July 2, 2023
42 mins read

ሃገራችንን ከመፍረስ፣ አዲስ አበባን ከጥፋት እንታደግ፣ – ደረጀ ተፈራ

Adanech Abebe 1 1 1

1.መግቢያ
ጥንታዊ ሮማውያን “Barbarians at the Gate” የሚል አገላለፁ ነበራቸው። አባባሉ የቆየ ታሪክ ያለው ሲሆን ህግና ስርዓት የማያውቁ አረማውያን የሮማን ከተማ በመንጋ በመውረር በከተማው ላይ ያስከተሉትን ውድመትና በነዋሪው ህዝብ ላይ የፈጸሙትን ተደጋጋሚ ዝርፊያና ፍጅት ለመግለጽ የተጠቀሙበት አባባል (Metaphor) ነው። በቅድመ ታሪክ እስካንዴኔቪያን ተብሎ በሚጠራው ሰሜን አውሮፓ አሁን ኖርዌይ፣ ስዊድንና ዴንማርክ በሚባሉት ሃገራት በአነስተኛ ግብርና፣ አሣ በማጥመድ፣ በባህር ላይ ንግድ እና ዝርፊያ (pirates) ላይ ተሰማርተው ይኖሩ የነበሩ ቫይኪንግ ወይም ኖርስ (Vikings/ Norse) የሚባሉ ማህበረሰቦች ነበሩ። እነዚህ ማህበረሰቦች በቤተሰብና በነገድ ተሰባስበው የሚኖሩ፣ በዛፍ፣ በተራራ፣ በውሃ፣ በመብረቅ እና በመሳሰሉ ተፈጥሮዎች ያመልኩ የነበሩ አረማዊ (Pagan) ሲሆኑ፣ ከዚሁ ቀድሞ ይኖሩበት ከነበረው አካባቢ በመነሳት ወደ ምዕራብ፣ መካከለኛው እና ወደ ቀረው የሰሜን አውሮፓ አካባቢዎች በመፍለስ ህጻን አዋቂ ሳይሉ ይዘርፉና በጭካኔ ይገድሉ ነበር። ለምሳሌ በ793 AD በሰሜን ኢንግላንድ ሊንዲስፌርን (Lindisfarne) በተባለ ቦታ የሚገኝ ገዳምን በመውረር በመነኮሳቱ ላይ አሰቃቂ ግድያና ዝርፊያ ፈፅመዋል። እንዲሁም በ911 AD ቻርለስ 3ኛ የተባለ ንጉስ በፈረንሳይ በነገሰ ጊዜ ሃገሩን ወረው በማስገደድ ኖርማንዲ (Normandy) በምትባል የፈረንሳይ ግዛት ላይ እንደሰፈሩ በታሪክ ይታወቃል። እዚህ ላይ ማስታወስ የሚገባን ነገር የቫይኪንግ ህዝቦችን ሁል ጊዜ ከጥፋት ጋር ማገናኘቱ ተገቢ አለመሆኑ ነው። በእርግጥ የቫይኪንግ ማህበረሰቦች ከእስካንዴንቪያን ምድር ተነስተው ነባሩን የአውሮፓን ህዝብ በመውረር የፈፀሙት ጥፋት ባይካድም በሌላ በኩል ደግሞ የመርከብ አሰራር ጥበብን፣ የባህር ላይ ጉዞን፣ አዳዲስ ደሴቶችን ፍለጋን (Ocean Navigation)፣ የባህር ላይ ንግድን እና የመሳሰሉትን ለነባሩ የአውሮፓ ህዝብ አስተዋውቀዋል፣ የእስካንዴንቪያን ህዝብንም ከሌላው የአውሮፓ ህዝብ ጋር በደም፣ በባህልና በቋንቋ ቀላቅለዋል።

እንደሚታወቀው ከጥንት ግዜ ጀምሮ በአደንና በተፈጥሮ የበቀሉ ዕፅዋትን በመሰብሰብ ይኖሩ ከነበሩ ማህበረሰቦች ጀምሮ፣ ከብት በማርባትና በግብርና ህይወቱን እስከሚመራው ብሎም እስካለንበት ዘመን ድረስ ሰዎች በኑሮ፣ በጦርነት፣ በረሃብ፣ በወረርሽኝ፣ በእምነት ምክንያት፣ በኢኮኖሚ ችግር፣ በተፈጥሮ ሃብት መመናመን እና በመሳሰሉት ምክንያቶች ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ሊሰደዱና ሲስፋፉ ኖረዋል። አዳም ከገነት ተሰዷል፣ በእምነት አባታችን የምንለው አብርሃም ከደቡባዊ ሜሶፖታሚያ ኡር ከምትባል ከተማ ተነስቶ እስከ ከንአን ምድር ተሰዷል። ሌላው ደግሞ ከላይ የተጠቀሱት የቫይኪንግ ህዝቦች በተጨማሪ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ኤስያ ድረስ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ከብት በማርባት ይኖሩ የነበሩ የሞንጎሊያ ፈረሰኞች (Mongols) እናገኛለን፣ ለእንግሊዝ እንደ ሃገር መፈጠር እርሾ የሆኑትን አንግሎ፣ ሳክሶን እና ጁትስ (Anglo, Saxon and Jutes) የሚባሉ ከጀርመን የፈለሱ ነገዶችን ናቸው። በትንሿ ኤስያ አናቶሊያ (Anatolia) በሚባል አካባቢ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ከብት በማርባት ይኖሩ የነበሩ የቱርክ (Turks) ነገዶች ለኦቶማን ኢምፓየር መፈጠር መነሻ ምክንያት ናቸው። ወደ አፍሪካ ስንመጣ ደግሞ በናይጄሪያ እና በካሜሩን ድንበር አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ባንቱ (Bantu) የሚባሉ ህዝቦች ከምዕራብ አፍሪካ ተነስተው ወደ ምሥራቅ አፍሪካ፣ መካከለኛው እና ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመፍለስ ቀደምት የአካባቢውን ነዋሪ ህዝቦችን ባህል ቋንቋ እና ማንነታቸውን አጥፍተዋል። ይሁን እንጂ አሁን በኮንጎ፣ በኬንያ፣ በሞዛንቢክ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በአካባቢው ለሚገኙ በመቶ ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የባንቱ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች መፈጠር ምክንያት ሆነዋል።

ወደ አውሮፓ የቫይኪንግ ህዝቦች ፍልሰትና ወረራ ስንመለስ እንደሚታወቀው የሮማን ኢምፓየር መንግስት ሃያል በነበረበት ጊዜ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ የአውሮፓ ጫፍ፣ ከሰሜን ብሪቴን እስከ ሜዲትራሊያን የባህር ዳርቻ የሚገኙ የሰሜን አፍሪካ አገሮችን፣ እንዲሁም የመካከለኛ ምስራቅን እና ትንሿ ኢስያን የሚያጠቃልል ነበር። የሮማን ኢምፓየር ግዛት ሰፊ በመሆኑ ከሮም ከተማ ሆኖ አጠቃላይ ግዛቱን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ በየግዛቱ ለሚያሰማራው ወታደር የሚከፈል ወጪ በየጊዜው እየጨመረ ሄደ። ከዚህም የገንዘብ/ የኢኮኖሚ ችግር ጎን ለጎን በሮማን የጦር መኮንኖቹ መሃል በተፈጠረ የስልጣን ሽኩቻና የሙስና አሰራር ምክንያት በ4ኛው መቶ ክ/ዘ ላይ ምዕራባዊ እና ምስራቃዊ የሮማን ኢምፓየር ተብሎ ለሁለት ተከፈለ። መቀመጫውን በጥንቷ የሮም ከተማ ያደረገው ምዕራባዊው የሮማን ኢምፓየር በየጊዜው ከጀርመን ምድር እየፈለሱ ወደ ሮም ከተማ የሚመጡ ማህበረሰቦች ለመቆጣጠር ከመሃላቸው የእነሱን ቋንቋ የሚናገሩትን መልምሎና አሰልጥኖ በመቅጠር ፍልሰቱን ለመቆጣጠር ቢሞክርም ተቀጣሪ ወታደሮች ከጎሳዎቻቸው ጋር እየተመሳጠሩ ችግሩን ይበልጥ አባባሱት። በመሆኑም መቀመጫውን የሮም ከተማ ያደረገው ምዕራባዊው የሮማን ኢምፓየር በነበረበት ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ለጥቂት ዘመናት ሲንገታገት ከቆየ በኋላ ከጀርመን ምድር የራይንን (Rhine) ወንዝ እየተሻገሩ ወደ ሮም ከተማ ያለማቋረጥ በሚፈልሱ ማህበረሰቦች (ጎሳዎች) የሮም ከተማ ተጥለቀለቀች። የከተማው ህዝብ ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ሄደ። ከተማዋ የምግብ አቅርቦት፣ የጤና እና የንጽህና አጠባበቅ ችግር አጋጠማት። የህዝቡ ብዛት የከተማው ኢኮኖሚና መሰረታዊ ልማት ሊሸከመው ከሚችለው አቅም በላይ እየሆነ መጣ፣ ስርዓት አልበኝነት በመስፋፋቱም በከተማው ዝርፊያና ቅሚያ ተበራከተ፣ የእምነት ተቋማት ረከሱ፣ መነኮሳት በቤተ መቅደስ ውስጥ ታረዱ፣ ሴቶች ተደፈሩ ማህበራዊ እሴቶች ተናጉ። ባጠቃላይ በሃገሩ ህግና ስርዓት ተፋለሰ፣ ከጥንት ጀምሮ በትውልድ ሲገነባ የመጣው የሮም የስነ መንግስት ስልጣኔና ታሪክ ፈራረሰ። የህዝቡ ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሮም ኢኮኖሚ ሊሸከመው ከሚችለው አቅም በላይ ሆነ። ዝርፊያ፣ ቅሚያ፣ ጩኸት እና አምባጓሮ እየተበራከተ በመምጣቱ ህዝቡ መኖር የማይችልበት ደረጃ ደረሰ፣ ውንብድናና ስርዓት አልበኝነት ነገሰ፣ የሮም ከተማ በችግሮች ተወጠረች። በመጨረሻም የከተማዋ ነዋሪ ስርዓት አልበኞችን በጊዜ አደብ ማስገዛት ባለመቻሉ፣ ዓይኑ እያየ ሃገሩ እጁ ላይ ፈራረሰች። ያቺን ጥንታዊት እና የጠቢባን ከተማ የሚታደጋት አጥታ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ህግን በማያውቁ በስርዓት አልበኛ ወራሪዎች ወደመች።

2.በሃገራችን የተደረገ የህዝቦች ፍልሰትና ውህደት (ባጭሩ)፣
ወደ ሃገራችን ስንመጣ ደግሞ በዮዲት ጉዲት ጦርነትና በአክሱም መንግስት መፍረስ የተነሳ፣ በቱርኮች እና በአረቦች፣ በሚሲዮናውያን እና እየሱሳውያን በፈጠሩት የእምነት፣ የፖለቲካና ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት፣ በዘመነ መሳፍንት በነበሩ የርስ በርስ ጦርነቶች፣ ፋሽስት ጣሊያን በከፈተብን ቀጥተኛ የወረራ ጦርነት፣ እንዲሁም በየዘመናቱ በተከሰቱ የውጪና የርስ በርስ ጦርነቶች፣ በዝናብ እጥረት፣ በረሃብ (በድርቅ)፣ በወረርሽኝ፣ በአርብቶ አደር ማህበረሰቦች በውሃና የግጦሽ መሬት ፍለጋ አሁን ደግሞ በዘር ፖለቲካ በፈጠረው ጥላቻ እና መለያየት ምክንያት ከአንዱ ወደ ሌላው የሃገራችን ክፍል የህዝቦች ፍልሰትና ስደት ተከናውኗል። ለምሳሌ ይልማ ደሬሳ የተባሉ በቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዘመን በሚኒስቴርነት ያገለገሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ከአባቶቼ በቃል ሲወርድ የሰማሁትና ከታማኝ ምንጮች ያነበብኩት ነው በማለት “የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን” በተባለ መጽሐፋቸው “ኦሮሞዎች ወደ ደጋ ኢትዮጵያ መውጣት” በሚል ምዕራፍ ስር ስለ ጥንታዊ የኦሮሞ ከብት አርቢ ጎሳዎች ወደ መሃል አገር አመጣጥ በተመለከተ እንዲህ ይላሉ፦ መጀመሪያ በባሊ ቆላማ አካባቢዎች በመቀጠልም ቀስ በቀስ ወደ ደጋማው የባሊ ተራራማ አካባቢዎች እና ለአባያ ሃይቅ ቅርብ በሆነ ለከብቶች በቂ ውሃና የግጦሽ መሬት ወደ ሚያገኙበት ለምለም አካባቢ በመፍለስ ሰፈሩ። የሰፈሩበትንም አካባቢ በኦሮምኛ ቋንቋ “መደ ወላቦ” ብለው ጠሩት። ትርጉሙም የወላቦ ምንጭ ማለት ነው። የአካባቢው የተፈጥሮ ልምላሜ ስለተስማማቸው ከብቶቻቸው እጅግ እረቡላቸው፣ የህዝቡም ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ በመምጣቱ ለከብቶቻቸው የግጦሽ መሬት ጥበት አጋጠማቸው በማለት ታሪኩን ይቀጥላሉ። እንግዲህ በዚህ ወቅት ነበር ግራኝ አህመድ መቀመጫውን ሸዋ ላይ ባደረገው የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት መንግስት ላይ የጀሃድ ጦርነት ያወጀው። በመሆኑም ግራኝ አህመድ ዘርፎና አቃጥሎ ያለ ጠባቂ ያስቀራትን ሃገር የኦሮሞ አርብቶ አደር ጎሳዎች አጋጣሚውን በመጠቀም በአባ ገዳዎች (ሉባዎች) እየተመሩ ጦርነት ያደከመውን ህዝብ በቀላሉ እያሸነፉ በሃገሩ ላይ መስፈር የቻሉት። በኦሮሞ ጥንታዊ ጎሳዎች የተደረገ ፍልሰትና መስፋፋት ኢትዮጵያ የውህደት ሃገር መሆኗን ይበልጥ የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ በመሆኑ ኢትዮጵያውያንን ሊያቀራርበን እና አንድ ቤተሰብ መሆናችችን የሚመሰክር ሆኖ ሳለ የኦሮሞ ጠባብ ብሔርተኞች ታሪክን በታሪክነቱ በመቀበል እውነትን አምነው መቀጠል ሲገባቸው ወራሪ ተባልን በማለት አፍራሸ ትርጉም በመስጠት የልዩነትና የጥላቻ መቀስቀሻ አደረጉት። ሃላፊነት የማይሰማቸው፣ የሞያ ስነምግባር የሌላቸው ጠባብ የኦሮሞ ልሂቃን በዚህም ሳያበቁ ያለፈን ታሪክን ለመቀልበስ ከአዕምሮዋቸው አፍልቀው በምድር ላይ ያልተፈጸመ አዲስ ትርክት ጽፈው በማህበረሰቡ ውስጥ አሰራጩ፣ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ በተማሪው የመማሪ መጽሃፍ በማካተት ቂም ያረገዘ ጨካኝና ይሉኝታ የማያውቅ፣ ማህጸን የሚተረትር፣ ሃይማኖትም፣ ምግባርም፣ ሰብአዊነትም የሌለው የሰው ስጋ የሚበላ፣ ደም የሚጠጣ አረማዊ ትውልድ ፈጠሩ።
ግራኝ አህመድ ከ1521 እስከ 1535 ዓ/ም ለ14 ዓመታት ያለማቋረጥ ባደረገው ጦርነት ጭፍሮቹ ከሃገር ወደ ሃገር እየተዟዟሩ በርካታ የክርስቲያን መኖሪያ መንደሮችን እና ቤተክርስቲያኖችን በማቃጠላቸው ክርስቲያኑ ህዝብ ተወልዶ ባደገበት በሃገሩ ላይ ተንከራታች ስደተኛ ሆነ፣ ከቤቱና ከእምነቱ ተለየ። እምነቴን አልቀይርም ያለውን እያደኑ በባርነት በመሸጥና በማሰደድ ሃገሩን አራቆቱት፣ ካህናቱም ንዋየ ቅዱሳኑን፣ መጻህፍትን፣ ታቦታቱን እና የመሳሰሉትን በየዋሻውና ሃይቅ ደሴቶች ውስጥ ሸሽገው ተሰደዱ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የግራኝን ጦርነት ተከትሎ ጥንታዊ የኦሮሞ ከብት አርቢ ጎሳዎች ከጦርነት እና ከስደት የተርፈውን ህዝብ በመውረር ሞጋሳና ጉድፈቻ በሚባሉ ባህላቸው ኦወረሙት፣ ህዝቡም በጊዜ ሂደት የኦሮምኛን ቋንቋ እና ባህሉን እየለመደ ሄደ። በመሆኑም አሁን የሚገኘው አብዛኛው የኦሮሞ ህዝብ የኦሮምኛን ቋንቋ ይናገር ባህሉን ይተግብር እንጂ ቀድሞ የአማራ፣ የጉራጌ፣ የጋፋት፣ የከንባታ፣ ሃድያ፣ ወላይታና የመሳሰለው ህዝብ የነበረ ነው። ይህንንም በዘመኑ የነብሩ የዓይን አማኞች የጻፏቸው የታሪካ መዛግብት ያረጋግጣሉ። ከነዚህም ውስጥ የአባ ባሕርይ ታሪካዊ ሰነዶች፣ የቬኑሱ የፍራ ማውሮ የዓለም ካርታ፣ የአሕመድ ግራኝ የግል ታሪክ ጸሃፊ የነበረው አረብ ፋቂህ የተጻፈው ፉቱሕ አል ሀበሻ፣ ፖርቹጋላዊው ቄስ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የጉዞ ማስታወሻዎች እና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል። ከዛም በመቀጠል ቼሩሌ፣ ኸበርላንድ፣ ሃንቲንግፎርድ፣ ኤች ሊዊስ እና የመሳሰሉ የጻፏቸው የታሪክ መዛግብት እና የምርምር ጽሁፎች ይህንኑ እውነት የሚያረጋግጡ ናቸው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በ July 24 2017 ከአድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በመካከለኛው ኢትዮጵያ በርካታ የራሳቸው ማንነት ያላቸው ህዝቦች እንደነበሩና እነዚህ ህዝቦች ዛሬ የት ገቡ? ለተባሉት