የሞኝ ሳቅ ወይ አለማወቅ

359838387 10232227475975917 5713408187103420016 n ኢትዮጵያም ሆነ ዜጎቿ በፖለቲካ ዉሳኔ ቁም ስቅል ማየት ከጀመሩ ድፍን ሶስት አሰርተ ዓመታት ተቆጥሯል፡፡

ይሁንና ዛሬም እንደትናንቱ የሞኝ ዘፈን እየዘፈነ በሞቱ የሚደሰት መኖሩ ምን ያህል አይነ ህሊናችን መጋረዱን፤ ንቃተ ህሊናችን መዝቀጡን ያሳያል፡፡

በኢትዮጵያ በአገር እና በህዝብ ላይ የደረሰዉን እና እየደረሰ ያለዉን ጥላቻ ስሩ የሆነዉን የፖለቲካ አስተሳሰብ እና ርዕዮተ ዓለም ለምን ብለዉ በግልፅ እና በአደባባይ የነበረዉን ፣የሆነዉን እና እየሆነ ያለዉን የሞገቱ እና ስለዕዉነት የሞቱ በአድር ባዮች እና በመኃል ሰፋሪዎች ትብብር የከፈሉት ዋጋ በማርከስ የገር እና የሕዝብ መከራ በማያባራ ጥላቻ ወለድ የክህደት ናዳ ታድሶ እንዲቀጥል ሆኗል፡፡

ያኔ እነ ፕ/ር አስራት አንድ አገር ፣አንድ ህዝብ ….ብለዉ ለህዝብ እና ለአገር ምስክርነት ሲቆሙ የሰማቸዉም ሆነ ጥሪያቸዉን ተረድቶ የተከተላችዉ እንዳዘሬዉ ያኔም በቁጥር ትንሽ በአላማ እና በአርቆ አስተዋይነት ግን ዕልፍ ነበሩ ፡፡

ያኔ የሆነዉ ዛሬ እየሆነ ያለዉ ነዉ ፡፡ ያንጊዜ አንድ አገር፣ አንድ ህዝብ ፣ አንድ ኃይማኖት ….የሚሉ የአገር እና የሕዝብ ወዳጆች የፖለቲካ ስርዓቱ (ኢህአዴግ) ቀንደኛ ጠላቶች ሆነዉ በማያወላዳ ሁኔታ በህግ እና በፖለቲካ ልባስ በጥላቻ ዘመቻ ለድፍን ሶስት አሰርተ ዓመታት ተወግዘዋል ፤ተዳክመዋል፡፡

በጥላቻ እና በእኛ ብቻ  የሰርዶ በል አስተሳሰብ በህገ-ኢህዴግ እና ፖለቲካ ዉሳኔ ኢትዮጵያዊነት ፣የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ  ፣የኢትዮጵያ አንድነት ፣ የክርስትና ዕምነት እና አመለካከት፣ የባህር በር መኖር የሚሻ የአሀዳዊነት እና አንድነት ናፋቂ  ዓማራነት እና ትምክህት በሚል የኢትዮጵያ ጠላቶች አጥቂ እና ኢትዮጵያዉያን ተጠቂ መሆናቸዉ የእያንዳንዱን ቤት የትፋት ሰደዱ እስኪያቃጥለዉ ብርቅ እና ድንቅ ሶስት ቀን ነዉ እያለ ዛሬን ደረሰ ፡፡

በሁሉም የአገሪቷ ክፍል ለዘመናት ሠዎች በማንነታቸዉ  እና በኢትዮጵያዊነታቸዉ  እንደ ወተት እየተገፋ ፣ እንደ ጥራጊ እየተደፋ እያየ እንዳላየ ያለፈ ጎረቤት ብቻ አልነበረም ፡፡ በህዝብ ስም  የሚኖር ተቋም ሁሉ ነበር ፡፡ ተቋማት የሚቆሙት እና የሚቆቋሙት ለሰዉ እና በሰዉ መሆኑን ከመርሳታቸዉ በላይ ተቋማቴም ሆነ አገር ሠዉ መሆኑን መረሳታቸዉ ለራሰቸዉ ተድላ ብቻ እንደሚኖሩ መስማት አለመፈላጋቸዉ ነበር ፡፡

ሁሉም በህዝብ እና አገር ስም ተቋቁመዉ ህዝብ እና አገርን መገልገል እንጂ ማገልገል የማይችሉትን ትተን የዕምነት ተቋማት በተለይም ቤ/ክርስቲያን ዕምነትም ፤አገርም ሠዉ ነዉ አለማለታቸዉ ትናንት በስዉር በቤተ ክርስቲያን ሲሆን የነበረዉ ቤተ ክርስቲያንን እና መኢመናንን የመለያየት ደባ በግላጭ ወደ ፖለቲካ አሰላለፍ እና ጥልፍልፍ ተደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን  በጥንታዊ መሰረት እና ሀብት የትኛዉም ዓለም ሊወዳደር እና ሊገዳደር የሚችላት እንዳልሆነች ጠላት ዲያቢሎስ ያዉቃል፡፡ ነገር ግን እንደ ዓለማዊ አስተዳደር የቤ/ክርስቲያን አስተዳደር ቤተ ክርስቲያን ማላት ሠዉ ነዉ ፤ከርስቶስ ሠዉ የሆነዉ ፤ሠዉ ሆኖ ሠዉን ለማዳን ሞቶ የተነሳዉ ለሠዉ ነዉ የሚል ባለመኖሩ እና ቸልተኝነት በቤተ ክርስቲያን ስርዓት መፋለስ ጠንቅ መሆን ነዉ ፡፡

