ቁም ነገር ተናጋሪ የሌለበት መንግስት……

ከዘካሪያስ አሳዬ

      የሚናገረው ውሸት የማያጣ መንግስት፣ የሕዝቡ አመል የማይታወቅበት ፣ የሚያዳምጠው መሪ ያጣ ህዝብ ።ይህ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ። እኛ ኢትዮጵያውያን እስካሁን ድረስ የሚነገረን እንጂ የሚያዳምጠን መሪ ለማግኘት አለመታደላችን ። ያለመታደል ብቻ ሳይሆን ብናገኝ እንኳን አሜን ብለን ለመቀበል ያልታደልን ፍጥሮች ሆነናል ። ልክ እንደሌሎቹ የአፍሪካ ወንድሞቻችን ስልጣን የባለስልጣኖች እንጂ የሕዝብ ሆኖ አያውቅም ። በዚህ ሁናቴ ነበር ኢትዮጵያ ውስጥ አዳማጭ ያገኘ ሕዝብ መስለን ስንታይ የነበርነው ። ትንሽ ሰዎች ወይንም የስርሀቱ ደጋፊዎች እንሆናለን አድማጭ አግኝተን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳገኘ አድርገን ስንሰብክ የነበረው በውሸት ለማስመሰል አድማጭ መሪ እንዳለን ስናወራ ከነበረ ግን ውሸት የትም አያደርስምና ዋጋ መክፈላችን አይቀሬ መሆኑንም መረዳት መቻል ይኖርብናል ።  << የህዝብ ይሁንታ >> የሚለውን ቃል መቀለጃ ከሆነባቸው ሀገሮች መካከል አንዷ የኛዋ ኢትዮጵያ እንደሆነች መናገር ደፋር አያስብለኝም ። ደግሞ እናውራው ፣ እንፃፈው ከተባለ ምሳሌውስ ቢሆን ሞልቶ ተርፎን የለ።

        እንደውም የህዝብ ይሁንታ ሳይሆን የአስተዳዳሪዎቻችን ወይንም የገዥዎቻችን ይሁንታ እንደሚፈፀም በገዥዎቻችን ይሁንታ ውለን እንደምናድር ። ገዥዎቻችን ሲፈልጉ የሚያጠግቡን ከደበራቸው ደግሞ በራብ የሚቆሉን ከነሱ በአስተሳሰብ ለየት ያለ አመለካከት ካለን ወይንም ሁናቴአችን ካላማራቸው ከርቸሌ የሚጠረቅሙን ፣ ትንሽ ከራሩ ደግሞ እንደ ዶሮ በረጅም ገመድ የሚያስሩን ፣ ያሻቸውንና ለነሱ የሚጠቅመውን ሕግ ካወጡ በኋላ በራችንን እያንኳንኩ << ኑ እንወያይ >> እያሉ የሚያላግጡብን ፣ በፖለቲካው አለም ሲበለጡ ፖለቲከኞቹን ማሳደድ፣ በነፃ ዕትመት ላይ ያሉ ሰዎች ሲፅፉ ሕዝብን ለማሳመፅ ነው ተብሎ ወደ ዘብጥያ ማውረድ ፣ ድምፃችን ከፍ ብሎ ለስልጣን መንበሩ የሚያሰጋ ከሆነ ደግሞ የሚያስበረግገንን ህግ አውጥተው የሚዳቆ ሕይወት እንድንገፋ የሚያደርጉን ፣ ከፈለጉ ደግሞ ፀረ_ ሽብርተኛ ብሎ አስሮ አስራ ምናምን አመት ወይም እድሜ ልክ አስሮ በይቅርታ የሚለቁ፣ ልማት አደናቃፊ ምንትሴ ,,,,,,,,ኧረ ምኑ ቅጡ !! እያሉ የሚያደክሙን አይደሉምን ?

ተጨማሪ ያንብቡ:  አዬነው ጽናቱን የጴጥሮስ ህይወቱን። (ሥርጉተ ሥላሴ)

    የኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ ለመናገር ሰፊ ስፍራ ስላለው ሩቅ መሄዱ ባያስፈልገንም ማለት ያለብኝን ብል ደስ ይለኛል ፣ ምን ሩቅ አስኬደን ? የሩቁንማ በምን አቅሜስ ፅፌ እዘልቀዋለውስ ? እናም ትናንት ከሚወዱት ቤተ_ መንግስት እስከ መቃብር እዘልቃለው።  ንጉስ ፣ ፕሬዝዳንት ወይንም ጠቅላይ ሚኒስቴር ይባል የነበረ ሰው ቤተ _ መንግስት ውስጥ ሲኖር ሞት አይደል አንዳች ነገር የሚደርስባቸው እንኳን የማይመስላቸው መሪዎች በሬሳ ስም ተጠርተው አልፈዋል ።

