May 5, 2023
5 mins read

አማራ ሆይ! እንኳን በይሁዳዊና በኤፍሬም ይሳቃዊ ሽምግልና በእውነተኛ ሽምግልናም የህልውና ተጋድሎ ከዳር አይደርስም!

Fano Ethiopia 1 1
#image_title

በላይነህ አባተ ([email protected])

እንደ ይህ አድግ ቁጥር አንድ ሁሉ በሕዝብ የቁጣ ማእበል የተጥለቀለቀው ይህ አድግ ቁጥር ሁለት ይሁዳዊ ሽምግልናን የወንበር ማስጠበቂያና የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ አድርጎ መጠቀም ተጀመረ ውሎ ኣድሯል፡፡  ክርስቶስ አእዋፍዋ የሆነውን ቅድስት ቤተክርስትያን ሳይቀር በይሁዳዊ የሽምግልና መሳሪያ ሊያጠፋ ተቀጣጥሎ የነበረውን ትግል  በይሁዳ ሽማግሌዎች አቀዝቅዞ ቤተክርስትያኗን እንደገና አደጋ ላይ ጥሏል፡፡

በታሪካዊትና መንፈሳዊት ኢትዮጵያ ሽምግልና ከእውነተኛ ችሎት እጅግ የበለጠ ርትኡ ፍርድ የመስጥትና ዘላዊ ሰላምን የማስፈን መለኮታዊ ሀይል ነበረው፡፡ የኢትዮጵያን መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶች እየጠራረገ የሰይጣንን የቅጥፈት፣ የሌብነት፣ የአውሬነትና የጭራቅነት መንፈስ ሲሰራና ሲተክል የኖረው ይሁዳው ይህ አድግ ከመጣ ጀምሮ ሽምግልና ተበዳይን ከበዳይ እግር የሚያስደፋና የሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ ሆኗል፡፡

ይህ አድግ ቁጥር አንድ ኤፍሬም ይስሀቅን የይሁዳዊ ሽምግልና መሪ ተዋናይ አድርጎ እደተጠቀመበት ሁሉ  በአምስት ዓመታት ውስጥ ወድ ሶስት ሚሊዮን ሕዝብ የጨፈጨፈና ያስጨፈጨፈው ከአስር ሚሊዮን ሕህዝብ በላይ ስደተኛ ያደረገው ይህ አድግ ቁጥር ሁለት ደሞ ስለሽምግልና ምንም የማያውቁትን ሆደ ኣደሮች የአማራ ሕዝብ መጨፍጨፊያ መሳሪያ አድርጎ መጠቀሙን እንደ ቀጠለ ነው፡፡

እንደነዚህ ዓይነት ለሕዝባቸው ደንታ የሌላቸው ባንዳ ሆዳሞች ጣሊያንም ሽማግሌ እያደረገ ወደ ፋኖዎች በአምስቱ ዘመን የአማራ ትግል ውስጥ ይልካቸው እንደነበር ታሪክና ትውልድ የሚያውቀው ነው፡፡ እንደነዚህ ዓይነት የታሪክ አተላ የሆኑ ሽማግሌ ነን ባይዎችን መና አርጎ ያስቀራቸው በዘመኑ የነበረው ፋኖና ደጀኑ ሕዝብ ነው፡፡ አማራ የህልውና ተጋድሎ በሚያደርግበት ወቅት የህልውና ትግሉን አደናቅፎ እርስት አልባ የሚያደርግና ተምድረ ገጥ እንዲጠፋ የሚያዘናጋ ሊያጠፉት ከተነሱት ጭራቆችም የከፋ ነው፡፡

እምነት ቀርቶ የአውሬ ያህል እንኳ የደመነፍስ ባህሪ ካልፈጠረባቸው የይህ አድግ አረመኔዎች በሽምግልና በኩል እርቅን፣ ፍትህንና ሰላምን መጠበቅ ከሳጥናኤል በረከትን ተጭራቅ ርህራሄን እየጠበቁ ሲንዘላዘሉ እንደመኖር ነው፡፡

አማራ ሆይ! እንኳን በይሁዳዊያን በኤፍሬም ይሳቃዊ ሽምግልና በእውነተኛ ሽምግልናም የህልውና ተጋድሎ ተዳር አይደርስም፡፡  በሽምግልና ህልውናውም ሆነ ነጣነቱን ያረጋገጠ ሕዝብ በዓለም የለም፡፡ አያቶችህም ይኸንን አላሳዩህም፤ አላስተማሩህም፡፡ ህልውናን የማረጋገጥ ትግል እንኳን ሰው ከትል እንደ አንበሳ ያሉ እንሰሳት የሚያደርጉት መንፈሳዊና አካላዊ ትግል ነው፡፡ አማራን እርስት አልባ ለማድረግና ለማጥፋት እየተኪያሄደ ያለው የአረመኔዎች ዘመቻ እንቅልፍ ሳይነሳው ሆዱን ሲቆዝር ኖሮ ትቢያ የሚሆን አማራ ከትልም ያነሰ ነው፡፡ አማራ እየደረሰበት ያለው እርስት አልባ የመሆንና የመጥፋት አደጋ እንኳን በቁም ያለን የሞተን አማራም ተመቃብር የሚቀሰቅስ ነው፡፡

 

ግንቦት ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።

በትግራይ የተፈጠረው ምንድነው?

January 23, 2025
የድሮ መሪዎች ያላደረጉትን ምሁር ጳጳሳቱ ያላስተዋሉትን ከፈረሰች ጎጆ ከባልቴት ቤት ገብቶ ክብሩን ዝቅ አድርጎ ውሀዋን ጠጥቶ ምግቧንም ተጋርቶ ያላለቀሰ ሰው ያንን ትይንት አይቶ ማን ይኖራል ከቶ? በዉሸት ፈገግታ ፊቱን አስመስሎ ፀሀይ የበራበት

ሰው በሰውነቱ – ከ ይቆየኝ ስሜ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ። የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !

January 22, 2025
Go toTop