ለአብነት አቡነ መርቆርዮስ በህይወት ሳሉ ፤ በሌላ ሲተኩ ፤ በአገር እና በህዝብ ላይ የሆነ መከፋፈል የክርስቶስ እንዳልነበር መመስከር አለመቻል፣ ይባስ ብሎ ኢትዮጵያን ብሎም የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያን ግዛቶች ለማፈራረስ እና ለመቁረስ ህወኃት ጦርነት አዉጆ  ለሁለት ዓመታት አሰቃቂ እና በታሪክ እና በትዉልድ አሳቃቂ ሠባዊ እና ቁሳዊ ዉድመት ማድረሱ ዓለም እያወቀ የእኛ ቤ/ክርስቲያን ሆነች የትቃቱ ሠለባ የሆነዉ ሠፊዉ ህዝብ ይቅርታ ሊጠየቅ፣ ከሳ ሊጠይቅ  እንዲሁም መብቱን ፣ሀብቱን ፣ማንቱን፣ ዳር ድንበሩን ….ላጣበት እና ለሳጣዉ  ህወኃት  በዓለም ህዝብ ፊት ሊጠይቅ እና ሊጠየቅለት ሲገባ ይቅርታ እንዲጠየቅ መፈለግ ሳይተርፈዉ ያበደረ ሳይቀበል ይሞታል ሆኗል፡፡

ለመሆኑ ዛሬ የትግራይ የቤተ ክርስቲያን አባቶች የቤተ ክርስተያንን ስርዓት እና ቀኖና ጥሰዉ የራሳቸዉን አደረጃጀት ፈጠሩ ብሎ መድከም እንዴት ይሆናል ፡፡ መጀመሪያ ዕመውነት እና ፍቅር ባልነበረበት ወይም በግላጭ ጥላቻ በነገሰበት እንዴት የኢትዮጵያን አገርነት ፣ የህዝቦችን ወገንነት የናቁ የማይታየዉን ክርስቶስን ሊያወቁ እና ፈሪኃ እ/ብሄር አድሮባቸዉ ከክፉ ነገር ሊጠነቀቁ ይችላሉ ፡፡

የኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ልጆች አይደሉም  ኢትዮጵያዉያን ከኢትዮጵያ ኦ/ስ ቤተ ክርስቲያን ጎን አይደለም ፊት ለፊት ነበሩ ፤ናቸዉ ፡፡ ይህ የምንለዉ ሁሉም ኢትዮጵያዉያን ኤደለም ዓለም የኢትዮጵያ ኦ/ስ ቤ/ክ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ድህነት ብቻ ሳይሆን ለመላዉ የሰዉ ልጂ ነፃነት እና ድህነት በተለይም ለጥቁር የሰዉ ልጆች ህልዉና ባለዉለታነቷን የዳኑት ቀርቶ ሊያጠፏት የሚኳትኑ ጠላቶች ከመናገር በላይ በተግባር ለጥፋት የማይቆርጡት ቅጠል ፤የማይወጡት ገደል አለመኖሩን መረዳት አለብን፡፡

አባታችን አቡነ ጴትሮስ ደረታቸዉን ለመተረየስ የሰጡት  ለኢትዮጵያ  ነበር ፡፡ ኢትዮጵያም ማለት ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ ፡፡ ኢትዮጵያዉያን ምንም  ይሁኑ ምን ፣ የትኛዉንም ዕምነት ይከተሉ  ዛሬ እኛ የምናጣላባትን ፤ጠላቶቿ የሚጠሏትን ኢትዮጵያ በህይወት እና በሞት መገኘቷን ነዉ፡፡

እነ አቡነ ተ/ኃይማኖት ህዝቤን ትተህ እኔን በማለት ከቀድሞዉ የኢትዮጵያ መሪ ኮ/ል መንግስቱ ኃ/ማርያም ጋር ፊት ለፊት ሲጋፈጡ የነበሩት አገልግሎቴም ፤ሞቴም ለሠዉ ነዉ ሠዉ በሌለበት አገር እና ኃይማኖት ባዶነት የወረሰዉ ንብ አልባ ቀፎ ነዉ ብለዉ ነበር ፡፡ ይህም ህዝብ እና አገር ከማስከበር በላይ የነበረዉን የፖለቲካ አስተሳሰብ በመግራት ራሳቸዉ ተወደዉ እና ተከብረዉ በፍቅር እና በክብር ማለፋቸዉ ብቻ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን እንዳዘሬ አልተደፈረችም ፡፡ እንኳን ቤ/ክ ት/ቤቶች እንኳ ክብር እና ፍቅር ነበራቸዉ ፡፡

አሁንም  ሳያዉቅ የሚስቅ ሞኝ መሆናችን የጨዉ ክምር ሲናድ ሞኝ ይስቃል ብልህ ያለቅሳል እንዲሉ ሁሉም በአገር ነዉና የማንኛዉም ዕምነት እና ኃይማኖት በአገር መሆኑን አዉቀን ኢትዮጵያን እንበል ያኔ ኢትዮጵያን የሚል ሁሉ የኢትዮጵያን ምሰሶ እንዳይላላ ዘብ ይቆማልለ፡፡

“ምንጊዜም ለነፃነት ዘብ መቆም ለነፃነት የሚሰጥ ዋጋ ነዉ ፡፡”

“ጠላት ጠላት ነዉ፡፡”

አንድነት ኃይል ነዉ

አለን ዘ ብሄረ አምበር

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Amhara
Previous Story

ያማራ ሕዝብ ዐብይ ስሕተት፤ በማንነቱ የሚጠሉትን ለመውደድ መሞከር

FB IMG 1690100013095 1 1
Next Story

ስለምን እንክርዳድ ዘርተን ስንዴ ማጨድ አማረን? – በዳዊት ሳሙኤል

Go toTop