   ካሉበት ዙፋን << ከሚወዱትና የሚወዳቸው >> ህዝብ በአንዲት በቅምጥል ቮልስና በጥቂት ወታደሮች እንዲወጡ የተደረጉት መሪ ቀዳማዊ ኃ/ ስላሴ የሚናገሩ እንጂ የሚያዳምጡ መሪ አልነበሩም ። ቢያዳምጡ ኖሮማ ልጁን ከአንድ በሬ ጋር እየገመደ በማረስ አብዛኛውን ለባለባቱ እየገበረ ለራሱ ሲሶ የሚወስደውን ምስኪን ገበሬ ( ጭሰኛ ) ድምፅ ይሰሙ ነበር ። ይህ የህዝብ ድምፅ እንዳይሰማቸው አቀበት ላይ የተቆለለው ቤተ_ መንግስት ከልክሏቸው ቢሆን ኖሮ እንኳን አፍንጫቸው ስር የገበሬው መበዝበዝ ዘልቆ የተሰማቸው የወቅቱ ደመ ሞቃት ተማሪዎች << መሬት ላራሹ >> እያሉ ሲጮሁ ይሰሙ ነበር ። መሪ ለመሆን የሚያስፈልገው ትልቁ ጥበብ  መስማትና መሰማት ነው ። መሪ የህዝቡን ድምፅ ጩኽትና ሮሮ ካልሰማ ምን ዋጋ አለው ? ጆሮ የሌለው መሪስ እንዴት ሊመራ ይችላል ?

     የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጥቁር ጥላሸት የቀባና የመታወቂያችንን ያህል በኪሳችን ይዘነው የምንኖረውን የረሀብ ታሪክ በሳቸው አገዛዝ ድፍን ወሎና የሰሜኑን ህዝብ ይቀምሰውና  ይልስው ሲያጣ አልሰሙም ነበር ።የህዝቡን የመቃተት ድምፅ የማይሰማ መሪ ፣ ህዝቡ ሲርበው የማይራብ ንጉስ ምን ይሰራል ? የኛ መሪዎች ግን ይናገራሉ እንጂ አያዳምጡም ታዲያ አለማዳመጥ ንጉሱንና ክብራቸውን አፈር ላይ የወደቀ ስጋ አደረጋቸው ፣ ሲያልቅ አያምር እንዲሉ ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአቢይና ጓደኞቹ በሽታ ከሌሎች ይለያል! - ይነጋል በላቸው

      እዚያ ቤተ_ መንግስት ውስጥ ጆሮን እንዳይሰማ የሚነሳ አንዳች ጅኒ ያለ እስኪመስል ድረስ የህዝብን ጥያቄ ተገን አድርጎ በአቋራጭ ወደ አራት ኪሎም ቤተ _ መንግስት የዘለቀው የወታደሮች ስብስብ ደርግም ጆሮውን ለማጣት ምንም ጊዜ አልፈጀበትም ። ደግሞ ጆሮ ለማጣት ? ደግሞ ላለመስማት ምን ችግር አለ ? አህጉሩ እኮ አፍሪካ ለዛውም ስልጣን የሚወደድበት እኮ ነው ። ሁሉንም አፍሪካ አገር ማለቴ አይደለም ልክ እኔ እንዳለውበት  ሀገር ከአፍሪካም ደግሞ የምስራቅ አፍሪካ ቁንጮ ለማለት ነው ።

     ጓድ መንግስቱ ኃ / ማርያሃም በግዜያዊ አስተዳደራቸው ደርግነትን የያዙት በትረ ስልጣን ስኳር ስኳር እያላቸው ጊዜያዊነቱን ወደ ዘላለማዊ ስልጣንነት ለመቀየር ባተሉ ። ስኳር ሲበዛ እሬት እሬት ማለቱ ላይቀርላቸው የህዝብን ድምፅ ፣ የህዝቡን ጩኸት የሚሰሙበትን ዥሮአቸውን ቆርጠው ጥለው እንደገደል ማሚቶ የራሳቸውና የራሳቸውን ድምፅ ደጋግሞ እየተሰማቸው ። የህዝብ ይሁንታ ሳይሰማቸው የራሳቸው ስልጣን ለማቆየት ሽር ጉድ ብለው አለፉ ።

     ያሁን ደግሞ ይባስ ቁም ነገር ተናጋሪ የሌለባትን አገር እንድትሆን ደፋ ደፋ እያደረጉ ያሉትን የገዥውን መንግስት ስናይ ደግሞ የባስ አታምጣ ያስብላል ። ያሁን መንግስት ደግሞ ለመጪው ትውልድም የተበላሸ ታሪክ እንዲወርስ በማድረግ፣ ሕዝብ እውነት እንዳያውቅ ማድረግ ፣ ዘር ክዘር በመለያየትና አገርን በመገንጠል፣ ለአገር የሚቆረቆረውን በማሳደድ የራሳቸውን ድምፅ በመስማት አብደው ደነቆሩ ። ምስኪን ያውን መንግስት አስተዳዳሪዎች የሕዝብን ድምፅ ባለመስማት መኖር አይቻልም ። አምባገነን መንግስታት ቅደሙ እኛ ባለስልጣናት እንከተላለን ድሮም መንገደኛ ፊትና ኋላ ነው ብለን በሰፈሯት ቁና መሰፈር አይቀርም ። የህዝብ ድምፅ ደግሞ በክላሽንኮቭ ጠመንጃ ወይንም በስናይፐር አይገደልም ። የህዝብ ድምፅ በተለይ ለአምባገነኖች እንቅልፍ የሚነሳ መንፈስ ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሰሚ ያለህ! ጋሰለ አረሩ፤ ‘የአማራ ብልጽግናም” ብአዴን፤ ብልጽግናም ይህ አድግ ነው!

    የወታደራዊው ደርግ አስተዳደር በአስራ ሰባት ዓመት አስተዳደሩ ካለመስማቱ ምን አተረፈ ? የኢህአዴግ አስተዳደርስ ከአምናው ሳይማር ዙሩን በማክረር፣ አምባገነንነቱን አክረው ምንስ አተረፉ ?  << ከምር የሆነ ለውጥ ያስፈልጋል >> እያሉ ላንቃቸው እስከሚሰነጠቅ የጮኹ ምሁራንን ፣ ጋዜጤኞች ፣ የፖለቲካ ሰዎችን ድምፃቸውን በመስማት ፈንታ ግማሾቹን የነብስ ግብር እንዲገብሩ ፣ ሌሎቹን በእስራት፣ ቀሪዎቹን ደግሞ በማሳደድ ምንስ ተጠቀሙ ?

      በደርግ ዘመን ፀረ _ ሽብርተኛ ፣ አብዮት ቀልባሽ ፣ አናርኪስት፣ የፍየል ወጠጤ ፣ወንበዴ ፣ የናት ጡት ነካሽ ፣ ገንጣይ ፣ አስገንጣይ ፣ ፀረ_ ሕዝብ ፣ ( የሚገርመው ግን በአገራችን ላይ ያሉ አምባገነኖች ሁሉ ፀረ_ ሕዝብ የምትለውን  ቃል አብዝተው ይወዷታል። ) ያሁኑ ደግሞ መንግስት ከላይ የጠቀስኳቸውን አጉልቶ ተናጋሪ ብቻ ሳይሆን ፈፃሚ ጭምር መሆኑ አይገርምም ?

 ምናልባት ከህዝብ ጎን የቆምን ነን ፣ ተቀናቃኞቻችን የህዝብ ፀሮች ናቸው ለማለትና ባልሰሩት ስራ ሞገስ ለማግኘት ሲሉ የሚጠቀሙበት ቃል ነው ።

   የሕዝቡ አመል የማይታወቅበት ያልኩት የተለያዩ የነፃው እትመት ጋዜጠኞች ፣ የፖለቲካም ድርጅቶች የሕዝብ ይሁንታ ወይም ለሕዝብ ነፃነት  ሲታገሉ የሕዝቡ ዝምታ ለምን ይሆን ? መልሱን ለአንባቢ  ፦

     በመጨረሻ ጹፌን በዚህ መልዕክት ልጨርስ ከመንግስት ጋር በማስመሰል ወይም በማሴር የምንሰራው ስራ፣ ከአምባገነኖች ጋር አብረን ፣ በጥቅም ተገዝተን ፣ አልያም በማንአለብኝነት ፣ በውሸት የሕዝብ ይሁንታ በመስረቅ የሚደረግ ስራ ነገ ዋጋ ያስከፍላልና እውነት በዋለችበት መዋሉ ጥቅሙ የጎላ ነው ።

  ታዲያ አለማዳመጠ በወለደው ጦስ እሱም ግብረ አበሩም የቅጣት ፅዋ መቅመስ የት ይቀር ።

   ቁም ነገር ተናጋሪ ያለባትንና ሕዝብን አድማጭ መንግስት ይስጠን !!

                                     ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!!

                                ከዘካሪያስ አሳዬ( edenasaye@yahii.com)

 

3 Comments

  1. Dear writer,
    You see the biggest problem we have to passive or reactionary attitude. If we want a leader who listens to us, we have to create one by removing those who show us arrogance and disregard. As far as we keep thinking like “may God give us a responsible leader …”, we will remain under a tyrant and his goons. It is a total humiliation to be ruled by the likes of Bereket, Azeb and their vassals.
    The salvation of Ethiopia can possibly come IF we do the following, among many other things:
    1-Stop discussing and eulogizing individuals and personalities and rather do exactly that for issues, concepts and ideas;
    2-Actively work to own and direct our lives – as opposed to passively expecting help and sympathy from others. Expecting reasonable behaviour from a tyrant is asking for mercy from a serial killer. You life belongs to you and you shall fight for all your rights. No pain, no gain!

Comments are closed.

Share