ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት”| ሰሜን አሜሪካ  የአንድነት እና አጋርነት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

በወቅታዊ የሀገራችን ኢትዮጵያ ጉዳይ
የዳግም ትግል አንድነት እና አጋርነት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

እንደሚታወቀው ለ27 አመታት የነበረውን ዘረኛ የህወሓት አገዛዝ ለመቀየር እና በምትኩ ፍትህ እኩልነት ነፃነት እና ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ የጎሣ ሥርዓት ተወግዶ መልካዓምድራዊ አስተዳደር ለመመስረት ከመሰል አላማና ግብ ካላቸው ድርጅቶች ጋር ስንታገል መቆየታችን ይታወሣል:: በሕዝባዊ አመጽ እና ከውስጥም ከውጭም በተቀናጀ የተቃውሞ ትግል ዘረኛውን የሕወሃት አገዛዝ ከስሩ ነቅሎ ለማስወገድ ሕዝባችን በተቃረብንበት ወቅት ከአሮጌው አገዛዝ ውስጥ በወጡ የራሱ ሰዎች ለውጡ ተቀልብሶ ጥገናዊ ለውጥ ተደረገ ።

በአጋጣሚው ወደ ስልጣን የወጣው የአብይ አስተዳደር  ሕዝባችን እና የተቃዋሚ ድርጅቶች በነበረው የነፃነት ጥማት ሙሉ ድጋፍ አግኝቶ በዓለም ለይ በየትኛውም ሀገር ታይቶ በማይታወቅ ከፍተኛ አድናቆት አግኝቶ ነበር:: ሆኖም ከህወሓት የፖለቲካ ፕሮግራም ያልዘለለውን ህገመንግስት እና ያለአግባብ የተቀየረውን የሀገራችንን ታርካዊ ሰንደቅ ዓላማ እንኳን በቦታው ሳይመልስ ቆይቶ ከዕለት ዕለት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገውን ሃገራዊ አንድነት ትቶ ወደ ከፉ ተረኛ የጎሣ ፖለቲካ ወርዷል::    በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዜጎች በዘራቸው ተለይተው  ሲፈናቀሉና ሲገደሉ ማየትና መስማት የዕለት ተዕለት ዜና ሆኖአል ። በመሆኑም እኛ “የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ህብረት” የሰሜን አሜሪካ ተጠሪዎች ። ከጊዜ ወደ ጊዜ ከምናያቸው ሁኔታዎች መንግስት ይታረማል በሚል ጊዜ ስንሰጥና ስንከታተልና አልፎም ተርፎም መንግስትን ለማገዝ ስንሞክር ቆይተናል:: ሆኖም በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ፖለቲካዊና መንግስታዊ መዋቅሩ አቅጣጫውን ስቶ መበላሸቱን በማመን ዳግም ወደትግል ለመመለስ ተገደናል ። በመሆኑም መሠል የትግል አላማ ካላቸው ድርጅቶች ጋር በሀገራችን ኢትዮጵያ ጉዳይ መሥራቱ ወቅቱ የሚጠይቀው አማራጭ የለለው ጉዳይ ሆኖ አግኝተናል ። በመሆኑም አዲስ ለተቋቋመው የአማራ ሕዝባዊ ግንባር  (አሕግ) የትግል አጋርነትና ድጋፋችንን መስጠታችንን የደቡብ ምዕራብ ሕዝብም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አውቀው ከጎናችን እንድትሰለፉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን  ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና ፓዎር ቻይና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የሃይድሮሊክ ስቲል ስትራክቸር ግንባታ ለማከናወን የ125.6 ሚሊዬን የአሜሪካን ዶላር ኮንትራት ተፈራረሙ

ግልባጭ :- እንዲአውቁት ” ለአማራ ሕዝባዊ ግንባር”
ፍትህ እኩልነትና ነፃነት ለመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

ደ ም ኢ ሕ ህ
ሰሜን አሜሪካ =====

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share