April 17, 2023
8 mins read

ያማራ ሕዝብ ሆይ፣ ደመቀ መኮንን እየተጫወተብህ እስከመቸ ይኖራል?  

339748900 160017223653443 5546421025620999721 n 2 1 1 1
#image_title
339748900 160017223653443 5546421025620999721 n 2 1 1 1
#image_title

ደመቀ መኮንን ለስሙ ያማራ ብልጽግና መሪ ነው፡፡  ያማራ ሕዝብ በታሪኩ አይቶት የማያውቀው መከራና ውርደት ሲደርስበት ግን፣ ይህ ያማራ መሪ ነኝ የሚል ግለሰብ ምን ተዳየ ብሎ እንዳይናገር፣ እንዳይጋገር አፉን ለጉሞ፣ ዝም ጭጭ ብሏል፡፡  የመሪነት ቦታውን ላማራ የሚቆረቆሩ ዶክተር አምባቸውን የመሰሉ ሰወች እንዳይዙት ደግሞ ግደሉኝ እንጅ አልለቅም በማለት ሙጥኝ ብሏል፡፡  የሱ በታቾች የሆኑት ያማራ ክልል ፕሬዚዳንቶች ደግሞ ከሕዝባቸው ጋር በቂ ትውውቅና መናበብ እንዳይኖራቸው ከጭራቅ አሕመድ ጋር እየተመሳጠረ በየ ስድስት ወሩ ይቀያይራቸዋል፡፡  ይህ አልበቃው ብሎት ደግሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ የሚያደርጋቸው እንደ ተመስግን ጡሩንህ ጃንደረባ፣ እንደ አግኘሁ ተሻገር ሰካራም፣ ወይም እንደ ይልቃል ከፋለ ሙትቻ የሆኑትን ሥራየ ብሎ እየመረጠ ነው፡፡

የሕዝብ መሪ ማለት የሕዝቡን ገፈት መጀመሪያ ቀማሽ ማለት ነው፡፡  የአማራ ሕዝበ በጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ መንግስት ፈጠቁን ሲፈጅ ግን፣ ያማራ መሪ ነኝ የሚለው ደመቀ መኮንን ተሞላቆ፣ ተንደላቆ ይኖራል፡፡  ያማራ ሕዝብ ላስቸኳይ ሕክምና እንኳን አዲሳባ እንዳይገባ እየተከለከለ፣ ደመቀ መኮንን ግን የጉንፋን ኪኒን ለመግዛት አሜሪቃ ይመላለሳል፡፡

ያማራ ሕዝብ ሕልውናውን ለማስጠበቅ ከፈለገ ደግሞ ደመቀ መኮንን በዚህ መንገድ እንዲቀጥል መፍቀድ የለበትም፡፡  እሱ የሚቀምሰውን ገፈት ደመቀ መኮንንም እንዲቀምሰው ማድረግ አለበት፡፡  ደመቀ መኮንንን ማቅመስ ባይችል ቤተሰቡን ማቅመስ አለበት፡፡  ቤተሰቡን ማቅመስ ባይችል ዘመዶቹን ማቅመስ አለበት፡፡  ዘመዶቹን ማቅመስ ባይችል ደግሞ ዘመድ አዝማዶቹን ማቅመስ አለበት፡፡

ደመቀ መኮንን ቢመከር፣ ቢመከር አልሰማ ስላል፣ በመከራ መመከር አለበት፡፡  ደመቀ መኮንን በእውቀትና በመንፈስ ደካማ የሆነ ሕጹጽ ስለሆነ፣ የእሳትን እሳትነት የሚያውቀው ሲፈጀው ብቻ ነው፡፡

 

ስለ ደመቀ መኮንን በጥቂቱ

ደመቀ መኮንን በትምህርቱ ብዙም ያልገፋ ከመሆኑም በላይ ራሱን በራሱ የሚያስተምር ዓይነት ሰው አይደለም፡፡  ወያኔ የትምህርት ሚኒስቴር አድርጎት የነበረውም ያልተማረ በመሆኑ ነበር፡፡  በዚያ ላይ ደግሞ የሚያውቃትን በደንብ መግለጽ የማይችል አንደበተ ግድር (challenged) ከመሆኑም በላይ በራስ መተማመን የሚባል ነገር ምናምኒትም እንደሌለው በግልጽ ያስታውቅበታል፡፡  ይባስ ብሎ ደግሞ ኃላፊነት መውሰድን እንደ ጦር የሚፈራ የዣግሬነት ሰብዕና (follower mentality) በጽኑ የተጠናወተው፣ ለጀሌነት እንጅ ለመሪነት ያልተፈጠረ ግለሰብ ነው፡፡

