April 11, 2013
5 mins read

የትግራይ መምህራን እሮሯቸውን እያሰሙ ነው

(አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

በኢትዮዽያ ዩኒቨርስቲዎች እየሰለጠነ ያለው የሰው ሃይል (ከምረቃ በኋላ) ብዙ ችግሮች እንደሚፈታተኑት ይታወቃል። ከነዚህ ችግሮች አንዱ ‘ስራ ኣጥነት’ ነው። የስራ ኣጥነቱ ምንጭ ደግሞ የፖለቲካ ሙስና ነው።

ሙሁራን ዜጎች የመንግስት ስራ (በሚፈልጉት ዓይነት) የሚይዙት ባገኙት ውጤት ሳይሆን በዘመድ ኣዝመድ ነው። የስራ ዕድገት (የደመወዝ ጭማሪ) የሚያገኙት በስራ ብቃታቸው ሳይሆን በፖለቲካ ኣመለካከታቸው (ለገዢው ፓርቲ ባላቸው ቅርበት ወይ ታማኝነት) ነው።

ከዩኒቨርስቲ የተመረቁ ዜጎች የፖለቲካ ታማኝነታቸው ካላስመሰከሩ የኢኮኖሚ ሽብር ይደርሳቸዋል፤ ዕድገት ኣያገኙም ወይም ከስራ እስከማባረር ድረስ ይደርሳሉ። ይህም ሁኖ ግን ብዙ ‘ስራ ኣጦች’ ኣሉ። (በኢትዮዽያ ዉስጥ ያለው ስራ ኣጥነት ባብዛኛው በፍትሕ እጦት ምክንያት የሚፈጠር ነው።)

በትግራይ ክልል በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ መምህራን በፍትሕ ችግር፣ በኑሮ ውድነት እየተሰቃዩ ይገኛሉ። ክልሉ ለዜጎች ስራ ፈጥርያለሁ ባይ ነው። ግን ብዙ መምህራን ቅሬታቸው እየገለፁ ይገኛሉ።

ባለፈው ሳምንት ነው። የትግራይ ክልል መንግስት ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በትግራይ ላሉ መምህራን በመማር ማስተማር (ፔዳጎጂ) ላይ ያተኮረ ስልጠና ለመስጠት ከመጋቢት 27 እስከ ሚያዝያ 1, 2005 ዓም ቀነ ቀጠሮ ይዞ ነበር። ስልጠናው በሽረ፣ ዓድዋ፣ ውቅሮና ኣላማጣ ነበር እንዲካሄድ የታቀደው።

በስልጠናው የሚሳተፉ መምህራን 1615 ሲሆኑ ሁሉም በዲግሪ መርሃ ግብር የተመረቁ ናቸው። ስልጠናው በሚሰጥበት ግዜ ታድያ ችግር ተፈጠረ። መምህራኖቹ ደስተኞች ኣይደሉም። “ ከስልጠናው በፊት ጥያቄዎቻችን ይመለሱልን” ኣሉ። ለካ እነኚህ በዲግሪ የተመረቁ ሙሁራን የተቀጠሩት በዲፕሎማ ማዓርግ ነው። ደመወዛቸው የሚከፈል በዲፕሎማ እርከን ሲሆን በወር 1233 (Monthly Gross Salary) ብር ብቻ ነው።

ይገርማል። እንዲህ ነው ምርቋኖቻችን ከዲግሪ ወደ ዲፕሎማ ሲያድጉ። 1233 ብር ግብር ሲቀነስበት ስንት ይቀራል??? 1233 ብር የጫማ ዋጋ ነው ወይ ከቤት ኪራይ ኣያልፍም። በ1233 ብር ደመወዝ ምን ሊሰራ ይችላል? (ኑሮ ውድነቱ ግምት ውስጥ ኣስገቡ)። ኣስተማሪዎቹ ዲግሪ ተምረው በዲፕሎማ ሲቀጠሩ ምን ዓይነት ሞራል ይሰማቸው ይሆን? ምን በልተውስ ያስተምራሉ?

ሰው እንኳን ሳይበላ ሊያስተምር ሳይበላ መኖርም (መተኛት፣ መቀመጥ፣ መንቀሳቀስ) ኣይችልም። ስለዚህ በዚህ ሞራልና ደመወዝ በኣግባቡ ሊያስተምሩ ኣይችሉም። አንዴ ተጎድተዋል። ተማሪዎችም ይጎዳሉ፣ ምክንያቱም በኣግባቡ ሊማሩ ኣይችሉም። ሳይበሉ ስለ ፔዳጎጂ ሊማሩ??? ስለዚ ይሄ ኣካሄድ (መምህራን ደረጃቸው በመቀነስና በኣነስተኛ ደመወዝ እንዲያስተምሩ ማስገደድ) ትውልድን ይገድላል።

ባጠቃላይ በኣስተማሪዎቹ ተቃውሞ ምክንያት ስልጠናው ኣልተሳካም። መንግስት ዲግሪ ለያዙ ሰዎች 1233 ብር ብቻ ሲከፍል የባለስልጣናቱ ዘመዶች የሆኑ ግን (ዲግሪ እንኳ ሳይኖራቸው) በትእምት ከ100, 000 (መቶ ሺ) ብር በላይ (አንዳንድ ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞች ሳይጨምር) እንደሚከፈላቸው ይታወቃል።

እስከ መቼ ይሆን በእንደዚህ ዓይነት ኣድልዎና ጭቆና የምንኖረው? እኔ ግን ይሄን ኣሰራር ኣልፈልገውም፣ እቃወመዋለሁኝ።

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop