ራስን እና አገርን  ካይቀሬዉ ሞት ለመታደግ በሚደረግ የህልዉና ትግል በአንድነት እና ህብረት ለነፃነት ዘብ መቆም የአሁን ግዴታ ነዉ

ዓለም  ዓለም  እንድትባል ያስቻላት ለሰዉ ልጂ  በአደራ የተሰጠች እና ሠዉም በነፃነት እና በአብሮነት ሊያስተዳድራት፣ ሊመራት እና እንደ ፍላጎቱ እና ችሎታዉ ሊያለማት፣ ሊጠቀምባት እና ለቀጣጥ ትዉልድም በላቀ አየያዝ ሊያስተላልፍ ነዉ ፡፡

የእኛዉ አንድ አገር ኢትዮጵያም አያት ቅድመ አያቶቻችን ህይታቸዉን ሠዉተዉ ፤አካላቸዉን አጥተዉ  በደም እና በአጥንት የመሰረቷት አገር ከላይ ከዓምላክ በተሰጠን ተፈጥሯዊ  መብት  በዕኩልነት እና በአንድነት ልናስተዳደራት፣ ልንመራት፣ ልንጠቀምባት እና ልንጠብቃት ነዉ ፡፡

ሆኖም የጥላቻ እና የልዩነት   ዕንክርዳድ ከተዘራበት ግንቦት ሀያ አስራ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓ.ም ጀምሮ ፡

  • ኢትዮጵያን እንደ አገር አለማየት ወይም ማጥላላት ፣
  • አንደኛዉን ማህበረሰብ በተለይም ዓማራን  እንደ ጠላት ፣
  • ክርስትና  ኃይማኖትን (ኦርቶዶክስ) የአንድ ማህበረሰብ  ሀብት እና ንብረት በማድረግ

ለፖለቲካ ንግድ ለመዋል ከቅድመ ኢህአዴግ ምስረታ አስቀድሞ የትህነግ የበረኃ የትጥቅ ትግል መነሻ እና መቀስቀሻ  ሆኖ መጀመሩ  ይህም እንደ አገራችን የዘመን አቆጣጠር  የካቲት 1968  ዓ.ም.  የትግራይ ህዝብ ነፃ አዉጭ ድርጂት (ት.ህ.ነ.አ.ድ)  የትግል አላማዉ ፀረ  ዓማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያ እና  ፀረ ኢምፔራሊዝም  ሆኖ መዳረሻዉ የትግራይ ዲሞክራቲክ ሪፐፕሊክ መመሠረት  እንደነበር  መዘንጋት የለበትም ፡፡ገፅ.18.

ከዚህም ሌላ አስቀድሞ በትግሉ መነሻ የዓማራዉን ኢትዮጵያዊ አንድነት እና ብሄራዊ ኩራት  በመረዳቱ የሸዋ  ተራማጂ ኃይሎች ትምክተኛ እና አድር ባይ በሚል  ቅድመ ስጋት እና ጥላቻ ፍረጃ በማግለል  ይህንም በህገ- ኢህአዴግ በመጨመር መላዉን እና ብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ ዓማራ ህዝብ ከፖለቲካ ተሳትፎ በማግለል በአገሩ ፣በራሱ እና በማንነቱ ላይ መገለል እና ክህደት ተፈጽሟል፡፡

ይህ ብቻ አይደለም አዲስቷን የትግራይ ሪፐፕሊክ ለመመስረት ያመች ዘንድ በመገኝጠል እና በቅኝ ግዛት ስም መዉጫ እና መማምለጫ መንገድ ለመክፈት  በዘመኑ የኤርትራ ጥያቄ  ላይ ብቸኛ እና ዋቢ ዕማኝ ሆኖ ኤርትራን ከዕናት አገር ኢትዮጵያ በመለየት በሚደረገዉ  ትግል ሁነኛ ተቆርቋሪ ሆኖ ራሱን  (ት.ህ.ነ.ግ) ያቀርባል ፡፡

ይህ ሁሉ በጨቋኟ  ዓማራ (ገፅ 15) ብሎ ለማጥላላት  እና ራሱን (ት.ህ.ነ.ግ) የነፃነት እና የዕኩልነት ሀዋርያ ለማድረግ ሲሞክር በሌላ በኩል  ዓማራ ጨቐኝ፣ የታሪክ እና ባህል…… ቀማኛ  በማድረግ በቁጥር 3 ህብረተሳባዊ ሁኔታዎች በሚል  ንዑስ ክፍል  ይገልፃል፡፡ገፅ.16

ይህም አስከ ዛሬ ጊዜ ድረስ የቀጠለዉ በኢትዮጵያ እና ህዝቦች ላይ የተጫነዉ የመከራ ቀንበር  እና የጠጫረዉ የጥፋት ዕሳት በኢትዮጵያ ፣ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያዊ መገለጫዎች ላይ  የማጥፋት የጠላት ሴራ ጥንስስ ነዉ ፡፡

ይሁንና ይህን በኢትዮጵያ እና ዓማራ ህዝብ ላይ የተጫነዉን የጥፋት እና ሞት  ቀንበር የኋላ ታሪክ ለማወቅም ሆነ አንብቦ መረዳት በማይችሉ አቅመ ቢስ “ድኖች እና የጥፋት ግብረ አበሮች ” የጥፋት ኃይሎች ለሶስት አሰርተ ዓመታት በኢትዮጵያ አንድነት ፣ በዓማራ ህዝብ ማንነት ፣ በኢትዮጵያዉያን  ዕምነት እና ባህል ላይ የተደረገዉን እና የሚደረገዉን የጥፋት ዘመቻ ከምንም ካለመቁጠር ወይም ድንገተኛ እና አጋጣሚ አድርጎ በምን ቸገረኝነት መመልከት ለዚህ አለማ ለቆሙት ቀርቶ በህዝቡ ላይ መሞት እና ባርነት የዕለት ተዕለት መለመድ ሆኗል፡፡

ከፀረ -ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት  መነሻ ከሆነዉ  የትጥቅ ትግል መመሪያ (ማንፌስቶ) አስከ ህገ-ኢህአዴግ ኢትዮጲያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያዊ ማንነትን በረሳ ከህዝብ እና ከአገር ይልቅ ለፖለቲካ ጥቅም እና ስም ሽፋን ዜጎች በማንነታቸዉ ለደረሰባቸዉ ሠባዊ እና ቁሳዊ በደል፣ ማንነት ተኮር ፍጂት( ጥቃት)፣ በዕምነት እና ባህል  እና ተቋማት ላይ ለደረሰ ጥፋት  በስሙ የሚጠራ እና ለምን የሚል ባለመኖሩ አሁንም በተደረሰበት ሁኔታ ላይ መገኘታችን አደር ባይነት ከሠባዊነት ፣ከአገር እና ከዕምነት  በላይ ስር ሰዶ ኢትዮጵያዊ ማንነት እና ሠዉነት ለመከራ እና ለሞት ምክነያት ሆኗል፡፡

የዕምነት ተቋማት እና መሪዎች ሳይቀሩ ላለፉት ሶስት አሰርተ ዓመታት በሠባዊ ክብር እና በዜጎች የግፍ ግድያ ፣ መፈናቀል እና ሁለንተናዊ ሠባዊ በደል  ዕዉነቱን አለማዉገዛቸዉ ዛሬ ላይ ከዜጎች ሞት እና መፈናቀል በላይ በዕምነት እና ሠዉ መሆን ላይ ቀጥተኛ ጥቃት እንዲደርስ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት በተለይም ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤ/ክርስቲያን ሆኑ ተከታዮቿ ለአገር እና ለህዝብ ካላቸዉ  ከፍተኛ ታኲ ድርሻ  አኳያ የሚደርስባቸዉ  ደባ ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያን ከስሩ ለመንቀል ከሚደረገዉ የዘመናት የክህደት እና ጥፋት ሴራ መሆኑን ዛሬም መረዳት አለመቻላችን ለመከራ ዘመናችን መራዘም ምክነያት ሆነናል፡፡

አገር እና ጥንታዊ ቅርስ እና ዉርስ እያወደሙ  ስለ አገር እና ህዝብ ዕድገት እና ህልወዎት ለማዉራት መከጀል ወይም ዝም ባይነት ከጥፋት ተባባሪነት አይለይም ፡፡

የሁላችንም የምትሆን አገር እንዲኖረን ከፈለግን ከምንም በላይ ነፃነታችንን እና ህልዉናችንን ለማረጋገጥ በአንድነት መቆም እና ጥፋተኞችን እና ከኃዲዎችን ከድርጊታቸዉ ጋር በግላጭ መጥራት እና ተጠያቂ ማድረግ ያስፈልጋል ፡፡

በቀድሞ የኢትዮያ መንግስት በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት በተከሰተ ግጭት የነጭ እና ቀይ ሽብር ለሞቱ ሠማዕታት በማሰራት እና የፖለቲካ ቅቡልነት ለማግኘት የተጋዉ ኢህአዴግ አስከ ዛሬ የሞተ ወቃሽ ሆኖ ራሱ ዜጎችን ጠላት እና ወዳጂ አድርጎ በመፈረጂ ከፍተኛ ሠባዊ እና ቁሳዊ ብሄራዊ ዉድመት ከዚያ አስከዛሬ አድርሷል ፤ነገር ግን ማንም ምንም ባለማለቱ በአገር እና በህዝብ ላይ ክህደት ፣ ጥቃት፣ሞት ስደት ፣ድህነት እና ዉርደት …ቀጥሏል፡፡

አሁንም ቢሆን ኢህአዴግ በብሄራዊ ደረጃ በአገር እና በህዝብ ላይ ላደረሰዉ  ክህደት ፣ጥቃት ፣ማንነት ተኮር የዘር ፍጂት ፣ በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት እና በማጥቃት አስከ ቀርብ ቀናት በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ለደረሰዉ እና እየደረሰ ላለዉ ጥቃት ተጠያቂ እንዲሆን እና በኢህአዴግ ብቸኛ  አምባገነን የበላይነት አገሪቷን በፈላጭ ቆራጭነት ሲያስተዳደር  በማንነታቸዉ ፍጂት እና ዕልቂት ለደረሰባቸዉ ኢትዮጵያዉያን የሠማዕታት መታሰቢያ ሊደረግላቸዉ ይገባል ፡፡

በግል እና በቡድን የፖለቲካ ስልጣን ምኞት  እና ለዚህ ስጋት አድርጎ በማየት በህዝብ እና በኃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደረግ ማንኛዉም ጥቃት በማንኛዉም መንገድ ጥፋት ካልሆነ እና ይህም ህዝብን እና አገርን በጥላቻ እና በበቀል ከማየት ዉጭ የሚያስገኘዉ ፋይዳ ባለመኖሩ ላአገሩ እና ለህዝብ የሚሰራ ሁላ ለዚህ ድርጊት አይደለም ኃሳብ በግልፅ ሊያወግዝ ይገባል ፡፡

የተገፋ እና ነጻነቱን ያጣ ህዝብ ጥያቄዉ ሊደመጥ እንጂ  በዕምነቱ እና በማንቱ ላይ ጥቃት የሚከፈትበት ከሆነ ከዚህ በላይ የሚሆነው ስለማይኖር  ለነፃነት እና ህልዉና መረጋገጥ  በስጋም በዕምነትም መሞት ስለማይፈቅድ  ነፃነት ወይም ሞት እንዲል ማስገደድ ለማንም አይበጂም ፡፡

“ለአገር እና ለህልዉና የሚደረግ የሞት ሽረት ትግል ለነፃነት የሚከፈል ዋጋ ነዉ  !”

አለን !

 

አንድነት ኃይል ነዉ !

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራው በዘሩና በማንነቱ እየተገደለ ያለው በአብይ አህመድ እና በሽመለስ አብዲሳ ቀትተኛ ትዛዝ ነው

1 Comment

  1. ዛሬ አደገኛው ጭራቅ ኦናግ ና ብልጽግና በወያኔ የተጀመረውን ኢትዮጵያን እንደ ሶማሊያ መበተን እንደ ሩዋንዳ እርስ በርስ ጦርነት እንዲሁም እስልምና ክርስቲያን ሀይማኖት አጥፍተው በጴንጤ ለመተካት ሥልጣኑን ለማጠናከር አማራን ከትግራይ አጋጭቶ ዛሬ አማራን በማጥፋት የቤት ሥራ ጀምረዋል ና የኢትዮጵያ ሕዝብ ነቅቶ እነዚህን ጠባብ ዘረኞችን በአንድነት መጥፋት አለበት ።
    በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዲያስፖራ ባንኮች በኩል የምላክ ሀዋላ ገንዘብ አቁሞ በግልሠቦች በኩል መላክ ።
    የጭራቆችን መከላከያን ለማዳከም ሽምቅና ደፈጣ ውጊያን የነሱን ባንዳዎችን በሁሉም ቦታ መግደል ።
    ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር በሃይማኖት ሳይከፉፈል በአንድነት በጣልያን ፋሺሽት ጣሊያኒን ላይ ያስመዘገበው ታሪክ ዛሬም በዘረኞች ጭራቆች መድገም አለበት

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share