ይህን በእውቀትና በመንፈስ ደካማ የሆነ የምድረገነት (ከሚሴ) ግለሰብ፣ ላኮመልዛ (ወሎ) የኦሮሞ ነው በሚለው የኦነጋውያን የፈጠራ ትርክት አጭበርብሮ ወደ ቀንደኛ ኦነጋዊነት ለመቀየር፣ ላጭበርባሪው ለጭራቅ አሕመድ እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡  የደመቀ መኮንን ተግባር በግልጽ የሚያመለክተው ደግሞ ግለሰቡ ጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ ስብከት ታውሮ፣ ከወያኔነት ወደ ኦነጋዊነት ተቀይሮ፣ ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ እንዲሉ ከራሱ ከጭራቅ አሕመድ በላይ ጽንፈኛ ኦነጋዊ ሁኖ፣ የኦነጋውያንን ፀራማራ አጀንዳ ከጭራቅ አሕመድ በላይ እያራመደ መሆኑን ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ መሪ ነኝ እያለ፣ አማራ ሕዝብ በኦነግ ሲጨፈጨፍ ዝንብ የሞተ ሳይመስለው ድመጹን አጥፍቶ የተቀመጠው፣ የአማራን ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላ በመሆኑ ብቻና ብቻ ነው፡፡   

የሰኔ አስራምስቱ የባሕርዳር ጭፍጨፋ ሚስጥር ቁልፉ ያለው ደመቀ መኮንን የአማራን ለምድ የለበሰ ኦነጋዊ ተኩላ መሆኑን በመረዳትና በጭፍጨፋው ወቅት ቦሌ አየር ወደብ ውስጥ ጃኖች መንፈላሰሻ  (vip lounge) ተቀምጦ ምን ሲያደርግ እንደነበር አጥብቆ በመጠየቅ ነው የሚባለውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡

ደመቀ መኮንን በራስ መተማመን  እጥረት የሚሰቃይ ሰው ስለሆነ፣ እነከሌ በማንነትህና በምንነትህ ይንቁሃል ብሎ በመስበክ ለበቀል እንዲነሳሳ ማድረግ ለሐሳዊ ተዋኙ (con artist) ለጭራቅ አሕመድ የሕጻን ጨዋታ ያህል ቀላል ነው፡፡  የፈሪ ብትር ሆድ ይቀትር እንዲሉ፣ እንደ ደመቀ ዓይነት ቱርቂ ለበቀል ከተነሳሳ ደግሞ ብትሩ በጣም አሰቃቂ ነው፡፡  ጭራቅ አሕመድ ደመቀ መኮንንን በበቀል ስሜት አነሳስቶ ባሕርዳር ላይ ለፈጸመው አሰቃቂ ወንጀል ግብራበሩ ካደረገው ደግሞ፣ ወንጀለኛነቱን እንደ ማስፈራርያ በመጠቀም ሲጠራው ወዴት፣ ሲልከው አቤት፣ ዝቀጥ ሲለው እስከየት የሚል፣ አፋሽ አጎንባሽ ሎሌው ያደርገዋል፣ አድርጎታልም፡፡

ባጭሩ ለመናገር ደመቀ መኮንን ማለት በወያኔ ዘመን ከወያኔ በላይ ወያኔ፣ በኦነግ ዘመን ደግሞ ከኦነግ በላይ ኦነግ እየሆነ፣ ለመጣ ለሄደው አማራበል ጭራቅ በሎሌነት በማደር አማራን የሚያስበላ ሎሌጭራቅ ነው፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ሕልውናውን በጭራቅ አሕመድ ላለማስበላት በሚያደርገው መራራ ትግል ላይ የመጀመርያው ርምጃ መሆን ያለበት ይህን ሎሌጭራቅ ባስፈላጊው መንገድ ጨርቅ ማድረግ ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

1 Comment

  1. አይ መከራቸው ህወአት እንደገና መምጣቱ ነው አሁንም ተስተካክለው ለመጫን ይጠብቁታል ማለት ነው? ህዝባቸውን ቢይዙ ይሄ ሁሉ ውርደት ባልመጣባቸው ነበር?ቆፍጠን ያለ የበላይ ልጅ ቦታውን ይዞት ቢሆን አለምነህ መኮንንን የአማራን ህዝብ በማዋረዱ ቢያንስ 25 አመት በረከት ስሞንን በሰራው ግፍና በደል ከአላምነህ ጋር እየተጫወት እንዲኖር 25 አመት አገኘሁ ተሻገር፤ንጉሱ ጥላሁን፤ደመቀ መኮንን፤ሰማ ጥሩነህ፤ተመስገን ጥሩነህንና ሌሎች ለሆዳቸው ያደሩትን ጨምሮ 23 አመት ተከልለው እንዲቀመጡ ያደርግ ነበር፡፡ አልሆነም

Leave a Reply

Your email address will not be published.

download 1
Previous Story

ወደነገ ለመድረስ፣ ዛሬን ማለፍ ግዴታ ነው። ዛሬ! አማራ በሕዝብ አመፅ የተደገፈ የትጥቅ ትግል ከማድረግ ውጭ አማራጭ የለውም።

Ethiopia
Next Story

ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ ትንሣኤ! -nሲና  ዘ ሙሴ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop