May 12, 2023
1 min read

ተወዳጇ ድምጻዊ ከዚህ ዓለም ድካም አረፈች

346662790 2102211263307694 5308676179388212487 n
#image_title

346662790 2102211263307694 5308676179388212487 n

ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣ የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።በዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃዎቿ የምትታወቀው በብዙ ኢትዮጵያዊያን በዘፈኖቿ የምትወደደው የድሮዋ ዘፋኝ፤ የአሁኗ ዘማሪት ሂሩት በቀለ በ80 አመቷ ከዚህ አለም በሞት ተለየች።

ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ያለችው ድምጻዊት ሂሩት በቀለ፣ በአደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል፡፡
ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡
የቀድሞ ድምጻዊት ከዛም ዘማሪት ሂሩት በቀለ በተወለደች በ80 ዓመቷ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው፡፡
ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣ የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።
Via፦ታዲያስ አዲስ

 

1 Comment

  1. ሂሩትዬ፤ ዜና እረፍትሽን ስሰማ የእንባ ዘለላዎቼን መቆጣጠር አልቻልኩም። በቅጽበት በትዝታ ብዙ አመታትን ወደኋላ ሄድኩኝ። “ህይወት እንደ ሸክላ”ን እና “እንደ ገበቴ ዉሃን” ደጋግሜ ከብዙ ዘመን በኋላ አዳመጥኩ። እንባዬ ከቁጥጥሬ ዉጭ ዝም ብሎ ወረደ። ምን ይባላል? እግዚአብሄር ነፍስሽን በአጸደ ገነት ያኑራት!
    ወጣቶች እያለን ለሂሩት አድናቆት እንዲህ ይባል ነበር።
    ካህን (ቄስ) ናቸው። በሙዚቃ ቤት በኩል ሲያልፉ በድንገት የሂሩትን ዘፈን ይሰሙና ድምጿ ይመስጣቸዋል።
    ካህን፤ ማነች ይቺ ዘፋኝ?
    መንገደኛ፡ ሂሩት ትባላለች። ምነው አባቴ?
    ካህን፣ አይ እንደው ይህንን ድምጿን ብታውሰኝ እና አንድ ቀን ቀድሼበት ብመልስላት። አሉ ይባላል።
    ታዲያ በዚያን ወቅት ሂሩት የፕሮተስታንት ሃይማኖት ተከታይ ሆና በዚህ ድምጽ አምላኳን ታመስግንበታለች ብሎ ያሰበ ሰው የነበረ አይመስለኝም።
    የሰላም እረፍት ይሁንልሽ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

182448
Previous Story

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቅንጡ ፕሮጀክቶችና የኢትዮጵያ የከፋ ድህነት

182451
Next Story

የባለስልጣኑ ቤት በቦምብ ተመታ/የጳጳሳት ሹመት ተራዘመ ሰበር መግለጫ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop