ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልዑክ ባሕር ዳር ገብቷል።
ልዑኩ በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እና የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች አቀባበል አድርገውለታል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳድር ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና ልዑካቸው በቆይታቸው ከርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እና ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች ጋር በሁለቱ ክልሎች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ጉዳዩ ለብዙዎች በግራም በቀኝም ግርም ቅርም እንደሚያሰኝ መረዳቱ አይከብድም። በዚህ ስህተተኛ የለም። በግሌ ግን ጥሩ ጅማሮ ነው እላለሁ። እንግዲህ የጠፋው ጠፍቷል። ሌላ ማለቂያ የሌለው ጥፋት ለልጆቻችን ካማቆየት ይልቅ ከእልህ ወጥተን እንደዚህ መነጋገር ከቻልን እና ሰላምን ማምጣት ከተቻለ፣ እስየሁ! ነው እንጂ ሌላ ምን ይባላል?
በቅርቡ ባህር ዳር ስለነበርኩ “ግንቦት 20” የሚለው መነሳቱን እንጂ አዲሱ ስም መጻፉን አላየሁም። ሁሉም በየነገስታቱ ስም ሲሰይም ባህር ዳር ለምን “ግንቦት 20” እንደተባለ ከድሮም ይገርመኝ ነበር። ስለዚህ መቀየሩ ግድ ሆኖ ሲያበቃ ቅያሬው ሥም የተሰጠው በስምምነት እና ህጋዊውን መንገድ ተከትሎ ነው ብዬ አምናለሁ።
ጌቾ በሮኬት የጋየውን የአየር ማረፊያውን ህንጻ ክፍል አይቶት ይሆን?
ሰላማችን ይብዛ!
ዳሹሬ ልጁ የሞተበት ቢነጋገር ጥሩ ነበር አሁን ግን የትላንት አስገዳዮች የዛሬ ተደራዳሪዎች ናቸው እኛ የሚል የለም እኛ አልተሳተፍንበትም። አማራ ክልል ያ ሁሉ ውድመት ደርሶ ትምህርት ቤቶች ሆስፒታሎች ጤና ጣቢያዎች ተነቃቅለው ሂደው ዛሬ ነቃዮቹ ገዳዮቹ በዚህ መልኩ ሲስተናግዱ በአለማዊዉም በስጋዊዉም መረዳት በጣም ከብዷል።