May 4, 2023
1 min read

የጎንደሩ ህዝባዊ እምቢተኝነት ሙሉ ዘገባ

182256
#image_title

https://youtu.be/jL1LrDn7VN8

 

1 Comment

  1. ምከር ቢጤ ብዬ ይቺን ጻፍኩ። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ደሬ ኒውስን አዳመጥኩ፣ “የጎንደር ከተማ ሙሉ በሙሉ በፋኖ ቁጥጥር ሥር ዉላለች” የሚል “የድል ብስራት” በሚመስል ቃና ሲያበስር ሰማሁት። ቀጠል አድርጎ “መከላከያ አካባቢውን ሙሉ ለሙሉ ለቆ ወጥቷል” ሲል ጨመረበት። ፋኖ በውጊያ አባሮት ነው? ወይስ በራሱ ፈቃድ? የሚለውን ደሬ አልነገረንም። ከአነጋገሩ ግን ያለ ምንም ውጊያ እንደሆነ ግልጽ ነው። ያ ማለት ምን ማለት ነው ስል “ፋኖ የጎንደር ከተማ ነዋሪን ሰብዓዊ ጋሻ አደረገው’ ወደሚል ዜና ቀየርኩት። ለምን አትሉም? በህዝቡ ካልተፈለገና ፋኖ ሰላም ካመጣለት መከላከያ እንኳን ከጎንደር ሙሉ ለሙሉ ከአማራ ክልል ቢወጣስ? ምን ችግር አለው? አቢይስ “መንገድ ክፈት፣ አትክፈት” ብሎ አተካራ ቢፈጥር እና በከተማ ዉጊያ አላስፈላጊ የሲቪል ህይዎት ቢጠፋ “ከድጡ ወደ ማጡ” ይሆንበታል። እንጂ ምን ይጠቀማል? እናም ጎንደር ምን ያህል “ራሷን ዘግታ” እንደምትቆይ የሚታይ ይሆናል ማለት ነው። የጎንደሩን አይተው ሌሎች የአማራ ከተሞችም “ከተሞችን ተቆጣጠር” የሚለውን የፋኖ ስትራተጂ ይቀላቀሉ ይሆናል። ግን ከተማ መቆጣጠር ለምን ያህል ጊዜ? ገምት ብትሉኝ ከሶስት እስከ አምስት ቀን፣ ከዚያ በላይ ሊሄድ አይችልም። በዛሬ ጊዜ እንኳን መንገድና ሱቅ ዘግቶ እንዲሁም ህዝቡ ኑሮውን አልቻለውም። ከአምስት ቀን በላይ ከሄደ ደግሞ አማራ ክልል የመንግስት መፈራረስ ጅማሬ በግልጽ መታየት ጀመረ ማለት ነው። በሌላ አነጋገር “ጉዞ ወደ ጎበዝ አለቃ ዘመን”። በአንድ በኩል “አቢይ አህመድ አማራን ሊያጠፋ ነው” እያሉ ክስ፣ በሌላ በኩል አቢይን የጎዱ ይመስል አማራ ክልልን ወደ ሥርዓት አልባነት መግፋት። በፋኖ አይነት ኢመደበኛ አደረጃጀት እና የተደበላለቁ አባላት የአማራን ያህል የተወሳሰበ የፖለቲካ ትግል መምራት አይቻልም። ጉዳዩ “የማን ቤት ጠፍቶ የማን ሊበጅ ያውሬ መውለጃ ይሆናል እንጂ” ከሆነም ዉጤቱን ለመናገር ነቢይ መሆን አይጠይቅም። ማንንም ለመብታችሁ አትታገሉ አይባልም፤ ታገሉ! ነገር ግን የዚህ አይነት ትግል ከስሜታዊነት፣ ከእልህ ወጣ ብሎ እውነትን መጋፈጥን ይጠይቃል። በአጭሩ፤ ከተሞችን ፋኖ ተቆጣጠረ። ከዚያስ?
    ሰላሙን ያብዛልን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

182246
Previous Story

የፓርላማ አባላት ያነሱት አስቸኳይ ጥያቄ | እነ ጃልመሮ ያቀረቡት አወዛጋቢ ሀሳብ ታወቀ

344570870 1003026964411601 4626722582031851119 n
Next Story

የብልፅግና መሪዎች “ከአልጋ ሲሉት ከአመድ” አባዜ!!

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop