በማድረግ፣ ከአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ በጉልበት በመንጠቅ በህገወጥ በመሰረቱት ሸገር ከተማ ዘር ተኮር በሆነ መዋቅራዊ አሰራር ቤት በማፍረስና መቶ ሽህዎችን በማፈናቀል፣ በአስር ሺህወች የሚቆጠሩትን በግፍ በማሰርና በማንገላታት፣ በመሰረታት ከተማ ወደ አዲስ አበባ አማራ እንዳይገባ በመከልከል፣ ባስታጠቁት የኦነግ ሰራዊት አማካኝነት ሰላማዊዉን ህዝብ እና ሰርቶ አደሩን አግተው በሚሊዮን የሚቆጠር ብር መቀበል፣ መክፈል ያልቻለውን መረሸን፣ በአዲስ አበባ አነስተኛ ስራ ሰርቶ ቤተሰቡን እንዳያስተዳድር መከልከል፣ እምነቱን በነፃነት እንዳያከናውን ማድረግ፣ የኦርቶዶክስና ሙስሊም እምነት ተከታይ የሆነ ከየመስሪያ ቤቱ በአማራነቱ በገፍ እንዲባረር በማድረግ መጠነ ስፊ እና ዘግናኝ ግፍ እየደረሰበት ይገኛል። ከዚህ ሁሉ በባሰ መንገድ ደግሞ ደም የጠማው የአብይ ኦነጋዊዉ ስብስብ፣ የአገር ድንበር መጠበቅ፣ ሉአላዊነት ማስከበር ሲገባው፣ አገሪቱን በሱዳንና ደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች አስወርሮ ምንም ለመከላከል ሙከራ ሳያደርግ በተቃራኒው ያለ የሌለ የጦር ኃይሉን ወደ አማራ ክልል በማዝመት ህዝቡን እየጨፈጨፈ ለድፍን ሶስት ወራት ቀጥሏል። አሁን ደግሞ ሆን ብሎ በጦር ሜዳ ተሸንፎ እንዳይወገድ ከታደገው ከህወሓት ጋር በመቀናጀት አማራውን ለማንበርከክ የማንነቱ ምልክት የሆኑትን ወልቃይትና ራያን በድርድር ስም በማደናገር ወይም በጦር ኃይል አሸንፎ ለህወሓት ለማስረከብና አማራውን ወደ ዳግም የባሰ ባርነት ለመክተት ዝግጁቱን እንዳጠናቀቀ ለመረዳት ችለናል።
የአማራው የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነው ፋኖ በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎንደርና ጎጃም ለአማራው ህልውና፣ ለኦርቶዶክስና እስልምና እምነቶች መከበር ብሎም ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለመታደግ ቀበቶውን አጥብቆ፣ ነፍጡን አንስቶ ጠላትን እየጣለ መስዋእትነትን እየከፈለ ይገኛል።
አብይ አህመድ አማራውን ብሎም የአዲስ አበባን ህዝብ በርሃብ ለመፍጀት ለአማራ ገበሬወች የአፈር ማዳበሪያ በመከልከል ገበሬው ዘር መዝራት ሲገባው ሆን ተብሎ የማዳበሪያ ስጡን አቤቱታ ሰልፍ ላይ እንዲጠመድ ተደርጓል።
የቁርጥ ቀኑ የአማራ ፋኖ በህዝቡ ሙሉ ድጋፍ የወራሪውን የአብይን የኦነግ ሰራዊት አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ብዙ የአማራ ከተሞችንና ቀበሌወችን የአብይ ተላላኪ ከሆነው ከብአዴን የግፍ አገዛዝ ነፃ እያወጣ፣ ከህዝቡ የተውጣጡ አስተዳደራዊ መዋቅር እየመሰረተ ቀጥሏል። በአማራው ፋኖና ህዝቡ ተናቦ እያመጣ ባለው እምርታዊ ለውጥ ከፍተኛ ስጋት ላይ የወደቀው የአብይ እህመድ አስተዳደርና ተላላኪው ብአዴን በአገር ሽማግሌ ወይም በሰፈር ድርድር አመካኝቶ እየተቀጣጠለ የመጣውን የአማራ ትግል ላይ ውሃ ሊቸልስበት እያሴረ ይገኛል። ከሰሞኑም በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በኩል በየወረዳዉ አስታራቂ ሽማግሌወች ተወክለው እንዲመጡ ትዕዛዝ መስጠቱን ከራሱ አንደበት ተሰምቷል። በመሰረቱ የፓለቲካ ጥያቄዎች ብሎም የነፍጥ ትግል መቋጫው ሙሉ ለሙሉ በማሸነፍ ወይም በድርድር መሆኑን እንገነዘባለን። ነገር ግን የአማራው ግዙፍ የፓለቲካ የማነንነት፣ የህልውና፣ የነፃነትና ፍትህ ጥያቄወች በድርድር ሰበብ በተሸረበ ሴራ መፍትሄ ሊመጣ እንደማይችል ሁሉም ታጋይ የሚስተው ጉዳይ አይደለም። ለአማራው ውድ ህይወታቸውን ለመሰዋት የተሰለፉ ኃይሎች የመከሩበት፣ አጀንዳ የቀረፁበት ብሎም ገለልተኛ ዓለም አቀፍ አደራዳሪ ኃይል የሚሳተፍበት ድርድር ጊዜውና ሁኔታው ሲፈቅድ ማድረጉ ተገቢ እንደሆነ እናምናለን። ከዚህ የተለየ በድርድር ሰበብ የሚደረግ የሽምግልና ወይም የድርድር ማደናገሪያ ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም።
ሌላው መታሰብ ያለበት ዋናው ነገር አብይ እህመድ የኦነግ ሰራዊቱንና በኦነግ ስር የወደቀውን መከላከያ ሰራዊቱን አቀናጅቶ ፋኖን ለማጥፋት ለሶስት ወራት ቢራወጥም ስለከሸፈበት አሁን እማራውን እርስ በእርሱ ተዋግቶ እንዲተላለቅ የአማራውን ሚሊሺያ፣ ፓሊስ፣ አድማ ብተና ብሎም የሰላም አስከባሪ ኃይል በሚል አማራው ክልል ውስጥ በብዛት እያሰለጠነ መሆኑ ለማወቅ ችለናል። አማራው ራስ በራሱ ከመጠፋፋት አፈሙዙን ወደ አብይ አህመድ ሥርዓትና ወደ ህወሓት ማዞር ያለበት መሆኑን ለማስገነዘብ እንወዳለን። ኦነግና ህወሓት ሁሉንም አማራ በጠላትነት እንደሚያዩት ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለበትም።
አብይ አህመድ አማራውን በወደብ ይገባናል ሰበብ ከኤርትራ ጋር ለማዋጋት ወይም ለማቃቃር እየሰራ መሆኑ ይታወቃል። መቸም አማራው ለህልውናውና ማንነቱ መከበር እያደረገ ባለው ትግል ወዳጅና ጠላቱ ማን እንደሆነ ለይቶ ስለተረዳ ለዚህ የአብይ ቅዠትና ሴራ ይጠለፋል ብለን አናምንም፣ መሆንም የለበትም።
አማራው ህልውናውንና ማንነቱን አስከብሮ ኢትዮጵያን ከመፍረስ በመታደግ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ሰላም ፍትህና ዕኩልነት ሊረጋገጥ የሚችለው በ1983 ዓመተ ምህረት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተጫነውን ዘረኛውንና አረመኔውን የኦነግ/ ህወሓት ስርዓት ከስሩ መንግሎ የስርዓት ለውጥ ማምጣት ሲቻል ብቻ መሆኑን ተገንዘቦ ይህን ለማሳካት የሚያስችለውን የጀመረውን አስተማማኝ የትግል ስልት አጠናክሮ መቀጠል
ይህ በፋኖ መሪነት በመሬት ላይ እየተቀጣጠለ ያለው የአማራ ህዝብ ተጋድሎ በውጭ በሚኖረው አማራና ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እናምናለን። ይህን ለማሳካት ለተጀመሩ የዲፕሎማሲ ጥረቶች ዲያስፖራው ጠንካራ ርብርብና ድጋፍ ማድረግ ይገባዋል፣ እያደረገም ነው።
ከአብይ አህመድ የኦነግ አፓርታይዳዊ አገዛዝ በአጭር ጊዜ አማራውንም ሆነ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ነፃ ለማውጣት እንዲቻል የሚከተሉትን የትግል ጥሪዎች እናቀርባለን፦
- የአማራ ህዝባዊ ግምባር፣ የአማራ ህዝባዊ ኃይል፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በሸዋ፣ የምስራቅ አማራ ፋኖ፣ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር፣ የወሎ ፋኖ፣ የቤተ አማራ ፋኖ የጀመሩትን የአማራ የህልውና ተጋድሎ ተናበው እየሰሩ ያሉትን አጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ የተቀናጀ የዲፕሎማሲና ሰብአዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ጠንክሮ መሰራት እንዳለበት ጥሪ እናደርጋለን። ይህንንም ትግል በአግባቡ ለመምራት የአማራ ህዝባዊ ግምባር መሬት ላይ የጀመረውን አመራር አጠናክሮ መቀጠል እንዲሁም በውጭ ግምባሩ ያቋቋመው የድጋፍ ግብረ ኃይል በውጭ የሚደረገውን ድጋፍ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲያስተባብር ዲያስፖራው ያለሰለሰ ድጋፍ ማበርከት ይኖርበታል።
- የአማራ ሚሊሺያ ፓሊስ አድማ ብተና ሰላም አስከባሪ ኃይል በሙሉ የአማራ ፋኖ ነፃ አውጭ እንጂ ጠላትህ ባለመሆኑ ጊዜ ሳታጠፋ ከፋኖ ጋር በመወገን በአማራው ጠላቶች ላይ እንድትነሳ ጥሪ እናቀርባለን።
- የአማራ አርሶ አደር በሙሉ የአፈር ማዳበሪያ እንዳታገኝ የተደረግኸው ማዳበሪያ ጠፍቶ ሳይሆን አንተንና ከተሜውን በርሃብ ለማንበርከክ ስለሆነ ዘላቂ መፍትሄው ከማዳበሪያ ማግኘት በዘለለ ይህንን አድሎአዊና ዘረኛ ስርዓት ማስወገድ በመሆኑ በልጆችህ የተጀመረውን የህልውና ትግል አጠናክረህ እንድትደገፍ ጥሪ እናደርጋለን።
- የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የኦነግንና ህወሓትን ኢትዮጵያን የማፍረስና ሁለት አዲስ አገራትን የመፍጠር ሴራ ተገንዝበህ፣ በአስቸኳይ በፋኖ ላይ ያነሳኸውን ነፍጥ ወደ ዘረኛው የአብይ አህመድ ስርዓት እንድታዞር እንጠይቃለን::ይህን በማድረግ አገርህን ከመፍረስ፣ እምነትህንና የእምነት ቦታህን ከመውደም ለመታደግ፣ ቤተሰቦችህን ከመገደል ወይም ከስደትና መፈናቀል ለማዳን ትችላለህ።
- በሽምግልናና የሰፈር ድርድር ሰበብ የአማራውን የህልውና ትግል ለመጥለፍ በሚደረገው የኦነግና ህወሓት የተቀናጀ ሴራ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ስርአዓቱን ለማስቀጠል እየተባበራችሁ ያላችሁ ወገኖች ከዚህ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ጥሪ እናቀርባለን።
- በአማራ ብልፅግና ውስጥ ያላችሁም ሆነ በአማራው ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ የመረራችሁ የአማራውን ፋኖ የህልውና ትግል ሳታመነቱ እንድትደግፉ እንጠይቃለን።
- ኦነጋዊው አብይ አህመድና ህወሓት በቅንጅት የማንነት መገለጫወችህን ወልቃይትና ራያን ለዳግም ፍጅትና ባርነት ሊዳርጓቸው ዝግጅታቸውን ስለጨረሱ ሁሉም አማራ ሆ ብሎ በመነሳት ይህን ቅዠታቸውን ከጅምሩ የማምከን እንቅስቃሴ እንዲያደርግ አአስቸኳይ ጥሪ እናደርጋለን።
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ምዕመናን ካህናት፣ የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ እንዲሁም በሌሎች እምነት ውስጥ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ይህንን ኦርቶዶክስንና ሙስሊሙን ሊያጠፋ የመጣ ኃይል ከስሩ ነቅሎ አገርን ከመፍረስ በማዳን ፍትሀዊ ስርዓት ለማምጣት የተጀመረውን የአማራ ህልውና ብሎም የኢትዮጵያ ነፃነት ትግል እንድትደግፉ ጥሪ እናቀርባለን።
- የህወሓትን አገርን የማፍረስ፣ ሃይማኖትን የማፋለስ ሴራ ያለወገዘው የትግራይ ህዝብ በኢትዮጵያና በራሱ በትግራይ ህዝብ ላይ ህወሓት ያደረሰውንና እያደረሰ ያለውን ጥፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት የኦሮሞ ህዝብ በስምህ እየነገደ ያለውን የአብይ አህመድ አገር የማፍረስ፣ ሃይማኖት የማፋለስ፣ ከአማራው ወገንህ ጋር ደም የማቃባት ሴራውን በአስቸኳይ እንድታወግዝና ለፍትህና ለአገር አንድነት ከሚታገሉ ኃይሎች ጎን እንድትቆም ጥሪ እናደርጋለን።
- በውጭ የምትገኘው አማራ የአገር አንድነት ሃይማኖትህና ፍትህ መስፈን የሚያሳስብህ ኢትዮጵያዊ በሙሉ የአብይን አፓርታይዳዊ ሥርዓት ለመገርሰስ የሚዋደቀውን የአማራ ህልውና ትግል በቁርጠኝነት እንድትደግፉ ጥሪ እናቀርባለን።
- አገርን ከመፍረስ፣ ሃይማኖትን ከመፋለስ ሊታደግ የሚያስችል የሥርዓት ለውጥንና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን ያካተተ እውነተኛ ድርድር ላይ የአማራ ህልውና ታጋዮች መሳተፍ እንድሚገባ ዝግጁነትን ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው በፅኑ እናምናለን።
የአማራው ህልውና፣ ፍትህ፣ ዕኩልነት፣ የእምነት ነፃነትና የኢትዮጵያ አንድነት በተባበረ ክንዳችን ይረጋገጣል!!!