ጥያቄ ሲመልሱ: “ከ16ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ከግራኝ አህመድ ጦርነት በኋላ ባለው 50 ዓመት ጊዜ ውስጥ የኦሮሞዎች መስፋፋት ነበር። “ይሄን ነገር ብዙ ኦሮሞዎች *ይክዳሉ* በኔ በኩል ግን ተቀባይነት የለውም” በማለት አስረግጠው ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ የደቡብ እና የምስራቅ ኢትዮጵያ ማህበረሰቦች የሆኑት ሃድያ፣ ጉራጌ፣ ከንባታ፣ ሲዳማ፣ ሶማሌ፣ ሃረሪ (አደሬ)፣ እና የመሳሰሉት ስለራሳቸው ታሪክ በፃፏቸው ሰነዶች እና በትውፊት በየማህበረሰቡ የሚነገሩ ታሪኮች ይህንኑ የኦሮሞ ጎሳዎች መስፋፋትና ወረራን የሚያረጋግጡ ናቸው።
ዶ/ር ነጋሶ ለአድማስ ጋዜጣ ከሰጡት ቃለመጠይቅ በተጨማሪ “የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ” ብለው በፃፉት መጽሃፍ በገፅ 296 ላይ በወለጋ ገላን በሚባል አካባቢ የፈለሱበት ምንጫቸው ቦረና የሆኑ የመጫና የቱለማ ኦሮሞዎች ወደ አካባቢው ፈልሰው በመምጣት ኦሮሞ ያልሆኑ ጋንቃ፣ ማኦ፣ ክዋማና ክዌጎየተባሉ ነባር የኢትዮጵያ ህዝቦችን በወረራ አጥፍተው እንደሰፈሩበት ገልፀዋል። የሰዮ (ቄለም) ወለጋ አካባቢ የነበሩ ከአስር በላይ የሆኑ የአካባቢው ነባር (Native) ማህበረሰቦች ሞጋሳ (ሚቲቻ) በሚባል ባህል ኦሮሞ እንዳደረጓቸው የእሳቸውም ቤተሰቦች በኦሮሞ ጎሳዎች ወረራ ከጠፋ “ዳሞት” ከሚባል ማህበረሰብ የተገኙ መሆኑን ከላይ በተገለጸው ከአድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ አረጋግጠዋል። በመሆኑም ይህ የኦሮሞ ትውልድ ማንነቱን ወደ ኋላ ሄዶ ቢመረምር የዘር ሃረጉ ከጥንቶቹ ከቦረና እና ከባሬንቱ አርብቶ አደር ጎሳዎች ይልቅ በሞጋሳና በጉድፈቻ ወደ ኦሮሞነት ከተቀየሩት ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር መሆኑን በተረዳ ነበር። ጥንታዊ የኦሮሞ ጎሳዎች ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔሮች ጋር በፈጸሙት ውህደት ምክንያት አሁን ያለው የኦሮሞ ህዝብ አንድ ወጥ (Homogeneous) ሳይሆን ወደ 80% የሚሆነው ኦሮምኛን ቋንቋ ተናጋሪ ይሁን እንጂ በደሙ ቅልቅል ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ዶ/ር ሃይሌ ላሬቦ በተለያዩ ጊዜያት ከኢሳት ቲቪ እና ከአውስትራሊያው SBS አማርኛ ማሰራጫ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ መግለጻቸው ይታወሳል።.
እንደሚታወቀው ሰዎች ከአንድ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ የሚያደርጉት መስፋፋት፣ ስደት ወይም ፍልሰት በየትኛውም የዓለማችን እና የሃገራችን ክፍል የነበረና የሚኖር በመሆኑ በታሪክ የተፈጸመን ያለፈ እውነታን ተቀብሎ ወደፊት መራመድ ስልጡንነት ነው። ነገር ግን የኦነግ መስራች ጠባብ ብሔርተኞች ነገሮችን በክፋት መንፈስ በማየት ወራሪ ተብለን ተሰደብን በማለት የፓለቲካ አመጽ መቀስቀሻ በማድረግ የኦሮሞን ህዝብ ለዘመናት አብሮ ከኖራቸውና ከተዋለዳቸው ማህበረሰቦች ጋር ዙሪያውን ሲያናክሱት ኖረዋል። ኢትዮጵያ በ82 ብሔረሰቦች አጥንትና ደም ተጠብቃ የኖረች፣ በሁሉም አስተዋዕጾ የተገነባች የጋራ ሃገራችን ሆና ሳለ ኦነጋውያን ኢትዮጵያ አማራ ማለት እንደሆነች በአዕምሮአቸው ስለው ኢትዮጵያና አማራ አንድ ናቸው፣ ባንዲራውም የአማራ ነው፣ በአማራ የባህል ተጽዕኖ ደርሶብናል፣ የአማራ ዶሮ ወጥ፣ ሽሮ፣ ክትፎ፣ የአማራ ሸማ፣ አማርኛ ቋንቋ ወዘተ በማለት የጋራ የሆነውን ነገር ሁሉ ለአንድ ብሔር በማሸከም የባህል ተፅዕኖ እንደደረሰባቸው ይናገራሉ። እነሱ በእንግሊዝ ሱፍና በአሜሪካ ጂንስ ዘንጠው ሲወጡ፣ ቁራን በአረብኛ ሲቀሩና የልጆቻቸውን ስም በአረብኛና በፈረንጅ ቋንቋ ሲጠሩ ግን የፈረንጆች ወይም የአረቦች ባህልና ቋንቋ ተጽዕኖ ደረሰብን ሲሉ አይሰሙም። እነዚህ የአማራ ባህል ተጫነብን ብለው የሚወነጅሉ ነገር ግን ለጆሮ በሚለሰልስ የሽንገላ ቃላት አሜኬላ የሚዘሩ፣ በተለይም በአንድ በኩል የአማራ ባህል ተጫነብን እያሉ የሚያላዝኑ በሌላ በኩል ደግሞ በጥንት ጊዜ ይኖሩ የነበሩ የኦሮሞ ከብት አርቢ ማህበረሰቦች (Pastoral Societies) በዋናነት ለከብቶቻቸው ተጨማሪ የግጦሽ መሬትና ውሃ ለማግኘት ያገለግል የነበረና እንደ ፊውዳሉም ሆነ የባሪያው አሳዳሪ ስርዓት ከዘመናችን ጋር የማይሄድ፣ የአንድ ማህበረሰብ ባህልና የባዕድ አምልኮት የሆነውን የገዳ ስርዓት በቃላት ጋጋታና የዲሞክራሲ ሜካፕ እየቀባቡ በቀሩት በኢትዮጵያ 81 ብሔረሰቦችና ህዝቦች ላይ ለመጫን ሲሯሯጡ ይታያሉ።
ሃገራችን ባሳለፈችው የታሪክ ጉዞ ብዙ ፈተና አልፋ፣ ስትወድቅ ስትነሳ እዚህ የደረሰች ናት። እውነታዎችን እንደወረደ በመቀበል ከታሪክ መልካሙን ተምረን፣ ክፉውን እንዳይደገም በማድረግ፣ ለተፈጸሙ ጥፋቶች ይቅርታ ጠይቀን እና ይቅርታ አድርገን ወደፊት መቀጠል ሲገባ በተለይም በየትኛውም የዓለማችን አካባቢ እንደተከሰተው ዓይነት በሃገራችንም በጥንታዊ የኦሮሞ ከብት አርቢ ጎሳዎች ፍልሰትና መስፋፋት እንደተፈጸመ አምኖ እንደ ጋራ ታሪካችን እንደመቀበል ጠባብ የኦሮሞ ብሔርተኞች በእልህና በጥላቻ ተሞልተው ህዝቡን ተጨቆንክ፣ ተስፋፊ ወራሪ “ጋ” ተብለህ ተሰደብክ፣ ሰማዩም መሬቱም ያንተ ነው ወዘተ በማለት ሲቀሰቅሱ፣ ጥላቻ ሲዘሩ፣ ጦር ሲያዘምቱ፣ ከተማ ሲያቃጥሉ፣ ከአሶሳ እስከ ጉራፈርዳ ደሃ ሲገድሉ ኖረዋል። ለምሳሌ ዶ/ር ዲማ ነጎ የተባለው የኦነግ መስራችና ሊቀ መንበር የነበረ አሁን ደግሞ የጠ/ሚ አብይ አህመድ አማካሪ የሆነ ሰው ከአሜሪካ ራዲዮ ጋዜጠኛ ከሆነቸው አዳነች ፍስሃዬ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ያለምንም ማስረጃ “ጋላ” ብሎ የጠራን አማራ ነው በማለት በሃሰት ሲወነጅል ተሰምቷል። ሌሎቹ ደግሞ በየትኛውም የዓለማችን ጫፍ ሊከሰት የሚችል የህዝቦችን መስፋፋትና መሰራጨትን በመካድ ኦሮሞ በመሬቱ ላይ በቅሎ እንደተገኘ ዛፍ አድርገው ሲተርኩ ይሰማሉ፣ የኦነግ አፈቀላጤ (propagandist) የሆነው ዶ/ር ህዝቅኤል ገቢሳ የትኛው ቃልቻ እንደነገረው ባይታወቅም ለፖለቲካ አላማው ሲል የኦሮሞን ህዝብ ከስብአዊ ፍጡርነት አውርዶ ከባህር ውስጥ እንደወጣ ጾታ አልባ እንስሣ እያደረገ በህዝብ ላይ ሲያላግጥ ተሰምቷል።
የመጀመሪያውን ውንጀላ ብንመለከት “ጋ*” የሚለው ቃል ትርጉምና የአጀማመር ታሪኩ ከሶማልኛ ቋንቋ ጋር የተገኘ መሆኑን እና የኩሽ ቃል እንጂ ሴማዊ ከሆኑት ከግዕዝም ሆነ ከአማርኛ ቋንቋዎች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌለው የቋንቋ ምሁራን ያስረዳሉ። ጥንታዊ የኦሮሞና የሶማሌ ጎሳዎች በጉርብትና ይኖሩ በነበረበት ጊዜ በግጦሽ መሬትና በውሃ ምክንያት ከሚያደርጉት አለመግባባት በተጨማሪ በእምነት ልዩነትም ይጋጩ ነበር። “ጋ*” የሚለው ቃል አጀማመር ከዚሁ ጋር የተገናኘ እንደሆነ ኽርበርት ሊዊስ የታባሉ አንትሮፖሎጂስት በጥናታቸው አረጋግጠዋል። ለምሳሌ በሶማልኛ ቋንቋ Gaal, Gaalo, Gaalnimo, Gaalada, Gaalabah የሚባሉ ቃላቶች ይገኛሉ። እነዚህ ቃላቶች ትርጉማቸው በአላህ የማያምን ወይም Infidel(s), Disbeliever ማለት ነው። ቃላቶቹም በሶማልኛ ቋንቋ  መዝገበ ቃላት ውስጥ የሚገኙ ስለሆኑ ማወቅ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በግሉ ማረጋገጥ ይችላል። ኽርበርት ሊዊስ (Herbert S. Lewis) የተባሉ ምሁር “ጋ*” የሚለው የሶማልኛ ቃል ትርጉሙ pagan, infidel, or non-Muslim እንደሆነ ይገልጻሉ። በራሱ በኦሮምኛም ቋንቋ ውስጥም ቢሆን “ጋ*” ከሚለው ቃል ጋር ተዛማጅነት ያላቸው በርካታ ቃላቶች አሉ። ለምሳሌ Gala (ግመል)፣ gala-na (ወንዝ)፣ ma-gaalaa (ከተማ)፣ gal-gala (ምሽት)፣ Gallee (ገሊ – ወደ ውስጥ ገባን)፣ gaaʼelaa (ጥንድ ወይም ባልና ሚስት) ወዘተ። ስለዚህ “ጋ*” የሚለው መጠሪያ መጀመሪያ እስልምና ያልተቀበለ አንዱ የሶማሌ ጎሳ ሌላውን የሚጠራበት የነበረ ሲሆን በመቀጠል እስልምና በመላው ሶማሌ ጎሳዎች ዘንድ ሲስፋፋ ለኦሮምኛ ተናጋሪው የሰጡት ስለሆነ በስደት ከሶማሌ ምድር ይዘውት የመጡት እንጂ እዚህ የተሰጣቸው አይደለም።
3.ማጠቃለያ፣
በለውጡ ወቅት ለማና ወርቅነህ መደመር በሚሉት በኦህዲድ የፖለቲካ ቁማር ኦነግን ሃገር ውስጥ እንዲገባ ካደረጉ በኋላ በርካታ የሰባዊ መብት ጥሰቶች፣ ዝርፊያ፣ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋና ተቆጥሮ የማያልቅ በርካታ ወንጀሎች እንዲፈጸም አድርገዋል። የኦህዴድ መንግስት እና ኦነግ ሸኔ በቅንጅት አጣዬን፣ ሸዋ ሮቢትን፣ ሻሸመኔና እና የመሳሰሉ ከተሞችን በእሳት አወድመዋል። ለትምህርት ወደ ዩኒቨርስቲ የገቡ የአማራ ልጃገረድ ተማሪዎችን በስም ለይተው በማፈን ለአመታት ሰወሩ። ቤንሻንጉል ክልል ዘልቀው በመግባት ከክልሉ አሸባሪዎች ጋር በመቀናጀት የአማራን ህዝብ ለይተው በመጨፍጨፍ በእስካቬተር እንደ ቆሻሻ እያፈሱ ቀበሩ። በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የህዝብ መኖሪያዎችን በቡልዶዘር አፈራርሰው ከአንድ መቶ 120ሺህ ህዝብ በላይ ቤት አልባ ተንከራታች ስደተኛ አደረጉ። አንዳንድ ሰዎች ታንኩም ባንኩም በእጃቸው እያለ ለምን ሃገርን በሰላም እያስተዳደሩ በህጋዊ መንገድ ጥያቄያቸውን አያቀርቡም ሲሉ ይሰማል። እውነቱ ከ19 ባንክ በላይ የዘረፈ፣ ከተማ ያወደመ፣ የፖሊስ መጋዘኖችን እየሰበረ የጦር መሳሪያ የታጠቀን፣ ንጹሃን ዜጎችን በግፍ የገደለ በፓርላማ አሸባሪ የተባለውን ኦነግ ሸኔን ለህግ ከማቅረብ ይልቅ የኦህዴድ/ ኦነግ መንግስት በተቃራኒው ህገወጥነትን እና ስርዓት አልበኛነትን በስተጀርባ ሆኖ የሚያስፋፉበት ዋናው ምክንያት ጥያቄያቸው ሃሰት እና በህግ የማይደገፍ (legitimate እንዳልሆነ) ስለሚያውቁ፣ በህግም ሆነ በታሪክ ውጤት እንደማይኖረው ስለተገነዘቡ ነው። ለሌባ ግርግር ያመቸዋል እንደሚባለው እነሱም በህገወጥነት እና በስርዓት አልበኝነት ህገወጥ ጥያቄያቸውን ለማሳካት እንደሆነ ግልጽ መሆን አለበት።
ወያኔ የአማራን እና የኦርቶዶክስን ጥላቻ እየጋተ ያሳደገው የኦህዴድ ብልጽግና መሪ የሆነው ሐሳዊ መሲህ አብይ አህመድ በለውጡ ወቅት ሆ ብሎ የደገፈውን የኢትዮጵያ ህዝብ ክዶና አሳዝኖ፣ የንጹሃን ደም ጠጥቶ ከማይጠግበው ከዘንዶው ኦነግ ሸኔና ከህወሃት ጋር ለእርቅ መቀመጡ ሳያንስ ህወሃት የመከላከያ ሰራዊት አባላትን እና መኮንኖችን በተኙበት በፈጀበት ወቅት ለሰራዊቱ መከታ የሆነውን እና የእሱንም መንግስት ከመፍረስ የታደገውን የሃገር ባለውለታውን የአማራን ህዝብ እና ፋኖ ላይ ጦርነት ከፈተ። አብይ አህመድ መልካም ያደረገለትን የአማራ ህዝብን መካዱና ደሙን ለማፍሰስ ጦሩን ማዝመቱ ከክፋትና ከእርኩስነት ውጪ መልካምነት ከሌለው ከአባቱ ሳጥናኤል የወረሰው ሴጣናዊ ባህሪው ስለሆነ ነው። ሃገራችን ሰው የሌላት፣ ጀግና ያልበቀለባት ይመስል የወፍ ዘራሾች መጫወቻ ሆነች። የኦህዴድ/ ኦነግ አሸባሪ መንግስት ጠላት ብለው የፈረጁትን የአማራ ህዝብ በኢኮኖሚ እንዲደቅና በረሃብ እንዲያልቅ ማዳበሪያ ከለከሉ፣ በጦርነቱ የፈራረሱ ክሊኒኮች፣ ት/ት ቤቶችና የመሳሰሉት ተቋማት እንዳይጠገኑ በጀት የለንም በማለት ከለከሉ፣ ህዝቡ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በወያኔ ቀንበር መሰቃየቱ ሳያንሰው የኦህዴድ መንግስት ለራያና ለወልቃይት በጀት አንሰጥም በማለት አገደ። እነዚህ እፍረትም ይሉኝታም የማያውቁ ስርዓት አልበኛ አረማውያን የ5 ሺህ ዓመታት የመንግስትነት ታሪክ ያላትን ሃገራችንን ለንደን ላይ 2009 እንደፎከሩት በማፈራረስ ወያኔና ኦነግ በ1983 ዓ/ም የሃገሪቱን ስልጣን እንደያዙ ከሌላው ህዝብ በመንጠቅ ጠፍጥፈው በፈጠሩት ከአንድ ትውልድ የዘለለ እድሜ የሌለውን ክልል የኦሮሚያ ሪፕብሊክ በማለት እንመሰርታለን እያሉ ይገኛሉ። ሲበቃ በቃ ነውና፣ የኢትዮጵያ ህዝብ በጊዜ ባለጌን ባለጌ በማለት ስርዓት ማስያዝ ካልቻለ ጠንቁ የከፋ ይሆናል።
ነጻነት ያለትግልና መስዋዕት በነጻ እንደማይገኝ በመረዳት የጋራ ቤታችን የሆነቸውን አዲስ አበባን ብሎም ኢትዮጵያን በዘንዶው ኦነግ ተውጣ ከመጥፋቷና አባቶቻችን ዋጋ የከፈሉላት ሃገራችንን ቀምተው ሃገር አልባ ተንከራታች ስደተኛ ሳያደርጉን በፊት እራሳችንን እና ሃገራችንን ከጨርሶ ጥፋት መታደግ የግድ ይለናል። ሮም በ Barbarian ወራሪዎች ጠፍታለች፣ እኛም ለህልውናችን እና ለነጻነታችን ካልታገልን አዲስ አበባም እንደ ሮም በአረመኔው ኦነግ/ ኦህዴድ/ ሸኔ ጥምር ሃይል ተመሳሳይ እድል የማያጋጥማት ምክንያት የለም። እነሱ ጨካኝና ይሉኝታ የማያውቅ፣ በትውልድ ቅብብሎሽ የተገነባ ከተማ በአንድ ቀን የሚያቃጥል፣ ማህጸን በሳንጃ የሚተረትር፣ ሃይማኖትም፣ ምግባርም፣ ሰብአዊነትም የሌለው የሰው ስጋ የሚበላ፣ አረማዊ ትውልድ አሰልጥነው ከለቀቁብን ትግላችን ከሰውም ከመንፈስም ጋር መሆኑን ተረድተን የምናደርገው ውጊያ ወደ ምድር ከተጣለው ከዘንዶውና በወገኖቻችን መቃብር ላይ ዛፍ እተክላለሁ ካለው ሐሳዊ መሲህ ጋር መሆኑን ተረድተን በአንድ እጃችን መስቀል በሌላው ደግሞ ነፍጣችንን አንግተን ከመነሳት ውጪ አማራጭ የለንም። እውነት ከእኛ ጋር ናትና የኢትዮጵያ አምላክ ከእኛ ጋር እንደሚሆን አትጠራጠሩ። ስለዚህ ሁላችንም ለነጻነታችን፣ ለህልውናችን፣ ለሃይማኖታችን፣ ለሃገራችን፣ ለታሪካችን እና ለቀጣዩ ትውልድ ስንል እንነሳ! -//-
ደረጀ ተፈራ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop